በ4 የምርጫ ክልሎች ምርጫ እንዲደገም ፍርድ ቤት ወሰነ፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁለተኛ የምርጫ ጉዳዮች ችሎት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ያቀረበውን የምርጫ ይደገምልን አቤቱታ እና ክርክርን ተከትሎ በአራት የምርጫ ክልሎች ምርጫ እንደገና እንዲካሄድ ወስኗል፡፡
ፍርድ ቤቱ ምርጫ እንዲደገም የወሰነባቸው አራቱ የምርጫ ክልሎች በደቡብ ክልል የሚገኙ ሲሆን እነዚህም የክልል ምርጫ የተካሄደባቸው ላስካ መደበኛ፣ ቁጫ ልዩ፣ ጉመር 2 እና ብርብር ምርጫ ክልሎች መሆናቸዉ ታዉቋል፡፡
ኢዜማ በ28 የምርጫ ክልሎች ሂደቱ ያለአግባብ ስለተፈፀመ ምርጫ እንደገና እንዲካሄድ ይደረግ በማለት 156 ገጾች ያየዘ አቤቱታ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምርጫ ጉዳዮች ችሎት ማቅረቡ እና በጉዳዩ ላይ ከምርጫ ቦርድ ጋር በችሎቱ ክርክር መካሄዱ ይታወሳል።
ኢዜማ በአቤቱታው ካካተታቸው ጉዳዮች "የእጩዎቼ ፎቶ እና ስም ዝርዝር ባለመካተቱ አልተወዳደርኩም" ያላቸውን የምርጫ ክልሎች መጥቀሱም ይታወቃል።
ምርጫ ቦርድም የት፣ መቼ እና በማን የሚል ዝርዝር ጉዳይ የያዘ አቤቱታ አልቀረበም በማለት መከራከሩን እና ችሎቱም በመዝገቡ ላይ ለዛሬ ለውሳኔ መቅጠሩን ይታወሳል።
በዚሁ መሠረት ችሎቱ በደቡብ ክልል አራት የምርጫ ክልሎች ማለትም በላስካ መደበኛ፣ በቁጫ ልዩ፣ በጉመር 2 እና በብርብር ምርጫ ክልልሎች የተካሄደው የክልል ምርጫ እንዲደገም መወሰኑን ኢቢሲ ዘግቧል።
ችሎቱ ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈው የኢዜማ እጩ ተወዳዳሪዎች ፎቶዋቸው እና የስም ዝርዝራቸው ያልተካተተ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እጩዎች አለመወዳደራቸውን በመጥቀስ ነው።
ኢዜማ በሌሎች 22 የምርጫ ክልሎች በተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ በድምፅ አሰጣጥ እና ቆጠራ ሂደት ላይ "ታዛቢዎች እንዳይሳተፉ ተደርገዋል" ሲል ያቀረበውን አቤቱታ በተመለከተ ዝርዝር ማስረጃ ባለማቅረቡ አቤቱታው በችሎቱ ውድቅ ተደርጓል።
በተመሳሳይ ኢዜማ አቤቱታ ያቀረበባቸው የጋምቤላ ከተማ እና ጊዮሌ ልዩ የምርጫ ጣቢያዎች የአቤቱታ ማቅረቢያ ጊዜው ካለፈ በኋላ የቀረበ በመሆኑ ችሎቱ የኢዜማን ክርክር አልተቀበለም።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ነሃሴ 21 ቀን 2013 ዓ.ም

በአዲስ አበባ የቤት ኪራይ ጭማሪ ለ90 ቀናት ታገደ::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በቀን 18/12/13 ባደረገው መደበኛ ስብሰባው የቤት ኪራይ ጭማሪን ለ90 ቀናት ለማገድ በቀረበ ደንብ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡
በዚህም መሠረት ደንቡ ከፀደቀበት 18/12/13 ዓ.ም ጀምሮ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ መጨመርም ሆነ ተከራይን ከቤት ማስወጣት ለ90 ቀናት የተከለከለ ሲሆን በቀጣይም ታይቶ ለተጨማሪ ቀናት ክልከላው ሊራዘም ይችላል ብሏል::
ደንቡን በመተላለፍ ጭማሪ የተደረገበት ተከራይ አቤቱታውን በፅሑፍ ለወረዳው ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት በማቅረብ መፍትሄ እንዲያገኝ የሚቻልበት ሥርዓት በደንቡ ተደንግጓል ተብሏል፡፡
ሙሉ መግለጫዉ የሚከተለዉ ነዉ፡-
የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪን ለመገደብ በወጣ ደንብ ላይ የተሰጠ መግለጫ፡-
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከተማችን የኑሮ ውድነት እየተባባሰ እንደመጣ የሚታወቅ ነው፡፡ የኑሮ ውድነቱ በአብዛኛው አሳማኝ እና ምንም አይነት ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የሌለው በሰውሰራሽ ምክንያቶች የተፈጠረ ነው፡፡ የኑሮ ውድነቱም የከተማችንን ነዋሪ ለከፍተኛ ችግር ዳርጓል፡፡
በሰሜን የሃገራችን ክፍል ሃገር በማፍረስ ተግባር ላይ የሚገኘውን የአሸባሪው ህወሃት እንቅስቃሴ ለማክሸፍ እየተደረገ ካለው ዘመቻ ጋር ተያይዞ የከተማችን ነዋሪ በገንዘብ መዋጮ፤ ለሠራዊት የሚሆን ስንቅ በማዘጋጀት፤ ደም ልገሳ እስከ ህይወት መስዋዕትነት እየከፈለ ባለበት በዚህ ወቅት ጥቂት ስግብግብ ግለሰቦች በተቃራኒው ቆመው ከኢትዮጵያዊነት ጨዋነት ፍፁም ባፈነገጠ መልኩ አሁን ካለው ችግር ላይ አላግባብ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ የተለያዩ ተግባራት ውስጥ ገብተው ይገኛሉ፡፡
መንግሥት እያጋጠመ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ከውጭና ከውስጥ ያሉ ጫናዎችን ተቋቁሞ ሀገር የማፍረስ ተግባር እንዲከሽፍና የዜጎች የኑሮ ጫና እንዲቀንስ የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል፡፡
በዚህም መሠረት እስከታችኛው የማኅበረሰብ ክፍልን የሚያሳትፍ የኢኮኖሚ አሻጥሩን ለመቀልበስ የተቋቋመው ግብረይል በርካታ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡
በአጭር ጊዜ ውስጥም ግብረሃይሉ ባካናወናቸው ተግባራት ተጨባጭ ለውጦች በመታየት ላይ ይገኛል፡፡
ከመሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ባሻገር አለግባብና የወቅቱን ሁኔታ ያላገናዘበ የቤት ኪራይ ጭማሪ የነዋሪውን ሕይወት በእጅጉ እየፈተነው ይገኛል፡፡
ይህም ወቅታዊ ሁኔታን በመጠቀም አላግብ ለመክበር የሚደረግ ከኢትዮጵያዊ ጨዋነትና መተሳሰብ ጋር በፍፁም የሚቃረን ተግባር ነው፡፡
በ2012 ዓ.ም የኮቪድ 19 ወረርሽ በሀገራችን መገኘቱ ተከትሎ በርካቶች ችግር ውስጥ በገቡበት ወቅት የከተማችን ነዋሪዎች እርስ በእርስ ከመረዳዳትና ማዕድ ከመጋራት አልፎ በርካታ ቤት አከራዮች የወራት የቤት ኪራይ ዋጋ ለተከራይ በራሳቸው ተነሳሽነት ቀንሰው ችግሩን በጋራ ለመፍታት ኢትዮጵያው የመረዳዳት እሴታችን የታየበት እንደነበር ይታወሳል፡፡
ይህም በወቅቱ በሕግ ተቀምጦ የነበረውን የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመር የሚከለክለውን ድንጋጌ ሳይጨምር ነው፡፡
አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት በቤት ክራይ ላይ ዋጋ ጭማሪ መታየቱን ነዋሪዎች ቅሬታቸውን እያሰሙ ነው፡፡
ስለሆነም አሁን እየታየ ያለውን አላግባብ የሆነ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ ለመገደብ የነዋሪውን ቅሬታ ምላሽ ለመስጠት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በቀን 18/12/13 ባደረገው መደበኛ ስብሰባው የቤት ኪራይ ጭማሪን ለ90 ቀናት ለማገድ በቀረበ ደንብ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡
በዚህም መሠረት ደንቡ ከፀደቀበት 18/12/13 ዓ.ም ጀምሮ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ መጨመርም ሆነ ተከራይን ከቤት ማስወጣት ለ90 ቀናት የተከለከለ ሲሆን በቀጣይም ታይቶ ለተጨማሪ ቀናት ክልከላው ሊራዘም ይችላል፡፡
ደንቡን በመተላለፍ ጭማሪ የተደረገበት ተከራይ አቤቱታውን በፅሑፍ ለወረዳው ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት በማቅረብ መፍትሄ እንዲያገኝ የሚቻልበት ሥርዓት በደንቡ ተደንግጓል፡፡
በዚሀ መሰረት በሚቀርቡ አቤቱታዎች ላይ ማጣራት ተደርጎ ጭማሪ ባደረገ አካል ላይ በደንቡ ተዘርዝሮ በተቀመጠው መሰረት ተጠያቂ የሚደረግ ይሆናል፡፡
ምንም እንኳን ይህ ደንብ የወጣው ዜጎችን ካላስፈላጊ ጫና ለመከላከልና ጥፋተኞችን ተጠያቂ ለማድረግ ቢሆንም ህብረተሰባችን በኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት ችግሮችን በመተሳሰብና በመደጋገፍ ለማለፍ ያሳየውን ኢትዮጵያዊ የጨዋነትና አብሮነት እሴቶቹን በማዳበር ይህን ወሳኝና አስቸጋሪ ጊዜ በጋራ ማለፍን ማዕከል በማድረግ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያ
ነሃሴ 22 ቀን 2013 ዓ.ም

ቱርክ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ቴክኖሎጂ በዓለም ላይ ካሉ ምርጥ ሶስት አገራት አንዷ ናት አሉ የቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን
የቱርክ ፕሬዝዳንት እንዳሉት ቱርክ በዘርፉ ከቀደምት ከሆኑ እና በከፍተኛ ደረጃ ላይ ከተቀመጡ ሶስት ሀገራት ውስጥ አንዷ ናት ማለታቸውን አናዶሉ ኤጀንሲ ዘግቧል።
በሰሜን ምዕራብ ባለች አንድ ግዛት በተከናወነ ወታደራዊ ስነ ስርአት ላይ የተገኙት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን “ቱርክ ሰው አልባ በሆነው የአየር ላይ አውሮፕላኖች ቴክኖሎጂ ውስጥ ከሦስቱ እጅግ የተራቀቁ አገሮች አንዷ ሆናለች” ብለዋል።
ቱርክ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ቀዳሚ አገር ለመሆን ቆርጣ መነሳቷን ያስረዱት ኤርዶጋን ቱርክ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ማዘጋጀት አለባት ሲሉ መደመጣቸውን አናዶሉ ዘግቧል።
የአገሪቱ ግብ በውጭ ሀገራት የአውሮፕላኖች ተልእኮ ውስጥ ለአገልግሎት የሚውሉ አጫጭር ማኮብኮቢያዎችን የሚይዙ እና በአውሮፕላን ተሸካሚዎች ላይ ሊያርፉ የሚችሉ የታጠቁ ድሮኖችን ማልማት ነው ብለዋል።
ያይኔ አበባ ሻምበል
ነሐሴ 24 ቀን 2013 ዓ.ም

Ethio Fm 107.8
ቱርክ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ቴክኖሎጂ በዓለም ላይ ካሉ ምርጥ ሶስት አገራት አንዷ ናት አሉ የቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን የቱርክ ፕሬዝዳንት እንዳሉት ቱርክ በዘርፉ ከቀደምት ከሆኑ እና በከፍተኛ ደረጃ ላይ ከተቀመጡ ሶስት ሀገራት ውስጥ አንዷ ናት ማለታቸውን አናዶሉ ኤጀንሲ ዘግቧል። በሰሜን ምዕራብ ባለች አንድ ግዛት በተከናወነ ወታደራዊ ስነ ስርአት ላይ የተገኙት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን…
የብራዚሉ ፕሬዝደንት ጃይር ቦልሶናሮ የወደፊት እጣዬ መገደል ፣መታሰር አሊያም ማሸነፈ ነው ሲሉ ተንብየዋል
የብራዚሉ ፕሬዝደንት ጃይር ቦልሶናሮ ከፊት ያለው ዘመኔ ከመገደል፣ አሊያም ከመታሠር ወይም ደግሞ ከማሸነፍ የሚያልፍ አይደልም ሲሉ ትንቢት ተናግረዋል።
የቀኝ ዘመሙ የብራዚል ፕሬዝደንት ቦልሶናሮ በሚቀጥለው ዓመት ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ያደርጋሉ።
ፕሬዝደንቱ ከግራ ዘመሙ ተቀናቃኛቸው የቀድሞው ፕሬዝደንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ ከባድ ፉክክር ይጠብቃቸዋል።
ቦልሶናሮ በወንጌላውያን መሪዎች ስብሰባ ላይ በሰጡት አስተያየት “ለወደፊት ሕይወቴ ሦስት አማራጮች አሉኝ መታሰር ፣ መገደል ወይም ማሸነፍ” ብለዋል።
በኋላ ላይ የመጀመሪያው አማራጭ “በምድር ላይ ማንም አያስፈራኝም” ከሚለው ጥያቄ ውጭ ነው ብለዋል።
ተቺዎች ግን ቦልሶናሮ ለሳምንታት በሚዘልቀው በብራዚል በ2022ቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የኤሌክትሮኒክስ የድምፅ አሰጣጥ ስርዓት ላይ ጥርጣሬን ለመዝራት የዶናልድ ትራምፕን የመሰለ ዘመቻ እያካሄዱ ነው ሲሉ ተችተዋል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል ።
በኤሌክትሮኒክ የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ለማጭበርበር የተጋለጡ መሆናቸውን ያለ ማስረጃ ሲከሱ ቁይተዋል ይህ ጥያቄ በብራዚል ዳኞች እና በሌሎች ባለሙያዎች ውድቅ ተደርጓል።

ታሊባን አሜሪካ ከአፍጋኒታን ለቃ መውጣቷን ተከትሎ 'ነፃ ሀገር' ሲል አውጇል
ታሊባን የአሜሪካ ጦር ከ 20 ዓመታት ወረራ በኋላ መውጣቱን እንደ “ታሪካዊ ጊዜ” በመግለፅ አፍጋኒስታን “ነፃ እና ሉዓላዊ” ሀገር ናት ብሏል።
የመጨረሻው የአሜሪካ ወታደሮች ከሀገር ሲወጡ የታሊባን ተዋጊዎች ዛሬ የካቡልን አውሮፕላን ማረፊያ ተቆጣጥረዋል።
ይህንን አጋጣሚም ለማክበርም የካቡል ሰማይ ሌሊቱን በተኩስ እና በርችት ሲናወጥ አንግቷል እንደ አልጀዚራ ዘገባ፡፡
የታሊባኑ ቃል አቀባይ ዛቢሁላህ ሙጃሂድ ከካቡል አውሮፕላን ማረፊያ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “የአፍጋኒስታን እስላማዊ ኢምሬት ነፃ እና ሉዓላዊ ሀገር እንደሆነ አንጠራጠርም።
“አሜሪካ ተሸነፈች… እናም አሁን በሀገራችን ስም ከሌላው ዓለም ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖረን እንፈልጋለን” ብለዋል።
ለአፍጋኒስታኖችም የታሊባን ሀይሎች “ነፃነታችንን እና እስላማዊ እሴቶቻችንን ይጠብቃሉ” በማለት ቃል ገብቷል።
የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ ኃላፊ የሆኑት ማሪን ጄኔራል ፍራንክ ማኬንዚ ቀደም ሲል የአሜሪካ ወታደሮች ከካቡል እንደወጡ አስታውቀዋል።
“እኛ ለመውጣት የፈለግነውን ሰው ሁሉ አላወጣንም ግን እኔ እንደማስበው ሌላ 10 ቀናት ብንቆይ እኛ ለማውጣት የፈለግነውን ሁሉ እናስወጣ ነበር”ብለዋል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአሜሪካ ወታደሮችን ለቀው እንዲወጡ ነሐሴ 31 ቀን ቀነ ገደብ አስቀምጠዋል።
ያይኔ አበባ ሻምበል
ነሐሴ 25 ቀን 2013 ዓ.ም

በአሁኑ ሰዓት የኦክስጅን እጥረት በሆስፒታሎች ማጋጠሙን የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከእለት ወደ እለት በከፍተኛ ደረጃ ከመሰራጨቱም በላይ ሰብዓዊ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ችግሮችን እያስከተለ ይገኛል ተብሏል፡፡
ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ህሙማን ቁጥርም ከ 7 ሳምንታት በፊት 180 የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት 602 ግለሰቦች በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝና በዚህም በየሆስፒታሉ የኦክስጅን እጥረት እያጋጠመ መሆኑን ኢኒስቲትዩቱ አስታውቋል፡፡
በኮቪድ 19 ወረርሽኝ የመያዝ ምጣኔ ከ6 ሳምንታት በፊት 1.6 በመቶ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ በያዝነው ሳምንት በአማካይ ወደ 16.5 ከመቶ ከፍ ማለቱ ተነግሯል፡፡
ከ7 ሳምንታት በፊት 11 ለሚሆኑ ህሙማን ሰው ሰራሽ አጋዥ የመተንፈሻ መሳሪያ የሚፈልጉ የነበረ ሲሆን በአሁን ሰዓት ግን ይህን ሰው ሰራሽ መሳሪያ የሚጠብቁ ህሙማን ቁጥር ወደ 80 አድጓል ተብሏል፡፡
በኮቪድ 19 ህይወታቸውን የሚያጡ ግለሰቦችም ከ6 ሳምንታት በፊት 11 ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ላይ ወደ 88 ከፍ ማለቱ ተነግሯል፡፡
ከዚህ በፊት በኮቪድ 19 ምክንያት ተመዝግቦ የነበረው የሞት ቁጥርም ከ85 በመቶ በላይ የሚሆኑት 45 ዓመት እድሜ ገደማ የሚጠጉ ቢሆንም አሁን ባለው ወቅታዊ መረጃ ግን ከ15-24 በሚገኙ የእድሜ ክልል ውስጥ ወረርሽኙ ጉዳት እያስከተለ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡
ሄኖክ ወ/ገብርኤል

በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቀዶ ህክምና ለማድረግ 3ሺ ታካሚዎች ወረፋ እየጠበቁ መሆኑ ተነግሯል።
በሆስፒታሉ የቀዶ ህክምና ክፍል ባለሙያዎች እንደነገሩን በውሀ እና በህክምና መሳሪያዎች በየጊዜው መበላሸት ምክንያት ብዙ ታካሚዎች የቀዶ ህክምና ቀጠሮአቸው እንደሚሰረዝ ገልጸዋል።
በአለም ጤና ድርጅት ከተቀመጠው የ5 በመቶ ስረዛ በላይ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በዚህ አመት ብቻ እስከ 19 በመቶ የቀዶ ህክምና ቀጠሮ መሰረዙንም ሰምተናል።
የላውንደሪ ማድረቂያው አለመስራትና ለህክምና የሚያስፈልጉ ልብሶች ለመድረቅ ጊዜ መውሰድም አንዱ ቀዶ ህክምናውን ከሚያዘገዩ ምክንያቶች ይጠቀሳሉ።
የቀዶ ህክምና መሰረዝ ደግሞ የወረፋ መጠበቂያ ዝርዝሩን ይጨምራል፤ በዚህም በአሁኑ ሰአት እስከ 3ሺ ታካሚዎች ወረፋ ሊጠብቁ ችለዋል ብለውናል የቀዶ ህክምና ክፍል ባለሙያዎቹ።
ችግሩ መች መፍትሄ ያገኛል ያልናቸው የአዲስ አበባ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ኤክስፐርት አቶ ተስፋዬ ሰለሞን የሆስፒታሉ ማኔጅመንት አይቶታል ችግሩ አሁን ካሉን ባዮሜዲካል ኢንጅነሮች በላይ ስለሆነ ሌሎች ልምድ ያላቸው ባለሙያዎችን ለማሰራት እየተዘጋጀን ነው ሲሉ ለጣቢያችን ምላሽ ሰጥተዋል።
መቅደላዊት ደረጄ

የኩላሊት ህሙማን እጥበት ለማድረግ በግል ሆስፒታል እስከ 36 ሺህ ብር ይጠይቃሉ ተባለ
የኩላሊት ህሙማን እጥበት ለማድረግ በግል ሆስፒታል ለአንድ ጊዜ እጥበት 3ሺህ በወር ደግሞ እስከ 36 ሺህ ብር ይጠይቃሉ ተብሏል።
ይሄንን ወጪ ለመቀነስ ለኩላሊት ህሙማን እጥበት ማድረጊያ በጤና ሚኒስቴር በግዢ ለመጀመርያ ዙር ይገባሉ የተባሉት 100 ማሽኖች እስካሁን ተገዝተው አልገቡም ሲሉ የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ሰለሞን አሰፋ ተናግረዋል።
በግዢ ይገባሉ የተባሉት ለኩላሊት ህሙማን እጥበት ማከናወኛ ማሽን ገብተው ቢሆን ኖሮ ለ አንድ እጥበት 500 ብር ብቻ ያስወጣል ብለዋል ።
በዚህም በቀን 400 የሚጠጉ ሰዎች አገልግሎት መስጠት ይችላል ተብሏል።
አሁን ባለው ሁኔታ ግን በግል ሆስፒታል ለአንድ እጥበት እስከ 3000 ብር እየተጠየቁ መሆኑን ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል።
በረድኤት ገበየሁ
ነሃሴ 25 ቀን 2013 ዓ.ም

በጋምቤላ በደረሰ ግጭት የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነገረ፡፡
በጋምቤላ ከተማ ትናንት ማምሻውን በተፈጠረ ግጭት የሶስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ አምስት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል፡፡
የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶማስ ቱት ለክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት እንደገለፁት በትላንትናው ዕለት ከጋምቤላ ከተማ 4 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከቀኑ 11 ሰዓት ከ30 አካባቢ ማንነታቸው ያልታወቁ አምስት ግለሰቦች በከፈቱት ተኩስ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ ሁለት ሰው ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል ብለዋል፡፡
ጉዳቱን ተከትሎ በከተማው በተከሰተው ግጭት የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉንና ሶስት ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ቢሮው አመላክቷል፡፡
በግጭቱ በአጠቃላይ የሶስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ አምስት ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን ያመለከተው ፀጥታ ቢሮው ጥፋተኞቹን ወደ ህግ ለማቅረብ የፀጥታ አካላት ያላሰለሰ ጥረት እያደረጉ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
ከግጭቱ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ አስር የሚደርሱ ግለሰቦች ቀደም ብሎ በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ተገቢውን ማጣራት እየተከናወነ እንደሚገኝ ቢሮው አስታውቋል፡፡
ግጭቱ በተፈጠረበት በጋምቤላ ከተማ ያለው ሰላም ወደ ነበረበት እየተመለሰ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን ህብረተሰቡ አካባቢውን ነቅቶ በመጠበቅ ከፀጥታ አካላት ጎን በመሆን አስፈላጊውን መረጃ እንዲሰጥም በቢሮው ሃላፊ ተጠይቋል፡፡

የወንጀል መናኸሪያ እየሆኑ ነው የሚል ቅሬታ የሚነሳባቸው ጅምር ህንፃዎች ላይ ልዩ ክትትል እያደረኩ ነው ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ
በከተማዋ በጅምር ያሉ ያላለቁ እና ግንባታቸው አልቆም ሰው ያልገባባቸው ህንጻዎች የወንጀል መናኸሪያ እየሆኑ ነው የሚል ቅሬታ እየተነሳ ይገኛል።
በእነዚህ ህንጻዎች ተሰባስበው ያለ ስራ የሚቀመጡ ወጣቶች እንዳሉ ነዋሪው ጥቆማ እየሰጠን ነው ፤ ጥበቃም ይደረግልን ብለው ጥያቄ እያቀረቡ ነው ሲሉ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አረጋግጠዋል።
በጥቆማው መሰረትም ፖሊስ በተለይ ሰው ያልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች እና ጅምር ህንጻዎች ላይ የተለየ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል ሲሉ ነግረውናል።
ህብረተሰቡም አካባቢውን በንቃት ከመጠበቅ ጎን ለጎን አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ሲያይ በአቅራቢያው ላለ የጸጥታ ሀይል እንዲያሳውቅም መልዕክት ተላልፏል።

የአሜሪካ ተራድኦ ደርጅት (USAID) መጋዘኖችን በአሸባሪው ህወሓት መዘረፋቸው ተገለጸ
አሸባሪው ህወሓት የአሜሪካ ተራድኦ ደርጅት መጋዘኖችን እንደዘረፈ በኢትዮጵያ የድርጅቱ ሚሽን ዳይሬክተር ሾን ጆንስ ተናገሩ፡፡
የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) የኢትዮጵያ ሚሽን ዳይሬክተር ሾን ጆንስ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ ህወሓት ሁኔታውን ያለአግባብ እየተጠቀመበት እንደሆነ እናምናለን ብለዋል፡፡
ከተረጂዎች ላይ እርዳታን በሃይል እየነጠቀ እንደሆነ ይሰማናል ያሉት ዳይሬከተሩ እርግጠኛ ሆነን መናገር የምንችለው ግን የአሸባሪው ህወሓት ቡድን አባላት ሰርገው በገቡባቸው አካባቢዎች ሁሉ ያሉትን የእርዳታ መጋዘኖቻችንን ዘርፈዋል፤ ይህ የምናውቀው ሀቅ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
አሁን በግልጽ የምናውቀው ነገር የህወሓት ወታደሮች በገቡባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ሁሉ የእርዳታ መጋዘኖችን ዘርፈዋል፣ መኪኖችን ሰርቀዋል በየመንደሮቹ ብዙ ውድመትን አድርሰዋልያሉት ዳይሬክተሩ ይህ ለተጎጂዎቹም ሆነ ለእኛ ለረጂዎቹ እጅግ አሳሳቢ ነው ብለዋል፡፡
የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) የኢትዮጵያ ሚሽን ዳይሬክተር ሾን ጆንስ ኢትዮጵያ ውስጥ የምንቀሳቀሰው ሀገሪቱ አሁን ችግር ላይ ስላለች አይደለም ብለዋል፡፡
ይልቁንም ኢትዮጵያ ዓለም ላይ ካሉ ምርጥ አጋሮቻችን መካከል አንዷ ነች ያሉት ዳይሬክተሩ ከኢትዮጵያ ጋር ስላለን አጋርነት በእጅጉ እንጨነቃለነ ነው ያሉት፡፡
አንዳንድ ጊዜ ህብረተሰቡ በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን የሚሰራጩትን ያልተረጋጋጡ ወሬዎች በመያዝ የኢትዮ አሜሪካ ግንኙነት እንደሻከረ ያስባሉ ያሉት ዳይሬክተሩ ነገር ግን እንደአሁኑ ከኢትዮጵያ ጋር ተባብረን የሰራንበት ጊዜ የለም ሲሉም ለኢብኮ ተናግረዋል፡፡

ቻይና ታዳጊዎች በጌሞች ላይ የሚያሳልፉትን ሰዓት ገደበች
ቻይና ታዳጊዎቿ በሳምንት ውስጥ በበይነ መረብ ጌሞች ላይ ማሳለፍ የሚችሉትን ጊዜ በሦስት ሰዓት ገደበች፡፡
ከአሁን በኋላ የሀገሪቱ ታዳጊዎች ጌሞችን መጫወት የሚችሉት አርብ እና የእረፍት ቀናት እንዲሁም በህዝባዊ በዓላት ወቅት ከምሽቱ 2 እስከ 3 ሰዓት ብቻ ይሆናል፡፡
ይህም ቀድሞ ወጥቶ ሲሰራበት ከቆየው ህፃናቱ በእያንዳንዱ ቀናት ለአንድ ሰዓት ተኩል እንዲሁም በህዝባዊ በዓላት ወቅት እስከ ሦስት ሰዓት ጌም በመጫወት እንዲያሳልፉ ይፈቅድ ከነበረው ሕግም ጠበቅ ያለ ነው፡፡
አዲሱ ሕግ በቻይና ያሉና በዓለም ዙርያም እውቅናን ያተረፉ አንዳንድ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን መነቅነቅ ጀምሯል፡፡
ለአብነት ውሳኔውን ተከትሎ ዝነኛው የጌም ኩባንያ ቴንሴንት የአክሲዎን ዋጋው በ0.6 በመቶ ሲወርድ የገበያ ዋጋውም ቀድሞ ጣርያ በነካበት ወቅት ከነበረው የ573 ቢሊዮን ዶላር አሁን ላይ ወደ 300 ቢሊዮን ዶላር አሽቆልቁሏል፡፡
ኔትኢዝ የተሰኘው ሌላኛው ኩባንያም እንዲሁ የአክሲዮን ዋጋው በ9 በመቶ ወርዷል፡፡
ሕጉ ቻይና ከጌም አንስቶ እስከ ክፍያ አገልግሎት የሚሰጡ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎቿ ተፅዕኖዋቸው ከሚገባው በላይ እንዳይሆን ለመቆጣጠር በማሰብ እየወሰደች ያለችው የቁጥጥር እርምጃ አካል ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ሀገሪቱ ላለፉት ዓመታት ከፍተኛ እድገት ሲያስመዘግቡ የቆዩትን የኤሌክትሮኒክ ንግድ እና በበይነ መረብ ትምህርት ሰጪ ኩባንያዎች ከፍትሀዊ ተወዳዳሪነት ጋር በተያያዘ አደብ ያስገዙልኛል ያለቻቸውን ደንቦች አውጥታ ነበር፡፡
በዚህም በበይነ መረብ አማካኝነት የሚሰጥ የተጨማሪ ሰዓት ወይም ቱቶሪያል ትምህርን በቅርቡ በማገድ በዘርፉ የተሰማሩትን ኩባንያዎችንም መና አስቀቀርታቸዋለች፡፡
ከሳምንታት በፊት ቴንሴንት እድሜያቸው ከ12 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት ጌሙን መጫወት እንዳይችሉና እንዲጫወቱ የሚፈቀደላቸውም በየቀኑ ከ1 ሰዓት በላይ በህዝባዊ በዓል ቀናት ደግሞ ከ2 ሰዓታት በላይ እንዳይጫወቱ መከልከሉን ቴክስፕሎር ዘግቧል፡፡
በዳዊት አስታጥቄ

ቅርሶች ከመፍረሳቸው በፊት እንዳንደርስ ያደረገን የመንግስት መስሪያ ቤቶች ምን ሊሰሩ እንደሆነ ቀድመን ባለማወቃችን ነው ሲል የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ገለፀ
የመንግስት መስሪያ ቤቶች ምን ሊሰሩ እንደሆነ ቀድመን አለማወቃችን ለቅርሶች እንዳንደርስ አድርጎናል ብሏል የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ በቅርሶች መፍረስ ብዙ ቅሬታዎች ተነስተዋል።
ከሰሞኑም የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽኑ የራስ ሀይሉ ተክለሀይማኖት መኖሪያ ቤት ፈርሷል በሚል የአዲስ አበባ ባህል ቱሪዝምና ኪነጥበብ ቢሮ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት እንደወሰደው ይታወቃል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ በበጀት አመቱ መጀመሪያ ላይ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ማን ምን ሊሰራ እንደሆነ ባለማወቃችን ለቅርሶች ልንደርስ አልቻልንም፣ የምናውቀው ማፍረስ ሲጀመር ነው ሲሉ የባለስልጣኑ የቅርስ ጥበቃና እንክብካቤ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ጌታቸው ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።
በተለያዩ የምክክር መድረኮች አብረውን ከሚሰሩ የመንግስት ቢሮዎች ጋር ለመገናኘት እንሞክራለን ያሉት ዳይሬክተሯ በእቅድ ዝርዝራቸው ላይ ቢያሳውቁን በጋራ ለመስራት እንችላለን ብለዋል።
በአዲስ አበባ ቅርሶች የያዙት ቦታ ያጓጓል ነገር ግን የከተማ ልማት ቅርሶችንም ታሳቢ ባደረገ መልኩ ሊሰራ ይገባል ሲሉም አጽኖት ሰጥተዋል።
በከተማዋ ያሉ ቅርሶች በእድሜ ብዛትና በግዴለሽነት ጉዳት እየደረሰባቸው እንደሆነ ተነግሯል።
የባለስልጣኑ የቅርስ ጥበቃና እንክብካቤ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ጌታቸው በአሁን ሰአት ያለው የአዲስ አበባ ነዋሪ የቅርስ አረዳድና አጠባበቅ የሚበረታታ ነው ያሉ ሲሆን አመራሩ ግን አውቆ ከማጥፋት ሊቆጠብ ይገባል ብለዋል።
አክለውም በዚሁ ከቀጠለ ከተማዋን ቅርስ አልባ ወደማድረግ እየሄድን ነው ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
መቅደላዊት ደረጄ
ነሐሴ 26 ቀን 2013 ዓ.ም

ሳፋሪኮም የሥራ እንቅስቃሴውን በተመለከተ ለመንግሥት ማብራሪያ ሰጠ
በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት ለመጀመር እንቅስቃሴ ላይ የሚገኘው ሳፋሪኮም፣ የሥራ እንቅስቃሴውን አስመልክቶ ለከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በዋና ሥራ አስፈጻሚው ፒተር ንዴግዋ የተማራው የሳፋሪኮም ልኡክ፣ ከገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሺዴ እና ሚኒስቴር ዲኤታው ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
በዚሁ በገንዘብ ሚኒስቴር ፍሬያማ በተባለው ውይይት ወቅት የሳፋሪኮም ኃላፊዎች ተቋማቸው በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እየሠራ የሚገኘውን እንዲሁም ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል ነው የተባለው፡፡
ከመንግስት የሥራ ኃላፊዎቹ መካከል የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሺዴ መንግስት በቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎቶች ጥራት እና ስርጭት ጋር ተያይዞ ለሳፋሪኮም ድጋፍ እንደሚደርግም መግለጻቸው ተመላክቷል፡፡
ሳፋሪኮም የሚመራውና አምስት ኩባንያዎች እና ተቋማትን ያካተተው ‹‹ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ›› የተሰኘው ጥምረት የሚያቋቁመው ኩባንያ፤ በኢትዮጵያ የቴሌኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት የማቅረብ ስራውን በጥር 2014 ለመጀመር እንዳቀደ ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡
ሳፋሪኮም ፣ ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ” የተሰኘው ጥምረት የኦፕሬሽን ፈቃድ የኦፕሬሽን ፈቃድ ለማግኘት 850 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ አቅርቦ ማሸነፉ ይታወቃል።

ፑቲን አሜሪካ በአፍጋኒስታን ያገኘችው ውጤት ‹ዜሮ› ነው ብለዋል
የአፍጋኒስታን የ 20 ዓመት ዘመቻ በአሳዛኝ ሁኔታ አብቅቷል እናም ዋሽንግተን ምንም አላገኘችም ሲሉ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተችተዋል፡፡
የአሜሪካ ጦር በአፍጋኒስታን ውስጥ የነበረው ቆይታ ከንቱ ነበር ሲሉ የሰላ ትችት ሰንዝረዋል።
ፕሬዝደንት ፑቲን ከወጣቶች ጋር ባደረጎት ስብሰባ ላይ እንደተናገሩት “የአሜሪካ ወታደሮች በአፍጋኒስታን ለ 20 ዓመታት ኖረዋል ፣ እና በእነዚህ 20 ዓመታት ውስጥ የአካባቢውን ህዝብ ሥልጣኔ ለማሳደግ ሳይሆን የኅብረተሰቡን የፖለቲካ አደረጃጀት ጨምሮ የራሳቸውን ፍላጎት ለመጫን ሞክረዋል ግን በእውነቱ አልተሳካላቸውም ማለታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
የትኛውንም ህብረተሰብ ላይ ቢሆን “ከውጭ ማንኛውንም ነገር መጫን አይቻልም” ነው ያሉት፡፡
የሩሲያው መሪ ምዕራባውያን አገሮችን እሴቶቻቸውን በምዕራባዊ ባልሆኑ ሀገሮች ላይ ለመጫን በመሞከራቸው ትልቅ ውድቀት ገጥሟዋል ሲሉ አጣጥለዋቸዋል፡፡
ያንን ለሚያደርጉት አሜሪካ እና በአፍጋኒስታን ለሚኖሩ ሰዎች የበለጠ ውጤቱ እጅግ አሳዛኝ ፣ ከባድ ኪሳራ፣ ድምር ውጤቱም ዜሮ ነው ”ብለዋል ፑቲን።

“በዓለም ዙሪያ 35 ሚሊዮን ሰዎች በረሃብ ይሞታሉ ወይም የመሞት አደጋ ተጋርጦባቸዋል” ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስጠነቀቀ
በዓለም አቀፍ ደረጃ 150 ሚሊዮን በምግብ እጥረት እየተሰቃዩ ሲሆን 16 ሚሊዮን የሚሆኑ ሕፃናት ደግሞ ለሞት ይጋለጣሉ ብሏል ድርጅቱ፡፡
አናዶሉ ኤጀንሲ የድርጅቱን ከፍተኛ ባለስልጣን ጠቅሶ እንደዘገበው ባለፈው ዓመት በ 55 ሀገሮች ወይም ክልሎች ውስጥ ቢያንስ 155 ሚሊዮን ሰዎች የምግብ ቀውስ ገጥሟቸዋል ፣ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ቁጥሩ አሁን ወደ 265 ሚሊዮን ከፍ ብሏል።
የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ፣ የኢኮኖሚ ድቀት ፣ የፖለቲካ አለመረጋጋት ፣ ወረርሽኞች እና ግጭቶች በዓለም ዙሪያ የሚጠበቀውን የምግብ ቀውስ ያባባሱ ምክንያቶች ሲሆን በአሁኑ ወቅት 821 ሚሊዮን ሰዎች ምግብ የማግኘት ችግር ገጥሟቸዋል ብለዋል።
ባለፉት 10 ዓመታት በተከሰተው የአየር ንብረት ለውጥ የደን ቃጠሎ እና ጎርፍ የበለጠ አውዳሚ እየሆነ መምጣቷን ጠቅሶ ፣ ይህ በሚቀጥሉት ዓመታት የምግብ ቀውስ ከሚያስከትሉ በጣም አስፈላጊ ነገሮች አንዱ መሆኑን አፅንዖት ተሰጥቶታል።
በአለም ውስጥ ምግብ የማግኘት ዕድል የሌላቸው ሰዎች ቁጥር ከ 700 ሚሊዮን ወደ 821 ሚሊዮን ማደጉን ነው የተነገረው ፣ “በጣም ከባድ እርምጃዎች ቢወሰዱም ባለፉት አምስት ዓመታት የምግብ ዋስትና የሌላቸው ሰዎች ቁጥር ቀስ በቀስ ጨምሯል” ብለዋል ባለስልጣኑ።
የተባበሩት መንግስታት ባለሙያ የአየር ንብረት ለውጥ እና የምግብ ቀውስ ዓለም አቀፍ ፖሊሲዎች የሚያስፈልጉ ዓለም አቀፍ ችግሮች ናቸው ብለዋል።
በአህጉራችን በአፍሪካ ውስጥ 98 ሚሊዮን ሰዎች አጣዳፊ የምግብ ችግር እንደሚገጥማቸው ድርጅቱ አስታውቋል፡፡
በ 2020 እጅግ አስከፊ የምግብ ቀውስ ካጋጠማቸው 10 አገሮች ውስጥ ደቡብ ሱዳን ፣ የመን ፣ ሶማሊያ ፣ አፍጋኒስታን ፣ ሶሪያ ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሄይቲ ይገኙበታል።