Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የኮቪድ-19 አንቲቦዲ (Antibody) የቅኝት ዳሰሳ አስመልክቶ የወጣ መግለጫ

በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ምርመራ ከጥር 29 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የተጀመረ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በሁሉም ክልሎች በሚገኙ ላቦራቶሪዎች እስከ ሰኔ 14 ቀን 2012 ዓ.ም 216¸328 ምርመራ ተደርጓል። ይህ የምርመራ አይነት የኮቪደ-19 በሽታ ያለበት ሰው ላይ ቫይረሱን ለመለየት የሚረዳ የሞለኪዩላር ምርመራ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በማህበረሰብ ውስጥ ያለውን የበሽታ ስርጭት ለመረዳት (surveillance) እና በአንጻሩ ምላሽ ለመስጠት እንዲሁም ይበልጥ ተጋላጭ በሆኑት የማህበረሰባችን ክፍሎች ላይ ያለውን የኮቪድ-19 በሽታ ስርጭት ለማወቅ የሚረዳ አንቲቦዲ ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ይታመናል፡፡ ይህ የአንቲቦዲ የቅኝትና ዳሰሳ ምርመራ አይነት በአገራችን ለምርምር ለመጠቀም እና ከላይ የተጠቀሱትን ዓላማዎች ለማሳካት ከሰኔ 15 እሰከ ሀምሌ 7 ቀን 2012 ድረስ በሀገራችን የሚካሄድ ይሆናል።

አንቲቦዲ ማለት ሰውነታችን ለበሽታ በሚጋለጠበት ወቅት ለበሽታው ከተጋለጠ ከአንድ እስከ ሶስት ሳምንት ድረስ በሽታውን ለመከላከል ሰውነታችን የሚያመርታቸው የበሽታ ተከላካዩች ናቸው። በሰውነታችን ውስጥ የአንቲቦዲ መመረት በእድሜ፣ የአመጋገብ ሁኔታ፣ የምንጠቀማቸው መድሁኒቶች፣ የበሽታው ከባድነት እና ተጓዳኝ በሽታዎች ላይ ይወሰናል። ምርመራው ከሰውነታችን ከ3-5 ሚሊ ሊትር ደም ናሙና በመውሰድ የሚደረግ ሲሆን የበሽታው ተከላካዮች (አንቲቦዲ) እንደየበሽታው ዓይነት የሚለያዩ ሲሆን ምርመራው ኮቪድ-19 ለመካላከል እና ለ መቆጣጠር ለሚደረገው የቅኝት ዳሰሳ ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው። ነገር ግን የአንቲቦዲ ምርመራ ውጤትን ብቻ ተጠቅሞ ህክምና መስጠት አይቻልም።

ይህ የቅኝት ዳሰሳ በሀገራችን ያለውን የኮሮና ቫይረስ በሽታ (ኮቪድ-19) ስርጭት ለማወቅ ከሰኔ 15 ቀን 2012 ጀምሮ በአዲስ አበባ፣ ድሬደዋ ከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በሁሉም ክልሎች ይካሄዳል። በመሆኑም ህብረተሰቡ፣ የጤና ባለሙያዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለትግበራው አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ እንጠይቃለን።
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 131 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው
.በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1297 ደርሷል
*****************************
(ኢፕድ)
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3238 የላብራቶሪ ምርመራ 131 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4663 ደርሷል።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 26 (10 ከጤና ተቋም እና 16 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን አንድ ናሙና ከማህበረሰብ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሰባ አምስት (75) ደርሷል፡፡

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሰማንያ አራት (84) ሰዎች (79 ሰዎች ከ አዲስ አበባ፣ 2ሰዎች ከኦሮሚያ፣ 2 ሰዎች ከትግራይ እና 1 ሰው ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1297 ነው።
ከአንድ እናት በአንድ ጊዜ የተወለዱ ሦስት ጨቅላ ህጻናት ኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው
=============================
በሜክሲኮ ከአንዲት እናት በአንድ ጊዜ አዲስ የተወለዱ ሦስት ጨቅላ ህጻናት በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ።
ጨቅላ ህጻናቱ በቫይረሱ አንዴት ሊያዙ እንደቻሉ በጤና ባለሙያዎች ላይ ግርታን የፈጠረ ሲሆን፤ የጤና ባለሥልጣናትም ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ነገር ሰምተው እንደማያውቁ ተናግረዋል።
ጨቅላ ህጻናቱ ምርመራ የተደረገላቸው ከተወለዱ በኋላ በሰዓታት ውስጥ ሲሆን ቫይረሱ እንዳለበት ከታወቀ ማንኛውም ሰው ጋር ምንም ዓይነት ንክኪ አልነበራቸውም ተብሏል። ቢ ቢ ሲ
በአዲስ አበባ ከተማ እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ መረጃዎችን ማግኘትና ሀሳብ መስጠት የሚቻልበት የኪነ ህንጻ እና ከተማ ማእከል ተከፈተ።

ማእከሉ መስቀል አደባባይ ፊትለፊት ላይ የተዘጋጀ ሲሆን የካፌ አገልግሎትና ዋይፋይ የተዘጋጀለት ነው።

በማእከሉ የትኛውም ዜጋ ስለከተማዋ እቅዶችና ፕሮጀክቶች መመልከትና የራሱን ሀሳብ በፅሁፍና በድምፅ መስጠት ይችላል።

የተሰጡት አስተያየቶች በቦታው የሚገኙ ባለሙያዎች በማሰባሰብ ለከንቲባው በየጊዜው የሚያቀርቡ ይሆናል።

የማእከሉ መቋቋም የከተማዋ ነዋሪ በከተማዋ ላይ ያለው ተሳትፎ እንዲጨምርና ስለ ከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች ላይ ግንዛቤ እንዲፈጠርና ግልፅነት ለመፍጠር ያለመ ነው።
ባለፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ 185 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3775 የላቦራቶሪ ምርመራ 185 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

በአጠቃላይ በአገሪቱ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4ሺህ 848 ደርሷል።

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 184 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 1 ሰው የውጭ ዜጋ ነው ተብሏል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 47 ወንዶች እና 138 ሴቶች ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸውም ከ3 ወር ህጻን እስከ 80 ዓመት እንደሚገኙም ተገልጿል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 160 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 2 ሰዎች ከሱማሌ ክልል፣ 7 ሰዎች ከኦሮሚያ፣ 1 ሰው ከሀረሪ ክልል፣ 4 ሰዎች ከአፋር ክልል፣ 2 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 1 ሰው ከጋምቤላ ክልል፣ 7 ሰዎች ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል እና 1 ሰው ከትግራይ ክልል መሆናቸውን ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 115 ሰዎች (81 ከአዲስ አበባ፣ 23 ከአማራ፣ 6 ከኦሮሚያ፣ 2 ከሀረሪ፣ 2 ከቤንሻንጉል ጉምዝና 1 ሰው ከትግራይ) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥርን 1412 አድርሶታል።

በአጠቃላይ ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ 3 ሺህ 359 ሰዎች ሲሆኑ ከነዚህ መካከል 38 በፀና የታመሙ መሆናቸው ተገልጿል።

በኢትዮጵያ እስካሁን 223 ሺህ 341 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል
አሜሪካ በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በግብጽ መካከል የተፈረመውን የመርህ ስምምነት እንድታከብር የአገሪቷ ጥቁር የኮንግረስ አባላት አሳሰቡ
***************************
(ኢ ፕ ድ)

አሜሪካም ሆነች ሌሎች አለም አቀፍ አካላት በኢትዮጵያ፣ በሱዳን እና በግብጽ መካከል እአአ በ2015 የተፈረመውን የመርሆች ስምምነት እንዲያከብሩ የአሜሪካ ጥቁር የኮንግረስ አባላት ስብስብ አሳሰበ።

የኮንግረስ አባላቱ ትናንት ባወጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ አሜሪካም ሆነች ሌሎች ዓለም አቀፍ ተዋንያን በሶስቱ አገራት መካከል እአአ በ2012 የተፈረመው የመርህ ስምምነት ማክበር አለባቸው ብለዋል።

ሶስቱ አገራት ወደ ስምምነት እንዲመጡ በአካባቢው ያሉ ዲፕሎማቶች በተለይም የአፍሪካ ህብረት ጉዳዩን እንዲፈታው አሜሪካም ሆነች ሌሎች አካለት ማገዝ አለባቸው ነው ያሉት።

ድርድሩ በጋራ ተጠቃሚነት፣ በመተማማንና በዓለም አቀፍ ህጎች መሰረት መጓዝ አለበት ያሉት አባላቱ፤ ይህ ታላቅ ግድብ ሲጠናቀቅ ለአፍሪካ ትልቁ የሃይል ምንጭ በመሆን ለኢትዮጵያም ብቻ ሳይሆን ለጎረቤቶቿ ጭምር የሚጠቅም ነው ብለዋል።

ግድቡ ከሶስቱ አገራት አንጻር ያለውን ፋይዳ በተናጠል በመግለጫቸው ያብራሩት የኮንግረስ አባላቱ፤ የግድቡ መጠናቀቅ ለግብጽ ግብርናም ሆነ ለሚዋዥቀው የወንዙ የውሃ ፍሰት አስተማማኝ በሆነ መልኩ የውሃ አቅርቦቷን ያሳድግላታል ብለዋል።

በተመሳሳይም ግድቡ ለሱዳን የውሃ አቅርቦት ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑን በመጥቀስ፤ በተለይም የደለል መጠንን በመቀነስ፣ ግብርናን በማስፋፋት የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦትን በማሳደግና የጎርፍ አደጋን በመከላከል በኩል ትልቅ ፋይዳ አለው ብለዋል። ለኢትዮጵያን ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን አብራርተዋል።

ከዚህ አንጻር የግድቡ መጠናቀቅ ለኢትዮጵያ ለግብጽ እና ለሱዳን የውሃ፣ የኤሌክትሪክ አቅርቦት እና ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ ብሎም ለቀጣናው የግብርና ስራ ያለው አስተዋጾ የላቀ መሆኑን አባላቱ ገልጸዋል።

በተዘረዘሩት ምክንያቶች ጥቁር የአሜሪካ የኮንግረስ አባላት የግድቡን መጠናቀቅ እንደሚደግፉና ለዚህም ሰላማዊ ውይይቶችን እንደሚያበረታቱ ጠቅሰው፤ የአፍሪካ ህብረት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለሚያደርጉት ሰላማዊና ሁሉንም ተጠቃሚ ለሚያደርግ ጥረት ድጋፋቸውን እንደሚሰጡ አስታውቀዋል።
እህትማማቾች በካቲካላ ሞቱ

ታህሳስ 21 ቀን 1965 ዓ.ም የታተመው አዲስ ዘመን ጋዜጣ እህትማማቾች በቅርብ ያገኙትን አረቄ በመጠጣታቸው ህይወታቸውን ስላጡ ታዳጊዎች ተተከታዩን ዘገባ አስነብቦ ነበር።

ወይዘሪት ብዙነሽ ገብሬና ወይዘሪት እመቤት ገብሬ የተባሉ እህትማማቾች የእህል አረቄ ጠጥተው መሞታቸውን ከሸዋ ፖሊስ ማስታወቂያ ክፍል የተገኘው ዜና ገለጠ። ልጆቹ ለሞት የበቁት ወላጅ እናታቸው አረቄውን ካወጡ በኋላ አልጋ ስር አስቀምጠውት ወደ ገበያ ሲሄዱ ከተቀመጠበት ቦታ አንስተው በመጠጣታቸው ነው።

ሟቾቹ አረቄውን እንደጠጡ በያሉበት ተዘርረው ወድቀው ነበር። በኋላ ግን ሰው ደርሶ ለህክምና ፍቼ ጤና ጣቢያ ተወስደው ህክምና ቢደረግላቸውም ለመዳን ተስፋ በማጣታቸው በ 10 ሰዓት ልዩነት ሁለቱም ህይወታቸውን አጥተዋል።

በሁለቱ እህትማማቾች ላይ ይህ የሞት አደጋ የደረሰው ታህሳስ አራት ቀን 1965 ዓ.ም በሰላሌ አውራጃ በግራር ጃርሶ ወረዳ ግዛት ፍቼ ከተማ ውስጥ ነው። ወይዘሪት ብዙነሽ ገብሬ ዕድሜዋ ስምንት ዓመት ሲሆን ፣ የወይዘሪት እመቤት ደግሞ ስድስት ዓመት መሆኑን የማስታወቂያ ክፍሉ ባገኘው ሪፖርት መሰረት አስረድቷል።
ኮሮና ዛሬ በኢትዮጵያ
የ114 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ ከኮሮና ቫይረስ ሙሉ በሙሉ አገግመው ከኤካ ኮተቤ ከሆስፒታል ወጡ

የ114 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ ከኮሮና ቫይረስ ሙሉ በሙሉ አገግመው ከኤካ ኮተቤ ሆስፒታል መውጣታቸውን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ያሬድ አግደው በፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

እኚህ የዕድሜ ባለፀጋ አሁን ላይ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙና ለተጨማሪ ህክምና የካቲት 12 ሆስፒታል ናቸው ተብሏል ።
ሸገር ዳቦና የዳቦ ዱቄት ፋብሪካ እየተመረቀ ነው
*********************
(ኢ ፕ ድ)

በሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ አባል በሆነው ሆራይዘን ፕላንቴሽን ኩባንያ አማካኝነት የተገነባው ሸገር ዳቦና የዳቦ ዱቄት ፋብሪካ በአሁኑ ወቅት እየተመረቀ ነው።

በመዲናዋ የሚስተዋለውን የዳቦና የዱቄት አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ በሰዓት 80 ሺህ ዳቦ የሚያመርተው ሸገር ዱቄት ፋብሪካ በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በተገኙበት እየተመረቀ ይገኛል።

ፋብሪካው ምርቱን ዝቅተኛውን የማኅበረሰብ ክፍል ባገናዘበ ዋጋ የሚያከፋፍል ሲሆን፤ ይህም በከተማው የሚስተዋለውን የዳቦ አቅርቦት ማነስና የዋጋ ንረት ከመቅረፉ በላይ፥ ከዳቦ ማምረት እስከ ማከፋፈል ድረስ ባለው ሰንሰለት ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ታውቋል።፡፡

ፋብሪካው በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በአራት ሄክታር ቦታ ላይ ያረፈ ሲሆን፤ በፕሮጀክቱ ሥራ ከ450 ሰዎች የሥራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከ400 በላይ ያገለገሉ የአንበሳ የከተማ አውቶብሶች ለዳቦ ማከፋፈያነት እንደሚውሉም ታውቋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ “እንሥራ” የተሰኘው አዲስ የሸክላ ሥራ ማዕከልን ጎበኙ

*************************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ “እንሥራ” የተሰኘው አዲስ የሸክላ ሥራ ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡

“እንሥራ በተሰኘው አዲስ የሸክላ ሥራ ማዕከል ለምትሠሩት እህቶቼና እናቶች እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት እወዳለሁ፤ የድካማችሁን ፍሬ በማየቴ ደስ ብሎኛል” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 141 ሰዎች ኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው
. በአጠቃላይ በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥርም 81 ደርሷል
******************************
(ኢፕድ)
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4675 የላብራቶሪ ምርመራ 141 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5175 ደርሷል።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 18 (4 ከጤና ተቋም እና 14 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ የተገኝበት ናሙና የለም። ከዚህ ባለፈ ሶስት በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 81 ደርሷል፡፡

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት 58 ሰዎች (44 ከአዲስ አበባ፣ 8 ከኦሮሚያ ክልል፣ 3 ከሶማሊ ክልል፣ 2 ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል፣ እና 1 ከትግራይ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1544 ነው።
ኢትዮጵያ በቀሪዎቹ ሁለት ሳምንትታት የግድቡን ቀሪ ስራዎች በማጠናቀቅ ሙሌት ትጀምራለች ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ
*******************
(ኢ ፕ ድ)

ኢትዮጵያ በቀሪዎቹ ሁለት ሳምንትታት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድቡን ቀሪ ስራዎች በማጠናቀቅ የውሃ ሙሌት ስራውን ትጀምራለች ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ

ጽህፈት ቤቱ አሁን ባወጣው መግለጫ ላይ እነደገለጸው፤ ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን ትናንት በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት ትናንት ባደረጉት ስብሰባ በግድቡ ሙሌትና አስተዳደር ላይ የሚደረገው ድርድር በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት እንዲጠናቀቅ ተስማምተዋል።

"ኢትዮጵያ በቀሪዎቹ ሁለት ሳምንትታት የግድቡን ቀሪ ስራዎች በማጠናቀቅ ሙሌት ትጀምራለች። በእነዚህ ሁለት ሳምንትት አገራቱ ከስምምነት ላይ ለመድረስ ወስነዋል" ሲል ነው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በመግለጫው የጠቀሰው።

በተጨማሪም የአፍሪካ ህብረት ጉዳዩን መመልከት መጀመሩ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት እንዲገለጥ፣ የአፍሪካ ህብረት እና የመሪዎች ጉባኤ ቢሮ አባላት ድርድሩን እንዲደግፉ፣ ኢትዮጵያ ሱዳን እና ግብጽ ከቃላት ጦርነት መካረር እና አላስፈዐላጊ መግለጫዎች እንዲቆጠቡ አቅጣጫ ተቀምጦ ልዩ የመሪዎች ስብሰባ ተጠናቋል ሲል መግለጫው አስታውቋል።

ስብሰባው የተጠራው በወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር በሆኑት የደቡብ አፍርካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ አማካኝነት መሆኑን የጠቀሰው መግለጫው፤ ከሶስቱ አገራት በተጨማሪ ኬኒያ፣ ማሊ እና የኮንጎ ዴሞክራቲክ መሪዎች መሳተፋቸው ተገልጿል።
በአቶ ጃዋር መሐመድ ላይ የ13 ቀናት እና በአቶ በቀለ ገርባ ላይ የ11 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ
**********************************
(ኢፕድ)
ከድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ ከተከሰተው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ ከሁለት ሳምንት በፊት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት የአቶ ጃዋር መሐመድን ጉዳይ የተመለከተው ፍርድ ቤት ተጨማሪ የ 13 ቀናት የምርመራ ጊዜ ለፖሊስ ፈቀደ።
መርማሪ ፖሊስ በዋነኛነት ብሔርና ሃይማኖት መሰረት ያደረገ ግጭት እንዲቀሰቀስ ተጠርጣሪው የነበረውን አስተዋጽኦ ጠቅሶ፤ በተለይ የአርቲስት ሃጫሉን አስከሬን አቶ ጃዋር በሚመራው ቡድን ወደ ኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ውስጥ በሃይል ለማስገባት መሞከራቸውን አስረድቷል። በዚህም አንድ የፖሊስ አባል ህይወት እንዲያልፍና ሶስት እንዲቆስሉ መሆኑን ገልጿል።
ይህ ሊሆን የቻለው ተጠርጣሪው በሰጠው ትዕዛዝ መሆኑን አመልክቷል። በተጨማሪም የስልክ ልውውጥ በማድረግ የአመጽ ቅስቀሳ ሲያደርግ እንደነበረ በመግለጽ ለነዚህ ሁሉ ጉዳዮች መርማሪ ፖሊስ ማስረጃ ማሰባሰቡን ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል። የምስክሮችን ቃል መቀበሉንም አስረድቷል።
በአዲስ አበባና በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የተጠርጣሪውን የአመጽ ጥሪ በመቀበል ወደ 181 ሰዎች ህይወት ማለፉን ያመለከተው መርማሪ ፖሊስ፤ ተጠርጣሪው በሚመራው ቡድን ስር በቁጥጥር ስር የዋሉ የጦር መሳሪያዎች በሙሉ ህገ ወጥ መሆናቸውን ገልጿል።
14 የምርመራ ቡድን ተዋቅሮ ተጨማሪ ማጣራት እያደረገ እንደሚገኝ ያመለከተው መርማሪ ፖሊስ ተጨማሪ ማስረጃ የማሰባሰብ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ አመልክቷል። ያልተያዙ ግብረ አበሮችን መኖራቸውን ያመለከተው መርማሪ ፖሊስ ተጨማሪ 14 የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠውም ጠይቋል።
ተጠርጣሪው አቶ ጃዋር መሃመድ በበኩላቸው ወንጀሉን አለመፈጸማቸውን ገልጸው፤ ጉዳዩ ድራማ ነው ሲሉ ተናግረዋል። የተተኮሰ ጥይት አለመኖሩን ተናግረው፤ የተተኮሰ ጥይትም ሆነ የሞተ ሰው አለመኖሩን በመግለጽ የሚበጀው ቁጭ ብሎ መነጋገር ነው ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል።
የተጠርጣሪው ጠበቆች በእስር ቤት ያለው አያያዝና የቤተሰብ ጥየቃ ሁኔታ እንዲስተካከል ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ጠይቀዋል።
ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን አዳምጦ የተጠርጣሪው አያያዝ ሁኔታና የቤተሰብ ጥየቃ እንዲስተካከል ትዕዛዝ በመስጠት መርማሪ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ 14 ቀናት የምርመራ ጊዜ የፈቀደው ፍርድ ቤቱ 14ኛው ቀን በዓል በመሆኑ በ13ኛው ቀን ለሐምሌ 22 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
በተያያዘ ሃምዛ አዳነ በተባለ ግለሰብ የምርመራ መዝገብ የሚጠሩ ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች ‘’የአቶ ጃዋር ግብረ አበሮች’’ በሚል ፖሊስ ያቀረባቸው ናቸው። እነዚህ ተጠርጣሪዎች በዕለቱ በነበረው የአስከሬን ቅሚያ ጋር ተያይዞ ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ እነዚህ አካላት መኖራቸው፣ በማህበራዊ ሚዲያ መቀስቀሳቸውን፣ አመጽ እንዲቀጣጠል
ማድረጋቸውን እና ቡድኑ የተደራጀና መሳሪያ የታጠቀ መሆኑን መርማሪ ፖሊስ ገልጿል።
ይህ ቡድን ተኩስ መክፈቱንና ህይወት መጥፋቱን እንዲሁም ቡራዩ ላይ በነበረው ትንቅንቅ የጸጥታ ሃይሎች ላይ ተኩስ በመክፈት የሁለት ሰው ህይወት እንዲጠፋ ማድረጋቸውን በምርመራ ማረጋገጡን ገልጿል።
በመሆኑም ተጨማሪ ማጣራት የሚያደ ርግባቸው ጉዳዮች መኖራቸውንና ያልተያዙ ግብረ አበሮች እንዳሉ በመግለጽ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል። በዚሁ መሰረት ቀሪ ምርመራውን አጠናቆ ለሐምሌ 22 ቀን 2012 ዓ.ም እንዲቀርብ ተጨማሪ 13 ቀናት ጊዜ ፍርድ ቤቱ ሰጥቷል።
በተመሳሳይ ሐምሌ 6 ቀን 2012 ዓ.ም ቀርበው ትዕዛዝ ለመስጠት ለትናንት ተቀጥሮ የነበረው የአቶ በቀለ ገርባ መዝገብ ላይ የተጠየቀውን የመርማሪ ፖሊስ 14 ተጨማሪ ቀናት የመረመረው ፍርድ ቤቱ 11 ቀናት በቂ እንደሆነ በመግለጽ ለሐምሌ 20 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
አቶ በቀለ ገርባ መኪናቸው በወንጀል ፍሬ ውስጥ የማትገኝ በመሆኑ በተወካያቸው በኩል መረከብ እንደሚችሉ መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ ገልጿል።
በተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት የተጠረጠሩት እነ አራፋት አወቀ እና እነ አዲሱ ቶሎሳ ላይ ለመርማሪ ፖሊስ ተጨማሪ 11 ቀናት የምርመራ ጊዜ በመስጠት ለሐምሌ 20 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።
በእነ አራፋት መዝገብ ስድስተኛ ተጠርጣሪ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸው በህክምና ላይ በመሆናቸው ጉዳያቸው ከህክምና በኋላ እንደሚታይ ፍርድ ቤቱ በመግለጽ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
አዲስ ዘመን ሐምሌ10/2012
የድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በህዝቦች መካከል
እልቂት ለመፍጠር ያለመ ነበር
************************************
(ኢፕድ)
ከሰሞኑ የድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማና በኦሮሚያ ክልሎች የተከሰተው ግርግር አሳዛኝና አሳፋሪ እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ። ድርጊቱ ለዘመናት አብረው በኖሩ ህዝቦች መካከል ጥርጣሬና አለመግባባት በመፍጠር በአገሪቷ የመጣውን ለውጥ ለመቀልበስ የታሰበ እንደሆነም ይነገራል።
በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ድርጊቱን በማውገዝ በጉዳዩ ላይ ሃሳባቸውን በመገናኛ ብዙሃን ሲያንሸራሽሩ ተደምጠዋል።
አዲስ ዘመን ጋዜጣ ያነጋገራቸው በአማራ የህዝብ ንቅናቄ አብን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጣሂር መሐመድ እንደገለፁት፤ የድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ የነበሩት እንቅስቃሴዎች በህዝቦች መካከል ጥርጣሬና አለመግባባት እንዲሁም እልቂት እንዲፈጠር ታስቦ የተቀነባበረ ነው። ይህን እኩይ ተግባር ለመፈፀም ዝግጁ የነበሩ አካላት እንዳሉም ማሳያዎች ነበሩ ብለዋል።
ለዚህም መንግስት በአሁኑ ወቅት ለህዝብ እያደረሳቸው ያሉ መረጃዎች በተለይም ድምፃዊው ከ OMN የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ ሲታይ ታቅዶ የተደረገ ለመሆኑ አንዱ ማሳያ ነው። የሚሉት አቶ ጣሂር፤ አርቲስቱ ታዋቂና በህዝቡ ያለውን ተወዳጅነት ተጠቅመው ህዝባዊ ግጭቶችን ለመፍጠር ተጠንቶ የተደረገ ለመሆኑ ሂደቶቹ ምስክሮች ናቸው ይላሉ።
አቶ ጣሂር አያይዘውም የአማራ ንቅናቄ አብን በወቅቱ ለአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ባለቤት ሰጥተው ጉዳዩን ሲያንሸራሽሩ የነበሩ ሚዲያዎችን ታዝቧል። በመሆኑም ጉዳዩ ወዳልተፈለገ ቀውስ ይገባልና መንግስት ጥንቃቄ ያድርግ የሚል መልዕክት ያስተላለፈ መሆኑን አስታውሰዋል። ነገር ግን መንግስት ጥንቃቄ ባለማድረጉና ፈጥኖ እርምጃ ባለመውሰዱ እንደተፈራውም ክቡር በሆነው የሰዎች ህይወት እና ንብረት ላይ ከፍተኛ እልቂትና ውድመት የደረሰ መሆኑን ተናግረዋል።
ለብጥብጡ የተመረጠው ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ መሆኑ ባይታወቅም እንዲህ አይነት የጥፋት አዝማሚያዎች ነበሩ። በተለይም በኦሮሚያና ደቡብ ክልል ያሉ ለጥፋት የተመረጡ ህዝቦች እንዳሉ ይታወቃል። የሚሉት አቶ ጣሂር፤ ለውጡ ከመጣበት ካለፉት ሁለት ዓመታት ወደዚህ በፅንፈኛው ኃይል “ይሄ የእኔ ክልል ነው፤ ከክልሌ ውጣልኝ” የሚል አይነት አዝማሚያዎችን እንደ ማስፈራሪያ ተይዘው ይንፀባረቁ እንደነበር አስታውሰዋል።
ስለዚህ አንድ ነገር በተከሰተ ቁጥር ሰለባ የሚሆኑ ህዝቦች እንዳሉ ይታወቃል። በተለይም የአማራ ህዝብ ተጎጂ የሚሆንበት አዝማሚያ በመኖሩ መንግስት ቅድመ ማስጠንቀቂያና ልዩ ጥበቃ ሊያደርግ እንደሚገባ ለብልፅግና ፓርቲና ለመንግስት የሥራ አመራሮች ይገልፁ እንደነበር አቶ ጣሂር ተናግረዋል።
ቢዘገይም አልቀርም እንደሚባለው ነውና አሁን ላይ መንግስት ቢዘገይም እየወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ያሉት አቶ ጣሂር፤ አሁን የደረሰው ጥፋት ከዚህ በፊት በተፈጠሩ ችግሮች ላይ ተጠያቂ መሆን የነበረባቸው ሰዎች ተጠያቂ ባለመሆናቸው የደረሰ ነው ይላሉ። ለአብነትም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በተደጋጋሚ እንደ ሀገር መከላከያ ሠራዊት በብዙ መጠን ሲያስመርቃቸው የነበሩ የልዩ ሃይል አባላት ያሉበት ሊታወቅ ይገባል። ምናልባትም ለዚህ ጉዳይ ተባባሪ ሆነው ህዝባችንን ለከፍተኛ እልቂትና ውድመት ዳርገውት ከሆነም መጣራት እንዳለበት አመልክተዋል።
መንግስት ፈጥኖ እርምጃ መውሰድ እንደነበረበትና የዘገየ መሆኑን የገለፁት አቶ ጣሂር፤ በሰው ደም ላይ የሚደረግ ትዕግስትና ሆደ ሰፊነት የለም። መቀጠልም የለበትም ብለዋል። የሰዎች ሕይወት እየጠፋ ንብረት እየወደመ ሆደ ሰፊ እንሁን ማለት የማያዋጣ ነው።
እስካሁንም የተጓዝንበት መንገድ የስጋት እንደመሆኑ ለቀጣይም ይህ መንገድ አገር እንደ አገር እንዲቀጥል አያስያደርግምና መንግስት በተጠናከረ መንገድ አጥፊዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ መውሰድ አለበት ሲሉም አሳስበዋል።
እንደ አንድ ዜጋም ሆነ እንደ ፖለቲካ መሪ በአገሪቷ የተረጋጋ ሁኔታ እንዲኖር እፈለጋለሁ። የሚሉት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በበኩላቸው፤ በአገሪቷ ያሉ ህዝቦች ለበርካታ ዘመናት በጋራ ተከባብረው የኖሩ ህዝቦች መሆናቸውን አስታውሰው ነገር ግን እንደዚህ አይነት የደፈረሰና ፅንፍ የወጣ ጉዳይ እስከዛሬ አልገጠመንም ይላሉ። ጥፋቱ ከማሳዘንም አልፎ በጣም የሚያሳፍር ነው። ግለሰብን አጥፍቶ ድራማ ለመስራት የተደረገ አጀንዳ ከሆነም ኋላቀር አካሄድ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
ያለንበት ዘመን 21ኛው ከፍለ ዘመን እንደመሆኑ ኋላቀር የሆነ የፖለቲካ ጨዋታ የምንጫወትበት የአስተዳደር ዘመን አይደለም። ያሉት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፤ በዚህ ወቅት መጫወት ያለብን ሰላማዊና ሰላማዊ ብቻ የሆኑ ሃሳቦችን በማንሸራሸር እንደሆነም ተናግረዋል። ነገር ግን ታዋቂ ግለሰብን ገድሎ በሚፈጠር ረብሻ መንግስት መገልበጥና ስልጣን ለመያዝ የሚያስቡ ካሉ እጅግ ኋላ የቀረ አስተሳሰብ ከመሆኑም በላይ አዋጭ አለመሆኑ አብራርተዋል።
ይሁንና ማንም ሆነ ማን በጥፋት ከተጠረጠረ መንግስት በተገቢው አካል መርምሮ ነፃ የሆነውን በነፃነቱ ማስተናገድ አለበት። ጥፋተኛውን ደግሞ ለፍትህ አካል ማቅረብ አንድ መንግስት ካለበት አገር የሚጠበቅ ነው። ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ከሞተ በኋላ መንግስት እያደረገ ባለው ክትትል የተያዙ ተጠርጣሪዎች አሉ። ይህ መሰረታዊና ተገቢ ተግባር ነው።
ይሁንና በመንጋ ወጥቶ የሀገር ሀብትና ንብረት እያጠፋ ያለው ወጣት ነገሮችን አዙሮ ማየት የሚችል አይመስልም። “ነገርን ከስሩ ውሃን ከጥሩ” እንደሚባለው መንግስት በሽታቸውን አውቆ ማከም እንዲችል ችግሩን ከሥሩ ማጥራት አለበት። በደቦ ወጥቶ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ወጣቶችን ማን ለምን ዓላማ እንደሚያሰማራቸው ከሥሩ ማጥራትና ተገቢውን እርምጃ መውሰድ ተገቢ ነው ሲሉም አሳስበዋል።
አዲስ ዘመን ሐምሌ 9/2012
ፍሬህይወት አወቀ
የታላቁ የህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት ተጠናቀቀ
--------------------------------------------------
የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ።
ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከተገኘው ከፍተኛ የዝናብ መጠን የተነሣ፣ የግድቡ የመጀመሪያ ዓመት የውኃ ሙሌት ተጠናቋል ያለው የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ውኃው በግንባታ ላይ ያለውን ግድብ አልፎ እየፈሰሰ እንደሚገኝ አስታውቋል።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ሙሌት ተጠናቀቀ
**********************************
የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ሙሌት መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የውሃ ሙሌቱ በስኬት መጠናቀቁን አስመልክተው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ክረምቱ ገና ሳይገባደድ የመጀመሪያው ዙር ሙሌቱ በጥቂት ቀናት ሞልቶ መጠናቀቁና መፍሰስ መጀመሩ ለአገሪቱ ትልቅ የድል ምዕራፍ መክፈቱን የሚያሳይ ነው ብለዋል።
ለግድቡ ግንባታ ድጋፍ ላደረገው የኢትዮጵያ ህዝብና በድርድር ሂደት ሙያዊና የዜግነት ህግዴታቸውን ለተወጡት ተደራዳሪዎችም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የአሁኑ ሙሊት በሁለት ተርባይን ኃይል ለማመንጨት የሚያስችል ምዕራፍ መሆኑን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ የግድቡ ግንባታ ዳር እንዲደርስ በድፕሎማሲውም ሆነ በግንባታው ሂደት ገና ብዙ ሂደት ይቀረዋል ብለዋል።
በመሆኑም ህዝብና መንግስት በተባበረ ጥረት ለአገራዊ ለውጥና ተጠቃሚነት በጋራ መስራታቸውን እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል።
የግድቡን ህልውና በዘላቂነት ለማረጋገጥም በተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአፋር ሰመራ ችግኝ ተከሉ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ጋር በመሆን፣ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በሚገኝ አዲስ ፓርክ ችግኝ ተክለዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው፤ የችግኝ የመትከያው ወቅት አጋማሽ ላይየተደረሰ ሲሆን፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሊተከል ከታቀደው 5 ቢሊየን ችግኝ መካከል እስካሁን 2.9 ቢሊየን ችግኞች ተተክለዋል።