Ethio iselamic gerup
486 subscribers
89 photos
9 videos
2 files
365 links
ethio iselamic geru
ኢስላማዊ ሀዲሶችን ትኩስ ትኩሱን ያገኛሉ አላማችን ኡማውን ማገልገል ነው ለጓደኛዎ ሼር ያድር አንዲትም ቃል ብትሆን ከኔ የሰማቹትን ለሌሎች አስተላልፋ ብለዋል ረሱል ሰ ዐ ወ 👇👇👇👇👇
ለአስተያየት( @dinuhamzabot
ሼር(@ethioiselamdawa)👈🤙
Download Telegram
የደረሰብህን መከራ መቀየር ከፈለግክ ቅድሚያ ያለህበትን ወንጀል ቀይር"
ኢብኑል ጀውዚይ(ረ.ዐ)
____
"ምናልባት እኮ አንተ በተኛህበት ካገዝከው ደሀ:ተርቦ ካበላኸው:አዝኖ ካስደሰትከው:ፈገግ ካልክለት መንገደኛ:ወይ ችግሩን ካቃለልክለት ችግረኛ ብዙ ፀሎቶች!የሰማይን በር እያንኳኩልህ ይሆናል"
ኢብኑል ቀዪም(ረ.ዐ)
_
"አደራችሁን ውሀ በማጠጣት ላይ በርቱ:አላህ እኮ ውሻን ውሃ ያጠጣ ሰው ወንጀል እንኳን ምሯል!እና ሙእሚንን ያጠጣ ሰው እንዴት አይምረው!
ኢማም አል ሻፊዒይ(ረ.ዐ)
____
የትኛዋ ስራ ጀነት እንደምታስገባህ አታውቅምና:ምንም ትንሽ ቢመስልህም እንኳን መልካምን ስራ ተግብር!
★★★
አንድ ፈተና ከአሏህ ዘንዳ የመጣ ቅጣት ይሁን፣አልያ ለወንጀል ማበሻ፣ወይም ደሞ ደረጃንና ምንዳን ከፍ ማድረጊያ መሆኑን እንዴት ነው ማውቀው???"በማለት አንድ ሰው ለኢማም ጁነይድ አል በግዳዲይ(ረ.ዐ) ጠየቃቸው!!!!
አማሙም እንዲህ በማለት መለሱለት👇
☞በመጣብህ ቅጣት ከተበሳጨህ ከአሏህ ዘንዳ የመጣ ቁጣ ነው
☞ትእግስት ካደረግክ ለወንጀልህ ማበሻ ነው
☞በአሏህ ውሳኔ ከተደሰትክ ደግሞ ደረጃህን ከፍ ማድረጊያ ነው።

ethio iselamic geru
ኢስላማዊ ሀዲሶችን ትኩስ ትኩሱን ያገኛሉ አላማችን ኡማውን ማገልገል ነው ለጓደኛዎ ሼር ያድር አንዲትም ቃል ብትሆን ከኔ የሰማቹትን ለሌሎች አስተላልፋ ብለዋል ረሱል ሰ ዐ ወ 👇👇👇👇👇
ለአስተያየት( @Mahmmedinhabot)
ሼር(@ethioiselamdawa)👈🤙
#የወፏ__ምክር

አንድ ሰው አንዲት በጣም ቆንጆ ወፍ በመዳፉ ውስጥ ይዞ ጨምቆ ሊገድላት ሲል
ከመሞቷ በፊት አንድ ወይም ሁለት ቃላት ትናገር ዘንድ እንዲፈቅድላት ጠየቀችው፡፡
እንዲህም አለች “እባክህ አትግደለኝ፡፡ ሶስት ጠቃሚ ምክሮችን እሰጥሃለሁ፡፡
የመጀመሪያው ምክር፤ በእጅህ ያለውን ነገር አትልቀቅ፡፡ ሁለተኛው ምክር፤ ስለሆነው ነገር
ሁሉ አትቆጭ፡፡” ካለችው በኋላ ዝም አለች፡፡
ሶስተኛውንም ምክር ትነግረው ዘንድ ሲጠይቃት “ሶስተኛው ምክር ለልጆችህና ለልጅ
ልጆችህ በጣም ጠቃሚ ስለሆነ ካለቀከኝ አልነግርህም፡፡” አለችው፡፡
በዚህ ጊዜ ሰውየው ሶስተኛውን ምክር ለመስማት በጣም ጓጉቶ ስለነበረ ወፏን ሲለቃት
ከአንድ ዛፍ ላይ በርራ ወጥታ “ምንድን ነበር ያልኩህ? ታስታውሳለህ?” ብላ ጠየቀችው፡፡
እርሱም “በእጅህ ያለውን ነገር አትልቀቅ ነው ያልሺኝ፡፡” አላት፡፡
“ሁለተኛውስ?”
“ስላለፈው ነገር ሁሉ አትቆጭ፡፡”
“አዎ፡፡ ነገር ግን የነገርኩህን ነገር አልተቀበልክም፡፡ ባትለቀኝ ኖሮ ከሆዴ ውስጥ ለልጅ
ልጆችህ የሚሆን ወርቅ ታገኝ ነበር፡፡ ይኸው ነው፡፡” አለችው፡፡
ሰውየው “ሶስተኛውስ ታዲያ?” አላት፡፡
እሷም “ሶስተኛው የሁለተኛው ምክር ድጋሚ ነው፡፡ ስላጣኸው ነገር አትቆጭ፡፡ ይኸው
ነው፡፡ ደህና ሁን፡፡ ምክሬንም ባለመቀበልህ በድህነት ትኖራለህ፡፡” አለችው፡
ethio iselamic geru
ኢስላማዊ ሀዲሶችን ትኩስ ትኩሱን ያገኛሉ አላማችን ኡማውን ማገልገል ነው ለጓደኛዎ ሼር ያድር አንዲትም ቃል ብትሆን ከኔ የሰማቹትን ለሌሎች አስተላልፋ ብለዋል ረሱል ሰ ዐ ወ 👇👇👇👇👇
ለአስተያየት( @Mahmmedinhabot)
ሼር(@ethioiselamdawa)👈🤙
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ ይህ ነገር ሁሉንም ሙስሊም ይመለከታል ወንድሜ እህቴ ይሄን ፎቶ ቢያንስ ለ2 ቀን ፕሮፋይል በማድረግ ለነቢያችን (ሰ ዐ ወ ) ያለንን ፍቅር እናሳይ ወላሂ ነቢዩ (ሰ ዐ ወ ) ለኛ ብለው ያለ እረፍት አልቅሰዋል ተደብድበዋል ተንገላተዋል ተሰቃይተዋል ብዙ አመት ያለ እንቅልፍ ለኛ አዝነው አንግተዋል ታዲያ ይሄን ሁሉ ነገር ለኛ ያረጉልንን ነቢይ እንዲ ሲሰደቡ ሰምተን ወንድም እህቶቼ ቢያንስ በዚ ፕሮፋይል እንቃወም ይሄን ማረግ ካቃተን ግን ወላሂ ነብሴ በእጁ በሆነችው በአላህ ስም እምላለው ለነቢዩ ምንም ፍቅር እንደሌለን እና የእሳቸውን ውለታ ረስተናል ማለት ነው

ለቻልነው ሰው ሁሉ ይሄን መልዕክት share እናርግ




ፊዳከ አቢ ወዐኡሚ ያ አሽረፈል ኸልቂላህ ያሙሂበል ረብ ያረሱለሏህ 😍😍❤️❤️❤️
Channel photo updated
የናፍቆት ደብዳቤ.....

የጦይባው አባቴ ፡እምነግርውህ አለኝ።
አንዲት የሐበሻ ወዳጅዎ `` የኔ ነቢ ምን ትመክሩኛላችሁ`` ስትላችሁ ••ስሜ ሲጠራ ተንሰፍሰፊ •• እንዳሏት ሰማሁ...
ውዴ ይሄ ከላምችሁ የብዙውን እንቅልፍ ነስቷልኮ!....ናፋቂዎ ፊዳ ይሁንሎትና ስለእርስዎ ደግሜ ላዋያችሁማ
የውስጥ ዐለሜን ነቀርሳ በእናንተው ገሽላጭ ንፋስ አገኘሁትና መዳሃኒቱን ክጀዬ ለናንተው አማከርኳችሁ....ወዳጆችዎን ከጎኔ ሰብስቤ።

ሶሃባችሁ ያለውን ሰምቼባችኋለው...ግን ለምን አባኮ? እንዴት ለኔ ለከንቱው ብለው ያንን ሙሸረፍ አካልዎ ያጎሳቁላሉ? የኔ ዐለም ሶሃባው የነገረኝኮ ••የዛህራ አባት የሚበሉት የገብስ ዳቦ ደረቅ ከመሆኑ የተነሳ ጉሮሯቸው ጋር ሲደርስ በውሃ...•• አልጨርሰውም አባኮ! እንዴት ለኔ ብለው ድፍን መዲና እማይበላውን የገብስ አይነት ከጓዳዎ ያስገባሉ? እጅዎ ምስራቅ እና ምዕራቡን ደባብሶ ካሳደገ በኋላ ደረቅ ገብስ ሲያነሱበት ጸሃይ ተጋረደችልዎት....ያንን የአሏህ ቃላት ሚስጥር የሚያንቆረቁር ውብ ከንፈርዎን ጣፋጭ ሲያርቁበት ጨረቃ ተገመሰችልዎት....እውነቱን እያወቃችሁት የምነግራችሁ ደግሞ ከጸሃይቷም ይሁን ከጨረቃ ስብራት የናፋቂዎ፡ ሐበሻ በቀይ ባህር ተጋርደው ወዲያ ማዶ ያሉት ልጆችዎ የልብ ሥብራት እንደሚብስ ነው........ድረሱልን የኔ ዐለም ካልሆነማ ሰላም የለም።

ከጣፋጩ በበላን ቁጥር የትዝታችሁ መጋዝ ደርሶ ላይ ውስጣችንን ከሚገዘግዘን ለአንዴም ቢሆን ከዚያ ለምለም ቁባ ሥር በመላኢካ ሰሪር አረፍ ብላችሁ ለእርሶ ተብሎ ከተተከለው የአዘል ዘይቱን ስትቀምሱ፡ እስከ ሰርመድ ከሚፈላላችሁ ወይን ስትጎነጩ እንያችሁ.....ወለው እንኳ በመናሜ!

💚💜ሰላም ይድረሶት ሆዴ
⤵️⤵️⤵️
@aymu_hubi💚
@aymu_hubi
Aýmú-hùbì
#Share woduchi😍
#Like for more eishqe
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ተናገሩ"አንድ ሰው በሞተ ጊዜ ዘመዶቹ በቀብር
ሥነስርአቱ ላይ ሲጨናነቁ አንድ እጅግ ያማረ ቆንጆ ሰው
በጭንቅላቱ በኩል ይቆማል።ጀናዛውም እንደተከፈነ ያ ሰው
በከፈኑ እና በሞተው ሰው ደረት መሀል ይሆናል።ከቀብር
ሥነስርአቱም በህዋላ ቀባሪ ቤተሰቦቹ ወደ ቤት ሲመለሱ ሁለት
ሙንከር እና ነኪር የተባሉ ምላኢኮች ወደ ቀብሩ በመምጣት
ጀናዛውንና ያንን ቆንጆ ሰው በመለያየት ያንን የሞተውን ሰው
በእምነቱ ጉዳይ ብቻውን በጥያቄ ሊያፋጡት ይሞክራሉ ። ሆኖም
ያ ቆንጆ ሰው ይናገራል "ይህ ሰው አጋሬም ጋደኛዬም ነው
ብቻውንም ልተወው አልችልም። እናንተ እንድትጠይቁት
ከተመደባቹ ስራችሁን መሥራት ትችላላቹ እኔ ግን ወደ ጀነት
መግባቱን ሳላረጋግጥ ትቼው እልሄድም"። ከዝያም ወደ ሞተው
አጋሩ በመዞር እንዲህ ይለዋል "እኔ አንዳንዴ ድምፅህን ከፍ
አርገህ ሌላ ጊዜ ደግሞ ቀስ ብለህ ስታነበኝ የነበርኩት ቁርአን
ነኝ ምንም አትጨነቅ፤ ከሙንከርና ነኪር ጥያቄና መልስ በኃላ
ምንም ጭንቀት አይኖርብህም"፤ጥያቄና መልሱም ካለቀ በኃላ ያ
ቆንጆ ሰው አል ማሉል አላ በተባሉ የጀነት መላኢኮች የተዘጋጀ
በመልካም ሽታ የሚያውድ እና ከ ሀር በተሰራ ልብስ የተዘጋጀ
አልጋ ያዘጋጅለታል።
2. ረሰል(ሶ.ዐ.ወ) እንደተናገሩት በቂያማ ቀን በአላህ ሱ.ወ ፊት
ስንቆም ከቁርአን የበለጠ ለኛ ሚከራከርልን አይኖርም
ከነብይያትም ከ መላኢኮችም በበለጠ።
3. እባክዎን ይህን መልእክት የቻሉትን ያህል ያስተላልፉ። ረሱል
(ሶ.ዐ.ወ) እውቀትን ከኔ ለሌላው አስተላልፉ አንድም አረፍተ ነገር
ብትሆን እንኩዋን ብለዋል።
4. ይህ መልእክት በ አላህ ፍቃድ በቀጣይ 7 ቀናት ቢያንስ 5
ሚልዬን ሰዎች እንዲዳረስ ዱአ እያደረግን ነው።
እባክዎን ይህን መልእክት ለ ቤተሰብዎ፣ ለዘመድዎትና
ላሚያውቅዋቸው ሁሉ በማስተላለፍ ከተትረፈረፈው የአላህ ምንዳ
ተጠቃሚ ይሁኑ።

ethio iselamic geru
ኢስላማዊ ሀዲሶችን ትኩስ ትኩሱን ያገኛሉ አላማችን ኡማውን ማገልገል ነው ለጓደኛዎ ሼር ያድር አንዲትም ቃል ብትሆን ከኔ የሰማቹትን ለሌሎች አስተላልፋ ብለዋል ረሱል ሰ ዐ ወ 👇👇👇👇👇
ለአስተያየት( @Mahmmedinhabot)
ሼር(@ethioiselamdawa)👈🤙
#አንድ_አፍታ

〽️ምክር ከጥበበኛው ሉቅማን ለልጁ

#share #share #share #share
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
〽️ #ልጄ_ሆይ ፧ በዝምታየ ተፀፅቼ አላውቅም ፡፡
•••••••••••••••
〽️ #ልጄ_ሆይ ፧ ከጠጣህበት የውሃ ጉድጓድ ውስጥ ድንጋይ አታስገባ፡፡
•••••••••••••••
〽️ #ልጄ_ሆይ ፧ ምላስክን ‘አላህ ሆይ ‘ ማለትን አለማምድ ለአላህ ጠያቂን የማይመልስበት ሰዓታት• አሉትና፡፡
••••••••••••••
〽️ #ልጄ_ሆይ፧ ከሌላ ሰው እጅ ካለ በሬ በእጅህ ያለች ወፍ ትበልጣለች ፡፡
••••••••••••••
〽️ #ልጄ_ሆይ ፧ ከመገረም ጋር አትሳቅ; ከማይመለከትህም ነገር አትጠይቅ፡፡
••••••••••••••
〽️ #ልጄ_ሆይ ፧ ሁለት ነገሮችን አታውሳ ፧ ሰዎች ወዳንተ ያደረጉትን በደልና ፣ ለሰዎች ያደረከውን መልካም ነገር፡፡
••••••••••••••
〽️ #ልጄ_ሆይ ፧ በጣም ጣፋጭ አትሁን ከንቀት እንዳትበላ መራራ አትሁን እንዳትተፋ ፡፡
•••••••••••••••
〽️ #ልጄ_ሆይ ፧ ከጥጋብ ላይ ጥጋብ ሆነህ አትመገብ ; ከምትመገበው ለውሻ ብጥለው የተሻለ ነው ፡፡
••••••••••••••••
〽️ #ልጄ_ሆይ ፧ የአላህን ፈራቻ ንግድ አድርገህ ያዘው ; ትንሽ የማይባል ትርፋማ ሆኖ ይመጣልሀል፡፡
join as

ethio iselamic geru
ኢስላማዊ ሀዲሶችን ትኩስ ትኩሱን ያገኛሉ አላማችን ኡማውን ማገልገል ነው ለጓደኛዎ ሼር ያድር አንዲትም ቃል ብትሆን ከኔ የሰማቹትን ለሌሎች አስተላልፋ ብለዋል ረሱል ሰ ዐ ወ 👇👇👇👇👇
ለአስተያየት( @Mahmmedinhabot)
ሼር(@ethioiselamdawa)👈🤙
አቡ ዓብደላህ ግመልህ
እንዴት ሆነች?

ከወጣት ሶሐቦች ውስጥ አንዱ ነው። ሳይሰልም በፊት ከአንዲት ኮረዳ ጋር ለየት ያለ ቅርርብ ነበረው።☺️ ኢስላምን ከተቀበለ በኋላ አንድ ቀን በመዲና ጎዳና ላይ ልጂቱ ጋር ተገጣጠሙ።😳 አይኑን ሳይሰብር ፍጥጥ ብሎ፣ አንገቱን ጠምዝዞ እያየ መንገድ ስቶ ከግድግዳ ጋር ተጋጭቶ ደምም ፈሰሰው። 😜

በዚሁ ሁኔታ ረሱላችን ጋር መጣሁ ይላል የዛሬው ኮከባችን ኸዋት ቢን ጁበይር (ረዐ)። ደሜን ሲያዩም "ምን ሆነህ ነው?" ብለው ጠየቁኝ። እኔም ስለሆነው ነገር ሁሉንም ነገርኳቸው ይላል። እርሳቸውም "እንዳይደግምህ። አላህ ለአንድ ባሪያው መልካምን ሲሻለት ቅጣቱን በዱንያ ያፈጥንለታል።" አሉት። (የጅህን ነው ያገኘኸው አሉት😀) አይ ! ረሱል

ኸዋታችን አንድ ከበድ ያለ ገጠመኙን እንደሚከተለው ይነግረናል:- ነብያችን (ሰዐወ) ጋር መረ-ዞህራን (ለመካ ቅርብ ስፍራ ነው) የተሰኘ ስፍራ ላይ አረፍን። ካረፍኩበት ድንኳኔ ወጣ ስል ሴቶች ሰብሰብ ብለው ይጫወታሉ። በጣም ተመሰጥኩ። ተመልሼ ዘነጥ የሚያደርገኝን ልብስ ለብሼ ተቀላቀልኳቸው።🤔 (ከነርሱ ጋር እየተጫወትኩ፣ ስሳሳቅ) ነብያችን (ስዐወ) ከማረፊያቸው ድንገት ወጡ።😳

ሲመለከቱኝም "አባ ዓብደላህ ከነርሱ ጋር ምን ትሰራለህ ?" አሉኝ። በድንጋጤ ብርክ ያዘኝ። ምላሴ ተያያዘ። ድብልቅልቅ ያለ መልስ ሰጠኋቸው። ይላል። "አንድ እየደነበረ የሚሮጥ አስቸጋሪ ግመል አለኝ። ለርሱ ማሰሪያ ገመድ ፈልጌ ነው።" አልኳቸው። 😂😂

እንድነሳ ካደረጉኝ በኋላ ለመፀዳዳት ሲሄዱ ተከተልኳቸው ይላል። ውዱእ አድርገው ከፂማቸው ውሃ እየወረደ መጡና። " አባ ዓብላላህ ግመልህ እንዴት ሆነ?" አሉኝ። ከዚያም ወደ መዲና ጉዟቸውን ቀጠሉ። ነብያችን ከዚያ በኋላ መንገድ ላይ ሲያገኙት ስለ ግመሉ በተደጋጋሚ ይጠይቁታል😀

መዲና ከደረሱ በኋላ ግን ኸዋት በጣም ስላፈረ ከመስጂድ ቀረ። እርሳቸው (ሰዐወ)፣ መስጂዱና ወንድሞቹ ሲናፍቁት አንድ ቀን ለናፍቆት ጭር ባለበት ሰዓት መስጂድ ገብቶ በተመስጦ ይሰግድ ጀመር። ነብያችንም(ሰዐወ) ከቤት ወደ መስጂድ ገቡና ቀለል ያሉ ረከዓዎችን ሰገዱ። ኸዋት መግባታቸውን ሲያውቅ እስኪወጡለት ድረስ ሰላቱን የባሰ አስረዘመው።😜

ሐቢባችን (ሰዐወ) ነቄ፣ ምርጥ ሙረቢና አስደናቂ ፍጡር አይደሉ😚 " ኸዋት እንደፈለግክ አስረዝም፣ እኔ እንደሆንኩ ሳትጨርስ ከዚህ አልሄድም" አሉት።😀😀
አስቡት ሶላት ውስጥ ምን ሊያስብ እንደሚችል 🤦‍♂️
ራሱ ይነግረናል " በቃ እውነቱን ተናግሬ ልገላገል ብዬ ወሰንኩ" ይላል። ቶሎ አሰላመተና ቀረባቸው። "አሰላሙ ዓለይኩም አባ ዓብደላህ ግመልህ እንዴት ሆነ?" አሉት። እርሱም " በእውነት በላኮት አምላክ እምላለሁ ከዚያ ቀን ጀምሮ ግመሉ አልፈረጠጠም" አላቸው። 😂 " አላህ ይዘንልህ" ብለውት ፋይል ዘጉ።

ነብያችን (ሰዐወ) ኸዋት እንዲህ ያለ ግመል እንደሌለው ያውቃሉ። ሴቶች ጋር የተቀመጠውም ቅፅበታዊ በሆነ ሰዋዊ ድክመት ምክንያት እንደሆነ ተረድተውታል። 🐪 የለህም ዋሽተኸኛልም አላሉትም። ነገርግን በተደጋጋሚዋ ጥያቄያቸው ውስጥ "እውነቱን አውቄያለሁ ተናግራት" እያሉት ነበር። ጉዳዩንም በርሱና በርሳቸው መሃል ብቻ አስቀሩት። ህዝብ ፊት አላሰጡትም።

አማኝም ይሁን አስተባባይ፣ ታዛዥም ይሁን ስህተት ላይ የሚወድቅ ጥፋተኛ፣ አዋቂም ይሁን ጃሂል፣ ሃብታምም ይሁን ድሃ፣ መሪም ይሁን ተመሪ ብንሆን ዞረን ዞረን ሰዎች ነን። በውስጣችን የብዙ ስሜቶች ፍቅር አብሮን ተፈጥሯል። ገንዘብ፣ ተቃራኒ ፆታ ወዘተ። ክደን ሳይሆን በሰዋዊ ስህተት ገብተን እናምፃለን። ወንጀል ከነድንበሩ ወንጀል ነው። በልሳናችን፣ ተግባራችንና ህልውናችን ልንርቅና ልንጠየፈው ግድ ይላል።

እና ምን ለማለት ነው

ያንተ ሚና ሰዎችን ከፈጣሪያቸው ጋር በማስተዋወቅ፣ ጥቅምና ጉዳት በጉልህ ይታዩ ዘንድ የብርሃን ጨረር በመሰለጥ ላይ ብቻ የተገታ ነው። የሰዎችን ነውር ሸፍን እንጂ አታዋርድ። ከቻልክ እዘንላቸው ካልቻልክ ግን አላህ ወደርሱ ተጣሪው እንጂ ፍጡራኑን አላፈናፍን ባይ ተቆጣጣሪ አድርጎ ስላልሾመህ ቦታህንና አቅምህን እወቅ። ኃይማኖተኝነት (አማኝነት) ከሕይወት ራስን ማግለል ሳይሆን በውስጧ ሆኖ አላህ ወደሚፈልገው አቅጣጫ መንጎድ ነው።
አብዱሮህማን ስይድ (ሜጢ)
🍃 #ሱረቱ አል-ፋቲሀ..........የአላህን ቁጣ ትከላከላለች::

🍃 #ሱረቱ ያሲን .........ከቂያማ ቀን ጥማት ትከላከላለች: :

🍃 #ሱረቱ አል-ዱኻን..........ከቂያማ ቀን ጭንቀት ትከላከላለች::

🍃 #ሱረቱ አል-ሙልክ..........ከቀብር ቅጣት ትከላከላለች::

🍃 #ሱረቱ አል-ካፊሩን..........በሞት ሰአት ከኩፍር ትከላከላለች::

🍃 #ሱረቱ አል ኢኽላስ..........ከኒፋቅነት
ትከላከላለች::

🍃 #ሱረቱ አል-ፈለቅ..........ከምቀኝነት
ትከላከላለች::

በቅንነት ቻናላችንን ሼር አድርጉልን👇👇
ethio iselamic geru
ኢስላማዊ ሀዲሶችን ትኩስ ትኩሱን ያገኛሉ አላማችን ኡማውን ማገልገል ነው ለጓደኛዎ ሼር ያድር አንዲትም ቃል ብትሆን ከኔ የሰማቹትን ለሌሎች አስተላልፋ ብለዋል ረሱል ሰ ዐ ወ 👇👇👇👇👇
ለአስተያየት( @Mahmmedinhabot)
ሼር(@ethioiselamdawa)👈🤙
እኔ ረመዳን ከመድረሱ በፊት ይቅርታ
ለመጠየቅ 1ኛ መሆን እፈልጋለሁ
"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""'""'"
•ምናልባት የሆነ ቀን ላይ ከራሴ ጋር ወይም ከሰዉ ጋር ሁኜ ሆን ብዬ ወይም ሳላስበዉ ብዙ ነገር አርጌ ይሆናል እናም፦

-ይቅርታ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ያስቀየምኩአችሁ
-ይቅርታ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ያማሁአችሁ
-ይቅርታ በኔ ምክኒያት ትንሽም ብቶን ያናደድኩአችሁ

በእርግጥ አላህ በሀሜት የተዘፈቀን ሰዉ የሚምረዉ የታማዉ አካል በይቅርታ ሲያልፈዉ እንደሆነ አዉቂያለሁ እና ይቅርታ (Awfu) ሳትሉኝ እንዳታለፉኝ
=እኔ ለአላህ ብዬ ይቅር (Awfu) ብይለዉ ።
*እንዲሁም መላኢካዎች በረመዳን ወር የተኮራረፉ ሰዎች ያሉበት ቤት ሲቀር ሁሉም ቤት ይገባሉ እስቲ ለማስታወስ ያክል እናንተስ ከማን ጋር ተቀያይማቹሀል (ተኮራርፈዋል) ?
ከአባት
ከእናት
ከወንደም
ከእህት
ከዘመድ
ከጎሮቤት
ከጓዋደኛ…… ከአሁኑ ለአላህ ብላቹህ ይቅር (Awfu) ተባባሉ
ይቅርታ ጥሪ ነዉና ነፍሳችንን ንፁህ እናድርገዉ ።
* አሁን ያለንበትም ሁኔታ አሳዛኝ ነዉ ድንገተኛ ሞት እጅግ በዝቷል አላህ መጨረሻችንን ያሳምርልን 🤲
@ በአካል የምታቁኝ በስምም ብቻ ይሁን የምታቁኝ ሁላችሁም ይሄን ፅሁፍ ያነበባችሁ በሙሉ ለፈጣሪ (ለአላህ) ብላችሁ ይቅር (Awfu) እንድትሉኝ እጠይቃችሁአለሁ
ይቅርታ
ይቅርታ
ይቅርታ
☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን✔️
JOIN 👇

@Adnan567mh

🌐💚💛❤️
#ረመዳን_11

አቡ ሁረይራ(ረ.ዐ) ባስተላለፉት ሐዲስ ላይ ነብያችን(ﷺ) እንዲህ ብለዋል:-

"ብዙ ጿሚዎች አሉ፤ ከጾማቸው የሚያተርፉት መራብና መጠማትን ብቻ ነው።"

የጾማችን ምንዳ እንዳይቀንስ ለቀልድም ቢሆን አላስፈላጊ
ንግግሮችን (ባህሪያቶችን) ማሳየት አይኖርብንም።

#ሚንበር_ቲቪ
#ሁለንተናዊ_ከፍታ!
የዓይን ምስክር ነኝ

© ኡስታዝ በድር ሁሴን

በ1997 የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የቅንጅት ፖርቲ ከፍተኛ አመራሮች ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ አቶ ልደቱ አያሌውና ሌላ ስማቸውን የማላስታውሳቸው የፖርቲው አመራር በሰሜን ሆቴል በጠሩት ስብሰባ ላይ ተገኝቻለሁ። በስብሰባው የተሳተፋት ሰዎች ቁጥራቸው ከአስር የማይበልጡ ተፅእኖ ፈጣሪ ተብለው የታሰቡ ሰዎች ናቸው።
የስብሰባው ዓላማ ስለ ቅንጅት ማንነት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ውስጥ የተሰራጨውን "ፕሮፖጋንዳ" ማረምና ማስተካከል እንደሆነ ተነገረን። ስለ ፖርቲው ገለፃ ከተደረገልን በኋላ ሙስሊሙ ድምፁን ለቅንጅት እንዲሰጥ ጥሪ ተላለፈልን።

ከታሳታፊዎች ጥያቄዎች መቅረብ ጀመሩ። ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል የመስጅድ ቦታ ጉዳይና የትምህርት ቤቶች ሂጃብ ክልከላ ይገኙባቸዋል። በርካታ መስጅዶች ህዝበ-ሙስሊሙ ከፍተኛ መስዋእትነት እየከፈለ ያቆማቸው ናቸው። ሙስሊም ሴት ተማሪዎችም በሂጃብ ሳቢያ ከፍተኛ እንግልት እየደረሰባቸው ነው። እነኝህን ችግሮች ለመፍታት የምትከተሉት ፖሊሲ ምንድን ነው? በዚህ ጉዳይ ላይ የፖርቲው አቋም ምንድን ነው? የሚሉ ጥያቄዎች ተነሱ።

አቶ ልደቱ አያሌው መልስ ሲሰጡ ሙስሊሙ ለዘመናት የቆዩ ችግሮቹን ሌላ አካል እንዲፈታለት ከመጠየቅ ይልቅ ራሱ በፖለቲካው ውስጥ መሳተፍ እንዳለበት ጠቅሰው "ኑ join አድርጉንና አብረን ለለውጥ እንስራ" የሚል ምላሽ ሰጡን።
ዶ/ር ብርሃኑ በወቅቱ የሰጡት ምላሽ ከ17 ዓመታት በኋላ ጆሮዬ ላይ ያቃጭላል፤ እንዲህ ነበር ያሉን:-

" እኔ የእስልምናም ሆነ የሙስሊም ጥላቻ የለኝም። አያቴ ሙስሊም ናቸው። ነገር ግን ሂጃብን በሚመለከት የለኝ አቋም የፈረንሳይ መንግሥት አቋም ነው። ይህንን በማለቴ የናንተን ድምፅ የማጣ ከሆነ ልጣው።"

ፈረንሳይ በሂጃብና በአጠቃላይ ኢስላማዊ መለያዎች ላይ የነበራትን/ያላትን አቋም ለሚያቅ ሰው ቁርጥ ያለ ምላሽ ነበር። ዶ/ሩ ሙስሊም ጠል አለመሆናቸውን ሊያስረዱ ጠርተውን ጠልነታቸውን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ አቋማቸውን አረዱን። የፖርቲው ወይም የሁሉም የፖርቲው አመራሮች እንደነበር ግልፅ ማስረጃ የለኝም። የዶ/ሩ አቋም ግን የት ድረስ ሊሄድ እንደሚችል ግልፅ አድርጎልናል።

ወደ ወቅታዊው ጉዳይ ስመለስ:-

ክቡር የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ያኔ ያንን አቋምዎን ስሰማ ያልኩትን ልንገርዎ፦ "እኒህ ሰው ጎበዝ ኢኮኖሚስት እንጅ ጥሩ ፖለቲከኛ መሆን አይችሉም" ነበር ያለኩት።

እርግጠኛ ነኝ እርስዎ ያስተምሩበት የነበረውና የፕሮፌሰርነት ማእረግ የሰጠዎ የአሜሪካ ዩንቨርስቲ ለተማሪዎቹ መስገጃ ቦታ እንዳዘጋጀ፣ አለያም ለተማሪዎቹ የትምህርት ሂደቱን በማያሰናክል መልኩ እምነታቸውን practice እንዲያደርጉ ሙሉ ነፃነት እንደሰጠ ያውቃሉ።

ሸሪዓን መሰረት ያደረጉ የፋይናንስ ተቋማትን በሚመለከ ባለፈው ምርጫ ቅስቀሳ ላይ ያንፀባረቁት አቋምና ስልጣን ቢይዙ እነኝህን ባንኮች የመገደብ ሃሳብ እንዳለዎ መግለፅዎ አሳዛኝ ሆኖ አልፏል። ምናልባት የብሄራዊ ባንክ ገዥ የመሆን እድል ቢያጋጥምዎ ይህንኑ አቋምዎን ሊጭኑ ነውን? በትምህርት ሚኒስትርንዎ እንዲህ ካንገላቱን ሃገር የማስተዳደር እድል ቢያገኙስ ምን ያደርጉን ይሆን?!
እናም እባክዎን በህዝብ ተመርጠው ሳይሆን ለፖለቲካ አካታችነት ሲባል የተሰጥዎን ስልጣን በ1997 የነገሩንን አቋምዎን ማራመጃ አያድርጉት። ከቻሉ የግል ፍላጎትዎንና ዝንባሌዎን ወደጎን ብለው ሰላትና ሂጃብ ሙስሊሞች የማይደራደሩባቸው የእምነታቸው ክፍል ስለሆኑ በአግባቡ የሚስተናገዱበት የህግ ማእቀፍ እንዲዘጋጅ ያድርጉ። ካልቻሉ ግን ሃገራችን ካለችበት ፈታኝ ሁኔታ በላይ ሌላ መከራ መሸከም አትችልምና ስልጣንዎን በመልቀቅ ለሃገርዎ ውለታ ይዋሉላት።
ሶሀቢዩ እኛን ቢመለከት ምን ይል ነበር?!

📌 T.me/ahmedin99

የአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) አንዴ ከጂሃድ እየተመለሱ በምሽት መንገድ ላይ ማረፍ ፈልገው አንድ ሸለቆዋማ አካባቢ ላይ ሰፈሩ። መላው ሰራዊት እንዲተኛና እንዲያርፍ ፈልገውም:—

" እኛ ልንተኛ ነው ማነው የሸለቆውን መግቢያ በመጠበቅ ከድንገተኛ የጠላቶቻችን ወረራ ሊጠብቀን ፈቃደኛ የሚሆነው ?"ሲሉ ጠየቁ።

በዚህን ጊዜ ሁለት ሶሀባዎች ይህን ከባድ ኃላፊነት ለመወጣት ተስማምተው ስራ ጀመሩ ከዛም አንዱ ለሌላኛው "እኔ የሌሊቱን ግማሽ ልጠብቅ፣ አንተ ደግሞ ግማሹን ትጠብቃለህ ተራ በተራ እንተኛ"ተባባሉ።

በዚህም መሰረት አንደኛው ተኛ ሌላኛው እየጠበቀ ለይል ሰላት መስገድ ጀመረ። እየሰገደ ሳለ ቀን ላይ በተደረገው ጂሃድ ባለቤቱ የቆሰለችና ድንገት ከጉዞ ሲመለስ በዚህ ቆስላ ያገኛት ባሏ" ከነሱ መሀል አንድን ሰው ሳላቆስልና ደምም ሳላፈስ አልመለስም" ብሎ ዝቶ ከቤቱ የወጣው አይሁዲ ከነቢዩና ባልደረቦቻቸው ማረፊያ መግቢያ ላይ ሲደርስ እየሰገደና ጌታውን እያናገረ (ቁርኣን እየቀራ) የአላህን ባሮችን የሚጠብቀውን ሶሃቢይ ከቅርብ ርቀት ተመለከተው....በያዘው ቀስትም ወርውሮ ወጋው ሶሀቢዩም ቀስ አድርጎ አውጥቶት ሰላቱን
ቀጠለ፣ለሁለተኛ ጊዜም ደግሞ ወረወረ አሁንም ወጋው እንደመጀመሪያው ቀስ አድርጎ አውጥቶ ጥሎት ሰላቱ ላይ ቀጠለ! በቀስት ሰውነቱን ቀጥታ እየተወጋ የማይወድቀውና የማይጮኸው ግለሰብ ሁኔታም እየገረመው ለሶስተኛ ጊዜ ወርውሮ ወጋው፣ ይህንም ቀስ አድርጎ አውጥቶ ጥሎት ሩኩዕ ከዛም ሱጁድ አድርጎ ከአጠገቡ የተኛውን አብሮት የሚጠብቀውን ሶሀቢይ ቀሰቀሰው እንቅስቃሴያቸውን ሲመለከትም አይሁዲው ቦታውን ጥሎ ጠፋ....

ሌላኛው ሶሀቢይ ልክ ሲባንን ዙሪያው በደም ተሞልቶ ሲመለከት ምን እንደገጠመው ጠየቀው የሆነውን በነገረው ጊዜም "ታድያ ምነው ልክ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደወጋህ አልቀሰቀስከኝም"? ሲልም ጠየቀው ይህ ልቡ በጌታው ቃል በቁርዓን ፍቅር የተሞላና ጥፍጥናውም ሁሉን ነገር ያስረሳው ውድ ሶሀቢይም "አንዲትን ሱራ ጀምሬ ነበር ሳልጨርሳት ማቆም አልፈለግኩም፣ ነቢዩ እርሳቸውንና ምዕምናንን የመጠበቁን ኃላፊነት ጥለውብኝ ባይሆን ኖሮ ነፍሴ እስካልወጣች ድረስ የሆነው ቢሆን ቁርዓኔን መቅራት አላቋርጥም ነበር" ብሎ መለሰለት!!!

ይህ ሶሀቢይ እኛን ቢመለከት ምን ይል ነበር?!
ethio iselamic geru
ኢስላማዊ ሀዲሶችን ትኩስ ትኩሱን ያገኛሉ አላማችን ኡማውን ማገልገል ነው ለጓደኛዎ ሼር ያድር አንዲትም ቃል ብትሆን ከኔ የሰማቹትን ለሌሎች አስተላልፋ ብለዋል ረሱል ሰ ዐ ወ 👇👇👇👇👇
ለአስተያየት( @Mahmmedinhabot)
ሼር(@ethioiselamdawa)👈
ምርጡን ጓደኝነት ላስተዋውቅህ ሀቢቢ....

ረሱል ሶለላ አለይሂ ወሰለም በኢስራ ወል ሚዕራጅ ጉዞ ሀድረተል ሙንተሀ ደርሰው ጅብሪል ከዚህ በላይ ማለፍ አልችልም ብሎ በተመለሰ ግዜ

.....አላህ ሱብሀነ ወተዓላ ብቸኝነት እንዳይሰማቸው ብሎ ከዛ በላይ ያስጎበኛቸውን መላይካ ፊቱን በውዱ ጓደኛቸው በአቡበክር ሲዲቅ ፊት አስመሰለላቸው ያኔ ተረጋጉ!

@Dinel_islam @Dinel_islam
🙏ጌታዬ ሆይ!!ጨንቆኛል አልኩህ (ከአላህ ራህመት ተስፋ አትቁረጡ አልክ!

....ካንተ ሌላ ማንም የለኝም አልኩህ (እኔ ከደም ስርህ የበለጠ ቅርብ ነኝ )አልክ

🙏አትርሳኝ አልኩህ (አስታውሱኝ አስታው ሳቹሃለሁኝ)አልክ.....

.. ተስፋን ስጠኝም አልኩህ (ከችግርም ጋር ደስታ አለ) አልክ

...ህልሜ እንዴት እውን ይሆንልኝ ይሆን አልኩህ (ለምኑኝ እቀበላቹሃለው)አልክ

🙏ጌታዬ ሆይ ጥራት ይገባህ ምን ያህል ቸር ነህ !!!

@Dinel_islam @Dinel_islam
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ተናገሩ"አንድ ሰው በሞተ ጊዜ ዘመዶቹ በቀብር
ሥነስርአቱ ላይ ሲጨናነቁ አንድ እጅግ ያማረ ቆንጆ ሰው
በጭንቅላቱ በኩል ይቆማል።ጀናዛውም እንደተከፈነ ያ ሰው
በከፈኑ እና በሞተው ሰው ደረት መሀል ይሆናል።ከቀብር
ሥነስርአቱም በህዋላ ቀባሪ ቤተሰቦቹ ወደ ቤት ሲመለሱ ሁለት
ሙንከር እና ነኪር የተባሉ ምላኢኮች ወደ ቀብሩ በመምጣት
ጀናዛውንና ያንን ቆንጆ ሰው በመለያየት ያንን የሞተውን ሰው
በእምነቱ ጉዳይ ብቻውን በጥያቄ ሊያፋጡት ይሞክራሉ ። ሆኖም
ያ ቆንጆ ሰው ይናገራል "ይህ ሰው አጋሬም ጋደኛዬም ነው
ብቻውንም ልተወው አልችልም። እናንተ እንድትጠይቁት
ከተመደባቹ ስራችሁን መሥራት ትችላላቹ እኔ ግን ወደ ጀነት
መግባቱን ሳላረጋግጥ ትቼው እልሄድም"። ከዝያም ወደ ሞተው
አጋሩ በመዞር እንዲህ ይለዋል "እኔ አንዳንዴ ድምፅህን ከፍ
አርገህ ሌላ ጊዜ ደግሞ ቀስ ብለህ ስታነበኝ የነበርኩት ቁርአን
ነኝ ምንም አትጨነቅ፤ ከሙንከርና ነኪር ጥያቄና መልስ በኃላ
ምንም ጭንቀት አይኖርብህም"፤ጥያቄና መልሱም ካለቀ በኃላ ያ
ቆንጆ ሰው አል ማሉል አላ በተባሉ የጀነት መላኢኮች የተዘጋጀ
በመልካም ሽታ የሚያውድ እና ከ ሀር በተሰራ ልብስ የተዘጋጀ
አልጋ ያዘጋጅለታል።
2. ረሰል(ሶ.ዐ.ወ) እንደተናገሩት በቂያማ ቀን በአላህ ሱ.ወ ፊት
ስንቆም ከቁርአን የበለጠ ለኛ ሚከራከርልን አይኖርም
ከነብይያትም ከ መላኢኮችም በበለጠ።
3. እባክዎን ይህን መልእክት የቻሉትን ያህል ያስተላልፉ። ረሱል
(ሶ.ዐ.ወ) እውቀትን ከኔ ለሌላው አስተላልፉ አንድም አረፍተ ነገር
ብትሆን እንኩዋን ብለዋል።
4. ይህ መልእክት በ አላህ ፍቃድ በቀጣይ 7 ቀናት ቢያንስ 5
ሚልዬን ሰዎች እንዲዳረስ ዱአ እያደረግን ነው።
እባክዎን ይህን መልእክት ለ ቤተሰብዎ፣ ለዘመድዎትና
ላሚያውቅዋቸው ሁሉ በማስተላለፍ ከተትረፈረፈው የአላህ ምንዳ
ተጠቃሚ ይሁኑ።

┄┄┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄┄
@Damemaka
🍀 @Damemaka🍀
ይህ የሲህር ምልክት ሳይሆን በጅን መያዝ አለመያዛችንን አመላካች ነው።

❶.የሰውነት የሚያስጠላ ጠረን ። ለሰው ሳይሆን ለራስ መሽተት

➋. ቶሎ ቶሎ መራብ አለመጥገብ

❸.የልብ በፍጥነት መምታት ወይም በየ ሰአቱ ልዩነት ልብ ፍጥነቱን ሲጨምር መሰማት።

❹.የጥርስ መፋጨት ። በተኙበት ጥርሶ በጣም መፋጨት።

❺.ለሊት ላይ ወይም ያለ ወትሮ የአፍንጫ መንሰር።
❻ የአውራ ጣት ህመም ይህም ለሊት ላይ ሲሆን። ቀን ቀን ደግሞ የመገጣጠምያዎች መታመም።

❼ ሰው ሁሉ ስለኔ ነው የሚያወራው ብሎ ማመን ቲቪ ሬድዮ ሁሉም ስለኛ አውቆ የሚያወራ ይመስለናል!

❽.የሚያስፈሩ ህልሞችን ማየት። ቅዠቶች መብዛት።

❾.ውልብ የሚሉ ነገሮችን መመልከት! ለኛ ብቻ ጅኖች ወይም ለሰው የማይታዩ ነገሮች መታየት ።

❿. ነገሮች ከመሆናቸው በፊት ቀድሞ የማወቅና ለማንም ያለመንገር ድብርት።

11.ስማችንን ማንም ሳይጠራ እኛ ግን የሚጠራ ሰው ይሰማናል! ለማንም የማይሰማ ድምፅ ለኛ መሰማት!

12.ሰውነት ላይ መበለዝ ያለ ምንም ጥቃት ሰውነት ይበልዛል!

13.ጨጓራ ህመም! ከመሬት ተነስቶ መታመም ምክንያቱም አይታወቅም!

14.ልብ ዝም ብሎ መፍራት መጨነቅ! በተለይ ከመግሪብ ኋላ!

ከዚህ አይነት ጥቃት በአሏህ ሃይል እንጠበቃለን፡፡ ከሸይጧን ጭፍሮችም ሸር እንዲሁ! በርሶ ላይ ማንኛውም አይነት ህመሞች ሲኖሩ በሲህርና በአለማዊ በሽታዎች ሲጠቁ አሏህም ካለ በኢስላማዊ እውቀት ብቁ የሆኑ የሩቅያህ ዶክተሮችን አለማዊ የሜዲካል ዶክተሮችን የሳይካትሪስት ዶክተሮችን ብሎም የሃዲስ ምሩቆችን እና የሸሪአ ምሩቅ ምሁሮችን ወደሚያገኙበት ወደ ቀልብ ዶክተር ቻናል በማምራት ዶክተር ወይም ኡስታዝ ብለው በማናገር ህክምናዎን በረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም መንገድ ብቻ ያግኙ፡፡
ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏህ

https://t.me/Qallbdoc
Channel photo updated