Ethiopian Digital Library
64.5K subscribers
231 photos
10 videos
713 files
280 links
በዚህ ቻናል
👉ትምህርታዊ መፅሐፎችን
👉ሪሰርቾችንና ፕሮፖዛሎችን
👉የሶሻልና የናቹራል መጽሐፎችን
👉የዩኒቨርስቲ እና የቴክኒክና ሙያ ሞጁሎችን
👉የጥያቄና መልስ ወርክ ሽቶችን እና
👉ልዩ ልዩ መጽሐፎችን በነፃ ያገኛሉ!

For any comments: @ethiodlbot
Download Telegram
የ2016 ዓ.ም መውጫ ፈተና ከሰኔ 14 - 21/2016 ዓ.ም ይሰጣል

ትምህርት ሚኒስቴር ሚያዝያ 9/2016 ዓ.ም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ፤ የመውጫ ፈተና ከሰኔ 14 እስከ 21/2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡ #MOE

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
የ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና የመስጫ ጊዜ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና የመስጫ ጊዜ አልተቀየረም መጀመሪያ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ከ15 -17/08/2016 ዓ.ም ይሰጣል::

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
#Inbox

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ወደ ትምህርት ሚኒስቴር ከመጣ ጀምሮ ለዩኒቨርሲቲ መምህራን በተለያዩ ስብሰባዎች የተናገራቸው ወይም ቃል የገባቸው ግን ፈፅሞ ያልተገበራቸው፦

👉 1. ለዩኒቨርሲቲ መምህራን ክብራቸውና ደረጃቸውን የሚመጥን በቂ የደመወዝ ጭማሪ እንዲደረግ ጠንክረን እንሰራለን።

👉 2. ለሶስተኛ ድግሪ (ፒኤችዲ) ተማሪዎች በቂ የምርምር ገንዘብና ጥቅማ ጥቅም ጭማሪ ይደረጋል አይደለም ጭማሪ ሊያደርግ ጭራሽ GAT ፈተና ለመፈተን 1000 ብር መመዝገቢያ ብሎ የሚከፈለኝ ወርሃዊ ደመወዝ ወር እስከ ወር አላደረሰኝም ከሚል መምህር ገንዘብ መሰብሰብ ጀመረ።

👉 3. ከክልልና ከዞን ከተማ መስተዳድር አካላት ጋር ተነጋግረን ለዩኒቨርሲቲ መምህራን ቤት መስሪያ ቦታ እንዲሰጥ እናደርጋለን።

👉 4. ብዙ ዓመት በማስተርስ ያስተማረ መምህርና አዲስ ማስተርስ የያዘ መምህር በፍፁም ተመሳሳይ ደመወዝ መከፈል የለባቸውም፤Horizontal እና Vertical career structure ተግባራዊ እንዲሆን እናደርጋለን።

👉 5. ከአሁን በኋላ የዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ባለስልጣናት ሹመት በብሄርና በ recommendation ሳይሆን በእውቀት (merit-based) እንዲሆን እናደርጋለን።

👉 6. ከአሁን በኋላ ለመማር ማስተማር የሚያገለግሉ ግብአቶች  በበቂ ሁኔታ በዩኒቨርሲቲዎች እንዲሟሉ ይደረጋል።

➡️የማይተገብሩትን ቃል መግባት እዳ ብቻ ሳይሆን ታማኝነትንና አመኔታን ያሳጣል።

To: የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር

CC: ለፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

From: ሙሳ ሙሃባ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
በአንድ ገጠር መንደር የሚኖሩ ሰው የታላቅ ወንድሙን ልጆች በበአል ማግስት ወደቤቱ ጠርቶ ሊጋብዛቸው አሰበ። ነገር ግን ዘመዶቹ ሁሉ እንደ እነሱ ሀብታም ባለመሆኑ ይንቁታል ፤ ቤቱም አይሄዱም። ለግብዣ ቢጠራቸውም እቤቱ ድርሽ አይሉም ። ይህ ደሀ ሰው ግን የወንድሙን ልጆች ስለሚወዳቸው ወደ እሱ ሊያቀርባቸው ይፈልጋል ።

ከዛም ሰውየው የወንድሙን ልጆች ሰብስቦ «የወንድሜ ልጆች ሆይ ፡ በበአል ማግስት ለምሳ ግብዣ ቤቴ ኑ አደራ እንዳትቀሩ፤ ግብዣውን ከ1000 ሰወች በላይ ያዘጋጁታል »ሲል አንዱ ልጅ « ብዙ ሰው ነው የምትጠራው ?» ብሎ ጠየቀው ።  አጎትየውም « እናንተን ብቻ ነው የጠራውት » ሲላቸው ግብዣውን የሚሰሩት ከ1000 ሰወች በላይ ከሆኑ ምን አይነት ግብዣ ቢሆን ነው በማለት በጉጉት አድረው የግብዣው ሰዓት ሳይደርስ አጎታቸው ቤት ሄዱ ።

ልጆቹ አጎታቸው ቤት ቢሄዱም ምንም የተለየ ዝግጅት አላገኙም ነበር ።አጎታቸው እያጫወታቸው ቆይቶ ምሳ ሰዓት ሲደርስ« ምሳ ቀርቦ ሁሉም ገበታ ላይ ቀረቡ» ፤ ሁሉም መብላት ጀመሩ ። ልጆቹ የተለየ ግብዣ ገና ይመጣል ብለው ቢጠብቁም ፣ ምንም አይነት የተለየ ነገር ሳያዩ ምግቡን በልተው ሲያበቁ ግራ በመጋባት አጎታቸውን ጠየቁት ። «አጎቴ እኛ የጠበቅነው ግብዣ ትልቅ ነበር ። አሁን የበላነው ምግብም የተለመደ ምግብ በመሆኑ ይህን ምግብ 1000 ሰው ይሰሩታል ብለን መገመት አቅቶናል» አሉት ። አጎትየውም «አዎ ልክ ናችሁ ፤ አስተውሉት ፣ ይህንን ምግብ ከ 1000 ሰው በላይ ሰርተውታል» አላቸው ። «እንዴት?!» በማለት ሁሉም ሰው ሲጠይቁት።

«ልጆቼ ይህን ምግብ ለመስራት ዱቄት ያስፈልገዋል። በመጀመሪያ ይህን ዱቄት ለመስራትም ስንት ሰወች ያስፈልጉታል ። አስቀድሞ መሬቱ ይታረሳል ፣ይዘራል፣ ይታረማል፣ ይኮተኮታል ፤ እያለ ከብዙ ልፋትና ድካም በሗላ ይታጨዳል ። ከዛ በፊት ማጭዱንም ለመስራት ብረት ያስፈልጋል ፤ብረቱ የሚሰሩትን ሰራተኞችን ብዛት አስቡት፤ ከታጨደ በሗላ ይፈጫል ፤ለመፍጨት ደግሞ ወፍጮ ያስፈልጋል ወፍጮውን ለመስራት ብዙ ሰወች አሉ። »እያለ በደንብ አስረዳቸው።

ልጆቹ በአጎታቸው ሀሳብ ተገረሙ፤ አንደኛው ልጅም «አጎቴ በቃ ተወው፤ ይህንን ሁሉ እንቁጠር ከተባለ ቀኑም አይበቃንም »አለ ። ልጆቹም በአጎታቸው ጨዋታ አዋቂነት በጣም ተገረሙ ፤ደስ የሚል ጊዜም ከአጎታቸው ጋር አሳለፉ።

ልጆቹ አጎታቸውን በጣም በመውደዳቸው ትርፍ ጊዜያቸውን ከአጎታቸው ጋር ማሳለፍ ጀመሩ። አባታቸውም ዘመድ አዝማዱም በልጆቹ ምክንያት ከአጎት ቤት መመላለስ አበዙ፤ የቤተሰቡም ፍቅር ጨመረ ።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
500 ብር የመክፈል እና ደረሰኝ የማቅረብ ግዴታ

የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች የአገልግሎት 500 ብር የመክፈል እና ደረሰኝ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው - ትምህርት ሚኒስቴር


ትምህርት ሚኒስቴር ሚያዝያ 9/2016 ዓ.ም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ፤ የመውጫ ፈተና ከሰኔ 14 እስከ 21/2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡ #ExitExam #Exit_Exam

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
በ2016 ዓ.ም 8.8 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነዋል - ትምህርት ሚኒስቴር

በፀጥታ ችግር ምክንያት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች 8.8 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

በኢትዮጵያ በግጭት ምክንያት 8,977 ትምህርት ቤቶች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 6,483 ሙሉ በሙሉ ዝግ መሆናቸውን በሚኒስቴሩ 'ትምህርትን በአደጋ ማስቀጠል' ባለሙያ ንጋቱ አበበ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

ሚኒስቴሩ እና የክልል ትምህርት ቢሮዎች በጋራ በመሆን የመማር ማስተማር ሒደቱን ለማስቀጠል ጥረት ቢያደርጉም፤ አሁንም በተለያዩ ቦታዎች በቀጠሉት ግጭቶች ምክንያት ችግሩን ለመፍታት አስቸጋሪ እንደሆነ ባለሙያው ጠቁመዋል፡፡

የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ የመማር ማስተማር ሒደቱን ለማስቀጠል የሚጠበቅባቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ባለሙያው ጥሪ አቅርበዋል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
በዓለማችን ለመጀመሪያ ጊዜ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የተሰሩ ሞዴሎች የቁንጅና ዉድድር ሊካሄድ ነዉ

እስካሁን በተለመዱት የቁንጅና ዉድድሮች ሴቶች ባላቸዉ ቁንጅና ተወዳድረዉ የቁንጅና አክሊል ይሸለሙ ነበር፡፡ አሁን ግን ውድድሩ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ውጤት በሆኑ ሞዴሎች መካከል ነው ይለናል የዴይሊ ሜይል ዘገባ፡፡

"ሚስ ኤ.አይ" የተሰኘዉ የቁንጅና ውድድር በዓለም አቀፉ የኤ.አይ ፈጣሪዎች ሽልማት አዘጋጆች (The World AI Creator Awards) ተሰናድቷል፡፡ ዓላማውም በዓለም አቀፍ ደረጃ የኤ.አይ ፈጠራ ስራ ዉስጥ ለሚሳተፉ አካላት እውቅና ለመስጠት ብሎም ለማበረታታት ነው። ሰዉ መሳይ ሮቦት ሞዴሎችን በመስራት ላይ ያሉ አካላት ምርቶቻችዉን በማስመዝገብ በውድድሩ ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

ተወዳዳሪ ሞዴሎቹ የተለያዩ የውበት እና መሰል መለኪያዎችን ያካተተ አጠቃላይ ግምገማን እንዲያልፉ ይደረጋል። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያላቸዉ ተፅዕኖ ፈጣሪነትና እዉቅናም ከግምት ውስጥ የሚገባ ይሆናል።

ውድድሩ ኤሚሊ ፔሌግሪኒ እና አይታና ሎፔዝ በተባሉ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተሰሩ ሁለት ታዋቂ ሞዴሎችን ጨምሮ በአራት ባለሙያዎች ይዳኛል። የዉድድሩ አሸናፊዎች የሚጋሩት 20 ሺ ዶላር የገንዘብ ሽልማት ተዘጋጅቷል፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞችን ከቁንጅና መለኪያ ዘዉድ ጋር አሸናፊዋ ትቀዳጃለች፡፡

ምንጭ:- የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
ሚያዝያ 15 (April 23) ዓለም አቀፍ የመጽሐፍ ቀን

የዓለም መጽሐፍ ቀን በየዓመቱ ሚያዝያ 15 ይከበራል።

ሚያዝያ 15 ለዓለምአቀፍ የመጽሐፍ ቀንነት የተመረጠበት ምክንያት የዊልያም ሼክስፒር እና ስፔናዊው የታሪክ ጸሐፊ ኢንካ ጋርሲላሶ ዴ ላ ቬጋ የሞቱበት ቀን በመሆኑ እንደመታሰቢያ እንዲሆን ነው።

በእዚህ ቀን በዓለምአቀፍ ደረጃ በተለይ ወላጆች ለልጆቻቸው መጻሕፍትን በስጦታ መልክ በመስጠት ያከብሩታል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
የሪሚዲያል ፈተና

የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም ፈተና ከሰኔ 3 -14 በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል!

#Remedial

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሥር የሚገኙት ዘንዘልማ እና ሰባታሚት ካምፓሶች በፀጥታ ችግር ምክንያት መዘጋታቸውን ሪፖርተር ዩኒቨርሲቲውን በመጥቀስ ዘግቧል

በሁለቱ ካምፓሶች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ የግብርና፣ የጤና፣ የጂኦሎጂ እና የዲዛስተር ማኔጅመንት ተማሪዎች የፀጥታው ችግር እስኪቀረፍ ከተማ ውስጥ ባሉ ካምፓሶች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ማድረጉን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ብርሃኑ ገድፍ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በዘንዘልማ እና በሰባታሚት ካምፓሶች ውስጥ ይማሩ የነበሩ በርካታ ተማሪዎች ከተማ ውስጥ ያሉ ካምፓሶች ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው፡፡

ዘንዘልማ እና ሰባታሚት ካምፓሶች በሚገኙባቸው አካባቢዎች የተኩስ ድምፅ በየጊዜው እንደሚሰማ የገለፁት ም/ፕሬዝዳንቱ፤ በተማሪዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ከአንድ ወር በፊት ወደተለያዩ የተቋሙ ካምፓሶች እንዲዘዋወሩ መደረጉን ገልፀዋል፡፡

በከተማዋ የሚገኙ የዩኒቨርሲቲው ካምፓሶች ውስጥ በቂ ቦታ በመኖሩ ተማሪዎቹ ምንም ዓይነት መጉላላት ሳይደርስባቸው ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ነው ብለዋል፡፡

አሁን ላይ ከሁለቱ ካምፓሶች ውጪ በሌሎች ካምፓሶች ላይ ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር እንደሌለ ም/ፕሬዝዳንቱ ገልጸው፤ በባህር ዳር ከተማ ካለው አንፃራዊ ሰላም አኳያ በርካታ ተማሪዎች ምህርታቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡

ከሁለቱ ካምፓሶች ውጪ አለመረጋጋቱ የተሻሻለ ቢሆንም፤ አልፎ አልፎ የተኩስ ድምፅ እንደሚሰሙ ተማሪዎቹ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ የዘንድሮ ተመራቂዎች የምረቃ ቀን መቼ እንደሆነ እስካሁን እንዳልተነገራቸውም አክለዋል፡፡ #ሪፖርተር

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የኦሮሚያ ትምህርት ትራንስፎርሜሽን ታክስ ፎርስ ተቋቁሞ እየተሰራ ነው - ኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ

በክልሉ በርካታ ጎበዝ ተማሪዎችን ለማፍራት የተለያዩ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ተገንብተው እየተሰራ እንደሚገኝ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቶላ በሪሶ ገልፀዋል፡፡

ቢሮው የኦሮሚያ ልማት ማህበር ካስገነባው ልዩ አዳሪ ትምህርት ፣ በክልሉ መንግስት ከተገነቡ ቦረና ሆስቴል እና ዶዶላ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ልምድ በመቅሰም ተማሪዎችን ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ በመመልመል በልዩ ትምህርት ቤቶች አንዲማሩ እያደረገ እንደሚገኝም ነው ኃላፊው ያነሰቱ፡፡

ከዚህ በፊት የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው ከ600 በላይ ከፍተኛ ውጤት የሚያስመዘግቡ ተማሪዎች ቁጥር ውስን እንደነበር የገለፁት ዶ/ር ቶላ በክልሉ ከፍተኛ ውጤት የሚያስመዘግቡ ተማሪዎች ቁጥርን ለማሳደግ ልዩ አዳሪ እና ልዩ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት የመማር ማስተማር ስርዓቱ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡

በዚህም አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ገልጸው ለዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት እና ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን በማስፋፋት ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ የሚችሉ ተማሪዎችን በብዛት ለማፋራት ትኩረት ተሰጥቶችት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰኔ ወር ይሰጣል

12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰኔ ወር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወቃል።

የዩንቨርሲቲ መውጫ ፈተና ሰኔ መጀመሪያ ከተሰጠ በኋላ የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ይሰጣል።

በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ምዝገባ እንዳደረጉ መገለፁም ይታወሳል፡፡

ለሦስተኛ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተናው፤ ዘንድሮ ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ለማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ለእያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት አይነቶች እንዲሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑ አይዘነጋም፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ይሰጣል

የ2016 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፈተናው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ባይቻልም በክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ ነው ብለዋል።

በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን ይወስዳሉ ሲሉ አሳውቀዋል። ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ገልጸዋል። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ በበኩላቸው ፤ ፈተናው በኦንላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ ነው ብለዋል።

ተማሪዎች በሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ እንደሚደረግ ገልጸዋል። የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሰጣቸው አመልክተዋል። ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ይጀመራል ብለዋል። #MoE

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
እንኳን ለሆሣዕና ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ለጽዮን ልጅ እነሆ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያ ላይና በአህያይቱ ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል በሉአት ተብሎ በነቢይ የተነገረው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ።

ደቀ መዛሙርቱም ሄደው ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ አህያይቱንና ውርንጫዋንም አመጡለት ልብሳቸውንም በእነርሱ ላይ ጫኑ ተቀመጠባቸውም።

ከሕዝቡም እጅግ ብዙዎች ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ ሌሎችም ከዛፍ ጫፍ ጫፉን እየቈረጡ በመንገድ ላይ ያነጥፉ ነበር።

የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር። ማቴ. 21፥4-9

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
ልዩ የመምህራንና የትምህርት አመራር የአቅም ማጎልበቻ የክረምት ስልጠና

ትምህርት ሚኒስቴር በቀን14/08/2016 ዓ.ም በቁጥር፡- 10/242/897/2016 በተፃፈ ደብዳቤ በትምህርት ስርዓቱ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ መኆኑን በመግለጥ ከዚህም መካከል የመምህራንንና ትምህርት አመራሮችን አቅም ለመገንባት በክረምት ልዩ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና መርሃ ግብርን በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ለመጀመሪያ ዙር የሚሰጥ ይሆናል::

በመሆኑ በዚህም ዙር በእንግሊዝኛ፣ ሂሳብ፣ በፊዚክስ፣ በኬሚስትሪ እና ባዮሎጂ የትምህርት መስኮች በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመምህርነትና በትምህርት አመራርነት በመስራ ላይ ያሉት ስልጠና የሚሰጥ ይሆናል፡፡ #የአዲስ_አበባ_ከተማ_አስተዳደር_ትምህርት_ቢሮ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
ኢትዮጵያውያን ጉምቱ የሕክምና ባለሙያዎች ወደ ሩዋንዳ

“የሺህ ተራራዎች ምድር” ተብላ የምትጠራው ትንሽዬዋ የምሥራቅ አፍሪካ አገር ሩዋንዳ የሕዝብ ቁጥር ከ15 ሚሊዮን ባይልቅም በጤናው ዘርፍ ግንባር ቀደም ከሚባሉት ተርታ ተመድባለች።

ዶክተር የቆየሰው በለጠ ነዋሪነታቸውን በሩዋንዳ ካደረጉ አንድ ዓመት ተኩል ሆኗቸዋል። በክሊንተን ሄልዝ አክሰስ ኢኒሺየቲቭ የሄልዝ ሲስተምስ ዳይሬክተር ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ። “በርካታ የሕክምና ባለሙያዎች ወደ ቦትስዋና በሚፈልሱበት ወቅት እኔ ተማሪ ነበርኩ” የሚሉት የሕብረተሰብ ጤና (ፐብሊክ ሄልዝ) ባለሙያው አሁን ደግሞ ተራው የሩዋንዳ እንደሆነ ይመሰክራሉ።

እሳቸው እንደሚሉት መጀመሪያ አንድ ሰው ወደ አዲስ አገር በሕክምና ሙያ ካቀና በኋላ ዕድሉ እንዳለ ለሙያ አጋሮቹ ያሳውቃል፤ ይሄኔ ነው ሐኪሞች ወደ ውጭ መውጣት የሚጀምሩት። የፐብሊክ ሄልዝ ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር የቆየሰው፣ በኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ከማገልገላቸውም በላይ በሙያቸው ምክንያት ዛምቢያን መኖሪያቸው አድርገው ነበር።

የጤና ባለሙያው እንደሚሉት አብዛኞቹ ሩዋንዳ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሐኪሞች 'ሰብ-ስፔሻሊስቶች' ናቸው።

“ይህ ማለት ለምሳሌ አንድ ሐኪም በውስጥ ደዌ አሊያም በማህጸን ወይም በሕፃናት ሕክምና ስፔሻላይዝ ያደርጋል። ከዚያ በኋላ ለምሳሌ በውስጥ ደዌ ሕክምና የልብ ስፔሻሊስት ሊሆን ይችላል። እንግዲህ ምን ያክል ትልልቅ ባለሙያዎች እንደሆኑ ያሳየናል ማለት ነው።”

ዶክተር የቆየሰው እንደሚሉት ምንም እንኳ የሩዋንዳው ትልቁ ኪንግ ፋይሳል ሆስፒታል ዋነኛው የኢትዮጵያውያን ሐኪሞች ቀጣሪ ቢሆንም ሌሎች 'ተሪሻሪ ሆስፒታሎች' ውስጥ ኢትዮጵያውያን ሐኪሞች ተቀጥረው ይሠራሉ። አክለው ኢትዮጵያውያን ሆስፒታሉን ከማስተዳደር ጀምሮ አንዳንዶቹ በስፔሻሊስት ሌሎቹ ደግሞ በሰብ-ስፔሻሊስት ደረጃ በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

ዶክተር ዘሪሁን አበበ የኪንግ ፋይሳል ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሲሆኑ፣ ዶክተር ሃና አበራ ደግሞ የጋስትሮኢንትሮሎጂ ክፍል ኃላፊ ናቸው።ዶክተር የቆየለት እንደሚሉት ቢያንስ ከ20 አስከ 30 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ዶክተሮች ሩዋንዳ ውስጥ ያገለግላሉ። የነርሶች እና የአንስቴዢያ ባለሙያዎች ቁጥር ግን እምብዛም አይደለም። ለሁለት እና ሦስት ወራት ወደ ሩዋንዳ መጥተው፤ በሙያቸው ሠርተው፤ ልምዳቸውን አካፍለው የሚሄዱ ባለሙያዎችም አሉ።

ፐብሊክ ሄልዝን ጨምሮ በሌሎች መስኮች በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ ከ10 እስከ 15 የሚሆኑ ስፔሻሊስቶችም እንዳሉ ዶክተሩ ይናገራሉ። “ኢትዮጵያ በቁጥርም በዓይነትም በጣም ብዙ የሕክምና ባለሙያዎችን ስላሰጠነች እነዚህ ባለሙያዎች መጥተው እየሠሩም እያሠለጡንም ነው ያሉት። እኛ የፐብሊክ ሄልዝ ባሙያዎች ደግሞ ስትራቴጂ የማውጣት እና የማማከር ሥራ እንሠራለን።”

“አንደኛው ኢትዮጵያውያን የሕክምና ባለሙያዎች ወደ ሩዋንዳ እየመጡ ያሉበት ምክንያት አገሪቱ ያወጣችው ስትራቴጂ የሥራ ዕድል መፍጠሩ ነው። ሩዋንዳ ያወጣችውን መስፈርት የሚያሟሉ በርካታ ባለሙያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ።” ነገር ግን ይላሉ ለበርካታ ዓመታት በፐበሊክ ሄልዝ ሙያ ያገለገሉት ዶክተር የቆየሰው፤ “ነገር ግን መሠረታዊው ምክንያት ግን ሌላ ነው።”

እሳቸው እንደሚሉት “ኢትዮጵያ ለሕክምና ባለሙያዎች እጅግ ዝቅተኛ ገንዘብ ከሚከፍሉ የዓለማችን አገራት መካከል ናት። ያለው ሁኔታ ብዙዎች ከአገራቸው ወጥተው ያለውን ዕድል እንዲሞክሩ የሚያደርግ ነው።” #BBC

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
በጎርፍ አደጋ የ4 ሰዎች ሕይወት አልፏል

በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ ንጋት ላይ በጣለው ዝናብ ሳቢያ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ወረገኑ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የ4 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
የ2016 ፈተና መረጃ ለ6ኛ ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች

6ኛ ክፍል (ለአዲስ አበባ)
በፈተና የሚካተቱ የት/ት አይነቶች:-
👉አማርኛ, እንግሊዘኛ, ሒሳብ, አካ/ሳይንስ እና ሞራል ሲሆኑ ለአፋን ኦሮሞ ተማሪዎች አፋን ኦሮሞ እና ገዳ ይጨምራል
✍️ሁሉም ፈተና የሚዘጋጀው ከ6ኛ ክፍል ብቻ(5ኛ ክፍልን አይጨምርም)

8ኛ ክፍል (ለአዲስ አበባ)
በፈተና የሚካተቱ የት/ት አይነቶች:-
👉አማርኛ, እንግሊዘኛ, ሒሳብ, ሶሻል ሳይንስ, አጠ/ሳይንስ, የዜግነት ት/ት እና ለአፋን ኦሮሞ ተማሪዎች አፋን ኦሮሞ እና ገዳ ይጨምራል
✍️ሁሉም ፈተና የሚዘጋጀው ከ8ኛ ክፍል ብቻ(7ኛ ክፍልን አይጨምርም)

12ኛ ክፍል
👉በ2016 ዓ.ም ለፈተና የሚሰጡ የትምህርት አይነቶችን  በሁለቱም ዘርፎች ስድስት፡ ስድስት የትምህርት አይነቶች ናቸው:: እነሱም :-

ሀ/የተፈጥሮ ሣይንስ
👉እንግሊዝኛ, ሒሳብ, ባዮሎጅ, ፊዚክስ, ኬሚስትሪ, ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴሰት

ለ/የማህበራዊ ሣይንስ
👉እንግሊዝኛ, ሒሳብ, ታሪክ, ኢኮኖሚክስ, ጅኦግራፊ, ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴሰት

የፈተና ዝግጅት:-
👉የኢኮኖሚክስ ፈተና ከ12ኛ ክፍል ብቻ
👉ሌሎች የትምህርት አይነቶች ከ9ኛ -11ኛ በአሮጌው ስርአተ ትምህርት እና 12ኛ ክፍል በአዲሱ ስርአተ ትምህርት ያጠቃልላል::
👉ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት በነበረው አሠራር መሠረት ይቀጥላል::

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ይሰጣል

👉የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።

👉የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሐምሌ 3 እስከ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ሐምሌ 9 እስከ 11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።

👉በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 30-ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ሐምሌ 6-7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት #Entrance2016

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
🇺🇸 ዲቪ 2025 ቪዛ ሎተሪ ውጤት ከሁለት ቀን በሗላ ይለቀቃል

2025 Entrant Status Check

👉DV-2025 Entrants may enter their confirmation information through the link below starting at noon (EDT) on May 4, 2024.

👉DV-2025 Entrants should keep their confirmation number until at least September 30, 2025.

Link: https://dvprogram.state.gov/

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library