Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
24.8K subscribers
41.2K photos
343 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማኅበር ኮሚቴ በኢትዮጵያ የሚያደርገውን የሰብአዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለፀ
********************
(ኢ ፕ ድ)

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማኅበር ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ሚርጃና ስፖልጃሪክ ኤገር ጋር በጽ/ቤታቸው ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም አቶ ደመቀ መንግሥት የሰላም ስምምነቱን በቁርጠኝነት እየተገበረ መሆኑን ገልፀዋል።

በአሁኑ ወቅትም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ምክንያት ተቋርጠው የነበሩ መሠረታዊ አገልግሎቶች በተጠናከረ መልኩ ወደ አገልግሎት እንዲጀምሩ እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል።

የሰብአዊ እርዳታ ተደራሽነትንም የማስፋፋት እና የማጠናከር ተግባራት እየተከናወነ ነው። በግጭቱ የወደሙ መሠረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባትና ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም ሁሉን አቀፍ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ መገባቱን ተናግረዋል።

ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማኀበር ኮሚቴ እስካሁን የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

በኢትዮጵያ በሰሜኑ ክፍል ተፈጥሮ በነበረው ግጭትና በድርቅ ምክንያት እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ወገኖችን ተደራሽ ለማድረግ መንግሥት እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም ገልፀዋል።

የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማኅበር ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ሚርጃና ስፖልጃሪክ ኤገር በበኩላቸው ማኅበሩ በኢትዮጵያ የሚሰጠውን ሰብአዊ ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ከሰላም ስምምነቱ በኋላ በኢትዮጵያ እየታየ ያለው ሁኔታ ተስፋ ሰጭ መሆኑን የገለጸው የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማኅበር ኮሚቴ በኢትዮጵያ በሁሉም አካባቢዎች ሰብአዊ እርዳታ ለሚሹ ወገኖች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የወልዲያ ከተማና አካባቢው የ24 ስዓት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘት ጀመረ
*****************
(ኢ ፕ ድ)

የወልዲያ ከተማና አካባቢው ከጥር 17 ቀን 2015 ጀምሮ የ24 ስዓት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘት ጀምሯል፡፡

ከደሴ ማከፋፈያ ጣቢያ በጊዜያዊነተ ኃይል ስታገኝ የቆየችው የወልዲያ ከተማ በአዲስ መልክ የተገነባው የወልዲያ ዶሮ ግብር ባለ230/33/15 የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ ተጠናቆ በከፊል አገልግሎት መስጠት በመጀመሩ ነው ተብሏል።

በአሁኑነ ወቅት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው ሶስት ባለ15 ኪ.ቮ ወጪ መስመሮች አገልግሎት መስጠት በመጀመራቸው የወልዲያ ከተማና አካባቢው የ24 ሰዓት አገልግሎት ማግኘት ጀምረዋል፡፡

በዚህም በከተማው የሚገኙ ጎንደር በር፣ በቅሎ ማነቂያ፣ ፒያሳ፣ ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ፣ አዳጎ፣ ገብርኤል አካባቢ፣ ሆስፒታል እና ሌሎች የገጠር አካባቢዎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

ቀሪ 15 ኪ.ቮ እና 33 ኪ.ቮ ወጪ መስመሮች አገልግሎት መስጠት ሲጀምሩ ቀድሞ ከወልዲያ ማከፋፈያ ጣቢያ አገልግሎት ያገኙ የነበሩ የሰሜን ወሎና አፋር አካባቢዎች ዳግም የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንደሚያገኘ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የትዊተር ገጽ ይከተሉ‼️
https://twitter.com/PressEthio
በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ከ225 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል
****
(ኢ ፕ ድ)

በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ከሀገር ውስጥ ታክስና ከወጪ ንግድና ቀረጥ ከ225 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ አስታወቁ፡፡

ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 54 ቢሊየን 622 ሚሊየን 624 ሺ 687 ብር ወይም በ31 ነጥብ 89 በመቶ እድገት ማሳየቱን ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡

እንደ ሚኒስትሯ ገለጻ፣ ከተሰበሰበው ገቢ ውስጥ የሀገር ውስጥ ገቢው ድርሻ 138 ነጥብ 82 ቢሊየን ብር ሲሆን አፈጻጸሙ ከተያዘው የ137 ቢሊየን ብር ዕቅድ አንጻር የ100.6 በመቶ ክንውን አስመዝግቧል፡፡

ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አኳያ በብር 33 ነጥብ 4 ቢሊየን ወይም 31 ነጥብ 7 በመቶ ዕድገት አሳይቷል ብለዋል፡፡

በወጪ ንግድና ቀረጥ በኩል 90 ነጥብ 26 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ብር 87 ነጥብ 11 ቢሊየን ገቢ ተገኝቷል፤ ከተያዘው እቅድ አኳያ 96 ነጥብ 51 በመቶ ክንውን አሳይቷል፡፡ ገቢው ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ክንውን አንጻር 21 ነጥብ 17 ቢሊየን ብር ወይም 32 ነጥብ 10 በመቶ ዕድገት እንዳለው ሚኒስትሯ አስታውቀዋል፡፡

በግማሽ ዓመቱ ለተመዘገበው አፈጻጸም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ከከፍተኛ አመራር እስከ ታች ፈጻሚ ድረስ ያሉትን አመስግነዋል፡፡ ግብር ከፋዮችም ለአፈጻጸሙ መገኘት ጉልህ ድርሻ ክብር ይገባቸዋል፤ ከተቋሙ ጋር በጋራ የሰሩ ባለድርሻ አካላትንም አመስግነዋል፡፡

በቀሪ ስድስት ወራት የተያዘውን እቅድ ለማሳካት ብቻም ሳይሆን ካቀድነው በላይ ለመፈጸም ግብር ከፋዮችም ሆኑ የግብር ሰብሳቢው ተቋም ሰራተኞች ተቀራርበው በመስራት ለግብር አሰባሰቡ ውጤታማ መሆን መሠራት እንደሚገባ ሚኒስትሯ ማሳሰባቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
«ኢትዮጵያ ካሏት የቀንድ ከብቶች 95 ከመቶው የዝርያ ማሻሻል ይፈልጋሉ»ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ
****************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ ካሏት አጠቃላይ የቀንድ ከብቶች ውስጥ 95 በመቶው የዝርያ ማሻሻያ ያልተከናወነባቸው በመሆኑ ዝርያ የማሻሻል ስራ ላይ ትኩረት መደረጉን የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ አስታወቁ።
በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ ካሉት 71 ሚሊዮን የቀንድ ከብት ውስጥ 95 በመቶው የዝርያ ማሻሻያ ስራ ያስፈልጋቸዋል፤ የዝርያ ማሻሻል ስራውን ስኬታማ ለማድረግ ግብርና ሚኒስቴር በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
በኢትዮጵያ የእንስሳት ዝርያን ማሻሻል ከተጀመረ 70 ዓመት ማስቆጠሩን የገለጹት ዶክተር ፍቅሩ፤ ይሁንና የቀንድ ከብቶቹ የዝርያ ማሻሻል ተግባሩ በተገቢው መልኩ ባለመከናወኑ እንደአገር ያለው የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶች አቅርቦት ደካማ መሆኑን አስረድተዋል።
የእንስሳት ተዋጽኦን ምርታማነትን ለመጨመር ዝርያን በማሻሻል ረገድ ከዚህ በፊት ያለው አፈጻጸም ደካማ ነው። ስለሆነም ያለፈውን ጊዜ ስራ በሚያሻሽል መልኩ ውጤት ለማምጣት የተደራጀ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።
በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንዲሁም በተለያዩ ክልሎችና ማዕከላት የተሻሻሉ ዝርያዎችን የማዳቀል፣ የመኖ ልማትን የማሳደግና የእንስሳቱን ጤና በመጠበቅ ረገድ በመመሪያ የተደገፉ ስራዎች....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=90923
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የትዊተር ገጽ ይከተሉ‼️
https://twitter.com/PressEthio
በገበያ ስርዓቱ ውስጥ እሴት የማይጨምሩ ተዋንያን ለዋጋ ግሽበቱ መንስኤ ሆነዋል
👉 የዋጋ ግሽበቱን ለማረጋጋት እስከ ፖሊሲ ማሻሻያ የዘለቀ መፍትሄ ይሻል
****************
(ኢ ፕ ድ)
በገበያ ስርዓቱ ውስጥ እሴት የማይጨምሩ በርካታ ተዋንያን መኖራቸውን፣ ዘርፉን በበላይነት የሚመሩና የሚከታተሉ ተቋማት በቂ የክትትልና የዕርምት ዕርምጃ አለመውሰዳቸው ለምግብ ዋጋ ግሽበቱ ምክንያት መሆናቸውን የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
የዋጋ ግሽበቱን ለማስተካከል እስከፖሊሲ ማሻሻያ የዘለቀ መፍትሄ እንደሚሻም ተጠቁሟል።
“የምግብ ዋጋ ግሽበት መንስኤዎችን እና የወደፊት መፍትኤ አቅጣጫዎችን” በተመለከተ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት አምራቾችን፣ የምግብ እጥረት የሚያጠቃቸው አካባቢዎች እና ከተሞችን ማዕከል በማድረግ ያጠናውን ጥናት በትናንትናው እለት ይፋ አድርጓል።
ጥናቱን ያቀረቡት የኢንስቲትዩቱ የግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲ ምርምር ማዕከል ኃላፊ ዶክተር ታደሰ ኩማ እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። በአሁኑ ሰዓት በቂ ትኩረትና ፈጣን ዕርምጃ መውስድ ካልተቻለ ሀገራዊ ስጋት ሆኖ መቀጠሉ አይቀሬ ነው። ለዚህ ደግሞ እስከ ፖሊሲ ማሻሻያ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=90918
ከኤሌክትሪክ ኃይል ኤክስፖርት 40 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገቢ ተገኝቷል
*************
(ኢ ፕ ድ)
ባለፉት ስድስት ወራት 39 ነጥብ 83 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ኤሌክትሪክ ኃይል ለጎረቤት ሀገራት ማቅረብ መቻሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገለፀ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ እንደሀገር 772 ሚሊዮን 393 ሺህ 74 ኪሎ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ኤክስፖርት ለማድረግ ታቅዶ ሲሠራ ቆይቷል። በስድስት ወራት ውስጥ 706 ሚሊየን 90 ሺህ 38 ኪሎ ዋት ሰዓት ኃይል ኤክስፖርት ማድረግ ተችሏል።
ከገቢ አንፃር ሲታይ ደግሞ የኤሌክትሪክ ኃይል ኤክስፖርት በማድረግ ወደ 44 ነጥብ 57 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ዕቅድ ተይዞ እንደነበር እና ማሳካት የተቻለው ወደ 39 ነጥብ 83 ሚሊየን ዶላር መሆኑን ገልጸዋል። በኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ገቢ ለማግኘት ከታቀደው የ11 በመቶና በገንዘብ ሲሰላ ደግሞ የ4 ነጥብ 74 ሚሊየን የዶላር ቅናሽ አሳይቷል ሲሉ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለተለያዩ ሀገራት ያደረገው የኤክስፖርት መጠን በተናጠል ሲታይም ወደ ጂቡቲ ኤክስፖርት ከተደረገው ኪሎ ዋት ሰዓት ኃይል የ21 ነጥብ 47 ሚሊየን ዶላር ገቢ አስገኘቷል፤ ወደ ሱዳን ኤክስፖርት ከተደረገውም የ18 ነጥብ 37 ሚሊየን ዶላር ሽያጭ ማግኘት መቻሉንም ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።
ዳይሬክተሩ አክለውም፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የጂቡቲን የኃይል ሽያጭ አፈፃፀም...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=90901
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የትዊተር ገጽ ይከተሉ‼️
https://twitter.com/PressEthio
ኮሚሽኑ ባለፉት ስድስት ወራት 1 ሺህ 544 የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን አስታወቀ
*************
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ባለፉት ስድስት ወራት 1ሺህ 544 አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፍቃድ መስጠቱን አስታወቀ። ከተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎችም ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን ጠቁሟል።
የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ወይዘሮ መሠረት ወልደማርያም እንደገለጹት፤ ኮሚሽኑ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 2ሺህ አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለመስጠት አቅዶ ወደ ተግባር የገባ ሲሆን፤ ከሀገርና ከአለም ነባራዊ ችግሮች ጋር ተያይዞ ለ1ሺህ 544 ባለሀብቶች አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ አገልግሎት መስጠት ችሏል።
በተመሳሳይ መልኩ በግማሸ ዓመቱ ከኢንቨስትመንት ፈቃድና ፈቃድ ነክ አገልግሎቶች፣ከተለያዩ ድጋፍና ጨረታ 16 ሚሊዮን ለመሰብሰብ አቅዶ 13 ነጥብ 58 ሚሊዮን ብር ገቢ ማግኘት ተችሏል ብለዋል።
ኮሚሽኑ በግማሽ ዓመት ውስጥ 16 ሚሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት አቅዶ በተለያዩ ምክንያቶች 13 ነጥብ 58 ሚሊዮን ብር..
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=90909
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የትዊተር ገጽ ይከተሉ‼️
https://twitter.com/PressEthio
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው ለስራ ጉብኝት ሱዳን ካርቱም ገብተዋል
***************
(ኢ ፕ ድ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው ለአንድ ቀን የስራ ጉብኝት ሱዳን ካርቱም ገብተዋል::
የሱዳን ሪፐብሊክ የሽግግር ሉዓላዊነት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ጄኔራል አብደል ፈታሕ አል ቡርሃን አቀባበል አድርገውላቸዋል::
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በፖለቲካው ሂደት ላይ ከተሠማሩ ከሱዳን የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተወያዩ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በፖለቲካው ሂደት ላይ ከተሠማሩ የተለያዩ የሱዳን የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እና ከሦስትዮሽ መፍትሔ አፈላላጊ ቡድን አባላት ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ውይይት፣ የኢትዮጵያ ጣልቃ ገብ ያልሆነ መርሕ ለራሷ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ጭምር የሚሠራ መሆኑን በማረጋገጥ የሱዳን ሕዝብና ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ሀገር በቀል መፍትሔዎችን እንዲፈልጉ አበረታቷል ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ዘግቧል።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን የትዊተር ገጽ ይከተሉ‼️
https://twitter.com/PressEthio