Ethiopian pilots (ambitious)👩‍✈️✈️
3.01K subscribers
539 photos
56 videos
7 files
89 links
We aimed to inspire young students and to provide latest information about aviation
Download Telegram
Happy new year
ET-BAA
A NEW ETHIOPIAN AIRLINES CARGO AIRCRAFT IS ARRIVING TO ADDIS ALL THE WAY FROM EVERETT, BOEING COMPANY ✈️

@ethiopianpilots
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
የኢትዮጵያ አይሮፕላን ምዝገባ ኮድ ከ ET-A ወደ ET-B ተሸጋገረ።

ኢትዮጵያ በሲቪል አቪዬሽን ከ80 ዓመት በላይ ታሪክ ያላት ሀገር ስትሆን በዓለም ዓቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) የአይሮፕላን ምዝገባ (Aircraft Registration) ኮድ መሠረት የሀገሩን መለያ የሚገልጹት ሁለት ፊደላት "ET" የሚለው ሆኖ ተመዝግቦላታል።

እነዚህ የመለያ ፊደላት ወይም ቁጥሮች ለሁሉም ሀገራት የተለያየ የሚሰጥ ሲሆን ለአብነትም የኬንያ "5Y" ፤ የኡጋንዳ "5Y" ፤ ቻይና "B"፤ ግብጽ "SU" ፤ ጀርመን "D" መጥቀስ ይቻላል።

ኢትዮጵያ የተሰጣት መለያ ፊደላት ከስያሜዋ ጋር ተመሳሳይነት ባለው መልኩ "ET" መደረጉ አጋጣሚ ብቻ ሳይሆን በወቅቱ የነበረን የዲፕሎመሲ አቅም፣ የቴክኖክራቶቻችን ብቃት እና ለአቪዬሽን የሰጠነው ቦታ ትልቅ በመሆኑ ጭምር የተገኘ ይሆናል ተብሎ ይታመናል።

በዚህ ምክንያት በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን በኩል የሚመዘገቡ ማናቸውም አይሮፕላኖች "ET" ን በማስቀደም፣ አንድ ጭረት (-) ካደረጉ በኋላ ባለ ሦስት አሐዝ ወይም ሆሄ ይጠቀማል።

በኢትዮጵያ የሲቪል አቪዬሽን ታሪክ አስካሁን ET-A ብሎ ጀምሮ ነበር ሁለቱ ፊደላት የሚቀጥሉት (ለምሳሌ፣ ET-ANY) ከዚህ በኋላ ግን ይህ የአይሮፕላን ምዝገባ ኮድ ወደ ET-B ተሸጋግሯል።

በ ET-B ፊደላት ዘር እና ብዜት ለመቀጠል፣ የመጀመርያው አይሮፕላን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው Boeing 777 ዕቃ ጫኝ አይሮፕላን ትናንት እኩለ-ሌሊት ላይ ከኤቨሬት ሲአትል ተነስቶ  በካፒቴን ዘላለም አንዳርጌ ዋና አብራሪነት እየተመራ የ16 ሰዓታት በረራ በማድረግ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ደርሷል።

ለኢትዮጵያ አየር መንገድ 10ኛውን የቦይንግ (Boeing 777-200LR) የጭነት አውሮፕላን ሲሆን አውሮፕላኑ ዘመናዊ ባለሁለት ሞተር ያለው መሆኑንና ከመቶ ቶን በላይ ጭነት የመሸከም አቅም እንዳለውም ተጠቅሷል።

አየር መንገዱ Echo Tango Alpha (ET-A) እየተባለ ለ75 ዓመታት የተጠራበትን ስያሜ ከዚህ ቀን ጀምሮ በመተው Echo Tango Bravo (ET-B) እያለ የሚጠራ ይሆናል ማለት ነው።

ይህ የአይሮፕላን ምዝገባ ኮድ፣ የግሉን አየር መንገዶችንም የሚጨምር ሲሆን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን በኢትዮጵያ ለሚመዘገቡ የግል አየር መንገዶች፣ አገልግሎቱ፣ የቁጥጥር (Regulatory) እና ፈቃድ ሰጪነት (Certifying)  ተግባር የሚያከናውን ይሆናል።

Credit : ኤሮቶፒያ የአቪዬሽን ሚዲያ፤ ዮናታን መንክር፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ

👋  @TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#HappeningNow

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰው ኃይል ሀብቱን ለማሳደግ፤ በራሱ ፍልስፍና እና ጠንካራ የስልጠና ሂደት ያሰለጠናቸውን 627 የአሺዬሽን ባለሙያዎችን እያስመረቀ ይገኛል።

ይህ በዚህ ዓመት በቅርቡ ካስመረቃቸው ከ1,500 የአሺዬሽን ባለሙያዎች ጋር ሲደመር፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ነው ተብሏል።

ዛሬ ተማሪዎቹን ያስመረቀውና በቅርቡ ከአካደሚ ወደ ዩኒቨርሲቲ ያደገው የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ አየር መንገዱ በ2035 ለወጠነው ዕቅድ ብቁ የሰው ኃይል ከማፍራት አንጻር ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል።

Credit : ኤሮቶፒያ የአቪዬሽን ሚዲያ፤ ዮናታን መንክር

👋  @TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from 🛫🛫The Pilot's🛬🛬 (🇳ate)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🛑BREAKING NEWS

A Japan Airlines passenger plane carrying 379 people appeared to have collided with a coast guard aircraft with six people on board. Footage shows the plane coming in to land before catching fire. The coast guard aircraft was being used to transport supplies after Japan suffered multiple devastating earthquakes. All passengers and crew from the commercial aircraft were evacuated, but five out of six coastguards were unaccounted for
@aviation_village
በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም ለምትገኙ የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ።
መልካም በዓል!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
Forwarded from Natnael Mekonnen
ዛሬ በመቐለ ምን አጋጠመ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ከተማ ተሳፋሪዎችን ጭኖ ከቀኑ 8:00 መቐለ አሉላ አባነጋ ኤርፖርት ሲደርስ ጎማው አከባቢ ባጋጠመው ችግር በፓይለቱ ድንቅ ብቃት ሰዎችን ሳይጎዱ ሊያርፍ ችሏል።
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥቆማ

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ፤ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ #በግል_ከፍለው የአዉሮፕላን አብራሪነት ስልጠና ለሚፈልጉ ጥሪ አቀረበ።

ዩኒቨርሲቲው ፤ ለአዉሮፕላን አብራሪነት ስልጠና ለአጭር ጊዜ የሚቆይ የ10% ቅናሽ ማድረጉንም አሳውቋል።

" በግል ከፍለው የአውሮፕላን አብራሪ ለመሆን ለሚማሩ ስልጠናውን ለመስጠት ተዘጋጅቻለሁ " ያለው የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩንቨርስቲ አመልካቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው ብሏል።

1ኛ. የትምህርት ደረጃ ፦ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት የወሰዱ፣ እንዲሁም ፦
* በሂሳብ፣
* በእንግሊዘኛ
* በፊዚክስ ዉጤት አመርቂ አፈጻጸም ያስመዘገቡ

2ኛ. ዕድሜ ፦ 18 እና ከዚያ በላይ

3ኛ. እንግሊዘኛ ፦ ደረጃ 4

4ኛ. ቁመት፦ 1ሜ 62 ሴ.ሜ እና ከዚያ በላይ

5ኛ. የጤና ሁኔታ፦ ደረጃ 1 የጤና ሰርተፊኬት

የስልጠናው ርዝማኔ 1 አመት ከ 3 ወር ነው ተብሏል።

" የተደረገው ቅናሽ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ነው " ያለው ዩኒቨርሲቲው ፤ " የምዝገባ ሂደቱን ለማወቅ እና ለበለጠ መረጃ በኢሜል አድራሻ ፦ etauinfo@ethiopianairlines.com / eaainfo@ethiopianairlines.com ያነጋግሩን " ብሏል።

ስልክ በመደወል መረጃ ለመቀበል የምትፈልጉም +251-115174600/8598 ነው ተብሏል።

ከዚህ ባለፈ የዩኒቨርሲቲውን ድረገፅ መመልከት ይቻላል ፦ ethiopianaviationuniversity.azurewebsites.net/admission/applyonline

@tikvahethiopia
Forwarded from Addis መረጃ
በተመሳሳይ ከፍታ ርቀት ላይ በመጓዝ ላይ የነበሩት የኳታር እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ስህተት ምክንያት ከመጋጨት ለጥቂት መትረፋቸዉ ተነግሯል።

ንብረትነቱ የኳታር አየር መንገድ የሆነዉ አዉሮፕላን ( ኳታር 6 ዩ) ከዶሃ ተነስቶ ወደ ኡጋንዳ ኢንቴቤ በ 38,000 ጫማ ከፍታ ላይ ሲበር የነበረ ቢሆንም በሞቃዲሾ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች አዉሮፕላኑ ወደ 40,000 ጫማ ወደላይ እንዲወጣ ተነግሮታል።

በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 6 : 32 ገደማ በተመሳሳይ በ39,000 ጫማ ከፍታ ርቀት ላይ ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ዱባይ ሲጓዝ ከነበረዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዉሮፕላን ( ኢቲ 602) ጋር የተፋጠጠዉ የኳታር አዉሮፕላን ከመጋጨት ለጥቂት መትረፉ ተዘግቧል።ሁለቱ ካፒቴኖች ስለ ክስተቱ ሲነጋገሩ የተቀረጹት ቅጂዎች ሁለቱም በሞቃዲሾ ከሚገኙ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች የተሳሳተ መመሪያ እንደተቀበሉ ያሳያል ተብሏል።

በሁለቱም አውሮፕላኖች ላይ የተገጠመው የግጭት ማስወገጃ ሲስተም (TCAS) ወዲያውኑ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፣ ይህም በታዘዘው ከፍታ ላይ ሌላ አውሮፕላን መኖሩን በማመልከቱ ምክንያት በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወት እንዲተርፍ ለማድረግ መቻሉ ዝግባዎች አመላክተዋል።ይህን ተከትሎ በሞቃዲሾ የሚገኙት የፀጥታ ኃይሎች በሶማሊያ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የሆኑትን ሙባረክ ኑር አሊን በቁጥጥር ስር እንዲዉል አደርገዋል።

Via Capital
@Addis_Mereja
Another brand new 737 MAX 8 is arriving tonight 👏(ET-BAI)
ዓመታዊው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል የመንግስት ሀላፊዎች፣ ዲፕሎማቶችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በደመቀ መልኩ ተከብሯል። የኢትዮጵያ አየር መንገድም ይህን ቀን አስመልክቶ ወደ እንግሊዝ ለንደን በሴቶች ብቻ የሚደረግ በረራ ያደርጋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ዓለምአቀፍየሴቶችቀን