Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ሰባት የውጭ ሀገራት አየር መንገዶች ዳግም ወደ ኢትዮጵያ በረራ ጀመሩ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
አዲስ አበባ፡- የኮሮና በሽታ ከተከሰተ በኋላ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የመንገደኞች በረራ አገልግሎት መነቃቃት በማሳየቱ ሰባት የውጭ ሀገራት አየር መንገዶች ወደ ኢትዮጵያ መብረር መጀመራቸውን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የኤር ናቪጌሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ክብረአብ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ የኮሮና ቫይረስ በሽታ ከተከሰተ በኋላ በርካታ ሀገራት በረራቸውን አቋርጠው ቆይተዋል። በአሁኑ ወቅት ግን በአየር ትራንስፖርት የመንገደኞች በረራ አገልግሎት መነቃቃት በማሳየቱ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የውጭ ሀገራት አየር መንገዶች ሰባት ደርሰዋል። በአማካይ በቀን ሰባት የውጭ ሀገራት አየር መንገድ አውሮፕላኖች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ላይ ናቸው።
እንደ ኤር ናቪጌሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሽመልስ ገለጻ፤ ኮሮና በሽታ በዓለም ላይ ከተስፋፋ በኋላ በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ መብረር ከጀመሩ አየር መንገዶች መካከል የዱባይ ፣ የቱርክ፣ የኳታር፣ የግብጽ፣ የሱዳን፣የኬንያ እና የጅቡቲ አየር መንገዶች ይገኙበታል። በአሁኑ ወቅትም በአማካይ ሁለት መደበኛ በረራ እና አምስት መደበኛ ያልሆኑ የመንገደኛ አገልግሎት የሚሰጡ አውሮፕላኖች ከውጭ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ እየበረሩ ይገኛሉ።
ጨፌ ኦሮሚያ 12ኛ መደበኛ፣ 5ኛ ዓመት 5ኛ የሥራ ዘመን ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡ ጉባኤው ዛሬ እና ነገ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክር የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ሎሚ በዶ ተናግረዋል፡፡
በሁለት ቀን ውሎው የ2012 ዓ.ም የሥራ አፈፃፀም እንደሚገመግምም ነው የተናገሩት፡፡
በኮሮና ምክንያት ችግር የደረሰባቸው 30 ሺ 87 ዜጎች ከስደት ወደሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል
*******************
(ኢ ፕ ድ)
አዲስ አበባ ፤ በተለያዩ ሀገራት በስደት ላይ የነበሩ እና በኮሮና በሽታ ምክንያት ችግር ውስጥ የወደቁ 30ሺህ 87 ኢትዮጵያውያን ወደሀገር ውስጥ መመለስ መቻሉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት፤ ዜጋ ተኮር የመንግስት ፖሊሲ ተግባራዊ በመደረጉ በኮሮና ምክንያት ለችግር የተጋለጡ እና በስደት የነበሩ 30ሺህ 87 ኢትዮጵያውያንን ወደሀገራቸው መመለስ ተችሏል።
በፍቃደኝነት ወደሃገራቸው የተመለሱ ዜጎች በአብዛኛው ከገልፍ እና ከጎረቤት ሀገራት የመጡ ናቸው።
አምባሳደር ዲና እንደገለጹት፤ በተለይ በአረብ ሀገራት እና በጎረቤት ሀገሮች በስደት የነበሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን በኮሮና በሽታ ወቅት ስራ በማጣት ጎዳና ላይ ሲወድቁ በየሀገራቱ የሚገኙ ቆንስላዎች ክትትል አድርገዋል። በተለይ በቤይሩት ከስራ ተባረው እና በመንገድ ላይ ተጥለው የነበሩ ኢትዮጵያውያንን በቆንስላው አማካኝነት ድጋፍ በማድረግ በፍቃደኝነት መመለስ ተችሏል።
በዚህ መሰረት ወደሀገራቸው እንዲመለሱ ከተደረጉ 30ሺ በላይ ዜጎች መካከል ከቤይሩት 656 ዜጎች፤ ከአቡዳቢ 72፤ ከሳዑዲ አረቢያ 3ሺህ 539፣ ከኩዌት ደግሞ 1 ሺህ 23 ዜጎች እንዲሁም በድንበር በኩል ከተለያዩ ጎረቤት ሀገራት 4ሺህ 792 ዜጎች ወደሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።
https://www.press.et/Ama/?p=35961
‹‹ትህነግ የተለያዩ ማንነቶችን ጨፍልቆ አንድ ማንነት ለመገንባት እየጣረ ነው›› አቶ አገዘው ህዳሩ የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ፕሬዚዳንት
*****************************
(ኢፕድ)
ህውሃት በትግራይ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ማንነቶችን በመጨፍለቅ አንድ ማንነት ለመገንባት ጥረት እያደረገ መሆኑን የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ፕሬዚዳንት አቶ አገዘው ህዳሩ አስታወቁ፡፡ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ህልፈተ ህይወት በኋላ የህወሃት አፈና መጠናከሩንም ገልጸዋል፡፡
የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ፕሬዚዳንት አቶ አገዘው ህዳሩ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ እንደገለጹት በትግራይ ውስጥ የተለያዩ ማንነቶች ያላቸው የራያ ፤የኩናማ ፤የሳሆ ፤የአገው እና የኢሮብ ሕዝቦች ቢኖሩም ሕውሓት እንደእርሳቸው አባባል ትህነግ ሁሉንም በአንድ ቅርጫት ውስጥ በመጨፍለቅ አንድ ማንነት ለመፍጠር ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
የራያ ህዝብ ከታሪክ አንጻር ትስስሩ ሰፊ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ ራያ ከኦሮሞ ማህበረሰብ ፤ከአማራ፤ከአገው ጋር ውህድ ማንነት ያለው ሲሆን በታሪክ ሂደትም የራሱን ማንነትን የፈጠረ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ሆኖም ግን የራያንም ሆነ በትግራይ ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ማንነቶችን ባለመቀበል ትህነግ በህዝቦች ላይ የተለያዩ በደሎችን በማድረስ ላይ ይገኛል፡፡
የራያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የራያ ማህበረሰብ የሚገኝበት አካባቢ በሙሉ እና በራያ ወረዳዎች የህዝቡን ማንነት እንዲገነባ ከምርጫ ቦርድ ፍቃድ የተሰጠው ቢሆንም ፓርቲው በራያ ውስጥ እንዳይንቀሳቀስ በትህነግ በርካታ ማስፈራሪያዎችና ጥቃቶች እየደረሱበት መሆኑን አቶ አገዘው ያስረዳሉ፡፡
የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲንና ሌሎች ትህነግን የሚቃወሙ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ባንዳ የሚል ተቀጽላ በማውጣት የማሸማቀቅ ስራ በመስራት ላይ መሆኑን የገለጹት አቶ አገዘው በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ 12 ከሚደርሱ ፓርቲዎች ውስጥም የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በግንባር ቀደምትነት ባንዳ ተብሎ መፈረጁንም ጠቁመዋል ፡፡
የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በግንባር ቀደምትነት ባንዳ ተብሎ በህወሃት የተፈረጀበትንም ዋነኛ ምክንያትን አቶ አገዘው ሲስረዱ ‹‹ የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ጠንክሮ ከወጣ ተመሳሳይ የማንነት ጥያቄ ያላቸው የአገው፤የኩናማ፤የሳሆ፤የውጅራትና የኢሮብ ማህበረሰቦች ትግላቸውን ማፋፋማቸው አይቀርም፡፡ስለዚህም የራያን የማንነት ጥያቄ ማፈን እና ጥያቄውንም የሚያነሱትንም እያሳደዱ ማጥፋት በዋነኝነት ትህነግ የሚከተለው ስልት ነው፡፡›› ሲሉ አብራርተዋል፡፡
በራያና አላማጣ ወረዳዎች የሚገኙ ነዋሪዎችን የራያራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ደጋፊዎች ናችሁ በማለት የማንገላታትና በልዩ ልዩ የማሰቃያ መንገዶች ተማረው አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑን የተናገሩት የፓርቲው ፕሬዚዳንት የራያ ማንነትን የሚያቀነቅኑ ግለሰቦችን አድኖ ከመግደል አንስቶ የማህበረሰቡን ሽማግሌዎችና ታዋቂ ግለሰቦችን ስልታዊ በሆነ መንገድ የመግደልና የማጥፋት ስራዎችን ሀገሪቱን ማስተዳደር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ሲከወን መቆየቱንም አብራርተዋል፡፡
ለተጨማሪ https://www.press.et/Ama/?p=35937
“የበላይነትን የለመደ እኩል ሁን ስትለው የተዋረደ ይመስለዋል”
አቶ ታዬ ደንደኣ
**********************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ ፦አንድ ጊዜ የበላይነትን የለመደ አካል እኩል ሁን ሲባል የተዋረደ ይመስለዋል ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታዬ ደንደኣ አመለከቱ። የህወሓት ጥገኛ ቡድን በሴራ ፖለቲካ የተካነ ስለመሆኑም የቀደሙ ታሪኮቹ ህያው ምስክሮች እንደሆኑ አስታወቁ
“የበላይነትን የለመደ እኩል ሁን ስትለው የተዋረደ ይመስለዋል”
አቶ ታዬ ደንደኣ
**********************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ ፦አንድ ጊዜ የበላይነትን የለመደ አካል እኩል ሁን ሲባል የተዋረደ ይመስለዋል ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታዬ ደንደኣ አመለከቱ። የህወሓት ጥገኛ ቡድን በሴራ ፖለቲካ የተካነ ስለመሆኑም የቀደሙ ታሪኮቹ ህያው ምስክሮች እንደሆኑ አስታወቁ ።

አቶ ታዬ ደንደኣ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት፤አሁንም ድረስ ምናልባትም በሚዲያዎች እንደሚሰማው ህወሃቶች እኛ በታሪክ ካለን አስተዋጽዖ አንጻር የተለየና የበለጠ ቦታ፤ስልጣንና ኢኮኖሚ ይገባናል ብለው በግልጽም ያነሳሉ። ከዚህ ባለፈም በዚህ አገር ውስጥ በአንድ በኩል የተዘረፉና የተሰረቁ በርካታ ነገሮች አሉ፤ እናም ይሄ ለውጥ መሰረቱን ይዞ በትክክለኛው አቅጣጫ የሚዘልቅ ከሆነ ምናልባትም ነገ ተጠያቂነት ይመጣል የሚል ስጋትም አለባቸው።

እነዚህ ሃይሎች ያለፈውን ትተን እሱ ስለማይጠቅመን መልካም ነገሮችን አጎልብተን የተበላሹትን ለማስተካከል ከዚህ ጀምረን እንስራ፤ የይቅርታ መንገድ እንከተል የሚለውንም ለማመን አልፈለጉም የሚሉት አቶ ታዬ፣ለማመን ያልፈለጉት ደግሞ እነርሱ ስለማይታመኑ ሁሉም እንደዛው ስለሚመስላቸው ነው ብለዋል። እነርሱ በአፋቸው የሚሉት ሌላ፤ በልባቸው የያዙት ሌላ ስለሆነ ሰው በቅንነት በዚህ ደረጃ ነው ለኢትዮጵያ የሚያዋጣው ብሎ ቢነገር ከራሳቸው አንጻር ስለሚመነዝሩት ይሄንንም ሊያምኑ አልቻሉም። እየተጠራጠሩ ነው የመጡት ሲሉ ያብራራሉ።

እንደ አቶ ታዬ ገለጻ፤ሁለተኛው ደግሞ እነርሱ ለዛ ክልልም ሆነ ማህበረሰብ በስሙ ነገዱበት እንጂ ለ27 ዓመታትም ሆነ ዛሬም ድረስ ያ ማህበረሰብ ችግር ውስጥ ነው። እነርሱ የሚሰሩት ለራሳቸው ስለሆነ ይህች ኢትዮጵያ እኛ ካልገዛናት፤ እኛ እንደፈለግን የማናደርጋት ከሆነች “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” አይነት የአህያ ብሂል ኢትዮጵያን ወይ እኛ እንግዛት ካልሆነ ደግሞ ትጥፋ በሚል እየተንቀሳቀሱ ናቸው።
ከዚህ አንጻር መልሶ ስልጣን ለመቆጣጠር ፍላጎት አለ፤ ያ የማይሳካ ከሆነ ደግሞ ኢትዮጵያ እንደ አገር መቀጠል የለባትም፤ እኛ የዛን ክልል ማህበረሰብ ለይተን እንገዛዋለን (እናስተዳድረዋለን ሳይሆን እንገዛዋለን ነው)፤ ሌላው ደግሞ ሀገር ሲቃጠል ዳር ሆነን እናያለን የሚል ስሜት አላቸው።

ይህ ሁሉ የሚሆነውም ለዚሁ ነው። ‹‹የሴራ ፖለቲካ የህወሓት የተካነበት ነው። የሚያውቁት የሚናገሩትም ይሄንኑ ነው። ››ያሉት አቶ ታዬ፣ይህንንም በምሳሌ ሲያብራሩ ደርግ የመሬት ላራሹ ጥያቄን ሲመልስ ሁሉም የኢትዮጵያ አርሶአደሮች በአዎንታ ነው የተቀበሉት መሆኑን ጠቅሰዋል። ‹‹ያንንም ትግራይ ላይም ጭሰኛ የነበሩ ዜጎች መሬት ሲያገኙ ደርግን ተቀብለውታል። ህወሓት መጀመሪያ መጥቶ ሲሰብካቸውም “እኛ መሬት አግኝተናል፤ ከዚህ በኋላ ሌላ አንፈልግም” ሲሏቸው፤ ሲያደርጉ የነበረው የደርግ ልብስ በመልበስ ደርግን መስለው ማታ ማታ እየገረፉና እየገደሉም ጭምር፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ እየመጡ ደርግ ገዳይ ነው፤ ደርግ እንደዚህ ነው፤ ይደፍራል፣ ይገድላል፣ ይገርፋል ብለው ይሰብኳቸው እንደነበር የሚያውቋቸው ይናገራሉ ሲሉ ያብራራሉ።

ከኢህአፓ ጋር የነበረውም ይሄው እንደሆነ ጠቅሰው፣አሲምባ ላይ በሴራ ነው በርካታ ሺዎች የኢህአፓ አባላት እንዲያልቁ የተደረገው ብለዋል።
እንደ አቶ ታዩ ገለጻ፤የሀውዜንም ሁኔታ ሰዎች የሚመለከቱት ያኔ ደርግ ከትግራይ ጥሎ ስለወጣ ከዚህ በኋላ የሰበካችሁን ትግራይን ነጻ እንድናውጣ ነበረ፤ ትግራይ ውስጥ ደርግ የለም፤ ስለዚህ ከዚህ በኋላ አንዘምትም በሚል ወታደሮቻቸው ጥያቄ ሲያነሱ በደርግም ውስጥ ከነበሯቸው ሰዎች ጋር በመቀናጀት በሴራ ያ እልቂት እንዲፈጠር አደረጉ። ከዛም ደርግ ከምንጩ ካልጠፋ በስተቀር እዚህ ሰላም ልናገኝ አንችልም የሚል ሰበካ አመጡ። እናም ከመጀመሪያው አንስቶ በሴራ ነው እዚህ የደረሱት። አሁንም በሴራ እንጂ በትክክለኛ መንገድ በያዝነው አስተሳሰብ ልናሸንፍ እንችላለን ብለው አምነውም አያውቁም።

ይሄ ሴራ ባለፉት 27 ዓመታትም በኦሮሞና በአማራ መካከል በኢህአዴግ ውስጥም በነበሩት ብአዴንና ኦህዴድ ውስጥም፤ ከዛ ውጪም በልሂቃን መካከል መቃቃር እንዲኖር ሆን ተብሎ የተሰራና የተሰላ ስሌት ነበር ያሉት አቶ ታዬ፣ ያ ስሌት ደግሞ አማራና ኦሮሞ ሊታረቅ የማይችል ቅራኔ አላቸው የሚል መሆኑን ገልጸዋል። ይሄንንም በመጽሐፍ ጭምር መጻፋቸውን ፣በሚዲያዎችና በጋዜጣም ብዙ መሰበኩን አቶ ታዬ ጠቅሰዋል።
ለተጨማሪ https://www.press.et/Ama/?p=36169
‹‹ለእውነተኛ ትግል በረሀ የገቡ ብዙ የትግራይ ልጆች በህወሃት ሴረኛ ቡድን ተገድለዋል›› ሊላይ ሃይለማርያም ረዳ የቀዳማይ ወያነ መስራች የብላታ ሃይለማርያም ልጅ
********************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ፦ ለእውነተኛ የህዝብ ትግል በረሀ የገቡ ብዙ የትግራይ ልጆች በህወሃት ሴረኛ ቡድን በበረሀ የትጥቅ ትግል ወቅት መገደላቸውን የቀዳማይ ወያነ መስራች የብላታ ሃይለማርያም ልጅ ሊላይ ሃይለማርያም ረዳ አስታወቁ። ህዝባችንን ከዚህ ማፍያ ቡድን እንታደገው ሲሉም ጥሪ አቀረቡ፡፡
አቶ ሊላይ ሃይለማርያም በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት፤ የበረሀ ትግል ሲጀመር ትግሉን የተቀላቀሉ ኃይሎች ሁለት ባህሪ ነበራቸው፡፡ አንደኛው የህዝቡን እውነተኛ ጥያቄ ይዞ ለመታገል የገባ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ከህዝብ ጥያቄ ይልቅ ስውር የሆነ ተልእኮ አንግቦ የተቀላቀለ ነው፡፡ ለተጨማሪ https://www.press.et/Ama/?p=36166
‹‹ለእውነተኛ ትግል በረሀ የገቡ ብዙ የትግራይ ልጆች በህወሃት ሴረኛ ቡድን ተገድለዋል›› ሊላይ ሃይለማርያም ረዳ የቀዳማይ ወያነ መስራች የብላታ ሃይለማርያም ልጅ
********************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ፦ ለእውነተኛ የህዝብ ትግል በረሀ የገቡ ብዙ የትግራይ ልጆች በህወሃት ሴረኛ ቡድን በበረሀ የትጥቅ ትግል ወቅት መገደላቸውን የቀዳማይ ወያነ መስራች የብላታ ሃይለማርያም ልጅ ሊላይ ሃይለማርያም ረዳ አስታወቁ። ህዝባችንን ከዚህ ማፍያ ቡድን እንታደገው ሲሉም ጥሪ አቀረቡ፡፡
አቶ ሊላይ ሃይለማርያም በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት፤ የበረሀ ትግል ሲጀመር ትግሉን የተቀላቀሉ ኃይሎች ሁለት ባህሪ ነበራቸው፡፡ አንደኛው የህዝቡን እውነተኛ ጥያቄ ይዞ ለመታገል የገባ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ከህዝብ ጥያቄ ይልቅ ስውር የሆነ ተልእኮ አንግቦ የተቀላቀለ ነው፡፡
1968 ዓ.ም ጥቅምት ወር ሕወሃትን እንደተቀላቀሉ ያስታወሱት አቶ ሊላይ፣ ገሰሰ አየለ፣ ሙሴ ወደ በረሀ የገቡት ለእውነተኛ የህዝብ ትግል እንደነበር አመልክተዋል። እነዚህ የትግሉ መስራቾች ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ እንደነበራቸውም አስታውቀዋል።
ገሰሰ አየለ፣የትግራይ መገንጠል የሚባለውን እንደማይቀበልና ስህተት መሆኑንም ይናገር እንደነበር አመልክተው፤ የስብሓት ነጋ እና የአባይ ፀሃየ ቡድን ይህ ስላልጣመው የውጪ ግንኙነት እንዲሰራ በሚል በሱዳን በኩል እንዲወጣ ተደርጎ በመንገድ በነሱ አጃቢዎች ሆነ ተብሎ መገደሉን ጠቁመዋል፡፡
ገሰሰ፣ ደደቢት በረሀ ሲሄዱ የተሻለ ኢኮኖሚ፣ መሳሪያና የተሻለ ህዝባዊ ድጋፍ እንደነበረው ጠቅሰው፤ የገሰሰ ወደ በርሀ መግባት አብዛኞቹ የሽሬ ልጆች ለትግል እንዲነሳሱ የሞራል አቅም ፈጥሮ እንደነበር አስታውሰዋል። በርካታ የሽሬ ልጆች ወደ ትግሉ መቀላቀላቸው ያስደነገጣቸው አቶ ስብሓት ነጋ፣ ‹‹ገሰሰ ፊውዳል ነው›› ብለው የስም ማጥፋት ዘመቻ እንደጀመረቡትም ተናግረዋል።
እየመጣ የአመራሩን ስፍራ በስፋት እንደተቆጣጠረው አመልክተው፤ ይህ ቡድን የሽሬ ልጆችን ‹‹ሰላይ ናችሁ›› በሚል ይገድል እንደነበር ተናግረዋል። በዚህ ሴራም ብዛት ያላቸው የሽሬ ልጆች መገደላቸውን አስታውቀዋል።
በወቅቱ ከኢዲዩ ጋር በተደረገው አስከፊ ጦርነት ብዙ ታጋዮች መሰዋታቸውን ጠቁመው፤ ከኢዲዩ ጋር ወደ ጦርነት ለመግባት ምንም ምክንያት አልነበረም ብለዋል። ችግሩን በውይይት መፈታት ይቻል እንደነበር የገለጹና ውጊያው አያስፈልግም ብለው ጥያቄ የሚያነሱ ሰዎች በወቅቱ እንዲገደሉ ተደርጓል ብለዋል።
ከ1967 እስከ 68 ዓ.ም የሽሬን ልጆች ካጸዱ በኋላ በ1969 ውጊያ የሚመሩ ሰዎች በአቶ ስብሓት ነጋ የቅርብ ዘመዶች መተካት መጀመራቸውን ገልጸዋል። ከዚያም ውጊያዎች መበላሸት መጀመራቸውን ያስተዋሉ ታጋዮች አቅም ያላቸው ሰዎች እያሉ ለምንድን ነው የማይመጥኑ ሰዎች እንዲመሩንና ውጊያ እንዲበላሽ የሚደረገው ሲሉ መጠየቅ መጀመራቸውንም ጠቅሰው፤ጉዳዩ በወቅቱ የመወያያ አጀንዳ ሆኖ እንደነበርም አስታውሰዋል።
መደመር መጽሐፍ በኦሮምኛ ቋንቋ በድምፅ ተዘጋጅቶ ቀረበ.. https://medemer.et/
የጠፋው ቅርስ በ50 ዓመቱ ተገኘ
*************************
(ኢ ፕ ድ)
በደቡብ ጎንደር ዞን አንዳቤት ወረዳ ከደብረ ሰላም ወርቻሜ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በ1962 ዓ.ም ጠፍቶ የነበረው የስንክሳር መጽሐፍ ተገኘ፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ፀሐይ ጸዳሉ ነጋሽ እንዳሉት ከጠፋ ከ50 ዓመታት በኋላ የተገኘው ስንክሳር ከመጋቢት እስከ ነሐሴ የሚነበበውን የመንፈቅ ምንባብ የያዘ ነው፡፡ ስንክሳሩ ከ20 ኪሎ ግራም በላይ ክብደት ያለው፡፡
ስንክሳር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም የቅዱሳንን እና የጻድቃንን ታሪክ የያዘ ትልቅ ዓመቱን መገልገያ ነው፡፡ በኢትዮጵያ አሉ ከሚባሉ የሚዳሰሱ ቅርሶች መካከልም ትልቅ ሀገራዊ ገጽታ እና ሃይማኖታዊ ግልጋሎት ያለው ነው፡፡
ቅርሱ ከጠፋ ጊዜ ጀምሮ የማፈላለግ ሥራ ሲከናወን ቆይቶ ሐምሌ 4/2012 ዓ.ም በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ደብረ-ገነት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በማዳበሪያ ተጠቅልሎ ጸሎት በሚያደርጉ እናቶች ተገኝቷል፡፡ ሕጋዊ ሂደቱን ተከትሎ ወደ ቦታው መመለሱንም ዋና ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡
መልአከ ፀሐይ ጸዳሉ እንዳሉት ዞኑ የበርካታ ታሪካዊ እና ሃይማኖታዊ ቅርሶች መገኛ ቢሆንም ተገቢ ጥበቃና እንክብካቤ ስለማይደረግላቸው ለጥፋት እየተዳረጉ ነው፡፡ ሀገረ ስብከቱም ከመንግሥት ጋር በመሆን በሰዎች እጅ የሚገኙ ቅርሶችን እያፈላለገ ነው፡፡ በዚህ ቅርሶች እየተገኙ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ በቅርቡም ሁለት ግለሰቦች ቅርስ ተገኝቶባቸው በሕግ ተጠያቂ ተደርገው በእስር ላይ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡ ነገር ግን ቅርስ በሚዘርፉ እና በሚያጠፉት ላይ የሚወሰደው ርምጃ አስተማሪ አለመሆኑን አንስተዋል፡፡
ቅርሶችን ለመንከባከብ በርካታ ሥራዎች ቢሠሩም ቅርሶች እየተዘረፉ መሆኑን የዞኑ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አስታውቋል፡፡ የሕዝቡ ተሳትፎ አናሳ መሆኑ፣ በአጥፊዎች ላይ የሚወሰደው ርምጃ ጠንካራ አለመሆኑ እና በርካታ ቅርሶች በሰዎች እጅ መገኘታቸው በምክንያትነት ተጠቅሰዋል፡፡
የመምሪያ ኃላፊዋ ወይዘሮ ሰናይት አስራደው እንዳሉት መንግሥት በቅርሶች ላይ ቁጥጥርና ክትትል እንደሚያደርግ እና አዳዲስ ቅርሶችን እንደሚመዘግብ አስታውቋል፡፡ የተመዘገቡት በየዓመቱ ኦዲት ስለሚደረግባቸው የመጥፋት ዕድላቸው ዝቅተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ማኅበረሰቡ ይሰረቅብናል በሚል በእጅ ያሉ ቅርሶችን ለማስመዝገብ ፈቃደኛ አለመሆን ግን ፈተና ሆኖ ቆይቷል፡፡ በሚፈለገው ደረጃ ባይሆንም ግንዛቤ በመፍጠር ብዙ ቅርሶች ከማኅበረሰቡ ተመልሰው ምዝገባ ተደርጎላቸዋልም ብለዋል፡፡
ቀደም ብሎ የተዘረፉ ቅርሶችን የማፈላለግ ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም መምሪያ ኃላፊዋ አስታውቀዋል፡፡ የታወቁ ጥንታዊ ቅርሶች ባሉባቸው ቦታዎችም የደብር ሙዚዬም በማሠራት ተገቢው እንክብካቤ ለቅርሶች እንደሚደረጉ ተመላክቷል፡፡
ሥራው በመንግሥት ብቻ ውጤታማ ስለማይሆን ሕዝቡ ቅርሱን ጠንክሮ ሊጠብቅ እንደሚገባም ወይዘሮ ሰናይት መክረዋል፡፡ በተለያዩ አጋጣሚዎች በእጃቸው ያሉ ቅርሶችን ለመንግሥት እንዲያሳውቁም ጥሪ አቅርበዋል ሲል የዘገበው አብመድ ነው።
የጠፋው ቅርስ በ50 ዓመቱ ተገኘ
*************************
(ኢ ፕ ድ)
በደቡብ ጎንደር ዞን አንዳቤት ወረዳ ከደብረ ሰላም ወርቻሜ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በ1962 ዓ.ም ጠፍቶ የነበረው የስንክሳር መጽሐፍ ተገኘ፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ፀሐይ ጸዳሉ ነጋሽ እንዳሉት ከጠፋ ከ50 ዓመታት በኋላ የተገኘው ስንክሳር ከመጋቢት እስከ ነሐሴ የሚነበበውን የመንፈቅ ምንባብ የያዘ ነው፡፡ ስንክሳሩ ከ20 ኪሎ ግራም በላይ ክብደት ያለው፡፡
ስንክሳር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም የቅዱሳንን እና የጻድቃንን ታሪክ የያዘ ትልቅ ዓመቱን መገልገያ ነው፡፡ በኢትዮጵያ አሉ ከሚባሉ የሚዳሰሱ ቅርሶች መካከልም ትልቅ ሀገራዊ ገጽታ እና ሃይማኖታዊ ግልጋሎት ያለው ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአፍሪካ 100 ስመ ጥር ግለሰቦች መካከል አንዱ ሆኑ
*****
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እ.አ.አ 2020 ላይ በአመራር ክህሎት ባበረከቱት አስተዋጽኦ ከአፍሪካ 100 ስመጥር ግለሰቦች መካከል በግንባር ቀደምትነት ተጠቃሽ ሆነዋል።
በዓለም የታዋቂ ሰዎችን ዝርዝር የሚያወጣው ተቋም /Reputation Poll International/ በተለያዩ ዘርፎች የ100 ስመ ጥር ግለሰቦችን ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል።
በስም ዝርዝሩም 47 ሴቶች እና 53 ወንዶች አፍሪካውያን በአመራር፣ በመዝናኛ፣ በትምህርት፣ በንግድ እና በበጎ አድራጎት ሥራዎች መመረጣቸው ተነግሯል።
ከእነዚህ መካከል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በአመራር ክህሎታቸው በኢትዮጵያ ባመጡት ለውጥ 100 ስመ ጥር ግለሰቦች መካከል ተጠቃሽ ሆነው ተመርጠዋል።
ከዚህም ባሻገር ኢትዮጵያዊቷ ቤተልሔም ጥላሁንን ጨምሮ ሁለት የአፍሪካ ግለሰቦች በቢዝነስ ዘርፍ ከስመ ጥር አፍሪካውያን ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን ሪፑቴሽን ፖል የተሰኘው ድረ ገጽ አስነብቧል።
ኢትዮ ቴሌኮም በ2012 በጀት አመት 47 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ገቢ አገኘ
የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ ገቢው ከእቅዱ 105 ነጥ ብ 1 በመቶ ብልጫ አለው ብለዋል።
ይህም ከባለፈው አመትም ጋር ሲነጻጸር በ31 ነጥብ 4 በመቶ ብልጫ መኖሩን ጠቁመው ÷ ተቋሙ ከውጭ የስልክ ጥሪ 147 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘቱን ገልጸዋል። ከዚያም ባለፈ 10 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ብድር መመለስ ተችሏልም ነው ያሉት።
የዚምባብዌ ሚኒስትር በኮሮናቫይረስ ሕይወታቸው አለፈ
----------------------------------------------------
የዚምባብዌ የግብርና ሚኒስትር ፔሬንስ ሺሪ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉን የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ገልፀዋል።
ሚኒስትሩ በኮሮናቫይረስ መሞታቸው የተረጋገጠው በምርመራ መሆኑንም የአገሪቱ መንግሥታዊ ጋዜጣ ሄራልድ ፕሬዚዳንቱን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
ሚኒስትሩ የአለም አቀፉ ጤና ድርጅት በሚያዘው በኮሮናቫይረስ ለሞቱ ሰዎች የሚደረገው የቀብር ስነ ስርዓት መመሪያ መሰረት በነገው እለት እንደሚቀበሩም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።
የ65 አመቱ ሚኒስትር በመዲናዋ ሃራሬ በሚገኝ የግል ሆስፒታል ረቡዕ እለት ሕይወታቸው ማለፉ BBC
#አረንጓዴአሻራ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመነን የልጃገረዶች አዳሪ ትምህርት ቤት በመገኘት ከትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ጋር ችግኝ ተክለዋል፡፡
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሊት የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ደስታቸውን እየገለጹ ነው
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሊት የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ደስታቸውን እየገለጹ ለግድቡ ያላቸውንም ድጋፍ እየገለጹ ነው።
በከተማዋ የተለያዩ መኖሪያ ሰፈሮች ህዝቡ በየቤቱ በራፍ በመሆን፤ በጋራ መኖሪያ ቤት ያሉ ደግሞ በየብሎኮቻቸው በረንዳ ላይ በመውጣት ድምጻቸውን ከፍ በማድረግ ደስታቸውን ገልጸዋል።
በተመሣሣይም ተሽከርካሪዎች ጡሩንባዎቻቸውን በማሰማት በግድቡ የመጀመሪያ ሙሊት የተሠማቸውን ደስታ እየገለጹ ነው።
በአፍሪካ ህብረት የሚመራውና ለጊዜው ተቋርጦ የነበረው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር ዛሬ ይቀጥላል
**************************
(ኢ ፕ ድ)
በአፍሪካ ህብረት መሪነት ለ11 ቀናት ሲካሄድ ቆይቶ ከሁለት ሳምንታት በፊት እ.አ.አ ሐምሌ 13/2020 የተቋረጠው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር ዛሬ ከሰአት ይቀጥላል።
ድርድሩ ከሳምንት በፊት ሊቀጥል የነበረ ቢሆንም በሱዳን በኩል በቀረበው ለአንድ ሳምንት የይዘግይልኝ ጥያቄ መሠረት ለአንድ ሳምንት መዘግየቱን የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የሶስትዮሽ ድርድሩ ከዛሬ ከሰዓት ጀምሮ ለቀጣዩ አንድ ሳምንት ይቀጥላል ተብሏል፡፡
የዚህ ሳምንቱ ድርድር ቀደም ሲል ከተካሄደው የ11 ቀናቱ ድርድር በኋላ ለመሪዎች በቀረበው ሰነድ መሠረት መሪዎቹ ባስቀመጠጡት አቅጣጫ የሚቀጥል ሲሆን፤ ኢትዮጵያ እንደ ከዚህ ቀደሙ ፍትሓዊና ምክንያታዊ ተጠቃሚነትን መሠረት ባደረገ ሁኔታ ሁሉንም ወገን ተጠቃሚ ባደረገ መልኩ ድርድሩን ለመቋጨት ትሠራለች ሲል ሚኒስቴር መስሪያቤቱ አስታውቋል።
ከነሃሴ መጨረሻ ሳምንት በፊት ምንም አይነት የቀጣይ አመት የትምህርት ምዝገባ ማካሄድ የተከለከለ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ
********************************
(ኢ ፕ ድ)
ከነሃሴ መጨረሻ ሳምንት በፊት ምንም አይነት የቀጣይ አመት የትምህርት ምዝገባ ማካሄድ የተከለከለ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች ምዝገባ ለማድረግ ወላጆችን እያስገደዱ መሆኑ እና ምዝገባ በማካሄድ ላይ መሆናቸው ተሰምቷል።
ይህንን በተመለከተም የትምህርት ሚኒስቴር የኮምኒኬሽን ጉዳዬች ዳይሬክተር ወ/ሮ ሐረጓ ማሞ ማንኛውም ትምህርት ቤት ከነሀሴ መጨረሻ በፊት ምንም አይነት ምዝገባ ማካሄድ እንማይቻል እና ይህንን ወሳኔ አልፈው ምዝገባ በሚያካሂዱ ትምህርት ቤቶች ላይም አስፈላጊው የዕርምት እርምጃ እንደሚወሰድ ገልፀዋል።
የምዝገባው የግዜ ሰሌዳ እንዲራዘም የተፈለገው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት መስፋፋትን ተከትሎ ወላጆች እና ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት የሚያደርጉትን ጉዞ በመግታት የ ቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ መሆኑን ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።
ወላጆች ከተሳሳተ መረጃ እራሳቸውን በመጠበቅ እና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በመከላከልእና መንግስት ትምህርት እንዲጀመር ሲያሳውቅ ብቻ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን አውቀው ልጆቻቸውን በእጃቸው ላይ የሚገኙትን የመማሪያ ቁሳቁሶች እንዲያነቡና እንዲያጠኑ ድጋፍ እንዲያደርጉ የትምህርት ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል።
የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ስዩም መስፍን "የፌደራል መንግስት፣ ኤርትራ እና አማራ ሊወረን ነው ታገሉ” በማለት የወጅራት ነዋሪዎችን ቢቀሰቅሱም ህዝቡ አሳፍሮ እንደመለሳቸው ተገለጸ
*************************
(ኢ ፕ ድ)
የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ስዩም መስፍን "የፌደራል መንግስት፣ ኤርትራ እና አማራ ሊወረን ነው ታገሉ” በማለት የወጅራት ነዋሪዎችን ቢቀሰቅሱም ህዝቡ አሳፍሮ እንደመለሳቸው ተገለጸ።
ትናንት በትግራይ ክልል የወጅራት ልዩ ስሙ ዓዲ ቀይሕ ነዋሪዎች የተካሄደውን ሰላማዊ ሰልፍ ያስተባበሩትና ስማቸው ሊገለጽ ያልፈለጉ ወጣቶች ለዝግጅት ክፍላችን እንደተናገሩት፤ በበቅርቡ የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ስዩም መስፍን የዋጅራት ህዝብን ህዝብ ሰብስበው፤ “ከድሮ ጀምሮ የወጅራት ህዝብ ጀግና ነው፤ አልገዛም ባይ ነው፤ ስለዚህ አሁንም የፌደራል መንግስት፣ ኤርትራ እና አማራ ሊወረን ነው ታገሉ” በማለት ቀስቅሰዋል።
የሰልፉ አስተባባሪዎች እንደገለጹትም፤ አቶ ስዩም የወረዳዋ ነዋሪዎች ያቀረበውን ጥያቄ ለማለባበስና ሌላ ውዥንብር ሊፈጥሩባቸው ቢሞክሩም
ህዝቡ ግን “እኛ የተሰበሰብነው ጥያቄያችን ልትመልሱልን መስሎን እንጂ ከማንም ጋር አንዋጋም በውጊያ ያተረፍነው ነገር የለም፤ ከሁሉም ጋር ተባብረን መልማት ነው የምንፈልገው” በማለት ለአቶ ስዩም መልስ እንደሰጧቸው የሰልፉ አስተባባሪዎች አስታውቀዋል።
ትናንት የተካሄደው ሰልፍም የህወሓት አመራሮች ጥያቄያችንን ከመመለስ ይልቅ የማፈንና ጥያቄውንም የማዳፈን አካሄዳቸው እየበዛ በመምጣቱ መሆኑንም ገልጸዋል።
በሰልፉ ከነበሩ መፈክሮች ውስጥ “ወረዳችን ይመለስልን፤ ለዛችን ባህላችን ይከበርልን፤ ወጣቱ እየተሰደደ ነውና ስራ ይፈጠርልን፤ ለውጥ እንፈልጋለን” የሚሉ እንደሚገኙበት አስተባባሪዎቹ ተናግረዋል።
ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ወረዳችን ይመለስልን የሚል ሰለማዊ ሰልፎች ቢደረጉም መንግስት ይሄን ከመመለስ ይልቅ ሌላ ስም በመለጠፍ እያሸማቃቸው እንደሆነ እነዚህ አስተያየት ሰጪዎቹ ገልጸዋል።
ጥያቄ ያቀረቡ ወጣቶችን እየመረጡ ማሰቃየት እስርና ድብደባም በህዝቡ እየተፈጸመባቸው እንደሆነ የሰልፉ አስተባባሪዎች ሳይገልጹ አላለፉም።
ተቋሙ ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት መዘረፉን አስታወቀ
********************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ:- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2012 በጀት ዓመት በአራት ክልሎች የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶች ላይ በተፈጸመ ዘረፋ ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ እንደደረሰበት አስታወቀ።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታዬ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በበጀት ዓመቱ በመላ አገሪቱ በተቋሙ ልዩ ልዩ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚፈጸሙ ዝርፊያዎች ተባብሶ መቀጠሉን ጠቁመው፤ በበጀት ዓመቱ በአራት ክልሎች ልዩ ልዩ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶች ላይ በተፈጸመ ዘረፋ ብቻ ተቋሙ 35 ሚሊዮን 621 ሺ 688 ብር ኪሳራ ደርሶበታል።
ዳይሬክተሩ እንዳብራሩት፣ አንድ ትራንስፎርመር በአማካኝ 400 ሺ ብር የሚያወጣ ሲሆን፣ ከ20 እስከ 25 ዓመት አገልግሎት ይሰጣል። እንዲሁም አንዱ ትራንስፎርመር በትንሹ እስከ 200 አባወራዎችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ የሚያደርግ በመሆኑ በመላ አገሪቱ በኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መሠረተ ልማቶች ላይ በሚደርሱ ስርቆቶች ተቋሙ አገልግሎቱን ለኅብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ፈታኝ ከማድረጉ ባሻገር በአገሪቱ ለሚታየው የኤሌክትሪክ አገልግሎት መቆራረጥ ዋነኛ ምክንያት መሆኑን ይናገራሉ።
አቶ መላኩ በበጀት ዓመቱ በኦሮሚያ ክልል 14 ሚሊዮን 130ሺ 314 ብር፣ በአማራ ክልል ሦስት ሚሊዮን 977ሺ ሦስት ብር፣ በአፋር ክልል 514 ሺ 370 ብር በደቡብ 17 ሚሊዮን ብር በድምሩ በአራቱ ክልሎች ልዩ ልዩ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶች ላይ በተፈጸመ ዘረፋ ብቻ ተቋሙ 35 ሚሊዮን 621 ሺ 688 ብር ኪሳራ እንደደረሰበት ተናግረዋል።
በበጀት ዓመቱ ተቋሙ በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶች ላይ ዘረፋ የፈጸሙና በኃይል ስርቆት ላይ በተሰማሩ 195 ግለሰቦች ላይ ክስ መመስረቱን ዳይሬክተሩ ጠቁመው፤ በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶች ላይ ዘረፋ የፈጸሙ 30 ግለሰቦች ከ3 እስከ 10 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት መቀጣታቸውን ተናግረዋል።
አዲስ ዘመን ሐምሌ 30/2012
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሰራተኞች አነስተኛ ደመወዝ ላላቸው ባልደረቦቻቸው ድጋፍ አደረጉ
****************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ፤ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሰራተኞች እና አመራሮች በተቋሙ ውስጥ ለሚሰሩና የወር ደመወዛቸው አነስተኛ ለሆኑ የስራ ባልደረቦቻቸው የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ።
“እኛው ለእኛው” በሚል መርህ የተደረገው ይሄው ድጋፍ የተቋሙ ሰራተኞችና አመራሮች ከወር ደሞዛቸው በመቀነስ ከለገሱት የተገኘ መሆኑን የድርጅቱ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወንድም ተክሉ አስታውቀዋል።
እንደ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገለጻ፤ ይህ ድጋፍ ትልቅ ስራ ነው ተብሎ የታሰበ አይደለም፤ ነገር ግን በአንድ ተቋም ውስጥ ሊኖር የሚገባውን የእርስ በእርስ መተሳሰብን ለማጠናከር ታስቦ የተደረገና ሌሎች መሰል ተቋማትም ይሄንኑ ተግባር እንዲያከናውኑ ለማነሳሳት ነው።
የዚህ አይነቱ እርስ በእርስ የመተሳሰብና የመረዳዳት ባህልን በተቋም ውስጥ መገንባት ከተቻለ ተቋሙ ሊያሳከው የሚፈልገውን ግብ ከዳር ለማድረስ እንደ አንድ ግብአት የሚረዳ ይሆናል ያሉት አቶ ወንድም፤ በሰራተኞች መካከልም መዋደድና መተሳሰብን የሚፈጥር ነው ብለዋል።
በቀጣይም በተቋሙ የሚታሰበው ትልቁ ስራ እነዚህ ሰራተኞች እራሳቸውን በኢኮኖሚ የሚጠቅሙበትን ሁኔታ ማመቻቸት መሆኑን የጠቆሙት አቶ ወንድም፤ የሰራተኛውን ችግር በቋሚነት ሊፈቱ የሚችሉ ስራዎች በተቋሙ እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።
ለሰራተኞቹ የተደረገውን ድጋፍ ያስተባበሩት ወ/ሮ ብርሃኔ ደመቀ እንደተናጉት፤ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ከተከሰተ ወዲህ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ አነስተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የኑሮ ጫናው በርትቶባቸዋል፤ ከዚህ አንጻር በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ውስጥ የሚገኙና የወር ገቢያቸው አነስተኛ የሆኑ ሰራተኞችን መደገፍ አስፈላጊ ሆኗል።
ይህንን የተቀደሰ ተግባር ከዳር ለማድረስም የድርጅቱ ሰራተኞችና አመራሮች ከወር ደመወዛቸው የሚቀነስ ገንዘብ በማዋጣት ለ43 የስራ ባልደረቦቻቸው ከጎናቸው መቆማቸውን በተግባር ማሳየት መቻላቸውን ወ/ሮ ብርሃኔ አብራርተዋል።
እንደ ወ/ሮ ብርሃኔ ገለፃ፤ እርስበርስ መረዳዳቱ በጣም አስፈላጊና ፈጣሪም የሚወደው ስራ ስለሆነ ድጋፍ የተደረገላቸውም ብቻ ሳይሆኑ ድጋፍ ያደረጉ ሰራተኞችም ደስተኛ ሆነዋል።
በእለቱ ድጋፍ ከተደረገላቸው ሰራተኞች መካከል የሆኑት ወ/ሮ ፀሀይ ደበሌ እና ወ/ሮ አበበች አስፋው እንደተናገሩት፤ የድርጅቱ ሰራተኞች ይህን መልካም ተግባር አስበው ድጋፍ በማድረጋቸው በእጅጉ ተደስተዋል። ይህ ክፉ ጊዜ እስኪያልፍ ድረስ እርስ በርስ እየተረዳዱ ማለፉን ፈጣሪ የሚወደው ተግባር ነው በሚል የስራ ባልደረቦቻቸው ያደረጉላቸው ድጋፍ ያልጠበቁት በመሆኑ ትልቅ ደስታን ፈጥሮላቸዋል። ለተደረገላቸው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሰራተኞችና አመራሮች ከዚህ በፊትም በተመሳሳይ የወር ደመወዛቸው አነስተኛ ለሆኑ ሰራተኞች ተመሳሳይ ድጋፎችን ማድረጉ ይታወሳል።
አዲስ ዘመን ሐምሌ 30/2012