Ethio-Terit SACCOS Official Channel
447 subscribers
681 photos
39 videos
183 links
አልመው ይቆጥቡ አቅደው ይበደሩ!
Kaayyoon qusadhaa, karooraan liqeeffadhaa!

Save purposely, borrow strategically!
Download Telegram
Forwarded from Aboma Ejara
ኢትዮ ጥሪት ቁጠባና ብድር ኀ/የተ/መ/ህ/ስ/ማህበር ለአንድ ሳምንት ያህል ሲያሰለጥናቸው የነበሩትን አዳዲስ ሰራተኞች ስልጠናውን ጨርሶ በዛሬው ዕለት ወደ ስራ አቀላቅሏል ።

አዲስ አበባ 5/12/2017

አገልግሎቱን በጥራት እና በስፋት ለማድረስ እየተጋ የሚገኘው ኢትዮ ጥሪት ቁጠባና ብድር ኀ/የተ/መ/ህ/ስ/ማህበር ለአንድ ሳምንት ያህል ሲያሰለጥናቸው የነበሩትን አዳዲስ ሰራተኞች ስልጠናውን ጨርሶ በዛሬው ዕለት ወደ ስራ አቀላቅሏል ።

  በዛሬ የጠዋት ፕሮግራም ላይም የተገኙት የማህበሩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ እንደሻው ተገኝ አዳዲስ ሰራተኞች በስልጠናው ሂደት ላይ ባሳዩት ዲሲፒሊን እና ተሳትፎ መደነቃቸውን ገልፀው ወደፊትም ከእነሱ ብዙ ነገር እንደሚጠብቁ እና እንደቤተሰብ እንደሚሰሩ ገልፀዋል ።

በመቀጠልም የማህበሩ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ሙላቱ በዕደ አዳዲስ ሰራተኞችን አመስግነው ማንኛውም አይነት ጥያቄም ሆነ እርዳታ ቢፈልጉ እስከ ማህበሩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ድረስ በመሄድ መጠየቅ እና መረዳት እንደሚችሉ ገልፀዋል።

በተጨማሪም የማህበሩ የማርኬቲንግ እና ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ክፍል ኀላፊ የሆኑት ዶ/ር አታክልት ኀይሉ ነባር ሰራተኞች አዳዲስ ሰራተኞችን አቅርበው እንዲተባበሩ እና እንዲያግዙ አርዓያም እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።


አዳዲስ ሰራተኞችም ወደ ኢትዮ ጥሪት በመቀላላቸው ዕድለኛ እንደሆኑና በዚህች አጭር ጊዜያት ብዙ ነገር እንደተማሩ ገልፀው ወደፊትም በጥራት እና በትጋት እንደሚሰሩ ተናግረዋል ።

በስተመጨረሻም ስልጠናውን በአግባቡ ለወሰዱት አዳዲስ ሰራተኞች ስልጠናውን መጨረሳቸውን የሚያሳይ ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።
2👍1
Forwarded from Aboma Ejara
Waldaan Hojii Gamtaa  Bu'uuraa Qusannoo fi Liqii Itiyoo Xirriit, hojjettoota haaraa torbee tokkoof leenjisaa ture gara hojiitti galche