Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የህዳሴ ግድቡ ግንባታ ሲጀመር የነበረው የህዝብ መነቃቃት በጣም አስደሳች ነበር። ምክንያቱም አባይ ብዙ ጊዜ ለዘፈን እንጂ ለአገር ልማት ውሎ ባለማወቁ፤ ለዘመናት እንዲሁ ቁጭት ሆኖ የኖረ ወንዝ ነው።

👉 ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሀይል ፍላጎት አላት። ይህን ፍላጎቷን ልታሳካ የምትችለው በዋናነት ከውሀ ሀብቷ ነው።

👉 የእናቶቻችን የከፋ የኑሮ ሁኔታ፤ በጭስ እና በማገዶ ሸክም ላይ የተመሰረተ መሆን፣ ተማሪዎቻችን በጨለማ ትምህርት መከታተል፣ እናም በአጠቃላይ አገሪቱ በሀይል እጦት ምክንያት ከፍተኛ ችግር ውስጥ ገብታ ረዥም አመታትን ተጉዛለች፤ አሁንም እየተጓዘች ነው።

👉 የህዳሴ ግድቡ ግንባታ መዘግየት የኤክትሮሜካኒካል እና ሀይድሮ ሜካኒካል ለመስራት የገባው የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን /ሜቴክ/ ግዳጁን ባለመወጣቱ ነው ዋናው ችግር።

👉 ሜቴክ በትዕዛዝ ያስገባው መንግስት ነው። በወቅቱ ሜቴክ አቅም የለውም፤ ብለን ከፍተኛ ክርክር አድርገናል። ክርክራችን አገሪቱን ሲመሩ ከነበሩ ሰው ጋር ነው፤ ነገር ግን ተቀባይነት አላገኘም።ትልቁ ስህተት እዚህ ጋር ነው የሚጀምረው።

👉 ስራው እንደተጀመረ በየወሩ ይገመገም ነበር። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በተለይ ከአቶ መለስ ህልፈት በኋላ በየወሩ መገምገም አቆመ። ስራውም በከፍተኛ ባለሙያዎችና ኃላፊዎች መገምገሙ ቀርቶ የህዳሴ ግድቡ ማስተባበሪያ ቦርድ ብቻ እንዲያየው ሆነ፤ ከቦርድም የተወሰነ ሰው ብቻ እንዲያየው ሆነ። 👉 የመብራት ሀይል ቦርድ እንኳን በሙሉ አቅሙ እየገመገመው አልነበረም። መጨረሻ በቦርድ ሰብሳቢው አመራርነት ብቻ መጓዝ ጀመረ።

👉 መጨረሻ በአስተባባሪ ቦርዱ ሰብሳቢና የፕሮጀክት ኃላፊው ብቻ መመራት ጀመረ። እንደ ዘርፍም ውሀ መስኖና ኢነርጂ መሳተፍ ሲኖርበት እንዲገለል ተደረገ።
ኮንትራቱን የሚያስተዳድረው መብራት ሀይል እና ቦርዱ ሜቴክ ላይ እርምጃ መውሰድ ይችሉ ነበር።

👉 ሜቴክን ፊት ለፊት የተጋፈጥንበት ሁኔታ ቢኖርም መስተካከል አለበት ያልነውን በግምገማ ውስጥም ያነሳንበት ሁኔታ አለ። የቦርዱም ሆነ የመብራት ሀይል ችግር የገዘፈ ነበር።

👉 ሜቴክ ከመብራት ሀይል ብዙ ፕሮጀክቶች ተሰጥተውት አንዳቸውንም ሳያከናውን ቀርቷል።

👉 በዚህ ረገድ ሜቴክ ከ5200 ሜጋ ዋት ወደ 6000 ሜጋ ዋት አሳድጓል የተባለውን መቀበሉ ትክክል አይደለም። በወቅቱ በዘርፉ ውስጥ አልነበርኩም ግን ትክክል እንዳልሆነ ዘርፉን ለሚመሩ ሰዎች አሳውቄ ነበር።

👉 የሀይል /ኢነርጂ/ ለውጥ በሌለበት ሜጋ ዋቱን ብታሳድግ ተቀባይነት የለውም። ለዚህ ነው አሁን የመጣው አመራር ይህን ያስተካከለው። ሌላው ሜቴክ ስራውን በጊዜ ባለመጨረሱ ሲቪል ስራውም ቆሞ ነበር።

👉 ከለውጥ በኋላ በአገሪቱ ቀድሞ ተፈጽመው ከነበሩ ስህተቶች ውስጥ በከፍተኛ ጥንቃቄ ከተገመገሙ ጉዳዮች አንዱ የህዳሴ ግድቡ ነው።

👉 የህዳሴ ግድቡ በተለይ ከለውጡ በኋላ ጥራቱን ጠብቆ በሚፈለገው ሁኔታ እየተጓዘ ነው፤ ውሃ ለመሙላት ደርሷል። በፕሮጀክቱ ግንባታ በዚህ መልኩ የተጓዘበት ጊዜ የለም።

👉 በሁለት አመታት ውስጥ ዓለም አቀፍ ባለሙያዎችን ማምጣት በራሱ ጊዜ ይፈልጋል። እንደ ሜቴክ አምጥተህ የምትሰጠው ስራ አይደለም። አሁን እኮ ለውጡ እየታየ ነው። 👉ዘገየ የሚለው ሀሳብ ለተራ የፖለቲካ ጥቅም ፍለጋ ካልሆነ በስተቀር ሚዛን የሚደፋ ትችት አይደለም።

👉 ድርድሩን በተመለከተ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ምንም የተለሳለሰ ነገር የለም። ነገር ግን ግብፆች ለውይይት እና ድርድር ሲመጡ የተለያዩ ውሸቶችን ይዘው ነው።

👉
የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል በወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥር ባሉ አንዳንድ መመሪያዎች ላይ ማሻሻያ ተደርጓል፤
የአስከሬን የላቦራቶሪ ውጤት ሳይገለጽ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎችን መቅበር ተከልክሎ የነበረው ክልከላ ተነስቶ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ በህበረተሰቡ የቀብር ሥነ ሥርዓት መሰረት መፈጸም ተፈቅዷል፤
አሁንም ግን በቀብር ስነ ስርዓት ላይ መገኘት የሚፈቀደው 50 ሰዎች ብቻ ናቸው፤
ከውጭ የሚገቡ ሰዎች በተለይም ወደ አገር ከገቡ በኋላ ባለፉት ሦስት ቀናት ውስጥ ከመጡበት አገር ተመርምረው ነጻ መሆናቸውን የሚያሳይ መረጃ ይዘው ከመጡ ናሙና ተወስዶ በቤታቸወ 14 ቀናት እንዲቆዩ ይደረጋል፤
በሌላ በኩል ነጻ መሆናቸውን የሚያረጋገጥ ሪፖርት ይዘው ለማይመጡ መንገደኞች ናሙናቸው ተወስዶ ለሰባት ቀናት በለይቶ ማቆያ እንዲቆዩ ይደረጋል፤
"እንሥራ" የሸክላ ስራ ማእከል ተመረቀ።

የሸክላ ስራ ማእከሉ ግንባታው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቀ ነው።

የሸክላ ስራ ማእከሉን ኢ/ር ታከለ ኡማና ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦች መርቀው ስራ አስጀምረውታል።

በማእከሉ 1000 በሸክላ ስራ ላይ የተሰማሩ እናቶች የመስሪያና የመሸጫ ቦታዎች ከተሟላ የማምረቻ ቦታ ከተሟላ ቁሳቁሶች ጋር የሚያገኙ ይሆናል።

የሸክላ ስራ የሙያውን ያህል ያልተከበረ የድካሙን ያህልም ጥቅም ያልተገኘበት ሆኖ ቆይቷል ያሉት ኢ/ር ታከለ ኡማ የከተማ አስተዳደሩ ይሄን ዘርፍ ባለሙያዎችን በሚያሳድግ ሀገርን በሚጠቅም መልኩ ለማሳደግ ይሰራል ብለዋል።

የሸክላ ምርቶቹ ከሀገር ውስጥ ገበያ አልፎ በአለም አቀፍ ደረጃ ገበያ እንዲያገኝ ከተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ንግግር እየተደረገ ነው ያሉት ኢ/ር ታከለ ዘርፉን የሚደግፉ የህግ ማሻሻያዎችም እየተዘጋጁ ነው ብለዋል።

በከተማዋ ከሸክላ ስራ ማእከሉ በተጨማሪ የሸማ ጥበብ ማምረቻና መሸጫ ማእከል ሽሮ ሜዳ አካባቢ እየተገነባ ይገኛል።
« ከስልጣን በሰላም ወርዶ በሰላም እንዲኖር እድል የተሰጠው ህወሃት ብቻ ነው»አቶ ኦሃድ ቤናሚ - የሚዲያ አማካሪ

• ከ20 ዓመታት በላይ የመሩት የሱዳን፣ ግብፅ፣ ቱኒዚያ፣ የሊቢያና የሌሎችም አረብ አገራት መሪዎች የተወገዱት በጦርነትና በአመፅ ነው::

• በዚህ ቀጠና በሰላም የወረደው ህወሃት ብቻ ነው፤ በሰላም ወርዶ በሰላም እንዲኖር እድል የተሰጠው ህወሃት ብቻ ነው::

• አሁን ያለው ትውልድ አንድ መሪ ከሁለት የምርጫ ዘመን በላይ እንዲቀጥል አይፈልግም::

• ከ25 ዓመታት በላይ የኖሩ መንግሥታት እየተዋረዱ፤ እየተገፉ የወረዱበት እውነታ ዓለም አቀፋዊ ክስተት ነው:: እኔ ህወሓት ምን እንደሚፈልግ አላውቅም::

• ህወሓቶች «አብይ አምባገነን ነው፤ ›ተጋሩ› እየተገደለ ነው» የሚሉት ነገር ሁሉ ውሸት ነው:: አንድ ነገር ልንገርሽ ፤ ህወሓት ከስልጣን ከተወገደ በኋላ እየተገደሉ፤ እየታፈኑ ያሉት የትግራይ ተወላጆች አይደሉም፤ የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች ናቸው::

• በየዩኒቨርሲቲውና በአንዳንድ የአገሪቱ አካባቢዎች ተፅዕኖ ሲደርስባቸው ያየነው አማራና የኦሮሞ ተማሪዎችን ነው::

• ህወሓት ምን እንደሚፈልግ ግልፅ አይደለም:: እዚህ አካባቢ በሰላም እንዲቀጥል የተፈቀደለት ብቸኛው መንግስት ህወሃት ብቻ ነው፤ ግን እየበጠበጠ ያለው ራሱ ነው::
• እውነቱን ለመናገር የባድመ ጦርነት የመሬት ጥያቄ አልነበረም:: ኢሳያስን የማደከምና ኤርትራን የመምታት ፍላጎት ስለነበር ነው::

• የኢትዮጵያን ህዝብ በኤርትራ ላይ ማስነሳት የምትችይው «መሬትህ ተወረረ» ስትዪው ብቻ ነው:: በወቅቱ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ በሻቢያ ላይ ትንሽ ቅሬታ ነበረበት::

• አገሪቱን ይመራው የነበረው ህውሃት በወቅቱ ኤርትራ ላይ የተጠቀመው የጦርነት ፖሊሲ ነው:: በወቅቱ የመሪና የአመራር ችግር ነበር::

• ላለፉት 20 ዓመታት ጦርነትም ሆነ ሰላም ሳይኖር የተቆየበት ዓመታት በተለይ የትግራይን ህዝብ የጎዳበት ሁኔታ እንደነበር እሙን ነው::

• ይህንን ሁኔታ ማስቀረት የቻለው የአብይ አስተዳደር ነው፤ ህውሃት20 ዓመት ሙሉ ችግሩን ታቅፎት ከመኖር ውጭ መፍትሄ ማምጣት አልቻለም:: ስለዚህ በዶክተር አብይ ትልቅ ለውጥ መጥቷል ብሎ በሙሉ ልብ መናገር ይቻላል:: -አቶ ኦሃድ ቤናሚ - የሚዲያ አማካሪ
የኢትዮጵያ ህዝብ ከህወሓት የሚፈልገው ሰላም ብቻ ነው:: የተጣለ አስተሳሰብ( አይዶሎጂ) ይዘህ፤ የ60ዎቹ የሁለተኛ ዓመት ተማሪዎች የቀረፀልንን አጀንዳ በ2012 ላለው ትልውድ ልታቀርበው አትችልም:: ዘመኑን የሚመጥን ሃሳብ ይዘህ መምጣት ይገባሃል የሚል መልዕክት ማስተላለፍ እፈልጋለሁ::

• በሌላ በኩል አንቀፅ 39 ላለፉት 27 ዓመታት ተነስቶ አያውቅም፤ አሁን ለምንድንው በትግራይ አካባቢ የሚነሳው? ህወሓት ከስልጣኑ ስለተባረረ ነው?

• በእኔ አስታሳሰብ ትግራይ ብትገነጠል መጀመሪያ የምትጎዳው ኢትዮጵያ ናት የምትመስለኝ:: ምክንያቱም ከአምስት ሚሊዮን በላይ የሚሆን ህዝብ ትግራይ ውስጥ አለ:: እሱን እናጣለን:: ምክንያቱም ቁጥራችን የሚጀመርው ከህዝብ ነው:: ስለመሬት፣ ስለማዕድንና ስለሃብት ከማውራታችን በፊት ልናጣ የምንችለውን ህዝብ ነው ማሰብ የሚገባን::

• በሁለተኛ ደረጃ በምትቀጥለዋ ትግራይ ምን ሊፈጠር ይችላል? ብዬ ሳስብ ደግሞ እሰጋለሁ:: ምክንያቱም በአንድ በኩል በጣም የመረረ ጥያቄ የሚያነሱ የአማራ ክልል ሰዎች አሉ:: ጅምላ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ተፈፅሞብናል የሚሉ አሉ:: በኤርትራ በኩል ያለውም ስሜት ጥሩ አይደለም::

• በታሪክ በተደጋጋሚ ከህወሓት ዘላቂ ግንኙነት ሊኖር እንደማይችል ኤርትራውያን ጠንቅቀው ያውቃሉ:: በምትገነጠል ትግራይ ውስጥ ኤርትራውያን በጣም ነቅተው የሚጠብቋት አገር ነው የምትሆነው:: አቶ ኦሃድ ቤናሚ - የሚዲያ አማካሪ
የግብጽ ሚዲያዎች በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ምንም አይነት ዘገባዎችን እንዳይሰሩ ታገዱ
**********************
(ኢ ፕ ድ)

የግብጽ መገናኛ ብዙሀን እና የማህበራዊ መዲያ ተጠቃሚዎች በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ምንም አይነት ዘገባዎችን እንዳይሰሩ ታገዱ።

የግብጽ የሚዲያ ምክር ቤት ባስተላለፈው እገዳ መሰረት፤ የአገሪቱ መገናኛ ብዙሀንና የማህበራዊ ሚዲያዎች ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና መሰል ጉዳዮች ምንም አይነት ዘገባ እንዳይሰሩ ተከልክለዋል።

ምክር ቤቱ በዚሁ እገዳው የትኛውም ሚዲያም ሆነ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጻፍም ሆነ ውይይት ማድረግ አይቻልም ብሏል።

ምክር ቤቱ ከዚህ በኋላ በመንግስት ከሚነገሩ መረጃዎች ውጭ የተጠቀመ ማንኛውም አካል ህጋዊ እርምጃ ይወሰድበታል ሲል እገዳውን ይፋ አድርጓል።

የግብጽ መንግስት ተቃዋሚዎች እገዳውን በማውገዝ ድምጻቸውን ያሳሙ ሲሆን፤ ድርጊቱን ሳንሱር ነው ብለውታል።

ይህ እገዳ በመንግስት ስፖንሰር አድራጊነት የተላለፈና የመረጃ ነጻነትን የሚጋፋ ውሳኔ ነው ሲሉም ውሳኔውን ተቃውመውታል።

ይህ አይነቱ እገዳ ከሞራል አንጻር ስህተትም ብቻ ሳይሆን ለህዝቡም የደህንነት ስጋት ነው ያሉት እነዚህ ወገኖች፤ መንግስት ወደዚህ አይነቱ ተግባር መግባቱ ከህዝብ መረጃ የመደበቅ ተግባር ማሳያ ነው ማለታቸውን ሚድል ኢስት አይ ባወጣው ዜና አስነብቧል።
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 399 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው
*****************************
(ኢፕድ)

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4848 የላብራቶሪ ምርመራ 399 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4469 ደርሷል።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 22 (8 ከጤና ተቋም እና 14 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት ናሙና የለም።

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ዘጠና አምስት (95) ሰዎች (82 ከአዲስ አበባ፣ 8 ከአማራ ክልል፣ 2 ከሶማሊ ክልል ፣ 1 ከትግራይ ክልል፣ 1 ከኦሮሚያ ክልል እና 1 ሰው ከጋምቤላ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1122 ነው።
የፀሀይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ ይህንን መስሎ ታይቷል
የጸሀይ ግርዶሽ በአላማጣ
በሕንድ በአንድ ቀን ከ15 ሺህ በላይ የኮሮናቫይረስ ህሙማን ተገኙ
----------------------------------------------------------------
ሕንድ በአንድ ቀን ውስጥ 15 ሺህ 413 በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ማግኘቷን በምርመራ አረጋገጠች።
ይህም በአገሪቱ ወረርሽኙ መገኘቱ ከታወቀ ወዲህ በአንድ ቀን የተገኘው ከፍተኛው የህሙማን ቁጥር ነው።
በዛሬው ዕለት የተገኘው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ከፍተኛ ቁጥር እስካሁን በሕንድ ያለውን አጠቃላይ የህሙማን ብዛት ወደ 410 ሺህ 461 ያደረሰው ሲሆን ይህም ከአሜሪካ፣ ከብራዚልና ከሩሲያ ቀጥሎ ሕንድን በዓለም አራተኛ ደረጃ ላይ እንድትቀመጥ አድርጓታል።
ከዚህ በተጨማሪ በበሽታው ምክንያት 306 መሞታቸው በዛሬው ዕለት የተነገረ ሲሆን በአጠቃላይ በአገሪቱ የሞቱትን ሰዎች ብዛት ወደ 13 ሺህ 254 አድርሶታል። ቢ ቢ ሲ
ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም ህይወታቸውን ላጡ የቀድሞ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮችና የፀጥታ አካላት መታሰቢያ የሰማእታት ሀውልት ለማቆም የመሰረት ድንጋይ ተጣለ።

የመሰረት ድንጋዩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ተመስገን ጥሩነህና ሌሎችም የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ነው የተቀመጠው ።

የደም ልገሳና ችግኝ ተከላም የሰኔ 15 ሰማእታት ዝክር ስነስርአት አካል ነው ሆኖ እየተተገበረ ነው። EBC
ግብጽ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን ከጎኗ ለማሰለፍ የምታደርገው ጥረት ከእምነቱ አስተምህሮ ውጪ መሆኑ ተገለጸ
. ግብጾች፣ የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን ስነልቦናም ሆነ አገራዊ አቋም አያውቁትም

አዲስ አበባ፡- ግብጽ በአባይ ጉዳይ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ከጎኗ ለማሰለፍ የምታደርገው ጥረት የኢትዮጵያውያንን የአገር ፍቅር ስሜት ያላገናዘበና ከሃይማኖቱ አስተምህሮ ውጪ በመሆኑ ከዚህ ድርጊቷ ልትቆጠብ እንደሚገባ የእምነቱ ከፍተኛ አባቶች ተናገሩ።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የመስጊድ ኢማም ሼህ የሱፍ ቃሲም በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳሉት፤ ግብጽ አባይን የምትመለከትበትና የምታስተሳስርበት መቀነት አጥሯታል። አሁን አሁን ደግሞ ይባስ ብሎ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ከጎኔ ይቆማሉ የሚል አሉባልታ በመንዛት ላይ እንደሆነች መስማታቸውን ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ጉዳዩ የኢትዮጵያን ሙስሊሞች ስነልቦናም ሆነ አገራዊ አቋም ፈጽሞ የማይወክልና ከእስልምና አስተምህሮት ውጪ ተራ ወሬ ተደርጎ የሚቆጠር እንደሆነም ገልጸዋል።

ግብጽ ከዚህ በፊት ስትከተላቸው የነበሩት የውዥንብር መንገዶች ረዥም ርቀት እንደማይወስዷት ተረድታለች። በዓለም የዲፕሎማሲና የፖለቲካ ሚዛን

ውሃ የማያነሱ መሆናቸውን የኢትዮጵያ አቋም ጠንከር ባለ ቁጥር እንድትገነዘብ እያደረጋት ነው። በዚህ የተነሳም የኢትዮጵያውያንን ጠንከር ያለ አቋም ማላላት፣ሲቀጥልም ርስ በርስ እንዲከፋፈሉ በማድረግ የከረሩ ግጭቶች እንዲፈጠሩ ማድረግን አልማ እየሰራች እንደሆነም ሼህ የሱፍ አስረድተዋል።

በየትኛውም ዓለም የሚገኙ ሙስሊሞች ወንድማማቾች ናቸው። ለዚህም የሚያስተሳስራቸው የእምነታቸው መሰረት የሆነው ‹‹ላኢላሃኢለሏህ ሙሐመድ ረሱለሏህ›› በአሏህ አንድነት እና በሙሐመድ (ሱ.ዐ.ወ) መላዕክተኛነት ማመን ነው። ነገር ግን ግብጽ የኢትዮጵያውያ ሙስሊሞችን ከግብጻውያን የእምነት ወንድሞቻቸው ጋር የሚያስተሳስራቸው የ ‹‹አባይ ወንዝ›› እንደሆነ አድርጋ ይዛ ብቅ ማለቷ በሙስሊሞች ዘንድ የተቀባይነት ቀቢጸ ተስፋን በማሳደሯ ከመሆን እንደማይዘል ሼህ የሱፍ አብራርተዋል።

በእስልምና ሃይማት ዙሪያ ጥናት በማድረግ የሚታወቁት ኡስታዝ ባህሩ ኡመር በበኩላቸው እንደገለፁት የእስልምና አስተምህሮ እኩልነትን፣ ፍትሃዊነትን ይሰብካል፣ ያስተምራል። ‹‹ወንድማማቾች

በአንድ ውሃ አጠቃቀም ላይ ቢጋጩ እንኳን›› ለውሃው ቅርበት ያለው ቀድሞ ይጠቀምና ወንድሙንም እንዲጠቀም ያድርግ›› የሚል ፍትሃዊ አስተምሮን እንደሚከተል በተለያዩ ‹‹ሐዲሶች›› ተጠቅሷል። ስለዚህ ፍትሃዊ ያልሆነና ሌሎችን የሚያስከፋ ተግባር መፈጸምን በእምነቱ አስተምህሮ በፍጹም የተከለከለ እንደሆነ አስረድተዋል።

ስለ እያንዳንዱ ነገር እምነቱ ፍትሃዊ የሆኑ አሰራሮችን ያስቀመጠ መሆኑ እየታወቀ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በአባይ ጉዳይ እኔን ይደግፋሉ፤ ይሄን ሐቅ በውስጥ ሰዎቼ አረጋግጫለሁ፤ የምትለው ግብጽ በፍጹም ከፕሮፓጋንዳነት ያለፈ እንደማይሆን ኡስታዝ ባህሩ ይናገራሉ።

‹‹ኢትዮጵያ አትጠቀም እኔ ልጠቀም›› የሚለው አስተሳሰብ ከሐይማኖት አንጻር ጭራሹን በሸሪዓ የተከለከለ እንደሆነ የተናገሩት ኡስታዝ ባህሩ ኡመር በእስልምና አስተምህሮ ፍትሃዊ ያልሆነ ጉዳይ ፈጽሞ የተከለከለ እንደሆነ ገልጸዋል።

ለተጨማሪ https://www.press.et/Ama/?p=34814
ግብጽ የህዳሴ ግድብ ድርድር በሂደት ላይ እያለ ጉዳዩን ወደ መንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት መውሰዷን ሱዳን አወገዘች
*****************************************
(ኢ ፕ ድ)

ግብጽ የህዳሴ ግድብ ድርድር በሂደት ላይ እያለ ጉዳዩ ወደ መንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት መውሰዷን እንደማይቀበለው የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ኡመር ቀመርዲን ተናገሩ።

ሚኒስትር ዴኤታው ለቢቢሲ አረበኛው እንደተናገሩት ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ውሃ ሙሌት ብትጀምር ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ወደ ግጭት አትገባም።

ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም ችግሩ በድፕሎማሲ መንገድ ብቻ እንዲፈታ ሱዳን እንደምትሰራ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ከጭምብል አጠቃቀማችን የሚታረሙ ስህተቶች
**************************
(ኢፕድ)
ዓለማችን ከምታስበው በላይ ጨካኝ፣ ከምታምነው በላይ ኃያልና ከምትገምተውም በላይ ጠንካራ በሆነባት የኖቭል ኮሮና ቫይረስ ምክንያት በከባድ የስቃይ ምዕራፍ ውስጥ ትገኛለች። ቫይረሱም በቴክኖሎጂ የመጠቁ፣በኢኮኖሚያ የበለፀጉና በህክምና አገልግሎት አቅርቦትም ሆነ ጥራት ከፊተኞቹ ተርታ ስማቸው የሚጠራላቸው አገራትን ሳይቀር አስጨንቃል። አሸብራል።

የጤናው ዘርፍ ጠቢቢን ብሎም የምርምር ተቋማትም ዓለም ከቫይረሱ ጋር ከተዋወቀችበት ጊዜ አንስቶ መድኃኒትና ክትባት ፍለጋ ሌት ተቀን ደክመዋል። የወረርሽኙን ስርጭት ለመከላከልና ጉዳቱን ለመቀነስ መድኃኒት ከሚሆኑት አንዱ የአፍን አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል መጠቀም መሆኑን ከመጠቆም የተሻገረ መፍትሔን መስጠት ግን አልሆነላቸውም።

ኢትዮጵያም ይህን የመፍትሔ አቅጣጫ በመከተል ዜጎቻ ጭንብል መጠቀም ግዴታቸው መሆኑን ካሳወቁ አገራት መካከል አንዷ ናት። ይሁንና ህዝቦቿ ተገቢውን የጭንብል አጠቃቀም ሂደት መከተልና ጥንቃቄ ማድረግ ላይ በግልፅ የሚታይ ድክመት እንዳለባቸው ይነሳል።

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሆነችው ወይዘሪት ሜሮን ሙሉጌታም፣ ‹‹በመዲናዋ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብልን በአግባቡ ከሚጠቀሙት ይልቅ የማይጠቀሙት ይበልጣሉ፣ በተለይ የአንዳንዱ ተግባር በጋራ ዓለምና ሰማይ ስር የብቻውን ጤና የሚያጣጣም፡ የሌሎችን ሕይወት እያደፈረሰ የራሱን ለማጥራት የሚታትር ይመስላል›› ትላለች።

ጭንብል በሚደረግበት ጊዜ አፍና አፍንጫን እንዲሁም አገጭ ድረስ መሸፈን እንደሚገባ ቢገለፅም፤ በርካቶች ከአፍንጫቸው ዝቅ በማድረግ ለአፋቸው ብቻ ሲጠቀሙ›› ይስተዋላል የምትለው ሜሮን፣አንዳንዱ ደግሞ ጭንብል ለመግዛት ሞክሮ ሲያስቀምጥ መታዘቧን ታስታውሳለች።

ከመሰል የአጠቃቀም ድክመት ባሻገር በአሁን ወቅት በየመንገዱ የሚሸጡና ከጨርቅ የሚሠሩ ጭንብሎች ምን ያህል የመከላከል አቅም አላቸው? የሚለውን በቅጡ አለመታወቁ መሆኑን የምትገልጸው ሜሮን፣ጭንብሎቹ በማን እና በምን መሠራት እንዳለባቸው የሚገልጽ መረጃ አለማግኘቷን ትመሰክራለች።

ከደረጃው መለየት አንስቶ አጠቃቀምና አወጋገድን በሚመለከት ሁሉንም የሚያስማማና የሚስማማ ሃሳብ መፍጠር እንዳልተቻለ በመጠቆም እነዚህን የተራራቁ የግንዛቤ ክፍተቶችን ማገናኘትም ለነገ የማይቀመጥ የቤት ሥራ እንዳልሆነ ታስገነዝባለች።

በተለይ ለውጥ በአንድነት እንጂ በመለያየት እውን አይሆንምና ወይዘሪት ሜሮን መደረግ ስላለበት ስትገልጽም፣ቫይረሱ እጅ እንድንሰጥ የሚያደርጉ መሰል ስህተታችንን ሳይውል ሳያድር በመሞረድና በማስተካከል በተለይ በቸልተኝነት በማድረግ በሰውነታችን ለሰው ሁሉ ጤና ጥብቅና እንቁም›› ስትልም ነው ጥሪ ያቀረበችው።

የየካቲት 23 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህሩ አቶ ኡመር አብዱም.፣ህብረተሰቡ ‹‹ከጭንብሉ ጋር እንዴት ተዋውቆና ተግባብቶ መኖር እንደከበደው ለመረዳት የአንዳንዶቹን ምግባርና ተግባር ማየት በቂ ነው›› ይላል።

በከፍተኛ ጥንቃቄ ፋይዳውን ተገንዝቦ ጭንብሉን በአግባቡ የሚጠቀም ባይጠፋም የአንዳንዱ የጭንብል አጠቃቀም ራሱን አስደስቶ ሌላውን የሚያስኮርፍ መሆኑንም ያነሳሉ። ጭንብል የሚለብሱት የራሳቸውን ጤና ለመጠበቅ የማይመስላቸውና የፀጥታ አካላትን ሲመለከት ጭንብል የሚያጠልቁም ለዚህ እሳቤ ምስክር አድርጎ ያቀርባል።

ለተጨማሪ https://www.press.et/Ama/?p=34817
የኮቪድ-19 አንቲቦዲ (Antibody) የቅኝት ዳሰሳ አስመልክቶ የወጣ መግለጫ

በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ምርመራ ከጥር 29 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የተጀመረ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በሁሉም ክልሎች በሚገኙ ላቦራቶሪዎች እስከ ሰኔ 14 ቀን 2012 ዓ.ም 216¸328 ምርመራ ተደርጓል። ይህ የምርመራ አይነት የኮቪደ-19 በሽታ ያለበት ሰው ላይ ቫይረሱን ለመለየት የሚረዳ የሞለኪዩላር ምርመራ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በማህበረሰብ ውስጥ ያለውን የበሽታ ስርጭት ለመረዳት (surveillance) እና በአንጻሩ ምላሽ ለመስጠት እንዲሁም ይበልጥ ተጋላጭ በሆኑት የማህበረሰባችን ክፍሎች ላይ ያለውን የኮቪድ-19 በሽታ ስርጭት ለማወቅ የሚረዳ አንቲቦዲ ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ይታመናል፡፡ ይህ የአንቲቦዲ የቅኝትና ዳሰሳ ምርመራ አይነት በአገራችን ለምርምር ለመጠቀም እና ከላይ የተጠቀሱትን ዓላማዎች ለማሳካት ከሰኔ 15 እሰከ ሀምሌ 7 ቀን 2012 ድረስ በሀገራችን የሚካሄድ ይሆናል።

አንቲቦዲ ማለት ሰውነታችን ለበሽታ በሚጋለጠበት ወቅት ለበሽታው ከተጋለጠ ከአንድ እስከ ሶስት ሳምንት ድረስ በሽታውን ለመከላከል ሰውነታችን የሚያመርታቸው የበሽታ ተከላካዩች ናቸው። በሰውነታችን ውስጥ የአንቲቦዲ መመረት በእድሜ፣ የአመጋገብ ሁኔታ፣ የምንጠቀማቸው መድሁኒቶች፣ የበሽታው ከባድነት እና ተጓዳኝ በሽታዎች ላይ ይወሰናል። ምርመራው ከሰውነታችን ከ3-5 ሚሊ ሊትር ደም ናሙና በመውሰድ የሚደረግ ሲሆን የበሽታው ተከላካዮች (አንቲቦዲ) እንደየበሽታው ዓይነት የሚለያዩ ሲሆን ምርመራው ኮቪድ-19 ለመካላከል እና ለ መቆጣጠር ለሚደረገው የቅኝት ዳሰሳ ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው። ነገር ግን የአንቲቦዲ ምርመራ ውጤትን ብቻ ተጠቅሞ ህክምና መስጠት አይቻልም።

ይህ የቅኝት ዳሰሳ በሀገራችን ያለውን የኮሮና ቫይረስ በሽታ (ኮቪድ-19) ስርጭት ለማወቅ ከሰኔ 15 ቀን 2012 ጀምሮ በአዲስ አበባ፣ ድሬደዋ ከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በሁሉም ክልሎች ይካሄዳል። በመሆኑም ህብረተሰቡ፣ የጤና ባለሙያዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለትግበራው አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ እንጠይቃለን።
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 131 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው
.በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1297 ደርሷል
*****************************
(ኢፕድ)
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3238 የላብራቶሪ ምርመራ 131 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4663 ደርሷል።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 26 (10 ከጤና ተቋም እና 16 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን አንድ ናሙና ከማህበረሰብ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሰባ አምስት (75) ደርሷል፡፡

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሰማንያ አራት (84) ሰዎች (79 ሰዎች ከ አዲስ አበባ፣ 2ሰዎች ከኦሮሚያ፣ 2 ሰዎች ከትግራይ እና 1 ሰው ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1297 ነው።
ከአንድ እናት በአንድ ጊዜ የተወለዱ ሦስት ጨቅላ ህጻናት ኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው
=============================
በሜክሲኮ ከአንዲት እናት በአንድ ጊዜ አዲስ የተወለዱ ሦስት ጨቅላ ህጻናት በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ።
ጨቅላ ህጻናቱ በቫይረሱ አንዴት ሊያዙ እንደቻሉ በጤና ባለሙያዎች ላይ ግርታን የፈጠረ ሲሆን፤ የጤና ባለሥልጣናትም ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ነገር ሰምተው እንደማያውቁ ተናግረዋል።
ጨቅላ ህጻናቱ ምርመራ የተደረገላቸው ከተወለዱ በኋላ በሰዓታት ውስጥ ሲሆን ቫይረሱ እንዳለበት ከታወቀ ማንኛውም ሰው ጋር ምንም ዓይነት ንክኪ አልነበራቸውም ተብሏል። ቢ ቢ ሲ
በአዲስ አበባ ከተማ እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ መረጃዎችን ማግኘትና ሀሳብ መስጠት የሚቻልበት የኪነ ህንጻ እና ከተማ ማእከል ተከፈተ።

ማእከሉ መስቀል አደባባይ ፊትለፊት ላይ የተዘጋጀ ሲሆን የካፌ አገልግሎትና ዋይፋይ የተዘጋጀለት ነው።

በማእከሉ የትኛውም ዜጋ ስለከተማዋ እቅዶችና ፕሮጀክቶች መመልከትና የራሱን ሀሳብ በፅሁፍና በድምፅ መስጠት ይችላል።

የተሰጡት አስተያየቶች በቦታው የሚገኙ ባለሙያዎች በማሰባሰብ ለከንቲባው በየጊዜው የሚያቀርቡ ይሆናል።

የማእከሉ መቋቋም የከተማዋ ነዋሪ በከተማዋ ላይ ያለው ተሳትፎ እንዲጨምርና ስለ ከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች ላይ ግንዛቤ እንዲፈጠርና ግልፅነት ለመፍጠር ያለመ ነው።
ባለፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ 185 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3775 የላቦራቶሪ ምርመራ 185 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

በአጠቃላይ በአገሪቱ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4ሺህ 848 ደርሷል።

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 184 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 1 ሰው የውጭ ዜጋ ነው ተብሏል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 47 ወንዶች እና 138 ሴቶች ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸውም ከ3 ወር ህጻን እስከ 80 ዓመት እንደሚገኙም ተገልጿል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 160 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 2 ሰዎች ከሱማሌ ክልል፣ 7 ሰዎች ከኦሮሚያ፣ 1 ሰው ከሀረሪ ክልል፣ 4 ሰዎች ከአፋር ክልል፣ 2 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 1 ሰው ከጋምቤላ ክልል፣ 7 ሰዎች ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል እና 1 ሰው ከትግራይ ክልል መሆናቸውን ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 115 ሰዎች (81 ከአዲስ አበባ፣ 23 ከአማራ፣ 6 ከኦሮሚያ፣ 2 ከሀረሪ፣ 2 ከቤንሻንጉል ጉምዝና 1 ሰው ከትግራይ) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥርን 1412 አድርሶታል።

በአጠቃላይ ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ 3 ሺህ 359 ሰዎች ሲሆኑ ከነዚህ መካከል 38 በፀና የታመሙ መሆናቸው ተገልጿል።

በኢትዮጵያ እስካሁን 223 ሺህ 341 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል