Ethio Fm 107.8
20.6K subscribers
7.92K photos
16 videos
4 files
2.31K links
በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!
Download Telegram
የደረጃ ሐ ግብር ከፋዮች ዓመታዊ ግብራቸዉን በቴሌ ብር መክፈል የሚችሉበት ስርዓት ተዘረጋ፡፡

ወደ 300 ሽህ የሚጠጉ የደረጃ ሐ ግብር ከፋዮች ዓመታዊ ግብራቸዉን በቴሌ ብር አማካኝነት መክፈል የሚያስችላቸዉን አሰራር ተግባራዊ ተደርጓል፡፡

አሰራሩን ተግባረዊ ያደረጉት ኢትዮ ቴሌኮምና የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ በመተባበር ነዉ፡፡

በዚህ የግብር ክፍያ ስርዓት፣የ 2014 በጀት ዓመት ግብራቸዉን የሚከፍሉ የደረጃ ሐ ግብር ከፋዮች ያለ ምንም እነብግልትና ዉጣ ዉረድ ግብራቸዉን እንዲከፍሉ ያስችላቸዋልም ተብሏል፡፡

አገልግሎቱ ከሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ የዋለ ሲሆን እስካሁንም 679 ሰዎች በዚህ ስርዓት ግብራቸዉን ከፍለዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

ዌብሳይት https://ethiofm107.com/

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሐምሌ 12 ቀን 2014 ዓ.ም
በአዲስ አበባ የሆቴል ግብዓት አቅራቢዎች ኤክስፖ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በሀገር ውስጥ ያሉ የተለያዩ የሆቴል ግብአት አቅራቢዎች ከሆቴሎችጋር የሚገናኙበት ኤክስፖ በኤሊያና ሆቴል አዘጋጅነት ነዉ በመካሄድ ላይ የሚገኘዉ፡፡
አሁን በሀገራችን ባለው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ላይ ተዳምሮ በርካታ ነገሮች ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡበት በዚህ ሁኔታ፣ ከሀገር ውስጥ አቅራቢዎች ጋር በጋራ የሚሰራበት ሂደት መፈጠሩ የተሻለ ዉጤት ያመጣል የሚል ተስፋ እንዳላቸዉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ሂሩት ካሰው ገልጸዋል።
ለሆቴል እና ቱሪዝም ዘርፉ የሚያገለግሉ ዕቃዎችን ከቀረጥ ነፃ በማስገባት ጭምር ለዘርፉ ድጋፍ ሲደረግ እንደነበርም ተናግረዋል።

በኮቪድ 19 ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት በደረሰባቸው የሆቴል እና ቱሪዝም ዘርፉ ላይ መነቃቃት እንዲኖር እና የተቀዛቀዘውን የሆቴል ኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ እንደሚኖረውም ሃላፊዋ ገልጸዋል።
የሆቴል ማሰልጠኛ ተቋማት፣ባንኮች፣ የኢንሹራንስ ድርጅቶች፣አየር መንገድ፣ ትራንስፖርት ፣የምግብ እና መጠጥ፣ የንፅህና መጠበቂያ አቅራቢዎች፣ደህንነት እና ጥበቃ፣የህክምና፣የመዝናኛ እንዲሁም የስዕል አቅራቢዎች የሚሳተፉበት ነው ተብሏል።
ዛሬ እና ነገ በሚካሄደው በዚህ ኤክስፖ ከ200 በላይ ተሳታፊዎች እና ከ10 ሺህ በላይ ጎብኚዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በእስከዳር ግርማ
ሐምሌ 12 ቀን 2014 ዓ.ም
ፈረንሳይ ሩሲያን በተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ልትተካ አስባለች::

ፈረንሳይና የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች በሃይል ዘርፍ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል፡፡
የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ፕሬዝዳንት ሙሃመድ ቢን ዛይድ ከፈረንሳይ አቻቸዉ ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በፓሪስ ተገናኝተዉ በነዳጅና በታዳሽ ሃይል ዘርፍ አብረዉ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
ፓሪስ ከሞስኮ ጋር ያላት ግንኙነት እየተቀዛቀዘ መምጣቱን ተከትሎ በአቡዳቢ ለመተካት ስለማቀዷ ታዉቋል፡፡

የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ነዳጅና እና ሌሎች የሃይል ምርቶችን ለፈርንሳይ እንደምታቀርብም ተነግሯል፡፡
አቡዳቢ ለአለም የነዳጅ አቅርቦቷን እንደምታጠናክር የገለፁት ቢን ዛይድ፣ በዋናነት ደግሞ ለፈርንሳይ ድጋፍ ታደርጋለች ነዉ ያሉት፡፡
ፈረንሳይን ጨምሮ የአዉሮፓ አገራት ከሩሲያ የሚያገኙት ነዳጅ አስተማማኝ ባለመሆኑ የመካከለኛዉ ምስራቅ አገራትን በመማፀን ላይ ናቸዉ፡፡

በአባቱ መረቀ
ሐምሌ 12 ቀን 2014 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

ዌብሳይት https://ethiofm107.com/

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
በአዲስ አበባ 96 ቦታዎች የእሁድ ገበያ ተቋቁመዋል ተባለ፡፡

"በሸማቾች የህብረት ስራ ማህበራት፣ የሰብልና የአትክልት አቅራቢዎች፤ የጅምላ ነጋዴዎችና በምግብ ማቀነባበርያ የተሰማሩ ፋብሪካዎች እንዲሁም በኦሮምያ ልዩ ዞን የሚገኙ የህብረት ስራ ማህበራትን በማሳተፍ በየሳምንቱ የእሁድ ገበያ በከተማዋ በተመረጡ 96 ቦታዎች የፍጆታ እቃዎች እየቀረቡ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

የእሁድ ገበያው በአምራችና በሸማቹ መሀከል የነበረውን የገበያ ሰንሰለት በመበጣጠስ፤ተጠቃሚው በቀጥታ ከአምራቾች ምርትን በወቅቱና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ በማድረግ የኑሮ ውድነት ጫናው ዝቅተኛ ገቢ ያለውን የማህበረሰብ ክፍል እንዳይጎዳ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡

በእነዚህ በተመረጡ የእሁድ ገበያዎች የሚቀርቡ የፍጆታ እቃዎች የዋጋቸዉን ተመጣጣኝነትና አቅረቦትን በተመለከተ አድማጮች አስተያየቶቻችሁን ልትሰጡበት ትችላላችሁ፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሐምሌ 12 ቀን 2014 ዓ.ም

Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

ዌብሳይት https://ethiofm107.com/

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችንን ይከታተሉ፦


በዛሬው የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችን ( ከ12:30-2:30)


-ከቤት ሳንወጣና ስፖርታዊ ጉዳዮችን ትሰማላችሁ

- በመንገዳችን ላይ፦ከአዲስ አበባ ወደ ክፍለ ሀገር ሲጓዙም ሆነ ከክፍለ ሃገር ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ እርስዎም የሚታዘቡት በጉዞ ወቅት በአንዳንድ የትራፊክ ፖሊስ አባላት ላይ የተመለከትነውን ትዝብት እናጋራችኋለን።

- በፍተሻ ሰዓታችን መነጋገር ሊደፈር፣አለመነጋገር ሊፈራ ይገበዋል በሚል የመነጋገር ባህላችንን እንፈትሻለን፤ የባለሙያ ምክረ ሀሳብም ይዘንበታል!

-በኢትዮ ገበያችን ፦
በቱሪዝም ዘርፍ ላይ የተሰማራዉ የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ዱባይ ቱሪዝም ለኢትዮጵያ አስጎብኚ ድርጅቶች አደርጋለሁ ስላላቸው የተለያዩ ድጋፎች እናነሳለን።

- ለጤናችን ዛሬ ትኩረቱን በዓለማችን እየተከሰተ ያለው ድርቅና ረሀብ በጤናችን ላይ የሚያደርሰው ተጽዕኖ ላይ አድርጓል

-በዓለም ጉዳይ፦ በዩክሬን ጉዳይ ትችት እየቀረበበት ስለሚገኘው የአውሮፓ ህብረት በትንታኔ አዘጋጅተንላችኋል።


- እንዲሁም ሌሎች አዳድስ የሀገር ውስጥና ዓለምዓቀፋዊ ጉዳዮችንም አሰናድተንላችኋል፤

እንድታደምጡ ተጋብዛችኋል።

ለአስተያየትዎ '6321' አጭር የጽሁፍ መልዕክት

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ንጋት ላይ በተካሄደ የ1 ሺህ 500 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ታደሰ ለሚ 8ኛ ሆኖ አጠናቀቀ።

የወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ንጋት 11፡30 ላይ ተካሂዷል።

ኢትዮጵያ በአትሌት ታደሰ ለሚ የተወከለች ሲሆን፥ አትሌቱ ስምንተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሐምሌ 13 ቀን 2014 ዓ.ም
Audio
የዛሬው የኢትዮ ማለዳ ዜናዎቻችን
10 ሽህ ብር ጉቦ ስትቀበል እጅ ከፍንጅ ተያዘች፡፡

የመሬት አስተዳደር የንብረት ግምት ባለሙያ የሆነች አንዲት ግለሰብ 10 ሺ ብር ጉቦ ስትቀበል እጅ ከፍንጅ መያዟን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

የጉለሌ ክ/ከተማ የመሬት አስተዳደር የንብረት ግምት ባለሙያ የሆነችው ግለሰብ አንድን ባለ ጉዳይ ጉዳይህን እኔ እጨርስልሀለሁ በማለት 10ሺ ብር ጉቦ ስትቀበል ሀምሌ 6 ቀን 2014 ዓ/ም እጅ ከፍንጅ ተይዛ አስፈላጊው ምርመራ ተጣርቶ ክስ እንደተመሰረተባት የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የግል ተበዳይ በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከድንበር ጋር የተያያዘ ጉዳዩን ለማስጨረስ በሄደበት አጋጣሚ ግለሰቧ 30 ሺህ ብር ጉቦ የጠየቀችው ሲሆን 10ሺ ብር ቅድሚያ እንደሰጣት እና ቀሪውን 20 ሺህ ብር ደግሞ ጉዳዩ ሲያልቅ ለመወሰድ መጠየቋን የግል ተበዳይ ለክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ አሳዉቋል፡፡
በመሆኑም ሐምሌ 8 ቀን 2014 ዓ/ም ጉቦውን ስትቀበል በፖሊስ እጅ ከፍንጅ ተይዛ አስፈላጊው ምርመራ ተጣርቶ ክስ እንደተመሰረተባት የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡
ማህበረሰቡ መሰል ወንጀል ፈፃሚዎችን ለህግ አካል አጋልጦ የመስጠት ልምዱ ይበል የሚያሰኝ ተግባር መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ተናግሯል፡፤
ወደፊትም ህዝብን እና መንግስትን የሰጣቸውን እምነት በማጉደል በማህበረሰቡ ላይ በደል የሚፈጽሙ አካላትን ወደ ህግ ለማቅረብ የሚደረገው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብሏል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 13 ቀን 2014 ዓ.ም
የኢራኑ ናሽናል እና የሩሲያዉ ጋዝ ፕሮም ታሪካዊ ነዉ ያሉትን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የኢራን ናሽናል ነዳጅ ኩባንያ እና የሩሲያዉ ነዳጅ አምራች ጋዝ ፕሮም ወደ 40 ቢሊዮን የሚጠጋ የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸዉን የኢራን የነዳጅ ሚኒስቴር ዜና ወኪል ሻና ዘግቧል፡፡
የኢራን ባለስልጣናት እንደገለጹት 20 ሚሊዮኑ ለኪሽ እና ለሰሜናዊ ፓርስ የጋዝ ማምረቻ የሚከፋፈል ሲሆን፤በቀን የ100 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ተጨማሪ ጋዝ እንዲያመርቱም ይረዳል ነዉ የተባለዉ፡፡

የሩሲያዉ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከኢራኑ አቻቸዉ ጋር ለመምከር ወደ ቴህራን ባቀኑበት ወቅት የሁለቱም ኩባንያ ሃላፊዎች በኦንላይን ባደረጉት ዝግጅት ነዉ ስምምነቱ የተፈረመዉ፡፡
ጋዝ ፕሮም የኢራን ናሽናል ነዳጅ ኩባንያን የኪሽ እና ሰሜናዊ ፓርስ የጋዝ ማምረቻ ቦታዎችን በማልማት ረገድ እንደሚደግፋት እንዲሁም ሌሎች ተጨማሪ ስድስት የጋዝ ማምረቻ ቦታዎችን በማልማትም ትብብር እንደሚያደርግ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

ጋዝ ፕሮም ከዚህ በተጨማሪም የተፈጥሮ ጋዝ አምራች ፕሮጀክትን እና የጋዝ ማስተላለፊያ ቱቦዎችን በመገንባት ኢራንን እንደሚረዳ ተገልጿል፡፡

ኢራን ከሩሲያ በመቀጠል በዓለም ሁለተኛዋ ከፍተኛ የጋዝ ክምችት ያላት ሀገር ብትሆንም፣ የአሜሪካ ማዕቀብ ከቴክኖሎጂ ጋር ግንኙነት እንዳይኖራት ያቀባት በመሆኑ ወደ ዉጭ የሚላከዉ የጋዝ ዕድገት አዝጋሚ እንዲሆን አድርጎታል፡፡
የሩሲያ-ዩክሬንን መዉረር በዓለም ነዳጅ እና የነዳጅ ገበያዉ ላይ ባሳደረዉ ተጽዕኖ ምክንያት የፑቲን የቴህራን ጉብኝት በከፍተኛ ሁኔታ የዓለምን ትኩረት የሳበ እንደሆነ አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

በእስከዳር ግርማ
ሐምሌ 13 ቀን 2014 ዓ.ም
በትላንትናው እለት በደረሰ የትራፊክ አደጋ ስምንት ሰዎች ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደረሰባቸዉ፡፡

ከአዲሱ ገበያ ወደ ፒያሳ በማቅናት ላይ የነበረ አይሱዙ የጭነት መኪና መንገድ በመሳቱ ምክንያት ነው አደጋው የደረሰው፡፡
በአደጋው ምክንያትም ስምንት ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ ሲሆን አደጋ የደረሰባቸው ሰዎች ወደ አቤት ጠቅላላ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡

እንደዚሁም በአካባቢው የነበሩ አምስት መኪኖችም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
አደጋ ያደረሰው የጭነት መኪናው መንገድ ስቶ ስለነበረ በሁለት የንግድ ሱቆች ላይም የንብረት ጉዳት ማድረሱ ነው የተነገረው፡፡
ዜናዉ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ያለዉ መረጃ ይህ ነዉ፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሐምሌ 13 ቀን 2014 ዓ.ም
ቻይና አሜሪካ በህዋ ላይ የምታደርገዉን ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንድታቆም አሳሰበች::

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ዣኦ ሊጂያን ዋሽንግተን በህዋ ላይ የምታደርገዉን ወታደራዊ እንቅሰቃሴ እንድታቆም አሳስበዋል፡፡
አሜሪካ በህዋ ላይ ትጥቅ በመታጠቅ ላይ ነች ያሉት ቃል አቀባዩ፣ከድርጊቷ በመቆጠብ የህዋ ደህንነትን ማስጠበቅ አለባት ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም አሜሪካ በህዋ ላይ የበላይነትን የማስፈን ስትራቴጅንና እንደ ዳይሬክት ኢነርጅ፤የተቆጣጣሪ ኮሙኒኬሽን ሲስተም በመዘርጋት ላይ እንደምትገኝም ተነግሯል፡፡
አገሪቱ አደገኛ የውጭ ጠፈር መሳሪያዎችን በከፍተኛ ሁኔታ በማዘጋጀትና በማሰማራት ላይ ትገኛለች ስትልም ቻይና ከሳለች፡፡
በተጨማሪም ዋሽንግተን በአለም አቀፍ ስትራቴጂካዊ መረጋጋት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል በተባለዉ ጠፈር ላይ ስለላ ስለመጀመሯም ቤጂንግ ማስታወቋን ሲ ጂ ቲኤን ዘግቧል፡፡

በቤዛዊት አራጌ
ሐምሌ 13 ቀን 2014 ዓ.ም
በ3 ሺህ የሴቶች መሰናክል ኢትዮጵያ የብርና ነሐስ ሜዳልያ አገኘች።


በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ንጋት ላይ በተካሄደ የሴቶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል የፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያ የብርና የነሐስ ሜዳሊያዎች አገኘች።

አትሌት ወርቅውሃ ጌታቸው የብር እና መቅደስ አበበ የነሐስ ሜዳሊያዎችን አስገኝተዋል።

የወርቅ ሜዳሊያውን የካዛኪስታን አትሌት አግኝታለች።

ኢትዮጵያ ሶስት የወርቅ፣ አራት የብር እና አንድ የነሃስ ሜዳሊያዎችን በመያዝ ከአሜሪካ ቀጥላ በሁለተኛ ደረጃ ተቀምጣለች።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሐምሌ 14 ቀን 2014 ዓ.ም
Audio
የዛሬው የኢትዮ ማለዳ ዜናዎቻችን 14-11-14
በሀገራችን ከ40 በመቶ በላይ የሞት ምጣኔ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች የሚከሰት ነዉ ተባለ፡፡

በሀገራችን ካለው የሞት ምጣኔ ከፍተኛውን ድርሻ የሚወስደው ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች የሚከሰት ሞት መሆኑ ተገልጿል።

ጤና ልማትና ፀረ ወባ ማህበር፣ ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች እያደረሱ ያሉት ጉዳት በሚል ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

የማህበሩ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አክሊሉ ጌትነት እንደተናገሩት፣ በሀገራችን ከሚከሰት ሞት ውስጥ 40 በመቶው የሚከሰተው ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ነው።

ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በሀገራችን ስር እየሰደዱ እንደሚገኙ ያነሱት ምክትል ዳይሬክተሩ ለዚህ ጉዳይ መባባስ ብዙ ምክንያቶች እንዳሉ ያነሳሉ።

አሁናዊው በሀገራችን ያለው የአመጋገብ ስርዓት አንዱ መሆኑን ያነሱት አቶ አክሊሉ፣ በይበልጥ በወጣቱ ዘንድ የተለመደው በፋብሪካ የተቀነባበሩ የታሸጉ ምግቦችን መመገብ ሲሆን፣ ይህም ተላላፊ ላልሆኑ የበሽታ አይነቶች ተጋላጭነታቸው እንደሚጨምር እንደሚያደርግ አንስተዋል።

ሌላው እና ዋናው ምክንያት ነው ተብሎ የሚነሳው ደግሞ ትምባሆ ማጨስ ፣አልኮል መጠቀም እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ ናቸው።

ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ተብለው የሚጠቀሱት የልብ ህመም ፣ካንሰር ፣የመተንፈሻ አካላት ህመም ፣የደም ግፊት እንዲሁም የስኳር ህመም ናቸው ።
በአለም አቀፍ ደረጃ ካለው የሞት ምጣኔ 71 በመቶው ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ሲከሰት ከዚሁ ጋር ተያይዞ በአመት በአለም 41 ሚሊዮን ሰዎች ህይወታቸውን ያጣሉ ተብሏል።

በእስከዳር ግርማ

ሐምሌ 14 ቀን 2014 ዓ.ም