Ethio-Terit SACCOS Official Channel
447 subscribers
681 photos
39 videos
183 links
አልመው ይቆጥቡ አቅደው ይበደሩ!
Kaayyoon qusadhaa, karooraan liqeeffadhaa!

Save purposely, borrow strategically!
Download Telegram
Forwarded from Aboma Ejara
የኢትዮ ጥሪት ቁጠባና ብድር ኀ/የተ/ህ/ስ/ማ በየሳምንቱ ለአባላቶቹ የሚሰጠውን ስልጠና ለ14ተኛ ዙር ዛሬም ሰጥቷል ።

አዲስአበባ 3/12/2017



በዋናነት የቁጠባ የብድር ና የማማከር አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው የኢትዮ ጥሪት ቁጠባና ብድር ኀ/የተ/የህ/ስ/ማ በየሳምንቱ ለአባላቶቹ የሚሰጠውን ስልጠና ለ14ተኛ ዙር ገላን ኮንደሚኒየም በሚገኘው በማህበሩ ዋና ቢሮ ዛሬም ሰጥቷል ።

  ስልጠናውንም የሰጡት የማህበሩ የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ክፍል ኀላፊ የሆኑት አቶ ተሾመ በቀለ ሲሆኑ ስልጠናው ለአባላቶች ጠቃሚ ይዘት እንዳለው ስልጠናውን ያልወሰዱ አባላትም በቀጣይ እንደሚዳረሱ ተናግረዋል።

   የስልጠናው ይዘቶችም ስለ ሕብረት ስራ ማህበራት ጥቅሞች እና መርሆዎች ፣ የኢትዮ ጥሪት አባላት መብት ና ግዴታዎች ፣ የብድር መስፈርቶች ፣ እና ከሌሎች መሰል ማህበራት የሚለይባቸውን እና መሰል ጉዳዮችን ይዟል።

በስልጠናው ላይም የማህበሩ የፋይናንስ ክፍል ኀላፊ የሆኑት አቶ አበበ ጋዲሳ  በበኩላቸው  የማህበሩ አባላቶች በዚህ ስልጠና በተገቢው መንገድ እየተሳተፉ ማህበሩንም ሆነ ራሳቸውን እንዲጠቅሙ ጥሪ አቅርበዋል ።

  በስልጠናው ከተሳተፉት አባላቶችም ይህ አይነቱ ስልጠና ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።  ሌላው በስልጠናው የተሳተፉት አባላቶች በበኩላቸው ከዚህ ስልጠና ብዙ ትምህርት እንዳገኙ እና በተግባር እንደሚያውሉ ተናግረዋል ።

   ስልጠናውም ከዚህ በፊት ከነበሩት ሳምንታት የበለጠ የተሳታፊ ብዛትም ሆነ ድምቀትም ታይቶበታል ።
👏1
Forwarded from Aboma Ejara
Waldaan Hojii Gamtaa Bu'uuraa Qusannoofi Liqii Itiyoo-Xirriit torbee torbeedhaan leenjii miseensota  isaatiif kennu marsaa 14ffaaf kenne
👏1