Ethiopian Digital Library
70.7K subscribers
982 photos
65 videos
755 files
595 links
በዚህ ቻናል ስለ
👉ትምህርት፣
👉ሥራ እና
👉ማህበራዊ ጉዳይ
መረጃ ያገኛሉ!

Contact: @ethiodlbot
Download Telegram
የ12ኛ ክፍል ሀጋር አቀፍ ፈተና በበይነ መረብ ለሚፈተኑ ተፈታኞች ቴክኒካል ድጋፍ ቡድን ተቋቁሞ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል፡፡

ተፈታኞች በበይነ መረብ ፈተና የሚያጋጥማቸውን ማንኛውንም ድጋፍ መጀመሪያ ላይ በትምህርት ቤታቸው ቀጥሎም በመፈተኛ ማዕከላት ካሉ የትምህርት አመራርና ቴክኒክ ድጋፍ ሰጪዎች ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡

ሆኖም ተጨማሪ ድጋፍ ሲያስፈልግ በሚከተለው ምስል ላይ በፌዴራል ደረጃ በየክልሉ ተከፋፍሎ ከተደራጀው የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ ቡድን ጋር በመገናኘት ድጋፍ ማግኘት የሚችሉ ማሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የፈተና ስርቆትንና ኩረጃን በጋራ እንከላከል!!

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
የቀድሞው የዚምባቡዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ እንዲህ ብለው ነበር

የአፍሪካ የትምህርት ስርዓት አስገራሚ ውጤቶች አሉት።

☄️ አንደኛ ደረጃ የሚይዙ ቀለሜና ጎበዝ ተማሪዎች ጥሩ ውጤት አምጥተው ህክምና እና ምህንድስና እንዲማሩ እድል ያገኛሉ።

☄️ ሁለተኛ ደረጃ የሚይዙት ደግሞ ህግ እና ማኔጅመንት ተምረው አንደኛ ደረጃዎቹን ያስተዳድሯቸዋል።

☄️ ዝቅ ብለው በሦስተኛ ደረጃ የሚገኙት ተማሪዎች ፖለቲካ ውስጥ ይገቡና አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ላይ ያሉትን ከላይ ሆነው ይቆጣጠራሉ።

☄️ በትምህርት ያልተሳካላቸውስ? ፖሊስና ወታደር ይሆናሉ። እነዚህ ፖለቲከኞችን ይቆጣጠራሉ፤ ደስ ያላላቸውን ፖለቲከኛ እስከ መግደል ይደርሳሉ፡፡

☄️ጭራሽ ክፍል ውስጥም ሆነ ትምህርት ቤት ገብተው የማያውቁት ደግሞ ነብይና ጠንቋይ ይሆናሉ። እነዚህን ደግሞ ሁሉም ይከተሏቸዋል!

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ፈጥነን እንድርስለት ለጋዜጠኛ ቴድሮስ ካሳሁን

እባካችሁ አግዙኝ ይላል በእዚህ ዮቱብ ላይ በለቀቀው በእራሱ ንግግር https://youtu.be/yOWKLq7DBos?si=pmL28PqlGgIHK2jI

Tewodros Kasahun Tekle ቴዎድሮስ ካሳሁን ተክሌ የመዝናኛ ፕሮግራም አቅራቢ ነው። በኢቢኤስ ቴሌቭዥን እና በፋና ቴሌቭዥን
የፋና ላምሮት የድምፃዊያን ውድድርን በራሱ ቀለም እና ፈጠራ በብቃት በመምራት ይታወቃል። የፋና ላምሮት የመጀመሪያው የመድረክ አስተዋዋቂ ነበር።
#ፋና_ላምሮትን ከምዕራፍ 1 እስከ ምዕራፍ 4 የመጀመሪያውን የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድርን በብቃት አቅርቦ ነበር።

ቴዲ በአሁኑ ሰዓት ሁለት ልጆቹን በኪራይ ቤት ጥሎ ፀበል ቦታ ነው የሚገኘው። የገንዘብ እጥረትም አጋጥሞታል። እባካችሁ እርዱኝ አግዙኝ እያለ ነው። ደጋግ ኢትዮጵያውያን ቴዲን ለመርዳት

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር ፦
1000298227707
ቴዎድሮስ ካሳሁን ተክሌ

የቻላችሁትን መርዳት ትችላላችሁ።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
"ማህበራዊ ሚዲያ የልጆቻችንን የማሰብ ችሎታ እያቀጨጨ በመሆኑ የእጅ ስልክ ክልከላ ለማድረግ እየተወያየን ነው" - ፕ/ር ብርሃኑ

በትምህርት ላይ ያሉ ልጆቻችን ከዘመኑ እኩል እንዲራመዱ በማለት የምንሰጣቸው የእጅ ስልክና እና የሚጠቀሟቸው ማህበራዊ ሚዲያዎች የማሰብ ችሎታቸው እንዳይዳብር እያደረጉ ነው ሲሉ የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ገልጸዋል፡፡ የተማሪዎች የእጅ ስልክ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፤ የማያነብ እና የማሰብ ችሎታው የተገታ ዜጋ እንድናፈራ የሚያደርግ መሰናክል መሆኑን ልብ ልንል ይገባል ብለዋል፡፡

“ተማሪ ከትምህርት ተቋማት እውነትን ሊሻ ይገባል!” ያሉት ሚኒስትሩ፤ የማሰብ ችሎታው የዳበረና ምክንያታዊ የሆነ ትውልድን ማብቃት ማህበራዊ ኃላፊነት መሆኑን በኢቢሲ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ መሰናዶ ላይ ገልጸዋል። በመሰናዶው የዘርፉ ምሁራን እና የሚመለከታቸው አካላትን ያሳተፈው መድረኩ ‘የትምህርት ጥራትን እንዴት እናስጠበቅ?’፤ ‘ከገባንበት ስብራትስ በምን መልኩ እንጠገናለን?’ የሚል ሃሳብ ተነስቷል።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የተማሪዎችን የትምህርት አቀባበል ሊረብሽ የሚችል በመሆኑ የእጅ ስልክ ክልከላ እስከማድረግ የደረሰ ቁጥጥር እንደሚደረግ በውይይቱ ላይ ጠቁመዋል፡፡ በሌላ በኩል ከትምህርት ሥርዓቱ ጋር በተያያዘ የመምህርነት ሙያን እንደቀደመው ጊዜ የሚከበር ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትሩ አመላክተዋል፡፡

"ይህን በማድረግ ሂደት ውስጥ ግን የመምህራንን መሰረታዊ ችግር መፍታት እንዳለብን አልዘነጋንም፤ እርሱ ላይ እየሰራን ነው" ሲሉም አክለዋል፡፡ በሌላ በኩል ትርፍን ብቻ ፈልገው ወደ ዘርፉ የሚገቡ የግል የትምህርት ተቋማት መስፋፋት ለዘርፉ ማሽቆልቆል የራሳቸውን አስተዋጽኦ አድርገዋል ነው ያሉት፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ኃያል የሚባሉ ሀገራት በዋናነት ትርፍ ላይ ያተኮሩ የግል የትምህርት ተቋማት እንደሌላቸውም አያይዘው አንስተዋል፡፡ በትምህርቱ ዘርፍ ከገባንበት ማጥ ለመውጣት የምናደርገው ማስተካከያ ውጤት በቅርብ ዓመታት ውስጥ ይመጣል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ ትውልድ ተኮር ለውጥ በመሆኑ በርካታ ዓመታትን እንደሚወስድ አስረድተዋል፡፡

ትምህርት ለግለሰቡ ከሚሰጠው ጥቅም ይልቅ ለማህበረሰቡ ያለው አስተዋፅኦ አያሌ በመሆኑ ሁሉም ሰው ለዘርፉ እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ ሊያበረክት ይገባል ብለዋል፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
ትምህርት ቤት ሞባይል ስልክ
Anonymous Poll
62%
ይከልከል
38%
አይይከልከል
የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል መልስ መስጫ ወረቀት (Answer Sheet)

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
ቀበሌ ጉቦ በግድ የተቀበለህን ግለሰብ በዕለቱ በሐይማኖት የአምልኮ ቦታ ፈጣሪን እየተማፀነ ብታገኙት ምን ይሰማችሗል?

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
መምህራንን እናመስግን

በትምህርት ዘመናቹ ምርጥ 3 መምህራኖቻችሁን ጥቀሱ!

የትምህርት ቤቱን ስም እና የሚያስተምሩትን ሰብጀክት/ኮርስ/ ጨምሩበት!

በሁሉም ደረጃ ያላችሁ መምህራን እንወዳችሗለን!

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
ኢትዮጵያዊቷ ቆንጆ ከአለም 2ተኛ ከአፍሪካ 1ኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቀቀች፡፡

በህንድ እየተከናወነ ያለው ሚስ ወርልድ የቁንጅና ውድድር አሁን ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡ በዚህ ውድድር የ109 አገራት ቆነጃጅት የተሳተፉ ሲሆን ‹‹ሚስ ወርልድ›› የሚል መጠሪያ በማግኘት የዘንድሮውን ዘውድ የጫነችው ታይላንዳዊቷ ኦፓል ሱቻታ ሆናለች፡፡

እሷን ተከትላ ኢትዮጵያን የወከለችውና በውድድሩ ላይ ‹‹ሚስ ኢትዮጵያ›› ተብላ ስትጠራ የነበረችው ሀሴት ደረጄ 2ተኛ ሆናለች፡፡ ሀሴት ከአለም 2ተኛ ትሁን እንጂ ከአፍሪካ 1ኛ በመሆን ከአህጉሪቱ ቆነጃጅት ሁሉ ቀዳሚ በመሆን አሸናፊ መሆኗን የውድድሩ አዘጋጆች አስታውቀዋል፡፡

ከአለም 3ተኛ የወጣችው የፖላንድ ተወዳዳሪዋ ስትሆን የማርቲንኪ ተወዳዳሪዋ 4ተኛ ሆናለች፡፡ ይህ ውድድር ለአንድ ወር በህንድ የተለያዩ ግዛቶች ሲከናወን ቆይቷል፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ ፖሊስ እና አሽከርካሪ ሲደባደቡ ሳሊተ ምህረት አካባቢ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
Exit Exam Schedule Sene, 2017

Sene 2, 2017: Management

Sene 3, 2017: Accounting

Sene 4, 2017: Marketing Management and Nursing (Comprehensive)

Sene 5, 2017:
Procurement and Asset Management
Psychology
Public Administration and Development Management
Public Health
Public relation and community studies/public relation
Software Engineering

and so on

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ወይ ጉድ ! 🤹🤹🤹

በትላንትናው ዕለት ከድምፃዊ ልጅ ሚካኤል ኮንሰርት በኋላ ከሚሊኒየም አዳራሽ ውጭ አንድ ወጣት የፌዴራል ልብስ ከለበሰ ሰው ጋር ሲፋለም ታይቷል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የጥንቃቄ መልክት

የሊንክዲን አካውንት እንከራያለን እያሉ እያጭበረበሩ ስለሆነ ተጠንቀቁ!

በዚህ ቻናል ማስታወቂያ የሰራንለት ግለሰብ ( @Linkedn_Rental_serveice ) አጭበርባሪ ሆኖ ተገኝቷል በዚህም ጉዳት የደረሰባቹ ቤተሰቦቻችን ይቅታ እንጠይቃለን!

ለወደፊቱ የተሟላ መረጃ ለማያቀርብ ግለሰብ በዚህ ቻናል ማስታወቂያ እንደማንሰራ እንገልጻለን::

እናንተም ማህበራዊ ሚዲያ ላይ አንዳንድ ስራዎችን ስትሰሩ የራሳችሁን ጥንቃቄ ማድረጋችሁን አትርሱ!

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
አስተያዬት ስጡበት?

የሀገራችን ፌዴሬሽን አወቃቀር በዚህ ካርታ ላይ እንደሚታዬው ሆኖ እንዲዋቀር ለምክክር ኮሚሽኑ በአጀንዳነት ቀርቧል::

የትኛው ስቴት ላይ ናቹ ገምቱ እስኪ?

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
በመውጫ ፈተና ውጤት ሳቢያ 90 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተዘጉ

የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተናን አስመልክቶ ባወጣው መመርያ መሠረት፣ ዘጠና ያህል የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከሚያስፈትኗቸው ተማሪዎች 75 በመቶ ያህሉን ማሳለፍ ባለመቻላቸው መዘጋታቸው ተነገረ፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ደኤታ አቶ ኮራ ቱሹኔ ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ባዘጋጀው የአፍሪካ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዓለም አቀፍ ጉባዔ ላይ እንደተናገሩት፣ ዘጠና ያህል የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተዘግተዋል፡፡

መንግሥት ከዚህ በፊት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ከሚያስፈትኗቸው ተመራቂዎች ውስጥ 75 በመቶና ከዚያ በላይ ባላሳለፉት ላይ ዕርምጃ እንደሚወስድ ከገለጸ በኋላ የተወሰደ ዕርምጃን በተመለከተ  ተጠይቀው፤ ‹‹ይህ መመርያ ከተላለፈ በኋላ ራሳቸው ላይ ዕርምጃ የወሰዱ ተቋማት አሉ፡፡ በተለይ ከግሎቹ 90 ያህል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተዘግተዋል፡፡ አብዛኞቹ መመርያውን ካዩ በኋላ ራሳቸውም እየዘጉ ናቸው፤›› በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

የቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ወንደሰን ታምራት (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ መንግሥት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ በሚል በወሰዳቸው ዕርምጃዎች ምክንያት የመንግሥትና የግል ዩኒቨርሲቲዎች መጎዳታቸውን ተናግረዋል፡፡

https://ethiopianreporter.com/141880/
ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ የተማረ ሰው ዲግሪው ተቀባይነት የሚኖረው ዲግሪውን ለመጀመር ከመመዝገቡ በፊት የሙያ ብቃት ምዘና ተፈትኖ ያለፈ ብቻ ሲሆን ነው ከዚህ ውጭ ዲግሪውን ጀምሮ ወይም ከጨረሰ በኋላ የሙያ ምዘና(COC) ቢኖረውም ዲግሪው ተቀባይነት የለውም::

@Ethiopian_Digital_Library