Ethio Fm 107.8
20.3K subscribers
7.39K photos
16 videos
4 files
2.3K links
በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!
Download Telegram
ኢ-ፍትሃዊ ድርጊቶች እየተፈፀመብኝ ነው ሲል የደቡብ ክልል የቁጫ ወረዳ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት ተናገረ።

ምክርቤቱ በዛሬው እለት በሰጠው መግለጫ ሰኔ 14/2013 ዓ.ም በተደረገው ምርጫ የብልጽግናን እና የቁጫ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ጨምሮ ሰባት ፓርቲዎች መሳተፋቸውን አንስቷል።

ነገር ግን ገዢው ፓርቲ በደቡብ ክልል የሚገኘውን የቁጫ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ቁሕዴፓ) መዋቅሩ በወረዳው ተቀባይነት እንዳይኖረው ህዝብ በሰላም እንዳይኖር ኢፍትሃዊ የሆኑ ተግባረትን እያደረገ ነው ብሏል።

የገዢው ፓርቲ አባል ያልሆኑ ግለሰቦችን ማሰር፣ንብረት ማውደም፣ ነጋዴዎች የንግድ ፍቃዳቸው እንዳይታደስ እና የኗሪነት መታወቂያን መከልከል በርካታ እንግልቶች እየተረሰባቸው መሆኑን የቁጫ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እና የቁጫ ወረዳ የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት ተወካይ አቶ ገነነ ግደሞ ተናግረዋል።

ይህ ደግሞ ለረጅ አመታት በአብሮነት በኖረ የአከባቢ ማህበረሰብ መካከል የባህል ግጭቶች እንዲነሱ ምክንያት እየሆነ ነው ተብሏል።
ነገር ግን አሁንም በህዝቡ መካከል ግጭት እንዳይነሳ የቻልነውን ሁሉ እያደረግን ነው ሲል የጋራ ምክርቤቱ አሳውቋል።

በርካታ ወጣቶች ለሌላው የፖለቲካ ፓርቲ ድምጽ በመስጠታቸው ምክንያት ለድብደባ ፣ለእስር እና አከባቢውን ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል ነዉ ያለዉ የጋራ ምክር ቤቱ።
በዚህም ምክንያት 500 አባወራዎች መኖሪያቸው ለቀው ተሰደዋል ብሏል።
ጉዳዩ ተደጋግሞ ለምርጫ ቦርድ ቢቀርብም ከምርጫ ቦርድ የሚላኩ ባለሞያዎችን እራሱ እያሰረ፣ገዢው ብልፅግና ፓርቲ በወረዳው እንዳሻው እያደረገ ይገኛል ሲል ገዥዉ ፓርቲን ኮንኗል፡፡

በመሳይ ገ/መድህን
ሐምሌ 20 ቀን 2014 ዓ.ም
1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሰዎች በወባ በሽታ ተይዘዋል፡፡

በሀገራችን በዚህ አመት ብቻ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዜጎች በወባ በሽታ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

የጤና ሚኒስቴር ድኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ካለፈው አመት ከነበረው ቁጥር 10 በመቶ ጭማሪ በማሳየት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዜጎች በወባ መያዛቸውን ገልጸዋል።
በሀገራችን 75 በመቶ የሚሆነው መልክዓ ምድር ለወባ ትንኝ መራባት ምቹ መሆኑን ያነሱት ዶክተር ደረጄ፣ በእነዚህ ቦታዎችም 52 በመቶ የሚሆኑ ዜጎቻችንም ይኖራሉ ነዉ ያሉት፡፡

በእነዚህ ቦታዎች በአመት ሁለት ጊዜ ወባ እንደሚከሰት የገለፁት ሚኒስቴር ዲኤታው፣ በተለይ የዝናብ ወቅቶችን ተገን አድርጎ በጣም ብዙ ሰዎችን እንደሚጎዳም አንስተዋል።

በተለይም በኮንስትራክሽን ፣መስኖ እና ግብርና ስራዎች በሚበዙበት ቦታዎች ለወባ ትንኝ መራባት ምቹ ቦታዎች ናቸው ያሉት ዶክተር ደረጄ፣ ድርቅ የነበረባቸው ቦታዎች ፣መጠለያ ካምፖች እና የፀጥታ ችግር ያለባቸው ቦታዎችም ምቹ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡
በማህበረሰቡ ደረጃ ያለው አረዳድ እና የግንዛቤ ማነስ እንዲሁም ወባን እንደ ገዳይ በሽታ አለመመልከት ፣አጎበርን በአግባቡ አለመጠቀም ለበሽታው መስፋፋት ትልቅ ድርሻ አለው ነዉ ያሉት፡፡

በዚህም አማራ፣ደቡብ ፣ደቡብ ምዕራብ ፣ኦሮሚያ እና ሲዳማ ክልሎች በከፍተኛ ደረጃ በሽታው የተከሰተባቸው መሆናቸውን ገልጸዋል ።
5 ነጥብ 5 ሚሊየን መመርመሪያ ኪት ለሁሉም ጤና ተቋማት መሰጠቱን፣4.5 ሚሊዮን ፀረ ወባ መድሐኒት እና 3 ሚሊዮን የአልጋ አጎበር መከፋፈሉን እንዲሁም 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ቤቶች የፀረ ወባ ኬሚካል ርጭት መካሄዱንም ገልፀዋል።

በእስከዳር ግርማ
ሐምሌ 20 ቀን 2014 ዓ.ም

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

ዌብሳይት https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
#ዜና ችሎት

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኛ የነበረችውን ወጣት የገደሉ ሦስት ወንጀለኞች የ13 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈረደባቸዉ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ እንዳለዉ ግለሰቦቹ ከልዩ ልዩ ማህበራዊ መብቶቻቸው ለአምስት አመት እንዲሻሩም ተወስኖባቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኛ የነበረችው ወ/ሮ እፀገነት አንተነህ መስከረም 6 ቀን 2014 ዓ/ም በግምት 12 ሰዓት ተኩል ገደማ ወደ ስራ ለመሄድ ከሰፈሯ ተነስታ የመስሪያ ቤቷን ሰርቪስ እስከምታገኝበት ቦታ ለመጓዝ ትራንስፖርት በመጠበቅ ላይ እንዳለች በረከት ብርሃኑ ፣ ዮናስ ካሳ እና ዳግም ውብሸት የተባሉ ሦስት ግለሰቦች በሰሌዳ ቁጥር ኮድ1-34039 ኦ/ሮ ባጃጅ ካሳፈሯት እና አስገድደው ወደ ሰዋራ ስፍራ በመውሰድ ገንዘብና ልዩ ልዩ ንብረቷን ይሰርቃሉ፡፡

ከዛም በኋላ በመግደል አስከሬኗን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዮ ቦታው ሰላም ፍሬ ጤና ጣቢያ አካባቢ መንገድ ላይ ጥለው መሰወራቸውን የተከሳሾቹ የክስ መዝገብ ያስረዳል፡፡

በወቅቱ ወንጀሉን የፈፀሙትን ግለሰቦች ለማወቅ አስቸጋሪ የነበረ ቢሆንም የአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዘርፍ ባደረገው ክትትል ወንጀል ፈፃሚዎቹ ወንጀሉን በፈፀሙ በዘጠነኛው ቀን መስከረም 15 ቀን 2012 ዓ/ም በቁጥጥር በማዋል በማግስቱ የወንጀሉን አፈፃፀም መርተው እንዲያሳዩ መደረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡

የተከሳሾቹን ጉዳይ ሲመለከተት የቆየው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት ሐምሌ 14 ቀን 2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት በረከት ብርሃኑ ፣ ዮናስ ካሳ እና ዳግም ውብሸት እያንዳንዳቸው በ13 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ ማስተላለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም በወንጀል ህግ አንቀፅ 123 መሰረት ከህዝባዊ መብቶቻቸው በተለይ በምርጫ ላይ ተካፋይ ከመሆን ፣ ለህዝብ አገልግሎት ስራ ከመመረጥ ፣ በሰነድ ወይም የውል ስምምነት ላይ ምስክር ከመሆን ፣ በቤተ ዘመድ ካለው መብት በተለይም የወላጅነት ስልጣን ከመያዝ ችሎታ ፣ ከሞግዚትነት እና የንግድ ፈቃድ የሚያስፈልገውን የሙያ ፣ የኢንዱስትሪ ወይም የንግድ ስራ ከመስራት መብታቸው ለአምስት ዓመት እንዲሻሩ ፍርድ ቤቱ ወስኗል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 20 ቀን 2014 ዓ.ም

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

ዌብሳይት https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ምዕራባውያን የፍትህ ተቆርቋሪነት ስብዕና የላቸውም አሉ።

የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ መግላጫ እየሰጡ ነው።

በመግለጫው ምዕራባውያኑ በተለይም አሜሪካ የፍትህ ተቆርቋሪ ለመምሰል የምታደርገው አካሄድ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።

ምዕራባውያኑ ሶሪያን፣ ኢራቅንና ሊቢያን የመሳሰሉ አገራትን አውድመው ዛሬ ላይ ለዩክሬን ተቆርቋሪ ነን የማለት ስብዕና ሊኖራቸው አይችልም ነው ያሉት።

ለዩክሬን ጦርነት መቀስቀስ የምዕራባውያን እጅ እንዳለበትም ሰርጌ ላቭሮቭ አስታውቀዋል ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን የተሳሳተ መረጃን እያሰራጩ የአለም አቀፉን ማህበረሰብ እያወዘገቡ ነው ሲሉ ወቅሰዋል።

የዩክሬኑ ጦርነትን ተከትሎ የአለም የምግብ ዋጋ መናሩን ያነሱት ላቭሮቭ ለዚህም ምዕራባውያኑን ተጠያቂ አድርገዋል።

ሩሲያ ዩክሬን ላይ የጀመረችው ልዩ ኦፕሬሽን ለችግሩ እንደ አንድ ምክንያት ቢጠቀሰም እያባባሱት ያሉት ግን እነ አሜሪካ ናቸው ብለዋል።

ላቭሮቭ ለዚህ እንደምክንያት ያነሱት ደግሞ ምዕራባውያን ለዩክሬን እያደረጉት ያለውን ወታደራዊ ድጋፍ ነው።

የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት በትናትናው ዕለት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል ።

በዛሬው ዕለት ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር በሩሲያ ኢምባሲ ችግኝ ተክለዋል።

በኡኑ ሰዓት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለዲፕለማሲ ማህበረሰብና ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ እየሰጡ ሲሆን ኢትዮ ኤፍ ኤምም መግለጫውን ተከታትሎ ተጨማሪ መረጃዎችን ወደ እናንተ የሚያደርስ ይሆናል።

በአባቱ መረቀ
ሐምሌ 20 ቀን 2014 ዓ.ም
#UPDATE

የሩሲያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በኢትዮጵያ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ለሚኒስትሩ ሽኝት አድርገዉላቸዋል፡፡


የሩሲያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በጥዋቱ መርሃ-ግብራቸዉ ምዕራባውያኑ በተለይም አሜሪካ የፍትህ ተቆርቋሪ ለመምሰል የምታደርገው አካሄድ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።

ምዕራባውያኑ ሶሪያን፣ ኢራቅንና ሊቢያን የመሳሰሉ አገራትን አውድመው ዛሬ ላይ ለዩክሬን ተቆርቋሪ ነን የማለት ስብዕና ሊኖራቸው አይችልም ሲሉም ተደምጠዋል።

ለዩክሬን ጦርነት መቀስቀስ የምዕራባውያን እጅ እንዳለበትም ሰርጌ ላቭሮቭ ተናግረዋል።


በአባቱ መረቀ
ሐምሌ 20 ቀን 2014 ዓ.ም
“ቅዱስነታቸው ቤተ ክርስቲያን ይወክላሉ”!


ቅዱስነታቸው ቤተ ክርስቲያን ይወክላሉ። እሳቸው ባሉበት ኹሉ ቤተ ክርስቲያን አለች። እሳቸውን የሚናገር እየተደፋፈረ ያለው ቤተ ክርስቲያንን ነው።"

የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም መግለጫ ሰጥተዋል።

ሐዋ. ፳፫፥፭ "በሕዝብህ አለቃ ላይ ክፉ ቃል አትናገር" የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል መነሻ በማድረግ መግለጫውን የጀመሩት ብፁዕ አቡነ አብርሃም በአንድ ቅዱስ ፓትርያርክ ላይ በጥራዝ ነጠቅነት የተሳሳተ መረጃ መስጠት ትክክል አለመሆኑን በመጥቀስ ቅዱስነታቸው ቤተ ክርስቲያን ይወክላሉ።

እሳቸው ባሉበት ኹሉ ቤተ ክርስቲያን አለች። እሳቸውን የሚናገር እየተደፋፈረ ያለው ቤተ ክርስቲያንን ነው። በዚህም ቤተ ክርስቲያን ታዝናለች" ብለዋል።

በሀገር ውስጥና በውጭ ላለችው ቤተ ክርስቲያን አባት የሆኑ አባትን በዚህ መንገድ መናገር ሉዓላዊ የሆነች የኢ/ኦ/ቤ/ክንን እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምእመናንን መድፈር ነው ያሉት ብፁዕነታቸው
ቤተ ክርስቲያንን በመከፋፈል ትርፍ ማግኘት አይቻልም ሲሉ አብራርተዋል።

ብፁዕነታቸው አክለውም ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናትን በውጪ ሀገር መትከል ከጀመረች ጀምሮ ጽላት በአሠራሯ መሠረት ትልካለች።

የታሪካዊ ቅርሶች ባለቤት እና ልጆቿ በረሃብ እየተገረፉ የጠበቁትን ሁኖ ሳለ ቤተ ክርስቲያን ቅርስ ታሸሻለች ብሎ ማሰብ ንስሐ ያስገባል።

ይህ የቅዱስነታቸውን ሳይሆን የቤተ ክርስቲያንን ክብር መንካት ነው ብለዋል።
መንግሥት ለምን ብሎ መጠየቅ እና መመርመሩ ተገቢ ነው።

ነገር ግን ቅርጽና ቅርስ መለየት ያስፈልጋል። በቀጣይም በጉዳዮ ላይ ግልፅነት ለመፍጠር ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ጋር በቀጣይ እንወያያለን በማለት በመግለጫቸው ጠቅሰዋል።


ምንጭ:-ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሐምሌ 20 ቀን 2014 ዓ.ም
በዓለም የአትሌቲክስ ሻምፒዮናው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን አዲስ አበባ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።
#አስተባብለዋል!

የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሐመድ ከቀናት በፊት ከግብጹ አቻቸው አል ሲሲ ጋር በካይሮ በሰጡት የጋራ መግለጫ በሕዳሴ ግድብ ግንባታና ውሃ ሙሌት ላይ ኦፊሴላዊ የጋራ አቋም አልያዙም ሲሉ የፕሬዝዳንቱ ቃል አቀባይ አብዱልከሪም ዓሊ ካት ለቢቢሲ ሱማሌኛ በሰጡት ቃል አስተባብለዋል።

ቃል አቀባዩ ሱማሊያ በግድቡ ላይ ስላላት አቋም ፕሬዝዳንት ሞሐመድ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ጨርሶ አላነሱም ብለዋል።

አል ሲሲ በኢትዮጵያ የተናጥል የግድብ ውሃ ሙሌት አደገኛነት ዙሪያ ከሞሐመድ ጋር መነጋገራቸውን በወቅቱ ስለመናገራቸው የግብጽ ዜና ምንጮች ዘግበው ነበር።

ቢቢሲ እንደዘገበው
የሐምሌ 21 ቀን 2014 ዓ.ም የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችን ከያዛቸው ጉዳዮች መካከል፦


በዛሬው የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችን ( ከ12:30-2:30)


-ከቤት ሳንወጣና ስፖርታዊ ጉዳዮችን ትሰማላችሁ

- በመንገዳችን ላይ፦ በመዲናችን አዲስ አበባ በየአካባቢው ያሉ ቆሻሻን ሰብስቦ በማስወገድ ስራ ላይ የተሰማሩ ማህበራት በነዋሪዎች ላይ ቅሬታ እያሰሙ ነው፤ አነጋግረናቸዋል።


- ለጤናችን፦ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ 325 ሚሊዮን ሰዎች ከጉበት በሽታ ጋር ይኖራሉ፡፡

በበሽታዉ ኢንፌክሽን ምክንያትም በዓመት ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ህይወታቸዉን ያጣሉ፤ብዙዎች ዝምተኛዉ ገዳይ ሲሉ የሚጠሩት ይህ የጉበት በሽታ ዛሬ በአለም አቀፍ ደረጃ ታስቦ ይውላል፤ በጤና መሰናዷችን እንመለከተዋለን።


- በፍተሻ ሰዓታችን፦ ሩሲያ የኢትዮጵያ ወሳኝ አጋር እንደምትሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ተናግረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አዲስ አበባ ላይ በሰጡት መግለጫ ምዕራባውያን የፍትህ ተቆርቋሪ ሊሆኑ አይችሉም ሲሉም ተደምጠዋል፤ ለምን?

በፍተሻችን ተመልክተነዋል።


-በኢትዮ ገበያችን ፦ ከጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ከ180 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፤

የሲሚንቶ ግብይትና ሥርጭት መመሪያን በማይተገብሩ አካላት ላይ ደግሞ እርምጃ ይወሰዳል ተብሏል፤
ከኢትዮ ገቢያችን ትሰሙታላችሁ።


-በዓለም ጉዳይ፦ አንድ ጉምቱ ዲፕሎማቷን ወደ ታይዋን ልትልክ የነበረችው አሜሪካ የቻይና ቁጣን ተከትሎ በድጋሚ አስብበታለሁ ብላለች።

ሁለቱ ሀገራት ዳግም መወዛገብ ጀምረዋል።

የእለቱ የዓለም አቀፍ ትንታኔያችን ትኩረት አድርጎበታል።


- እንዲሁም ሌሎች አዳድስ የሀገር ውስጥና ዓለምዓቀፋዊ ጉዳዮችንም አሰናድተንላችኋል።

የእለቱን ኢትዮ ማለዳ የምታቀርብላችሁ ያይኔአበባ ሻምበል ናት።

እንድታደምጡ ተጋብዛችኋል።


ለአስተያየትዎ '6321' አጭር የጽሁፍ መልዕክት

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን


Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

ዌብሳይት https://ethiofm107.com/
#ኮርተንባችኋል!


የአትሌቲክስ ልዑካን ቡድኑ ባረፈበት ስካይ ላይት ሆቴል በማርሽ ባንድ የታጀበ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡

በአቀባበሉ ላይ የልዑካን ቡድኑ ቤተሰቦች ፣ክለቦችና ፌደሬሽኖች የአበባ ባረፈበት ስካይ ላይት ሆቴል የአበባ ጉንጉን አበርክተዉለታል፡፡


ቡድኑ ካረፈበት ስካይላይት ሆቴል ተነስቶ ወደ መስቀል አደባባይ አቅንቷል፡፡
አትሌቶቻችን ባስመዘገቡት ታላቅ ድል ኢትዮጵያ ስሟ በዓለም አደባባይ ከፍ ብሎ እንዲጠራ አድርገዋል፡፡


ለዚህም ከፍ ያለ ክብር እንሰጣቸዋለን!

ሁላችንም እንኳን ደስ አለን!

ኮርተንባችኋል!



ፎቶ--ኢፕድ