ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5274 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሃያ ዘጠኝ (129) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3759 ደርሷል።
ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 18 (11 ከጤና ተቋም እና 7 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት ናሙና የለም። ከዚህ ባለፈ ሁለት በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ስልሳ ሶስት (63) ደርሷል፡፡
በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት አንድ መቶ አስራ አንድ (111) ሰዎች (109 ከአዲስ አበባ እና 2 ከድሬዳዋ) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 849 ነው።

ዴክሳሜታሶን በኮሮናቫይረስ ታማሚዎች ላይ ያስገኘውን ውጤት መልካም ነው፣
.የመድሃኒቱ ጠቀሜታ በጸና በታመሙ ሰዎች ላይ እንጂ ቀለል ያለ ህመም ባላቸው ላይ አይደለም - የዓለም ጤና ድርጅት
****************************
(ኢፕድ)
በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ዴክሳሜታሶን በተባለው መድኃኒት ላይ የተደረገው ሙከራና ያስገኘውን ውጤት በበጎ እንደሚመለከተው የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም እንዳሉት "ይህ ኦክስጂንና የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ ለሚያስፈልጋቸው የኮሮናቫይረስ ህሙማን ላይ የሚያጋጥምን ሞት የሚቀንስ የመጀመሪያው መድኃኒት ነው" ብለዋል።
በሙከራው ይህ መድኃኒት በኮሮናቫይረስ በጽኑ ከታመሙ ሰዎች የአንድ ሦስተኛውን ሕይወት መታደግ እንደሚችል እና በወረርሽኙ ሰበብ ኦክስጂን በሚያስፈልጋቸው ሰዎች ላይ የሚያጋጥምን ሞት በአንድ አምስተኛ ሊቀንስ እንደሚችል ለድርጅቱ የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ ግኝት አመልክቷል።
ድርጅቱ እንዳለው የዴክሳሜታሶን ጠቀሜታ በኮቪድ-19 በጸና በታመሙ ሰዎች ላይ እንጂ ቀለል ያለ ህመም ባለቸው ላይ እንዳልሆነ አመልክቷል።
ዴክሳሜታሶን ከ1960ዎቹ (እአአ) ጀምሮ በተለያዩ ህመሞች ምክንያት የሚያጋጥሙ እብጠቶችን ለመቀነስና የተወሰኑ አይነት የካንስር ህመሞችን ለማከም ጥቅም ሲውል ቆይቷል።

‹‹የህዳሴ ግድቡ ግንባታ በወቅቱ ቦርድ ሰብሳቢ በነበሩት ዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል አድራጊ ፈጣሪነት በፍጥነት ተዳክሞ ለከፍተኛ ኪሳራ ተዳርጓል›› ሲሉ የቀድሞው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትርና፤ በሩሲያ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ አስታወቁ፡፡
አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት ፣ የህዳሴ ግድቡ አቶ መለስ በህይወት እስከነበሩበት ጊዜ ድረስ በየወሩ ይገመገም የነበረ ሲሆን ከእርሳቸው ህልፈት በኋላ በየወሩ መገምገሙ ቀርቷል፡፡
የወቅቱ የቦርድ ሰብሳቢ በክላስተር አደረጃጀት በሁለት ወር አንድ ጊዜ እንዲታይ ብለው አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን አስታውሰው ፣ ሰብሳቢው አሠራሩን ተግባራዊ ሳይደርጉ መቅረታቸውንም አመልክተዋል። በዚህ ሁኔታ የህዳሴ ግድቡን ፕሮጀክት የመብራት ኃይል ቦርድ አካልም ይገመግመው እንዳልነበር ጠቁመዋል::
ፕሮጀክቱን በሚመለከት በየጊዜው ለቦርዱ ጥያቄ እናቀርብ ነበር ያሉት አምባሳደር አለማየሁ፣ ቦርዱም ገምግሞ ወደ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የግምገማውን ውጤት አይልክም ነበር ብለዋል፡፡ የዘርፉ ባለቤት ብንሆንም ተገልለን ነበር፤ ሪፖርትም ከመብራት ኃይል እየወሰድን ጉድለቶቹን እንናገር ነበር ሲሉም ተናግረዋል::
እንደ አምባሳደሩ ገለጻ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከመብራት ኃይል የሚያገኘውን መረጃ ይዞ እንደ ዘርፍ መግለጫ በሚሰጡበት ወቅት እንኳን ‹‹ምን አግብቷችሁ ነው መግለጫ የምትሰጡት›› በማለት በቦርድ ሰብሳቢው በኩል ቁጣ ይደርስባቸው እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
በዚህ ሁኔታም ፕሮጀክቱ ከህዝብ ፕሮጀክትነቱ ወርዶ የአንድ ግለሰብ ፕሮጀክት ሆኖ እንደነበር አመልክተዋል። ይህም የግድቡን ግንባታ ለውድቀት ከመዳረጉ ባለፈ ‹‹በአገራችን ታሪክ የሚያሳዝን ድርጊት ሆኖ አልፏል›› ብለዋል፡፡

‹‹ግብፅ በአባይ ውሃ አጠቃቀም ላይ ያላት ምርጫ ከኢትዮጵያጋር መተባበር ብቻ ነው››
‹‹በአባይ ውሃ የኢትዮጵያ መብት፣ ከግብፅ የተረፈ መሆን የለበትም›› ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ በአአዩ መምህርና የዓባይ ውሃ ጉዳይ ተመራማሪ
*****************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ፡- ‹‹ዛሬም ሆነ ወደፊትም ግብፅ በአባይ ውሃ አጠቃቀም ላይ ያላት ምርጫ ከኢትዮጵያ ጋር መተባበር ብቻ ነው›› ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና የአባይ ውሃ ጉዳይ ተመራማሪና ተደራዳሪ ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ ገለጹ፡፡
ፕሮፌሰር ያዕቆብ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደተናገሩት፤ ለግብፅ ሌላ አማራጭ ማማተር ከንቱ ነው፡፡ ግብፅ፣ ሱዳን ወይም የትኛውም ሌላ ወገን ማወቅ ያለበት እ.ኤ.አ ከ2015 የመርህ መግለጫ ሰነድ በስተቀር ኢትዮጵያ ከግብፅም ሆነ ከሱዳን ጋር አስገዳጅ ውለታ እንደሌላት ነው፡፡
‹‹በአባይ ውሃ የኢትዮጵያ መብት፣ ከግብፅ የተረፈ መሆን የለበትም›› ያሉት ፕሮፌሰሩ፣ ይህ ከሆነማ ኢትዮጵያ የውሃ መብት ሉዓላዊ ባለቤትነት አይኖራትም ማለት ነው›› ብለዋል፡፡
እንደ እርሳቸው ገለጻ፤ እስከዛሬም ድረስ ግብፅ የምትሄድበት አካሄድ የማይገባት አካሄድ መሆኑ መታወቅ አለበት። የአባይ ውሃ ከኢትዮጵያ ይነሳል። ለወደፊቱም እንዲሁ ይቀጥላል። ድንበር ተሻጋሪ ሀብት ስለሆነ በመተሳሰብና በመተባበር በውሃ ሀብቱ ሁሉም መጠቀም ይችላል። ስለዚህም የግብፅ ፍላጎት የሌሎች ውሃ ተጋሪዎች ጥቅም፣ መብትና የልማት ፍላጎት ሊረመርም አይገባም፤ አይችልምም። ምንጊዜም ቢሆን የግብጽፅ ፍላጎት በጉልበት ሌሎች ላይ ሊጫን አይችልም። በጦርነትም አይሆንም።
‹‹ኢትዮጵያውያን ለግብፅ የተሳሳተ ፍላጎት ሲባል ጥቅማቸውን ዘንግተው እጃቸውን አጣጥፈው መብታቸውን ጥለው ይቀመጣሉ ተብለው አይታሰብም።›› ሲሉም ጠቅሰው፤ ግብፅ በጦርነት ፍላጎቷን ለመጫን ስንት ጦርነት ትዋጋለች? ስንት ጊዜስ ትዋጋለች? የግብፅን ጦርነት በትህትና የሚያስተናግድ ማንን ታገኛለች።›› ሲሉም አብራርተዋል።
ፕሮፌሰር ያዕቆብ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን ሌሎች የናይል ውሃ አመንጪ አገሮች የራሳቸውን
ጥቅምና መብት ጥለው ግብፅን በትህትና አያስተናግዱም። የጦርነት ሐሳብ የተሳሳተ ብቻ ሳይሆን የቂል አስተሳሰብም ጭምር ነው። በተለይ ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ በጦርነት የውሃ ፍላጎቷን ለማሟላት ማሰቧ በዲፕሎማሲና በመተሳሰብ የመሽራት ሐሳቡም ሆነ እውቀቱ ርቋታል ማለት ነው።
ለተጨማሪ https://www.press.et/Ama/?p=34609

www.press.et
‹‹ግብፅ በአባይ ውሃ አጠቃቀም ላይ ያላት ምርጫ ከኢትዮጵያ ጋር መተባበር ብቻ ነው ›› ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ በአአዩ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና የዓባይ ውሃ ጉዳይ ተመራማሪ…
የፀሐይ ግርዶሹን ለመመልከት ሊመጡ የሚችሉ 20ሺህ ቱሪስቶችን እና ሳይንቲስቶችን በኮሮና ሳቢያ ኢትዮጵያ እንዳጣች ተገለጸ
***************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ፡- በመጪው እሁድ የሚጠበቀውን የፀሐይ ግርዶሽ ክስተት ለመመልከት ብለው ሊመጡ የሚችሉ 20ሺህ ቱሪስቶችን እና ሳይንቲስቶችን ኢትዮጵያ በኮሮና በሽታ ምክንያት ማጣቷን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
ከጎብኚዎች ሊገኝ የሚችለው ገቢ በበሽታው ምክንያት ቢቀርም የሀገርን ገጽታ ከማስተዋወቅ አንጻር ግን ክስተቱን በቀጥታ በማህበራዊ ድረገጽ እና የቴሌቪዥን ስርጭት ለዓለም ህዝብ ለማስተላለፍ የባለሞያዎች ቡድን ወደላሊበላ እና ባህርዳር ከተሞች መላኩን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ይልማ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ ሰኔ 14 ቀነ 2012 ዓ.ም በኢትዮጵያ የሚታየውን የፀሐይ ግርዶሽ ለገቢ ማስገኛ፣ ለመልካም ገጽታ ግንባታ እና ለወጣት ኢትዮጵያውያን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ማነቃቂያነት እንዲውል ታስቦ ቅድመ ዝግጅት ሲካሄድ ቆይቷል። ተመሳሳይ ክስተቶች በሌሎች ሀገራት ሲታዩ በአንድ ቀን 20ሺህ ቱሪስት እንደሚገኝ በመታወቁ በኢትዮጵያም ተመሳሳይ ቁጥር ያለው የውጭ ዜጋ እንደሚገኝ ተገምቶ ነበር። ይሁንና ኮሮና በመከሰቱ የአንድ ቀኑን ተፈጥሯዊ ክስተት ለመመልከት ብለው ይመጡ የነበሩ ቱሪስቶችን ኢትዮጵያ አጥታለች።
እንደ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ፤ ቱሪስቶችንና የተለያዩ ሳይንቲስቶችን በኢትዮጵያ ለማስተናገድ ባይቻልም የግርዶሹን ክስተት በቀጥታ በማህበራዊ ድረገጽ እና በቴሌቪዥን በማስተላለፍ የሀገርን ገጽታ ለዓለም ለማስተዋወቅ ዝግጅት ተደርጓል። ለሥራውም ባህርዳርን እና ላሊበላ ከተሞችን ጨምሮ ወደሦስተ ቦታዎች አነስተኛ ቴሌስኮፖች እና የተለያዩ የፀሐይ ግርዶሹን መመልከቻ
መሳሪያዎች ተልከዋል። መሳሪያዎቹን የሚቆጣጠሩ እና የቀጥታ ስርጭቱን ሥራ የሚያሳልጡ ባለሙያዎችም ወደአካባቢዎቹ ተንቀሳቅሰዋል። በዚህምተግባር መላው ዓለም ክስተቱን እንዲከታተለው ከማድረግ ባለፈ ኢትዮጵያ በሳይንሱ ረገድ እያበረከተችው ያለውን አስተዋጽኦ ለዓለም ለማሳየት ጥረት ይደረጋል።
ኢንስቲተዩቱ ከዓለም አቀፉ እና ከአፍሪካ የአስትሮኖሚ ድርጅቶች ጋር በቅንጅት የፀሐይ ግርዶሹን በተመለከተ የሚደርሱ መረጃዎችን ለዓለም ለማሳወቅ እየሠራ መሆኑን የገለጹት አቶ አብዲሳ፤ ይህም ኢትዮጵያ በሳይንሱ ዘርፍ ያላትን ተሳትፎ የምታሳድግበት አንዱ መንገድ መሆኑን ተናግረዋል።
ለተጨማሪ https://www.press.et/Ama/?p=34639

ኢትዮጵያ በኮሮና ምክንያት በአንድ ቀን 20 ሺህ ቱሪስቶችን እንደምታጣ ተጠቆመ | የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
"ለኮቪድ-19 ህሙማን የሚውለውን ዴክሳሜታዞን የተባለውን መድሀኒት በተመለከተ በእንግሊዝ መንግስት የተካሄደውን ጥናት እና ሪፖርት በዝርዝር ተመልክተነዋል፡፡ የህክምና ጉዳዮች አማካሪ ቡድናችን እና የጤና ባለሙያዎች አማካሪ ምክር ቤት፣ የሰጠንን ምክረ ሀሳብ መሰረት በማድረግ፣ ኦክሲጅን ወይም የመተንፈሻ መሳሪያ እገዛ ለሚያስፈልጋቸው የኮቪድ-19 ህሙማን አነስተኛ መጠን ያለው ዴክሳሜታዞን እንደ ድኝገተኛ ህክምና ለመጠቀም ተወስኗል። ህክምናውን አስመልክቶ ዝርዝር መመሪያ በቅርቡ ይወጣል"
- ዶ/ር ሊያ ታደሰ የጤና ሚኒስትር
- ዶ/ር ሊያ ታደሰ የጤና ሚኒስትር
‹‹የህዳሴ ግድቡን ሸጣችሁታል›› የሚሉና መሰል ሀሳቦች ይሰማሉ። ለማን ይሸጣል። ሻጭም ገዥም የለም። ግድብ መርከብ አይደለም አንስተህ ለሌላ አገር አትሸጠውም።
👉ባይሆን የግድቡን መረጃ እየወሰዱ ከሌሎች ስራውን ከማይደግፉ አገራት ጋር መደራደር ነው መሸጥ ማለት።
👉 የህዳሴ ግድቡን በሚመለከት ለመሸጥ የሚደረግ ድርድር የለም። ድርድር ያለው ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ላይ ነው፤
👉በዚህ የኢትዮጵያ መንግስት በተለይ የዶክተር አብይ አቋም የፀና ነው። አቶ ኃይለማርያምም ሆነ አቶ መለስ የነበራቸው አቋም የፀና ነው፤ የሚዋዥቅ አይደለም።
👉 ድርድርን በሚመለከት ባለፈው ጊዜ ዶክተር አብይ ሩሲያ መጥቶ ነበር። ከግብፅ ፕሬዚደንት አልሲሲ ጋርም ሆነ ከፕሬዚደንት ፑቲን ጋር ሲወያይ ነበርኩ።
👉ከአልሲሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ዶክተር አብይ ‹‹ግድቡን በሚመለከት አሁን የቀረው ጉዳይ የቴክኒክ ስለሆነ እኛው እንጨርሰው፤ የትም አንውሰደው›› ብለው ነግረዋቸው ተስማምተው ነበር።
👉 አልሲሲ በወቅቱ ለዶክተር አብይ ያነሱላቸው ሀሳብ ላስታውስህ ‹‹ፓርላማ ላይ ግድቡን በሚመለከት እዋጋለሁ ብለሀል›› ብለው ጠይቀውት ነበር። ዶክተር አብይ በምላሻቸው ‹‹ፕሮጀክቴን ከአደጋ እከላከላለሁ ማለት ምን ነውር አለው?
👉 ደግሞም ወታደር ነኝ ፕሮጀክቱ ላይ አደጋ የሚያደርስን አካል መከላከል አለብኝ፤ ምን ስህተት አለው ብለህ ነው›› ብለው እስከመመለስ ደርሰዋል እንኳን ጥቅምን አሳልፈው ሊሰጡ ቀርቶ።

የህዳሴ ፕሮጀክቱን የመብራት ሀይል ቦርድ አካል አይገመግመውም ነበር። በዚህ ጉዳይ በየጊዜው ለቦርዱ ጥያቄ እናቀርብ ነበር። ትልቁ ችግር ቦርዱም ገምግሞ ወደ ውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር የግምገማ ሪፖርቱን አይልክም ነበር።እኛ ግን ሪፖርቶችን ከመብራት ሀይል እየወሰድን ጉድለቶቹን እንናገር ነበር።
👉 በዚሁ ሁኔታ ውስጥ የምናገኘውን መረጃ ይዘን እንደ ዘርፍ መግለጫ በምንሰጥበት ወቅት ‹‹ምን አግብቷችሁ ነው መግለጫ የምትሰጡት›› በማለት በቦርድ ሰብሳቢው በኩል ቁጣ ይደርስብን ነበር።
👉ቦርድ ሰብሳቢው ለግድቡ እኔ ብቻ ነኝ ቢሉም በዚህ ረገድ እርምጃ ከመውሰድ ይቅል ሽፋን በመሆን አልፈውታል።
👉 በዚህ ሁኔታም ፕሮጀክቱ ከህዝብ ፕሮጀክትነቱ ወርዶ የአንድ ግለሰብ ፕሮጀክት ሆነ። ይህም የግድቡን ግንባታ ለውድቀት ከመዳረጉ ባለፈ በአሀገራችን ታሪክ የሚያሳዝን ድርጊት ሆኖ አልፏል።
👉 የህዳሴ ግድቡ ስራና ውሳኔዎች ወደ አንድ ሰው ፕሮጀክት ሆነ/One man project/ የሚለው ስያሜ በሚገባ ይገልፀዋል። ይህም ሁኔታ ነው ግድቡን ለውድቀት የዳረገው።
👉 ይህ ትክክል እንዳልሆነ ለቦርድ አባላት ስናነሳ ነበር። ምናልባት በወቅቱ የቦርድ አባላት ከነበሩት ውስጥ የተወሰኑትን አስታውሳለሁ።
👉 የቦርድ ሰብሳቢው ዶክተር ደብረፂዮን ነው። አባላት ደግሞ ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ደበበ የሚባል፣ ወርቅነህ ገበየሁም አንድ ወቅት ነበር፤ ከንግድ ባንክ ተወካይ፤ ረዘም ያለ ጊዜ ስለሆነ እነዚህን ብቻ አስታውሳለሁ። እነዚህን አባላት ፕሮጀክቱን ይገመግሙ ነበር ወይ ተብለው ሲጠየቁ እንደማይገመግሙ ይናገሩ ነበር።
👉 ህዳሴ ግድቡ በተለይ በአንድ ሰው አድራጊ ፈጣሪነት ብቻ ከተሸጋገረ በኋላ ስራው በፍጥነት ተዳክሞ ለመቆም በቅቷል።

የህዳሴ ግድቡ ግንባታ ሲጀመር የነበረው የህዝብ መነቃቃት በጣም አስደሳች ነበር። ምክንያቱም አባይ ብዙ ጊዜ ለዘፈን እንጂ ለአገር ልማት ውሎ ባለማወቁ፤ ለዘመናት እንዲሁ ቁጭት ሆኖ የኖረ ወንዝ ነው።
👉 ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሀይል ፍላጎት አላት። ይህን ፍላጎቷን ልታሳካ የምትችለው በዋናነት ከውሀ ሀብቷ ነው።
👉 የእናቶቻችን የከፋ የኑሮ ሁኔታ፤ በጭስ እና በማገዶ ሸክም ላይ የተመሰረተ መሆን፣ ተማሪዎቻችን በጨለማ ትምህርት መከታተል፣ እናም በአጠቃላይ አገሪቱ በሀይል እጦት ምክንያት ከፍተኛ ችግር ውስጥ ገብታ ረዥም አመታትን ተጉዛለች፤ አሁንም እየተጓዘች ነው።
👉 የህዳሴ ግድቡ ግንባታ መዘግየት የኤክትሮሜካኒካል እና ሀይድሮ ሜካኒካል ለመስራት የገባው የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን /ሜቴክ/ ግዳጁን ባለመወጣቱ ነው ዋናው ችግር።
👉 ሜቴክ በትዕዛዝ ያስገባው መንግስት ነው። በወቅቱ ሜቴክ አቅም የለውም፤ ብለን ከፍተኛ ክርክር አድርገናል። ክርክራችን አገሪቱን ሲመሩ ከነበሩ ሰው ጋር ነው፤ ነገር ግን ተቀባይነት አላገኘም።ትልቁ ስህተት እዚህ ጋር ነው የሚጀምረው።
👉 ስራው እንደተጀመረ በየወሩ ይገመገም ነበር። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በተለይ ከአቶ መለስ ህልፈት በኋላ በየወሩ መገምገም አቆመ። ስራውም በከፍተኛ ባለሙያዎችና ኃላፊዎች መገምገሙ ቀርቶ የህዳሴ ግድቡ ማስተባበሪያ ቦርድ ብቻ እንዲያየው ሆነ፤ ከቦርድም የተወሰነ ሰው ብቻ እንዲያየው ሆነ። 👉 የመብራት ሀይል ቦርድ እንኳን በሙሉ አቅሙ እየገመገመው አልነበረም። መጨረሻ በቦርድ ሰብሳቢው አመራርነት ብቻ መጓዝ ጀመረ።
👉 መጨረሻ በአስተባባሪ ቦርዱ ሰብሳቢና የፕሮጀክት ኃላፊው ብቻ መመራት ጀመረ። እንደ ዘርፍም ውሀ መስኖና ኢነርጂ መሳተፍ ሲኖርበት እንዲገለል ተደረገ።

ኮንትራቱን የሚያስተዳድረው መብራት ሀይል እና ቦርዱ ሜቴክ ላይ እርምጃ መውሰድ ይችሉ ነበር።
👉 ሜቴክን ፊት ለፊት የተጋፈጥንበት ሁኔታ ቢኖርም መስተካከል አለበት ያልነውን በግምገማ ውስጥም ያነሳንበት ሁኔታ አለ። የቦርዱም ሆነ የመብራት ሀይል ችግር የገዘፈ ነበር።
👉 ሜቴክ ከመብራት ሀይል ብዙ ፕሮጀክቶች ተሰጥተውት አንዳቸውንም ሳያከናውን ቀርቷል።
👉 በዚህ ረገድ ሜቴክ ከ5200 ሜጋ ዋት ወደ 6000 ሜጋ ዋት አሳድጓል የተባለውን መቀበሉ ትክክል አይደለም። በወቅቱ በዘርፉ ውስጥ አልነበርኩም ግን ትክክል እንዳልሆነ ዘርፉን ለሚመሩ ሰዎች አሳውቄ ነበር።
👉 የሀይል /ኢነርጂ/ ለውጥ በሌለበት ሜጋ ዋቱን ብታሳድግ ተቀባይነት የለውም። ለዚህ ነው አሁን የመጣው አመራር ይህን ያስተካከለው። ሌላው ሜቴክ ስራውን በጊዜ ባለመጨረሱ ሲቪል ስራውም ቆሞ ነበር።
👉 ከለውጥ በኋላ በአገሪቱ ቀድሞ ተፈጽመው ከነበሩ ስህተቶች ውስጥ በከፍተኛ ጥንቃቄ ከተገመገሙ ጉዳዮች አንዱ የህዳሴ ግድቡ ነው።
👉 የህዳሴ ግድቡ በተለይ ከለውጡ በኋላ ጥራቱን ጠብቆ በሚፈለገው ሁኔታ እየተጓዘ ነው፤ ውሃ ለመሙላት ደርሷል። በፕሮጀክቱ ግንባታ በዚህ መልኩ የተጓዘበት ጊዜ የለም።
👉 በሁለት አመታት ውስጥ ዓለም አቀፍ ባለሙያዎችን ማምጣት በራሱ ጊዜ ይፈልጋል። እንደ ሜቴክ አምጥተህ የምትሰጠው ስራ አይደለም። አሁን እኮ ለውጡ እየታየ ነው። 👉ዘገየ የሚለው ሀሳብ ለተራ የፖለቲካ ጥቅም ፍለጋ ካልሆነ በስተቀር ሚዛን የሚደፋ ትችት አይደለም።
👉 ድርድሩን በተመለከተ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ምንም የተለሳለሰ ነገር የለም። ነገር ግን ግብፆች ለውይይት እና ድርድር ሲመጡ የተለያዩ ውሸቶችን ይዘው ነው።
👉

የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል በወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥር ባሉ አንዳንድ መመሪያዎች ላይ ማሻሻያ ተደርጓል፤
የአስከሬን የላቦራቶሪ ውጤት ሳይገለጽ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎችን መቅበር ተከልክሎ የነበረው ክልከላ ተነስቶ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ በህበረተሰቡ የቀብር ሥነ ሥርዓት መሰረት መፈጸም ተፈቅዷል፤
አሁንም ግን በቀብር ስነ ስርዓት ላይ መገኘት የሚፈቀደው 50 ሰዎች ብቻ ናቸው፤
ከውጭ የሚገቡ ሰዎች በተለይም ወደ አገር ከገቡ በኋላ ባለፉት ሦስት ቀናት ውስጥ ከመጡበት አገር ተመርምረው ነጻ መሆናቸውን የሚያሳይ መረጃ ይዘው ከመጡ ናሙና ተወስዶ በቤታቸወ 14 ቀናት እንዲቆዩ ይደረጋል፤
በሌላ በኩል ነጻ መሆናቸውን የሚያረጋገጥ ሪፖርት ይዘው ለማይመጡ መንገደኞች ናሙናቸው ተወስዶ ለሰባት ቀናት በለይቶ ማቆያ እንዲቆዩ ይደረጋል፤

"እንሥራ" የሸክላ ስራ ማእከል ተመረቀ።
የሸክላ ስራ ማእከሉ ግንባታው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቀ ነው።
የሸክላ ስራ ማእከሉን ኢ/ር ታከለ ኡማና ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦች መርቀው ስራ አስጀምረውታል።
በማእከሉ 1000 በሸክላ ስራ ላይ የተሰማሩ እናቶች የመስሪያና የመሸጫ ቦታዎች ከተሟላ የማምረቻ ቦታ ከተሟላ ቁሳቁሶች ጋር የሚያገኙ ይሆናል።
የሸክላ ስራ የሙያውን ያህል ያልተከበረ የድካሙን ያህልም ጥቅም ያልተገኘበት ሆኖ ቆይቷል ያሉት ኢ/ር ታከለ ኡማ የከተማ አስተዳደሩ ይሄን ዘርፍ ባለሙያዎችን በሚያሳድግ ሀገርን በሚጠቅም መልኩ ለማሳደግ ይሰራል ብለዋል።
የሸክላ ምርቶቹ ከሀገር ውስጥ ገበያ አልፎ በአለም አቀፍ ደረጃ ገበያ እንዲያገኝ ከተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ንግግር እየተደረገ ነው ያሉት ኢ/ር ታከለ ዘርፉን የሚደግፉ የህግ ማሻሻያዎችም እየተዘጋጁ ነው ብለዋል።
በከተማዋ ከሸክላ ስራ ማእከሉ በተጨማሪ የሸማ ጥበብ ማምረቻና መሸጫ ማእከል ሽሮ ሜዳ አካባቢ እየተገነባ ይገኛል።

« ከስልጣን በሰላም ወርዶ በሰላም እንዲኖር እድል የተሰጠው ህወሃት ብቻ ነው»አቶ ኦሃድ ቤናሚ - የሚዲያ አማካሪ
• ከ20 ዓመታት በላይ የመሩት የሱዳን፣ ግብፅ፣ ቱኒዚያ፣ የሊቢያና የሌሎችም አረብ አገራት መሪዎች የተወገዱት በጦርነትና በአመፅ ነው::
• በዚህ ቀጠና በሰላም የወረደው ህወሃት ብቻ ነው፤ በሰላም ወርዶ በሰላም እንዲኖር እድል የተሰጠው ህወሃት ብቻ ነው::
• አሁን ያለው ትውልድ አንድ መሪ ከሁለት የምርጫ ዘመን በላይ እንዲቀጥል አይፈልግም::
• ከ25 ዓመታት በላይ የኖሩ መንግሥታት እየተዋረዱ፤ እየተገፉ የወረዱበት እውነታ ዓለም አቀፋዊ ክስተት ነው:: እኔ ህወሓት ምን እንደሚፈልግ አላውቅም::
• ህወሓቶች «አብይ አምባገነን ነው፤ ›ተጋሩ› እየተገደለ ነው» የሚሉት ነገር ሁሉ ውሸት ነው:: አንድ ነገር ልንገርሽ ፤ ህወሓት ከስልጣን ከተወገደ በኋላ እየተገደሉ፤ እየታፈኑ ያሉት የትግራይ ተወላጆች አይደሉም፤ የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች ናቸው::
• በየዩኒቨርሲቲውና በአንዳንድ የአገሪቱ አካባቢዎች ተፅዕኖ ሲደርስባቸው ያየነው አማራና የኦሮሞ ተማሪዎችን ነው::
• ህወሓት ምን እንደሚፈልግ ግልፅ አይደለም:: እዚህ አካባቢ በሰላም እንዲቀጥል የተፈቀደለት ብቸኛው መንግስት ህወሃት ብቻ ነው፤ ግን እየበጠበጠ ያለው ራሱ ነው::

• እውነቱን ለመናገር የባድመ ጦርነት የመሬት ጥያቄ አልነበረም:: ኢሳያስን የማደከምና ኤርትራን የመምታት ፍላጎት ስለነበር ነው::
• የኢትዮጵያን ህዝብ በኤርትራ ላይ ማስነሳት የምትችይው «መሬትህ ተወረረ» ስትዪው ብቻ ነው:: በወቅቱ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ በሻቢያ ላይ ትንሽ ቅሬታ ነበረበት::
• አገሪቱን ይመራው የነበረው ህውሃት በወቅቱ ኤርትራ ላይ የተጠቀመው የጦርነት ፖሊሲ ነው:: በወቅቱ የመሪና የአመራር ችግር ነበር::
• ላለፉት 20 ዓመታት ጦርነትም ሆነ ሰላም ሳይኖር የተቆየበት ዓመታት በተለይ የትግራይን ህዝብ የጎዳበት ሁኔታ እንደነበር እሙን ነው::
• ይህንን ሁኔታ ማስቀረት የቻለው የአብይ አስተዳደር ነው፤ ህውሃት20 ዓመት ሙሉ ችግሩን ታቅፎት ከመኖር ውጭ መፍትሄ ማምጣት አልቻለም:: ስለዚህ በዶክተር አብይ ትልቅ ለውጥ መጥቷል ብሎ በሙሉ ልብ መናገር ይቻላል:: -አቶ ኦሃድ ቤናሚ - የሚዲያ አማካሪ

የኢትዮጵያ ህዝብ ከህወሓት የሚፈልገው ሰላም ብቻ ነው:: የተጣለ አስተሳሰብ( አይዶሎጂ) ይዘህ፤ የ60ዎቹ የሁለተኛ ዓመት ተማሪዎች የቀረፀልንን አጀንዳ በ2012 ላለው ትልውድ ልታቀርበው አትችልም:: ዘመኑን የሚመጥን ሃሳብ ይዘህ መምጣት ይገባሃል የሚል መልዕክት ማስተላለፍ እፈልጋለሁ::
• በሌላ በኩል አንቀፅ 39 ላለፉት 27 ዓመታት ተነስቶ አያውቅም፤ አሁን ለምንድንው በትግራይ አካባቢ የሚነሳው? ህወሓት ከስልጣኑ ስለተባረረ ነው?
• በእኔ አስታሳሰብ ትግራይ ብትገነጠል መጀመሪያ የምትጎዳው ኢትዮጵያ ናት የምትመስለኝ:: ምክንያቱም ከአምስት ሚሊዮን በላይ የሚሆን ህዝብ ትግራይ ውስጥ አለ:: እሱን እናጣለን:: ምክንያቱም ቁጥራችን የሚጀመርው ከህዝብ ነው:: ስለመሬት፣ ስለማዕድንና ስለሃብት ከማውራታችን በፊት ልናጣ የምንችለውን ህዝብ ነው ማሰብ የሚገባን::
• በሁለተኛ ደረጃ በምትቀጥለዋ ትግራይ ምን ሊፈጠር ይችላል? ብዬ ሳስብ ደግሞ እሰጋለሁ:: ምክንያቱም በአንድ በኩል በጣም የመረረ ጥያቄ የሚያነሱ የአማራ ክልል ሰዎች አሉ:: ጅምላ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ተፈፅሞብናል የሚሉ አሉ:: በኤርትራ በኩል ያለውም ስሜት ጥሩ አይደለም::
• በታሪክ በተደጋጋሚ ከህወሓት ዘላቂ ግንኙነት ሊኖር እንደማይችል ኤርትራውያን ጠንቅቀው ያውቃሉ:: በምትገነጠል ትግራይ ውስጥ ኤርትራውያን በጣም ነቅተው የሚጠብቋት አገር ነው የምትሆነው:: አቶ ኦሃድ ቤናሚ - የሚዲያ አማካሪ

የግብጽ ሚዲያዎች በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ምንም አይነት ዘገባዎችን እንዳይሰሩ ታገዱ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
የግብጽ መገናኛ ብዙሀን እና የማህበራዊ መዲያ ተጠቃሚዎች በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ምንም አይነት ዘገባዎችን እንዳይሰሩ ታገዱ።
የግብጽ የሚዲያ ምክር ቤት ባስተላለፈው እገዳ መሰረት፤ የአገሪቱ መገናኛ ብዙሀንና የማህበራዊ ሚዲያዎች ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና መሰል ጉዳዮች ምንም አይነት ዘገባ እንዳይሰሩ ተከልክለዋል።
ምክር ቤቱ በዚሁ እገዳው የትኛውም ሚዲያም ሆነ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጻፍም ሆነ ውይይት ማድረግ አይቻልም ብሏል።
ምክር ቤቱ ከዚህ በኋላ በመንግስት ከሚነገሩ መረጃዎች ውጭ የተጠቀመ ማንኛውም አካል ህጋዊ እርምጃ ይወሰድበታል ሲል እገዳውን ይፋ አድርጓል።
የግብጽ መንግስት ተቃዋሚዎች እገዳውን በማውገዝ ድምጻቸውን ያሳሙ ሲሆን፤ ድርጊቱን ሳንሱር ነው ብለውታል።
ይህ እገዳ በመንግስት ስፖንሰር አድራጊነት የተላለፈና የመረጃ ነጻነትን የሚጋፋ ውሳኔ ነው ሲሉም ውሳኔውን ተቃውመውታል።
ይህ አይነቱ እገዳ ከሞራል አንጻር ስህተትም ብቻ ሳይሆን ለህዝቡም የደህንነት ስጋት ነው ያሉት እነዚህ ወገኖች፤ መንግስት ወደዚህ አይነቱ ተግባር መግባቱ ከህዝብ መረጃ የመደበቅ ተግባር ማሳያ ነው ማለታቸውን ሚድል ኢስት አይ ባወጣው ዜና አስነብቧል።

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 399 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው
*****************************
(ኢፕድ)
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4848 የላብራቶሪ ምርመራ 399 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4469 ደርሷል።
ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 22 (8 ከጤና ተቋም እና 14 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት ናሙና የለም።
በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ዘጠና አምስት (95) ሰዎች (82 ከአዲስ አበባ፣ 8 ከአማራ ክልል፣ 2 ከሶማሊ ክልል ፣ 1 ከትግራይ ክልል፣ 1 ከኦሮሚያ ክልል እና 1 ሰው ከጋምቤላ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1122 ነው።

በሕንድ በአንድ ቀን ከ15 ሺህ በላይ የኮሮናቫይረስ ህሙማን ተገኙ
----------------------------------------------------------------
ሕንድ በአንድ ቀን ውስጥ 15 ሺህ 413 በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ማግኘቷን በምርመራ አረጋገጠች።
ይህም በአገሪቱ ወረርሽኙ መገኘቱ ከታወቀ ወዲህ በአንድ ቀን የተገኘው ከፍተኛው የህሙማን ቁጥር ነው።
በዛሬው ዕለት የተገኘው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ከፍተኛ ቁጥር እስካሁን በሕንድ ያለውን አጠቃላይ የህሙማን ብዛት ወደ 410 ሺህ 461 ያደረሰው ሲሆን ይህም ከአሜሪካ፣ ከብራዚልና ከሩሲያ ቀጥሎ ሕንድን በዓለም አራተኛ ደረጃ ላይ እንድትቀመጥ አድርጓታል።
ከዚህ በተጨማሪ በበሽታው ምክንያት 306 መሞታቸው በዛሬው ዕለት የተነገረ ሲሆን በአጠቃላይ በአገሪቱ የሞቱትን ሰዎች ብዛት ወደ 13 ሺህ 254 አድርሶታል። ቢ ቢ ሲ