Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
89.6K subscribers
3.53K photos
132 videos
2 files
398 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ዛምቢያ በረራ ማድረግ የጀመረበትን 25ኛ ዓመት በሉሳካ በደማቅ ሁኔታ አከበረ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የንግድ ዘርፍ ዋና ኃላፊ አቶ ለማ ያዴቻ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ዛምቢያ የሚያደርጋቸው በረራዎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን በማሳለጥ ረገድ ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙ አስምረውበታል።
አየር መንገዳችን አሁን ላይ ወደ ሉሳካ 11 እንዲሁም ወደንዶላ በሳምንት 5 ጊዜ በመብረር ላይ ሲገኝ፤ በቅርቡም ወደ ንዶላ የሚደረገውን በረራ ወደ 7 ከፍ በማድረግ ወደ ዛምቢያ የሚደረጉትን አጠቃላይ ሳምንታዊ በረራዎች 18 የሚያደርስ ይሆናል።
ብቃት ባላቸው ባለሞያዎቻችን ታግዘን ካሰቡበት ቦታ ልናደርስዎ ተዘጋጅተናል፣ ይምጡ አብረውን ይጓዙ።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት የጀመረበትን 78ኛ ዓመት መጋቢት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. በልዩ ድምቀት አከበረ። በዝግጅቱም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ እና የንግድ ዘርፍ ዋና ኃላፊው አየር መንገዱ ከ78 ዓመት በፊት የመጀመሪያ በረራውን ወዳደረገባት የካይሮ በረራ ላይ የተገኙ ሲሆን ለመንገደኞች አገልግሎት በማቅረብ ደንበኛን በትህትና በማገለገል የአመራር ተምሳሌት መሆን እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በዕለቱም ብሔራዊ አየር መንገዱ በጾም ላይ ላሉ ክቡራን መንገደኞቹ መልካም የጥሞና ግዜን ለመመኘት ያዘጋጀውን ስጦታ በተርሚናሉ ውስጥ አበርክቷል።
“የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰባት አሥርት ዓመታት በላይ በነበረው ጉዞው ስኬታማ ሆኖ እንዲቀጥል ያስቻለው የማይለዋወጥ ወጥ አቋም በመያዝ በትጋት በመሥራቱ ሲሆን ይህን እድገትን ለማስቀጠል የደንበኞች አገልግሎት ላይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ ነው።”

አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ
ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች
እንኳን ለ1445ኛው የዒድ ዓልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ዒድ ሙባረክ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመሪያውን ዓለም-አቀፍ በረራ ያደረገው ከ78 ዓመታት በፊት መጋቢት 30 ቀን 1938 ዓ.ም ወደ ግብፅ ካይሮ ነበር። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለያዩ ጊዜያት የገጠሙትን ፈተናዎች በስኬት በማለፍ ዛሬ ላይ በአፍሪካ እጅግ ግዙፍ፣ ትርፋማ እና የበርካታ ዓለም-አቀፍ የአቪዬሽን ሽልማቶች ባለቤት ለመሆን በቅቷል። አየር መንገዳችን በዓለም ተወዳዳሪ ከሚባሉ ቀዳሚ አየር መንገዶች ተርታ መሰለፉ የስኬት ተምሳሌት እንዲሆን አስችሎታል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #78ስኬታማአመታት #ትውስታ
በረራዎ ምቾት የተሞላበት እንዲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዳዲስና ከተፈጥሮ ጋር ተስማሚ የሆኑ የበረራ ላይ የግል መገልገያዎችን በማራኪ የቀለም አማራጮች ማቅረቡን ሲያበስር በደስታ ነው!
የዕለት ከዕለት ትጋታችን ጉዞዎ ምቾት ያልተለየው መሆኑን ማረጋገጥ ነው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #አገልግሎት
78 ስኬታማ ዓመታትን እያከበረ የሚገኘው የአቪዬሽን ኢንዳስትሪው ፈር ቀዳጅ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለበረራ ደህንነት፣ ለደንበኞች ምቹ እና ዘመኑን የሚመጥን አገልግሎት ለመስጠት ያለውን ቁርጠኝነት እና የዘወትር ትጋት አጠናክሮ ይቀጥላል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #78ስኬታማዓመታት
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዲጂታል አማራጮቹ በተጨማሪ ደንበኞቹ ባሉበት ሁሉ አዳዲስ የቲኬት ሽያጭ ቢሮዎችን በመክፈት ላይ ይገኛል። አሁንም በሲ.ኤም.ሲ አካባቢ ፀሀይ ሪል እስቴት ፊት ለፊት በሚገኘው አዲስ-አፍሪካ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽንና ኤግዚቢሽን ማዕከል የመጀመሪያ ወለል ላይ አዲስ የቲኬት ሽያጭ ቢሮ መክፈቱን ሲያበስር በታላቅ ደስታ ነው። ቀልጣፋ የትኬት ሽያጭ አገልግሎታችንን አቅራቢያዎ በሚገኙ ዘመናዊ የሽያጭ ቢሮዎቻችን ማግኘት ይችላሉ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምንጊዜም ለመንገደኞቹ ምቹ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ይተጋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ