Ethio Fm 107.8
20.5K subscribers
7.8K photos
16 videos
4 files
2.31K links
በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!
Download Telegram
የዛሬ የመስከረም 22 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን
"አርሰናል ዘንድሮ ዋንጫ ያነሳል" - ሳካ

የአርሰናሉ አጥቂ ቡካዮ ሳካ መድፈኞቹ የፕሪምየር ሊግ ዋንጫውን በማንሳት የ21 ዓመታት ጥበቃቸውን የሚቋጩት "በዚህ ዓመት ነው" አለ።

የሚኬል አርቴታ ቡድን ባለፉት ሁለት የውድድር ዘመናት ከማንቸስተር ሲቲ በመቀጠል ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቅቋል።

አርሰናል በ2003-04 የውድድር ዘመን በአርሰን ቬንገር እየተመራ አንድም ጨዋታ ሳይሸነፍ ዋንጫ ካሸነፈ በኋላ ለፕሪምየር ሊግ የዋንጫ ክብር አልበቃም።

እንግሊዛዊው ከሲቢኤስ ስፖርት ጋር ባደረገው ቆይታ "በራሳችን ላይ አላስፈላጊ ጫና ማሳረፍ አልፈልግም። ሆኖም ዘንድሮ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ እንደምናሸንፍ አስባለሁ" ብሏል።

አቤል ጀቤሳ

መስከረም 22 ቀን 2017 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcasWebsite https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
የኢትዮጵያ ዲያስፖራዎች ሳምንት በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

የኢትዮጵያ ዲያስፖራዎች ሳምንት በገና በዓል ሰሞን በአዲስ አበባ ቀጥሎም በካናዳ ቶሮንቶ ሊካሄድ መሆኑ ተነግሯል።

የኢትዮጵያ ዲያስፖራዎች ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ቃላብ ግርማ በመላው አለም የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሃገራቸው እውቀታቸውን፣ጉልበታቸውንና ገንዘባቸውን ፈሰስ እንዲያደርጉ ታስቦ ነው ይህ መረሃ ግብር የተቀረፀው ብለዋል።

አቶ ቃላብ እንዲህ አይነት ክንውኖች በዲያስፖራዎች ዘንድ መነቃቃት እዲፈጠር ታልሞ ነው የተዘጋጀው፤በዲያስፖራው ሳምንት፤ የኤግዚቢሽን ሲንፖዚየም፣የእራት ግብዣና የዲያስፖራዎች ሩጫ መዘጋጀቱን ነግረውናል።

የኢትዮጵያ ዲያስፖራዎች ማህበር ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ደመቀ ነጋሳ በበኩላቸው በሌሎች ሀገራት ትላልቅ ስራዎችን የሰሩት ዲያስፖራዎች ናቸው ብሏል፡፡
በእኛም ሀገር ያሉ ዲያስፖራዎች ከፖለቲካ እንቅስቃሴ ወጥተው ለሀገር ልማት እንዲረባረቡ ለማድረግ ያስችላል ነዉ ያሉት፡፡

በመሆኑ አቶ ደመቀ በሃገራችን ከ 5 ሺህ በላይ በልማት ላይ ተሰማርቷል፡፡

አሁንም ሌሎች ወደሃገራቸው መጥተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ በእንቅስቃሴው ላይ እንቅፋት ሊሆኑበት በሚችለው የፖሊሲና የአሰራር ማነቆዎችን ለመፍታት እንዲሁም ከሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ የሚያገኝበትን ሂደት ለመፍጠር በመስራት ላይ እንገኛለን ብለዋል ።

ልዑል ወልዴ

መስከረም 22 ቀን 2017 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcasWebsite https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
በጅቡቲ የባህር ዳርቻ ሁለት ጀልባዎች በመስመጣቸው በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ሲሞቱ 61 ሰዎች ጠፍተዋል ተባለ፡፡

በጅቡቲ የባህር ዳርቻ ሁለት የስደተኛ ጀልባዎች ተገልብጠው ቢያንስ 45 ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ ብዙ ሰዎች ጠፍተዋል ሲሉ ባለስልጣናት ተናግረዋል።

ጀልባዎቹ ከመስመጣቸው በፊት 310 ሰዎችን አሳፍረው ከየመን መነሳታቸውን የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) አስታውቋል።

የጅቡቲ የባህር ጠረፍ ጠባቂ "እስካሁን ድረስ 61 ግለሰቦች የጠፉ ሲሆን የማፈላለጉ ስራም ያለ እረፍት ቀጥሏል" ብለዋል።

ከሰኞ ጀምሮ በአይኦኤም የተደገፈ ትልቅ ፍተሻ እየተካሄደ ሲሆን 115 በህይወት የተረፉ ሰዎችን ማዳኑን የጅቡቲ የባህር ጠረፍ ጠባቂ ገልፀዋል።

"የጠፉትን ለማግኘት እና የተረፉትን ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ ቁርጠኞች ነን" ብሏል ኤጀንሲው በመግለጫው።

ጀልባዎቹ የሰመጡት በጅቡቲ ሰሜናዊ ምዕራብ ሖር አንጋር ክልል አቅራቢያ ካለ የባህር ዳርቻ በ150 ሜትሮች (492 ጫማ) ርቀት ላይ መሆኑን የባህር ዳርቻ ጥበቃው ጨምረው መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በሐመረ ፍሬው

መስከረም 22 ቀን 2017 ዓ.ም
የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲው ተፈፃሚ በሆነባቸው ሁለት ወራት የተረጋጋ የውጭ ምንዛሪ ከባቢን መመልከት እንደተቻለ ጠ/ሚ ዐቢይ ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ ዛሬ ጠዋት ተሰብስቦ፤ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም አካል የሆነውንና በቅርብ የተደረገውን የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያዎች አፈፃፀም መገምገሙም ገልፀዋል።

ፖሊሲው ተፈፃሚ በሆነባቸው ሁለት ወራት የተረጋጋ የውጭ ምንዛሪ ከባቢን መመልከት መቻሉንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

“የገቢ ግባችንም የተቀመጠለትን ግብ በመምታት በታለመለት መንገድ ላይ ይገኛል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)።

ያለፉት ሁለት ወራት ፖሊሲው በስኬታማ አፈፃፀም ላይ መሆኑን እንዳሳየ ነው የገለጹት።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መስከረም 22 ቀን 2017 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcasWebsite https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
የነገ የመስከረም 23 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን
የ 2024 የአፍሪካ ሀገራት የቻን ማጣሪያ ጨዋታዎች ድልድል የሚካሄድበት ቀን ታውቋል።

የማጣሪያ ውድድሩ በሁለት ዙሮች በደርሶ መልስ መርሐ ግብር ኢንደሚካሄድ  ተገልጿል ።

በዚህም መሰረት የማጣሪያ ተጋጣሚዎች ቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ በግብፅ ካይሮ በሚደረግ የእጣ ማውጣት ስነስርዓት የሚለዩ ይሆናል።


ኢትዮጵያ በውድድሩ ለመሳተፍ በሁለተኛው ዙር ስትሳተፍ በደርሶ መልስ ካሸነፈች ማለፏን የምታረጋግጥ ይሆናል።

የዘንድሮው የቻን ውድድር በኬንያ ፣ ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ በጋራ ያዘጋጅቷል።

አዘጋጆቹ በቀጥታ ማለፋቸውን ተከትሎ ከሴካፋ ሀገራት አንድ ኮታ የሚጨመር ሲሆን የውድድሩ ተሳታፊ ሀገራት ከ 18 ወደ 19 ከፍ እንደሚደረጉ ታውቋል።

የመጀመሪያ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ ከጥቅምት 15-17 ባሉት ቀናት እንዲሁም የመልስ ጨዋታዎች ከጥቅምት 22-24/2017 ባሉት ቀናት ይደረጋል።

የሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ ከ ታህሳስ 11 - 13 እንዲሁም የመልስ ጨዋታዎች ከታህሳስ 18-20/2017 ባሉት ቀናት ይካሄዳል።

የ 2024 የቻን አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ከጥር 24 እስከ የካቲት 21/2017 ዓ.ም ይካሄዳል።

በጋዲሳ መገርሳ
የድምጽ ብክለት በሚያስከትሉ ተቋማት ላይ  እርምጃ መውሰድ መጀመሩን የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ባደረገዉ ድንገተኛ ኦፕሬሽን አብዛኞቹ ከተቀመጠዉ ስታንዳርድ በላይ ድምፅ እንደሚለቁ አረጋግጫለው ብሏል።

በቅርቡ የድምፅ ልኬት ከተደረገባቸዉ ተቋማት መካከል ባርና ሬስቶራንቶች፣ ግሮሰሪዎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ይገኙበታል ተብሏል።

አዲስ አመት ከገባም ወደ 4 በሚጠጉ ተቋማትን ላይ ቅጣት ለማስተላለፍ ዝግጅቱን እንደጨረሰ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ  አቶ ዲዳ ድሪባ  ነግረውናል።


  የድምፅ ልኬት ኦፕሬሽኑ በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች መከናወኑን ገልጸው በተለይ ከነዚህ ተቋማት ከምሽት 3:00 ሰዓት በኋላ የሚለቁት ከፍተኛ የሆነ ድምፅ በነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ችግር እየፈጠረ በመሆኑን አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እየወሰዱ እንደሚገኙም ነግረውናል።

የድምጽ ብክለቱን የፈጸሙ ተቋማት የሚቀጡበት መነገድን የነገሩን ሃለፊው የመጀመሪያው ለ12 ሰዓት የማሸግ ስራ እና የገንዘብ ቀጣት እንደሚጠብቃቸው አንስተው ከዛ በኋላ ግን ወደ ንግድ ፍቃድ ስረዛ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

ለአለም አሰፋ

መስከረም 23 ቀን 2017 ዓ.ም
የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች፦

• ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ላይ

• ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ

• ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ

• ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ አጠገብ እንዲሁም ለቀላል ተሽከርካሪ ጥላሁን አደባባይ (አራተኛ ክፍለ ጦር ላይ)

• ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለገሀር መብራት ላይ

• ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድዮም ለሚጓዙ ቴሌ ማቋረጫ

• ከራስ ሆቴል ወደ ስታድዮም ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ራስ ሆቴል ላይ

• ከሃራምቤ መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት ላይ

• ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ

• ከካዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስደው መንገድ ካዛንቺስ ሼል አጠገብ እንዲሁም

• ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA የሚወስደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ

ከመስከረም 24 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ ፖሊስ አስታውቋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መስከረም 23 ቀን 2017 ዓ.ም
የዛሬ የመስከረም 23 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን