በወረኢሉ ከተማ የግብርና ምርምር ማዕከል ሊገነባ ነዉ፡፡
የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስትቲዩት በ500 ሚሊየን ብር 23ኛውን የግብርና ምርምር ማዕከል በአማራ ክልል ወረኢሉ ከተማ ለመገንባት በዛሬዉ እለት የመሰረት ድንጋይ አስቀምጧል፡፡
የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን እንደገለጹት የማዕከሉን ግንባታ በማዘመን የተሞክሮ ማዕከል እንዲሆን ይሠራል፡፡
የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስትቲዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ችሎት ይርጋ የግብርና ልማቱን ለማፋጠን የሚያስፈልጉ ቴክኖሎጂዎችን ለመፍጠር እና ለማላመድ የምርምር ማዕከላት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
እንደ አሚኮ ዘገባ ግንባታው ፍጥነት እና ጥራትን መሰረት አድርጎ በአምስት ዓመት ውስጥ እንደሚጠናቀቅም አመላክተዋል፡፡
በአማራ ክልል በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ ወይዘሮ አይናለም ንጉሴ ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ለሚደረገው ሽግግር የምርምር ማዕከሉ ግንባታ ወሳኝ መሆኑን አብራርተዋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ግንቦት 09 ቀን 2014 ዓ.ም

ፖፕ ፍራንሲስ እና የስጦታ መኪናቸዉ፡-
የዓለም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ የወቅቱ የዓለማችን ዉድ መኪና ላምቦርጊኒ በስጦታ ተበርክቶላቸዉ ነበር፡፡
መኪናዋ እጅግ ዉድ ከመሆኗ ባሻገር ጥይት የማይበሳት መሆኗ ተነግሯል፡፡
ፖፑ ግን ይህ ሁሉ ለእኔ አያስፈልገኝም በማለት በስጦታ የቀረበላቸዉን መኪና አልጠቀምም ብለው ለሰብአዊ እርዳታ እንዲዉል መኪናውን መሸጣቸው ተነግሯል፡፡
በመጀመሪያ ፖፕ ፍራንሲስ መኪናውን በአክብሮት ከተቀበሉ፣ በኃላ አገላብጠው አዩና ፈገግ አሉ፤ አመሰገኑም፤ ፊርማቸውንም አኖሩ።
በስጦታ መልዕክ የተሰጣቸው ይህንን ላምቦርጊኒ መኪና በ3 ሚሊዬን ዶላር ሸጠው ሁሉንም ገንዘብ በአፍሪካ ለሚገኙ ህጻናት ማሳደጊያ ማዕከላት እርዳታ አድርገዋል፡፡
እንደእኔ ላለ ሐጥያተኛ እና ቀላል ሰው ይህ የተጋነነና የበዛ ቅንጦት ነው፤ ነገር ግን ገንዘቡ ለብዙ ህጻናት ነፍስ መዳኛ እና ህልማቸውን ማሳኪያ ይሆናል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ምንጭ፡-ቫቲካን ኒውስ
በሔኖክ ወ/ገብርኤል

የመንግስት መስሪያ ቤቶች በየአመቱ ለማስታወቂያ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ያደርጋሉ ተባለ፡፡
ሁሉም የመንግስት መስሪያ ቤቶች መስሪያ ቤታቸውን እና ስራቸውን ለማስተዋወቅ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚያደርጉ ተነግሯል ፡፡
የመንግስት መስሪያ ቤት ሆነው ይህን ያህል መጠን ያለው ገንዘብ ማውጣታቸውም ተገቢነት እንደሌለው ነው የኢትዮጵያ ሚዲያ ካውንስል የተናገረው፡፡
የካውንስሉ ምክትል ጸሀፊ አቶ አማረ አረጋዊ እንደተናገረው የመንግስት መስሪያ ቤቶች ይህንን ገንዘብ ማውጣታቸው ሳይሆን የሚያስገርመው ማስታወቂያቸውን የሚያስነግሩት በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ብቻ ነው ብለዋል፡፡
ይህ በመሆኑም የፍትሀዊነት ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ ገብቷል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የግል ወይም የንግድ መገናኛ ብዙሀን በፋይናንስ እጦት ከፍተኛ ችግር ውስጥ መሆናቸውም ነው የተጠቆመው፡፡
በመሆኑም የሚመለከተው የመንግስት አካል ማስታወቂያ የሚያስነግሩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ፍትሀዊ አሰራር መከተል አለባቸው ተብሏል፡፡
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከፍተኛ የገቢ ማሽቆልቆል ያጋጠማቸው የንግድ ወይም የግል ሚዲያ ተቋማትን ለመደገፍ መንግስት ውጤታማ አሰራር ሊከተል እንደሚገባም ተነግሯል ።
በሄኖክ ወ/ገብርኤል
ግንቦት 10 ቀን 2014 ዓ.ም

የፌደራል መሬት ባንክ እና ልማት ኮርፖሬሽን ኢንቨስት ማድረግ ለሚፈልጉ ባለሃብቶች አዲስ እቅድ ማምጣቱን ገለፀ።
የፌደራል መሬት ባንክ እና ልማት ኮርፖሬሽን ኢንቨስት ማድረግ ለሚፈልጉ ባለሃብቶች አዲስ እቅድ ማምጣቱን የኮሚሽኑ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሌንሳ መኮንን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
እርሳቸው እንዳሉት ለባለሃብቱ የታቀደው እቅድን በተመለከተ፣ ኮሚሽኑ ምን ያክል ይዞታ አለው፣ ለየትኛው ኢንቨቨስትመንት ይሆናል የሚለውን በቅድሚያ አጣርቷል ብለውናል፡፡
በተያያዘም ገበያ ወደ ኢትዮጲያ እንዴት እንሳብ የሚለውን ላይም እየሰራን እንገኛለን ነው ያሉት ፡፡
የታሰበው አዲስ እቅድ አለም አቀፋዊ የሆነ፣ በኢትዮጲያ ላይ የሚደረግ ከውጭ ኢንቨስትመንት ማድረግ የሚችሉ ኢነቨስተሮችን እንዲመጡ የሚጋብዝ መሆኑን ወ/ሮ ሌንሳ መኮንን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ኢንቨስት ለማድረግ ምቹ ሁኔታ የለም እየተባ የሚነሳውን ሃሳብ በተመለከተ ወና ዳይሬክተሯ ሲመልሱ ምቹ ሁኔታ እንኳ ባይኖር ይህ ሁኔታን ተቀብሎ ኢንቨስት ለማድግ ፈቅዶ የሚመጣን ለመቀበል እና ለማበረታታት እገዛም ለማድረግ ነው እየሰራን ያለነው ብለውናል፡፡
ለኢንቨስመንቱ ቅድሚያ የሚሰጠው በሚል የተለዩ ዘርፎችም የቤት ልማት ፣ ጤና እና የህክምና ተቋማት መገንባት ፣ ትምህርት ፣ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እንዲሁም ግብርና መሆናቸውን ተናግረዋል ፡፡
አቅምና ፈጠራን የሚያሳይ ፕሮፖዛል እንደሚቀበሉ የተናገሩ ሲሆን ፤ በፋይናንሱ ደግሞ ምን ያክል ያስወጣል የሚለውን ዝርዝር ፕሮፖዛል እንዲያመጡ እንጠብቃለንም ብለዋል።
በረድኤት ገበየሁ

በቤንች ሸኮ ዞን ኩጃ ቀበሌ ከፍተኛ የጸጥታ ስጋት መኖሩ ተነገረ፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወደህ በኩጃ ቀበሌና ከተማ አካባቢ ግድያ ፣ የእንስሳትና የጦር መሳሪያ ዝርፊያ እየተፈጸመ መሆኑን የዞኑ ነዋሪዎች ተናግረዋል ፡፡
ነዋሪዎቹ እንዳሉት ለወረዳው የጸጥታ መዋቅር በወቅቱ ብናሳውቅም በፍጥነት ያለመድረስ ሁኔታዎች ይታያሉ ብለዋል፡፡
የዞኑ መንግስትም በዞንና በወረዳ የሚገኙ አመራሮች ላይ ጥብቅ ፍተሻና ክትትል ሊያደረግ እንደሚገባም አንስተዋል፡፡
ይህም በነዋሪውና አመራሩ መካከል ከፍተኛ ጥርጣሬና አለመተማመንን ፈጥሮ ቆይቷል ብለዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም የዞኑም ሆነ የወረዳው አመራር የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ያለምንም ልዩነት ማስጠበቅ ተቀዳሚ ተግባራቸው አድርገው ሊሰሩ ይገባል ሲሉ ነው የተናገሩት።
የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀበሌ መንገሻ ለኢትዮ ኤፍኤም እንደተናገሩት በአካባቢው ለተፈጠሩ የጸጥታ ችግሮች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የአመራሩ እጅና ተሳትፎ አለበት ሲሉ ተናግረዋል ፡፡
እንደ ዞን ከአመራሩ ጋር በተደረገ ግምገማዎችና የጸጥታ መዋቅሩ ተቀናጅቶ መስራት ከጀመረ በኋላ በዞኑ አንጻራዊ ሰላም መምጣቱን ገልጸው ሰላሙን ዘላቂ ለማድረግ የህብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ነው አስተዳዳሪው የተናገሩት፡፡
አሁን ላይ ጫካ ከገቡ ሽፍቶች በላይ በከተማ የጦር መሳሪያ አቀባዮች ፣ ቀለብ ሰፋሪዎችና ሎጂስቲክ አመቻቾች ችግር እየፈጠሩ መሆኑን ገልጸው ህብረተሰቡ እነዚህን አካላት ለመንግሰት አሳልፎ ሊሰጥ ይገባል ብለዋል፡፡
በጦር መሳሪያ መብዛት ሰላም አይረጋገጥም ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ሰላም ወንድማማችነትና እህትማማችነትን በማጠናከር ፣ ጥርጣሬና አለመተማመንን በማስወገድና ወንጀለኞችን አሳልፈን ስንሰጥ ብቻ ነው ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ዶክተር ካሳ እንደተናገሩት የኩጃ ቀበሌ ነዋሪዎች በቅድሚያ በጉያቸው የያዟቸውን ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎችና ለሽፍቶች ስንቅ አቀባዮችን ለህግ አሳልፈው ሊሰጡ ይገባል ብለዋል።
ለአብነት በቅርቡ ከወረዳው ከተዘረፉ 7 የጦር መሳሪያዎች 6ቱ ኩጃ ከተማ ላይ የተሸጡ መሆናቸውን ፖሊስ አረጋግጧል ብለዋል፡፡
ይህ እያለ ቀበሌዋም ሆነ ወረዳው ሰላም ሊሆን አይችልም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ኔቶ ከሩስያ ድንበር 60 ኪሎ ሜትሮችን በሚርቀው የኢስቶኒያ ግዛት ውስጥ ወታደራዊ ልምምድ ማድረግ ጀምሯል::
ጉዳዩን በተመለከተ ከሩስያ ጋር የሚያያዝ አይደለም ብሏል ኔቶ::
ኢስቶኒያ የምታስተናግደው ይህ ወታደራዊ ልምምድ በምድር የባህር ፣ አየር እና የሳይበር ተከላካይ ወታደሮችን ጭምር ያካተተ ነው ተብሏል፡፡
ልምምዱ ከ15ሺህ በላይ ወታደሮችን ከ 14 በላይ የኔቶ እና ከኔቶ ውጭ የሆኑ ሃገራትን ፊንላንድን እና ስዊድንን ጭምር ያቀፈ ነው፡፡
ይህኛው ልምምድ ሩስያ በዩክሬን እያካሄደች ካለችው ወታደራዊ ዘመቻ ጋር የሚያያይዘው ነገር እንደሌለም እወቁልኝ ብሏል ኔቶ፡፡
ከ20 በላይ ሃገራት እና ከ30 ሺህ በላይ ወታደሮች የተሳተፉበት ኔቶ ያሰናዳው ስልጠና ከዚህ ቀደም መካሄዱን ቢቢሲ በዘገባዉ አስታዉሷል፡፡
በአብዱሰላም አንሳር

ፔንታጎን ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የጦር መሳሪያ ሙከራ አደረገ::
የአሜሪካ መከላከያ መስሪያ ቤት እንዳስታወቀው፣ የተሳካ ያለውን የሃይፐር-ሶኒክ ሚሳኤል ሙከራ ማድረጉን ይፋ ሲያደርግ በተደጋጋሚ ከሽፎበት እንደነበርም አልሸሸገም፡፡
ከድምፅ በ5 እጥፍ ፍጥነት መምዘግዘግ ይችላል የተባለለት ይህ መሳሪያ፣ ኢላማውን ከ3 ተደጋጋሚ መክሸፍ በኋላ በ4ኛዉ ማሳካቱን አስታውቋል፡፡
በካሊፎርኒያ ግዛት እንደተሞከረ የተገለጸዉ ይህ መሳሪያ በተለያዩ ወታደራዊ የስራ ሃላፊዎች ትልቅ ስኬት ተደርጎ መቆጠሩን የሲ ኤን ኤን ዘገባ አመልክቷል፡፡

ቶጎ ከሁለት አመታት በኋላ ድንበሯን ከፍታለች።
ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ቶጎ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ይረዳ ዘንድ ከሁለት አመት በፊት ድንበሮቿን ከዘጋች በኋላ በትናንትናው ዕለት ድንበሯን እንደምትከፍት ተናግራለች።
ሀገሪቱ በዚህ ወር 32 የኮቪድ ታማሚዎችን ብቻ የመዘገበች ሲሆን፥ የሞተ ሰውም የለም።
“የ COVID-19 ጉዳዮች መቀዛቀዝን ከግምት ውስጥ በማስገባት ሁሉም ድንበሮቻችን ይከፈታሉ” ሲል የቶጎ መንግስት በሰጠው መግለጫ ተናግሯል።
መንገደኞች የክትባት ማረጋገጫ እስካቀረቡ ድረስ ነፃ እንቅስቃሴ ሊቀጥል ይችላል ሲልም አክሏል።
የቶጎ ጎረቤቶች በሰሜን ቡርኪናፋሶ፣ በምዕራብ ጋና እና በምስራቅ ቤኒን ናቸው። በዚህም ባለሥልጣናቱ የመከላከያ እርምጃዎችን ማክበር መቀጥል አለብን ብለዋል ።
ባለፈው አመት መጋቢት ወር የጀመረው የክትባት ዘመቻም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መንግስት አስታውቋል።
በኤፕሪል መጨረሻ 32 በመቶ የሚሆኑት የሀገሪቱ ጎልማሶች ሙሉ በሙሉ መከተባቸው ታውቋል። የኮቪድ-19 ጉዳዮች በቁጥር እያሽቆለቆሉ በመምጣታቸው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች በቅርብ ወራት ውስጥ ርምጃዎች እንዲላሉ እየጠየቁ ነበር።
የቶጎ የመሬት እና የአየር ድንበሮች እ.ኤ.አ. በማርች 2020 የተዘጉ ቢሆንም የአየር ድንበሮች በዚያው አመት ነሐሴ ላይ እንደገና ተከፍተዋል። የባህር ድንበሮች ግን በጭራሽ አልተዘጉም።
ባለፈው ነሀሴ ወር አንዳንድ ወጣቶች ድንበሮች እንዲከፈቱ እና ንግድ እንዲቀጥል በመጠየቅ ከጋና ጋር በሚያዋስናቸው ድንበር ላይ ተቃውሞ አሰምተዋል።
ወረርሽኙ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ቶጎ 37,023 የኮቪድ ታማሚዎችን መዝግቧል ፣ ከእነዚህ ውስጥ 273 ሰዎች ለሞት መዳረጋቸው የኤ ኤፍ ፒ ዘገባ ያመለክታል፡፡
በእስከዳር ግርማ

‹‹እኛ ለትግራይ ህዝብ ለመድረስ የምዕራባዊያን ቡራኬም፣ አስገዳጅነትም፣ ጫናም ያስፈልገናል የሚል ዕምነት የለኝም የትግራይ ህዝብ የኢትዮጵያ አካል ነዉ ህዝባችን ነዉ›› አቶ ክርስቲያን ታደለ
የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ የተለያዩ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ስለ ሰብዓዊ እርዳታ በተለያየ ግዜ የሀገራችንን መልካም ገጽታ በሚያጎድፍ ሁኔታ ሲያነሱ ይታያል፤ ነገር ግን እኛ ለትግራይ ህዝብ ለመድረስ የምዕራባዊያን ቡራኬም፣ አስገዳጅነትም፣ ጫናም ያስፈልገናል የሚል ዕምነት የለኝም የትግራይ ህዝብ የኢትዮጵያ አካል ነዉ ህዝባችን ነዉ ሲሉ ለዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሰብዓዊ እርዳታ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡
መንግስት መሰረታዊ በሆነ መንገድ ለትግራይ ህዝብም ሆነ አሸባሪዉ ህወሃት ላፈናቀላቸዉ የአፋር እና የአማራ ወገኖቻችን ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ እንዳያደርስ ዋነኛ ማነቆ የሆነበት ምንድነዉ? ሲሉ ጥያቄያቸዉን ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር እና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደመቀ መኮንን ያቀረቡት አቶ ክርስቲያን ታደለ ፤
‹‹ከተለምዷዊ የፖለቲካ ጫና ማሳደር ነዉ›› ከሚለዉ በዘለለ መንገድ መነሻዉ ምንድነዉ የሚለዉን ግለጽ የሆነ ማብራሪያ እንዲሰጠን እንፈልጋለን ሲሉም አክለዋል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በሰጡት ምላሽም ፤የገባዉ ተሽከርካሪ እንዳይወጣ እየተደረገ ፣ለማድረስም የደህንነት ችግሮች እየተነሱ ከአቅም በላይ የሆኑ ጥያቄዎች ሲያስተጓጉሉን ቆይተዋል ፤ነገር ግን በዚህ ሁኔታ ዉስጥ እንኳን ትግራይ ላሉ ተጎጂ ቤተሰቦች ዕርዳታ የማድረስ ሃላፊነት እና ግዴታ እንዳለብን እናዉቃለን ሲሉም ገልጸዋል፡፡
በቅድሚያ በመንግስት በኩል የተናጠል የተኩስ አቁም ስምምነት የተደረገዉ ለሰብዓዊ ድጋፍ ሁኔታዎችንን ለማመቻቸት መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ ይህ በተደረገ በሳምንታት ጊዜ ዉስጥ ግን ወደ አፋር እና አማራ ክልሎች ወረራ መካሄዱን አንስተዋል፡፡
‹‹ይህ ወረራ በተካሄደበት ሁኔታ፣ በየትኛዉም መልክ ወደ እዛ እርዳታ ለማስገባት ከአቅም በላይ ነዉ፤ በአየር መሰረታዊ የሚባሉ የመድሀኒት እና ቅድሚያ የሚሰጣቸዉ ጉዳዮችን ግን ለማድረስ ሞክረናል›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት ከ1200 በላይ የዕርዳታ አቅርቦት የጫኑ መኪኖች ወደ መቀሌ ቢገቡም፣ እዛዉ መቅረታቸዉን አንስተዋል፡፡ ይህ ደግሞ የሰብዓዊ ዕርዳታዉን ማሰናከል ነዉ ያሉ ሲሆን፣ መኪኖቹ ከመቅረታቸዉ በላይ ለወታደራዊ እንቅስቃሴ እንደዋሉም አክለዉ ተናግረዋል፡፡
በተመሳሳይ ወደ ትግራይ የሚሄደዉን ዕርዳታ ያህል ወደ አፋርም መሄድ እንዳለበት እንደሚያምኑ የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አማራ ክልል ረጅም ጊዜ በወራሪዉ ቁጥጥር ስር ዉሎ ስለነበር ዕርዳታዉን ለማድረስ አልተቻለም ብለዋል፡፡
እንደ ምክንያትም ወደ ክልሉ ለማስገባት እድሉ ቢገኝም ግን ስርጭቱን የሚያካሂዱ ተቋማት ቀድመዉ በትግራይ ክልል የዘረጉትን ስርዓት አይነት ለአማራ ክልል የተመቻቸ ስርዓት አለመዘርጋታቸዉን አንስተዋል፡፡
በአንድ በኩል በድርቅ ምክንያት የተጎዱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወገኖች አሉን ፣በሌላ በኩል ጦርነቱ በተካሄደበት ቦታ ያሉ የምግብ ዋስትና ድጋፍ የሚፈልጉ ዜጎች አሉ፤ ሙሉ ለሙሉ ተፈናቅለዉ የመጡ እንዲሁም በየቤቱ የሚገኙ ጦርነቱ ተጋላጭ ያደረጋቸዉ ሰዎች አሉ፤ስለዚህ ያለንን ሀብት ለዚህ ትኩረት በማድረግ ከዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ጋርም በመሆን እርዳታዉን የማፋጠን ስራ ነዉ የምንሰራዉ ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ለምክርቤቱ ወራሪዉ የህወሃት ሃይል ከአፋር ከወረዳ ማዕከላት እና ከተወሰኑ ወረዳዎች ወጥቷል እንጂ ዛሬም ድረስ በዚህ ወራሪ ሃይል ቁጥጥር ዉስጥ ያሉ ቀበሌዎች ስለመኖራቸዉም ተናግረዋል፡፡
እስከዳር ግርማ

አዳማ ከተማ አሰልጣኙን አሰናበተ::
አዳማ ከተማ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 24 ጨዋታዎች አከናውኖ 27 ነጥቦችን በመሰብሰብ 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል ፡፡
በዚህ የውድድር ዘመን 14 ጊዜ አቻ ተለያይቷል ፡፡
በ24ኛው ሳምንት ጨዋታው በባህርዳር ከተማ ተሸንፏል ፡፡ የአዳማ ከተማ አመራሮች ከአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ጋር ከተለወያዩ በኋላ በስምምነት ተለያይተዋል ።
ከቀጣዩ የሰበታ ከተማ ጨዋታ ጀምሮ ቡድኑን ምክትል አሰልጣኙ ይታገሱ እንዳለ እንደሚመራው ታውቋል።
ኢትዮ ኤፍ 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የአዉሮፓ ህብረት ከሩሲያ የሚያስገባዉን የጋዝ መጠን ከ40 ወደ 26 በመቶ መቀነሱን ተናግሯል፡፡
በአንድ አመት ግዜ ዉስጥ የአዉሮፓ ህብረት ከሩሲያ የሚያስገባዉን የጋዝ መጠን ከ40 ወደ 26 በመቶ መቀነሱን ተናግሯል፡፡
የአዉሮፓ ህብረት ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ሌየን እንደገለጹት ከአምናዉ ጋር ሲነጻጸር በዚህ ዓመት ከሩሲያ የሚገባዉን የጋዝ መጠን መቀነሳቸዉን ተናግረዋል፡፡
ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደገለጹት አምና 40 በመቶ የሚሆነዉ የአዉሮፓ ህብረት ሀገራት የነዳጅ ፍላጎት በሩሲያ የተሟላ ሲሆን፣ዘንድሮ ግን ወደ 26 በመቶ ዝቅ ለማድረግ ችለናል ብለዋል፡፡
የአዉሮፓ ህብረትን ፖሊሲ በተለይ ደግሞ በሀይል አቅርቦቶች ላይ ያለዉን ጉዳይ ‹‹በትክክለኛዉ መንገድ እየሄደ ነዉ›› ሲሉ የገለጹ ሲሆን ፤ በተጨማሪም ‹‹አዉሮፓ ህብረትን በድጋሚ በሀይል መሙላት›› ለተሰኘዉ አዲሱ ዕቅድ ፈጣን ለዉጦች እንዲያስመዘግብ በጋራ መስራት እንዳለባቸዉም አጽንኦት ሰጥተዉ ተናግረዋል፡፡
ይህ አዲሱ ዕቅድ በሩሲያ ነዳጅ ላይ ጥገኛ የሆነዉን የአዉሮፓ ህብረትንከጥገኝነቱ ለማላቀቅ፤ በዉስጡ የሚገኙ የተለያዩ ፋብሪካዎች እና ኩባንያዎች የጸሀይ ሀይል ላይ ትኩረታቸዉን አድርገዉ እንዲሰሩ የሚያስገድድ መሆኑ አር ቲ ኒዉስ
ዘግቧል፡፡

"የአማራ ክልል መንግሥት ሕግ የማስከበር ሙሉ አቅም አለው" ርእሰ መሥተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ፡፡
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በወቅታዊ ጉዳዮች መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም የአማራና የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላት ወያኔና የወያኔ ፈረሶች ናቸው ብለዋል።
በግንባር አካባቢ የወያኔ ፈረስ ሆነውነው የሚያገለግሉትን ኃይል አዘጋጅተን እየተፋለምን ነው ሲሉ ገልጸዋል።
የአማራ ክልል የፀጥታ ምክር ቤት በዝርዝር አጥንቶ ክልሉን ለማዳከም የሚሠሩ ጠላቶች መኖራቸውን አረጋግጧል ብለዋል። የውስጥ ጠላቶችን ለመዋጋት የውስጥ አንድነታችንን ማጠናከር አለብን ነው ያሉት።
የኅብረተሰቡ በሰላም ወጥቶ የመግባት እንቅስቃሴ ችግር ውስጥ እየወደቀ መኾኑንም ተናግረዋል። ውስጡን እያዳከመና እየከፋፈለ የሚገኝ ኃይል እንዳለም አረጋግጠናል ነው ያሉት።
ሕገወጥ ተኩስ በአጭር ካልተቀጨ በስተቀር ለኅብረተሰቡ ስጋት ይኾናልም ነው ያሉት። የልማት እንቅስቃሴዎች በሰላማዊ ሁኔታ እንዳይከናወኑ እየተደረገ መኾኑን መገንዘባቸውንም ተናግረዋል።
የኮንትሮባንድ ንግድም ፈታኝ እየሆነ መምጣቱንም ገልጸዋል። አንዳንዱ ሕገ ወጥ ንግድ በጦር መሳሪያ ጭምር እየታገዘ መኾኑንም ጠቁመዋል።
በታጠቁ ኃይሎች ምክንያት የመንግሥት አቅጣጫዎች እንዳይተገበሩ የሚያደርጉ መፈጠራቸውንም ተናግረዋል።
ሃይማኖትን ሰበብ በማድረግ እርስ በርስ በማጋደል ክልሉ የፀጥታ ስጋት ውስጥ እንዲቆይ የሚያደርጉ ሁኔታዎች መገኘታቸውን አመላክተዋል። ይህም ለውጭ ጠላት ተገላጭ እንዲኾን እያደረገ መኾኑንም መገምገማቸውንም ጠቁመዋል።
በየደረጃው ያለ አመራር እየተሳተፈበት የሕግ ማስከበር ሥራው እየተከናወነ መኾኑንም አስታውቀዋል። እየተወሰደ ያለው የሕግ ማስከበር ሥራ ጅማሮው አበረታች መኾኑንም አንስተዋል።
ሕገ ወጥ የመሬት ወረራን በማስለቀቅ እና ሕጋዊ ለማድረግ እየተሠራ መኾኑንም ገልጸዋል። የሕግ ማስከበር ሥራው አስፈላጊና ስኬታማ እንደሚኾን ተናግረዋል።
ሕግ የማስከበር ሥራችንን አጠናክረን እንቀጥላለንም ብለዋል። የአማራን ሕዝብ ሰላምና ደኅንነት ለመጠበቅ እንሠራለን ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ እርስ በርሱ የተከፋፈለ ሕዝብ ለጠላት ተጋላጭ መኾኑንም አንስተዋል።
ሕግ የማስከበሩ ሥራ የመንግሥትን ኃላፊነት የሚያረጋግጥ እና ሕዝብን የመታደግ መኾኑንም አስታውቀዋል። ወጣቶች ከመንግሥት ጋር በመኾን ለሕግ ማስከበሩ ሥራ እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል።
እንደ አሚኮ ዘገባ ተጠርጣሪዎችን እየያዙና በውይይት ወደ መደበኛ እንቅስቃሴያቸው እንዲመለሱ የማድረግ ሥራ እንደሚሠራም አንስተዋል።ያለ አግባብ የተያዙ ሰዎች ካሉ አጣሪ ኮሚቴው እያጣራ አፋጣኝ መፍትሔ ይሰጣል። ጥፋተኞች ግን በሕግ አግባብ ሊቀጡ ይገባል ነው ያሉት። ከክልሉ ውጭ ተይዘው ጠፉ የሚባሉት ትክክል አይደለም መስተካከል አለበትም ብለዋል። የተፈጠረ ስህተት ካለም መታረም አለበት ነው ያሉት።
የክልሉ መንግሥት ሕግ ለማስከበርና ሙሉ አቅም አለው ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ ሕገወጦችንና ሥርዐት አልበኞችን የመቆጣጠር አቅም አለው ነው ያሉት። እየተወሰደ ያለውን የሕግ ማስከበር ሥራ ኅብረተሰቡ ከአሉባልታ ተቆጥቦ በጥንቃቄ እንዲመረምረውም አሳስበዋል።
የጦር ነጋሪት እየጎሰመ ያለውን ጠላት በመከላከያ ሠራዊት፣ በልዩ ኃይል፣ በሚሊሻና በፋኖ ሕዝባችን ደጀን አድርገን እንመክታለን ነው ያሉት።
ሕዝቡ እንዲከፋፈል ዘመቻ እንደተከፈተበትም ተናግረዋል። ሕዝቡ ተከፋፍሎ እንዲዳከም እየተደረገ ነው፤ ሕዝቡ ይሄን መገንዘብ አለበት ብለዋል።
መንግሥት እያደረገ ያለው ሕገወጦችንና ሥርዐት አልበኞችን መቆጣጠር እንጂ ሌላ ዓላማ የለውምም ብለዋል። ሕገ ወጦች ተጠያቂ መኾን አለባቸው፤ ያላጠፋ ነጻ ይኾናልም ነው ያሉት። "በሕገወጦች ላይ ያለ ምኅረት እርምጃ መውሰድ አለብን፤ ይህ የመንግሥት ተግባር ነው" ብለዋል።
"የአማራ ክልል መንግሥት የጦር መሳሪያ አያስፈታም፤ የክልሉ መንግሥት ፋኖን የሚያዋክብ አይደለም፣ ፋኖዎችን አመሰግነናል፣ ሸልመናል፣ ነገር ግን በፋኖ ስም የሚነግዱ አሉ፤ በነጻነት እና የአማራ የክብር ስም በኾነው ፋኖ እየተንጠላጠሉ ሕገ ወጥ ተግባር ለመፈጸም የሚፈልጉ አሉ፤ ሕግ ስናስከብር ፋኖ ነው የሚባለው ውሸት ነው፣ እኛ ሕገወጦችን እንጂ ፋኖዎችን የመንካት ዓላማ የለንምም" ነው ያሉት። ዓላማችን የዜጎችን ሰላምና አንድነት ጠብቀን የጋራ ጠላታችን በጋራ መጠበቅ ነው ብለዋል።
የመንግሥትን ሥራ የሚገዳደር ኃይል ሊኖር አይችልምም ብለዋል። ሕዝቡ ከፀጥታ መዋቅር ጎን እንዲሰለፍም ጥሪ አቅርበዋል። ሰላምና ደኅንነታችን በራሳችን እንገባ፣ ይህን የማድረግ አቅም አለንም ብለዋል። ማርኮ የያዘ ሰው መሣሪያውን አይነጠቅም፣ ነገር ግን ማስመዝገብ አለበትም ብለዋል።
መሳሪያውን ለችግር ጊዜ እንዲጠቀምበት የሚያደርግ ስልጠና እንሰጣለን ፣ መሳሪያ ያላቸው እንዲያስመዝግቡ ጥሪ እናቀርባለን። በተጀመረው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ጥሩ ለውጥ መገኘቱን የገለጹት ርእሰ መሥተዳድሩ በቅርቡ ከተኩስ ድምፅ ነጻ የኾኑ ከተሞችን እንፈጥራለንም ብለዋል።
ከሕግ ማስከበሩ በተቃራኒ የቆሙት ኹሉ ለአማራ ሕዝብ የማያስቡ መዃናቸውንም አንስተዋል።
ለአማራ ሕዝብ ተቆርቋሪ የኾነ ለሕዝብ ሰላምና ደኅንነት መሥራት እንደሚገባውም አንስተዋል። የተያዙ ግለሰቦችን በአግባቡ እንይዛለንም ብለዋል። ኅብረተሰቡ ሕገወጦችን እያወጣ እንዲሰጥም ጥሪ አቅርበዋል።
ሰላምን ለማስከበር በሰላማዊ መንገድ እንሠራለን፣ ከአቅም በላይ ሲኾን እርምጃ እንወስዳለንም ብለዋል።

ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የደረሱበት ሳይታወቅ ከቆዩ ከሁለት ቀናት በኋላ ባሕር ዳር እንዳሉና ደህና መሆናቸውን የሚገልጽ መልዕክት እንደደረሳቸው ባለቤታቸው ተናገሩ።
ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ሰኞ ግንቦት 08/2014 ዓ.ም. ከቤታቸው ረፋድ ላይ ከወጡ በኋላ የደረሱበት ሳይታወቅ እስከ ረቡዕ አመሻሽ ድረስ ቆይተዋል።
ባለቤታቸው ወ/ሮ መነን ኃይሌ ረቡዕ ምሽት ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት የጄነራል ተፈራ ጠበቃና የሚያውቋቸው ሰዎች ባለቤታቸው ባሕር ዳር ውስጥ በሚገኘው ዘጠነኛ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እንዳሉ ገልጸዋል።
ወ/ሮ መነን ባለቤታቸው በላኩት መልዕክት ደህና መሆናቸውን እና አሁን ያሉበት ቦታ በመግለጽ ቤተሰባቸው እንዲረጋጋ መልዕክት ልከዋል ብለዋል።
ቢቢሲ ይህንኑ በተመለከተ ከአማራ ክልል የፀጥታና ደኅንነት እንዲሁም ፖሊስ ማብራሪያ ለመጠየቅ ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።
የቀድሞው የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ሰኞ ዕለት መሰወራቸውን ተከትሎ ቤተሰቦቻቸው ለደኅንነታቸው ሰግተው የነበረ ሲሆን የአዲስ አበባ ፖሊስም ሆነ የፌደራል ፖሊስ ስለጉዳዩ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ እንደተነገራቸው ባለቤታቸው ገልጸው ነበር።
ባለፈው የካቲት ወር ላይ ከልዩ ኃይል አዛዥነታቸው ተነስተው የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አማካሪነት ሹመት ቢሰጣቸው ሳይቀበሉት መቅረታቸው ይታወሳል።

የወባ ስርጭት ስጋት ባለባቸው የአማራ ክልል አምስት አካባቢዎች በሰዎቹ እጅ ላይ የሚገኘው የወባ መከላከያ አጎበር የአገልግሎትጊዜው ያለፈበት ነው ተባለ።
በአማራ ክልል አምስት አካባቢዎች የአጎበር መተኪያ ጊዜያቸው አልፎ ተቀያሪ ለማግኘት እየተጠባበቁ እንደሚገኙ የአማራ ክልል የወባ መካከል እና መቆጣጠር ፕሮግራም አሰተባባሪ አቶ ዳምጤ ላንክር ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
በክልሉ አምስት አካባቢዎች ማለትም ሰሜን ሸዋ ላይ ( ሸዋሮ ቢት) ፣ እንሳሮ ፣ ደቡብ ወሎ ላይ ( ቃሎ) ፣ ማዕከላዊ ጎንደር እና ጎንደር ዙርያ መሆናቸውንም ለጣቢያችን አስታውቀዋል፡፡
አጎበር የሚተካላቸው እና የመተኪያ ጊዜው ያለፋቸው አካባቢዎች መኖራቸውን ለጤና ሚኒስቴር ማስታወቃቸውን እና መልስ እየጠበቁ መሆኑንም አቶ ዳምጤ ተናግረዋል።
ጤና ሚኒስቴርም ግዢወው ተፈፅሞ ቦርደር ላይ እንደሚገኝ በመግለፅ አስከ ግንቦት መጨረሻ እንደሚያገኙ እንደነገራቸውም ገልጸዋል ፡፡
በተያያዘም ማዕከላዊ ጎንደር እና ጎንደር ዙሪያ ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ደምቢያ ፣ ( ጣና ተፋሰስ አካባቢ) የወባ ስርጭት እየጨመረ መሆኑንም የክልሉ የወባ መካከል እና መቆጣጠር ፕሮግራም አሰተባባሪው አቶ ዳምጤ ላንክር አንስተዋል፡፡
አጎበር ለለማደል ፕሮግራም ከማመቻቸት ባሻገር ስርጭቱ ባየለባቸው አካባቢዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ እና መቆጣጠር በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ ለነዋሪዎች ስልጠና እየተሰጠ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል ፡፡
በረድኤት ገበየው
ግንቦት 11 ቀን 2014 ዓ.ም

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ስለተፈፀመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት የቀረበው ሪፖርት እንዳስደነገጠው ገልጿል ።
የአውሮፓ ህብረት የሰብዓዊ መብት ልዩ መልዕክተኛ ኤሞን ጊልሞር በትናንትናው ዕለት ለሶስት ቀናት ከተለያዩ የሚመለከታቸው አካላት ጋር ስላደረጉት ውይይት ጋዜጣዊ መግለጫ ስጥተዋል ።
በመግለጫውም ከሰብዓዊ መብት ጥሰት አንፃር የቀረበው ሪፖርት እንዳስደነገጣቸው ለጋዜጠኞች ተናግረዋል ።
በኢትዮጵያ በነበራቸው የሶስት ቀን የስራ ውይይት በትኩረት ለማየት የሞከሩት ከሰብአዊ መብት ጋር ተያይዞ ሶስት ጉዳዮችን እንደነበር አንስተዋል ።
እነርሱም የሰብአዊ እርዳታ ሁኔታ፣ አገራዊ የምክክር ሂደት እና የሰብዓዊ መብቶች እና ተጠያቂነት እንደነበሩ አብራርተዋል ።
ከሰብአዊ እርዳታ አንፃር ብዙ አስቸጋሪ እና ምቹ ያልሆኑ ሁኔታዎች እንዳሉ ያነሱት ልዩ መልዕክተኛው የአስተዳደር ችግር ፣ ቴክኒካል ጉዳዮች እና የተቀሩት ደግሞ የሰብዓዊ ዕርዳታ ማድረሻ መንገዶች መሆናቸውን ገልጸዋል ።
ይህንንም ችግር ከተለያዩ የመንግስት ተወካዮች ጋር እንደተወያዩበት እና መልዕክቱም በሚገባ ለመንግስት ደርሷል ብለው እንደሚያምኑ ገልፀው ፣ ችግሩ ተፈትቶ በተስተካከለ መልኩ ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ብቻ ሳይሆን ከድርቁ እንዲሁም አሁን በሀገራችን ላለው አስፈላጊ የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚደርሱም አክለዋል ።
ከአገራዊ ምክክር አንፃርም እንደ አውሮፓ ህብረት በኦባሳንጆ ሲደረግ የነበረውን ዘላቂ ሰላም የማምጣት ሂደት በእጅጉ እንደሚደግፉ ገልፀዋል።
በተጨማሪም አሁን በጅምር ላይ ያለው አገራዊ የምክክር ሂደት ሁሉን አካታች መሆኑ አስፈላጊ ጉዳይ መሆኑንም አንስተዋል ።
"ከእራሴ ልምድ እና ከሌሎችም እንዳየሁት ሴቶችን የምክክር ሂደት ውስጥ ማስገባቱ እጅግ ወሳኝ ነው" ሲሉ ያክላሉ ።
ሶስተኛው እና የመጨረሻው ጉዳይ የነበረው ከሰብአዊ መብቶች እና ተጠያቂነት አንፃር የተደረገው ውይይት መሆኑን ያነሱት ልዩ መልዕክተኛው ፤ በቀረበው ከአንድ አመት ከግማሽ በላይ በነበረው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሪፖርት በእጅጉ መደንገጣቸውን ገልፀዋል ።
በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሀየር ኮሚሽን ፎር ሂዩማን ራይትስ በጋራ ያወጡትን ሪፓርት መመልከታቸውን የገለፁት ኤሞን ጊልሞር አጥፊዎቹ ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል ።
መቼ፣የት፣ማን አደረጋቸው የሚሉትን ትተን እዚህ የተመለከትነው ጉዳይ ከፍርድ ውጭ የሆነ ግድያ እና አሰቃቂ የሆነ ፆታ ተኮር ጥቃቶችን ነው፣ ይህም በእኛ ዘንድ በፍፁም ተቀባይነት የሌለው ጉዳይ ነው ሲሉ ገልጸዋል ።
በዚህም መሰረት ገለልተኛ የሆነ ኮሚቴ ተቋቁሞ በጥምር የተሰራውን የምርመራ ስራ እንዲገመግም ሀሳብ ማቅረባቸውንም ተናግረዋል ።

በአዲስ አበባ አውራ ጎዳናዎች የሚታዩት የቢልቦርድ ማስታወቂያዎች የደረጃ ጥራት ችግር አለባቸው ተባለ፡፡
ይህ ያለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ነው፡፡
ባለስልጣኑ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ህገ ወጥ የውጭ ማስታወቂያዎችን ለመከላከል አደረኩት ባለው ጥናት ከ400 በላይ ቢልቦርዶች ደረጃቸውን የጠበቁ አይደሉም ሲል ለኢትዮ ኤፍኤም አስታውቋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነትና የኮሙዪኒኬሽን ዳሬክቶሬት የሆኑት አቶ አረጋዊ ማሩ ለኢትዮ ኤፍኤም እንደተናገሩት ህጋዊ አሰራሩን ለመከተል ከ155 ሺህ በላይ ህገ ወጥ የውጭ ማስታወቂያዎች ላይ እርምጃ ወስደናል ብለውናል፡፡
በመዲናዋ ለውጭ ማስታወቂዎች ግልጋሎት የሚውሉ አካባቢዎች በተለያዩ ደረጃዎች ተለይዋል የተባለ ሲሆን ማስታወቂያዎችን ህጋዊ ማድረግ የሚያስችል ስታንዳርድ መዘጋጀቱንም ኢትዮ ኤፍኤም ከባለስልጣኑ ሰምቷል፡፡
የውጭ ማስታወቂያ ለሚያዘጋጁ ድርጅቶች ዳግም ምዝገባ በማድረግ የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ የሚሰጥም ይሆናል ነው የተባለው፡፡
ድርጅቶችም ደረጃቸውን የጠበቁ ማስታወቂያዎችን ብቻ ለማህበረሰቡ ተደራሽ እንዲያደርጉ ምልእክት ተላልፏል፡፡
ባለስልጣኑ ለከተማዋ ውበት የሚመጥኑ የውጭ ማስታወቂያዎች በብዛት ባለመኖራቸው በመዲናዋ ገጽታ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እየፈጠረ እንደሆነም አስታውቋል፡፡
በመዲናዋ ህገ ወጥ የውጭ ማስታወቂያዎችን ለመከላከል ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ለኢትዮ ኤፍኤም አስታውቋል፡፡
በየዉልሰዉ ገዝሙ

በዓለም ዋንጫ ሴት ዳኞች ጨዋታ ይመራሉ::
በካታር በሚከናወነው የወንዶች ዓለም ዋንጫ በውድድሩ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት ዳኞች ጨዋታ እንደሚመሩ ተነገረ ፡፡
ፈረንሳዊቷ ስቴፋኒ ፍራፓርት ፣ ሩዋንዳዊቷ ሰሊማ ሙካንሳንጋ እና ጃፓናዊቷ ዮሺሚ ያማሺታ በካታር የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎችን እንዲመሩ ተመርጠዋል ፡፡
በሶስት ሴት ረዳት ዳኞች እንደሚታገዙም ታውቋል ፡፡
የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዳኞቹ ማይክል ኦሊቨር እና አንቶኒ ቴይለር በውድድሩ ጨዋታዎችን እንዲመሩ ከተመረጡ አርቢትሮች መካከል ሆነዋል ፡፡
በአጠቃላይ 36 ዋና ዳኞች ፣ 69 ረዳት ዳኞችእና 24 የቨ.ኤ.አር ዳኞች ተመርጠዋል ፡፡
በአቤል ጀቤሳ

‹‹ሩሲያ ወደ ሌሎች ሀገራት የምትልካቸዉ የምግብ ግብዓቶች የዓለምአቀፉን የምግብ ቀዉስ ይፈታሉ›› የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፡፡
ከሩሲያ፣ዩክሬን እንዲሁም ከቤላሩስ የሚላኩ እንደ ምግብ እና ማዳበሪያ ያሉ ግብዓቶች ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ የከፋ እና የማያቆም የምግብ ቀዉስ መመልከት የማይፈልግ ከሆነ በዓለምዓቀፉ ገበያ ላይ እንዲሸጥ ሊፈቅድ ይገባዋል ሲሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ ተናግረዋል፡፡
እዚህ ላይ ግልጽ መሆን ያለበት ጉዳይ ለምግብ ቀዉሱ ከዩክሬን የሚላኩ የምግብ ግብዓቶች እንዲሁም ከሩሲያ እና ቤላሩስ የሚላኩ የምግብ እና የማዳበሪያ ግብዓቶች በገበያዉ ላይ ከመፈቀዳቸዉ ዉጭ ሌላ አስተማማኝ የሆነ መፍትሄ የለም ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዉ ተናግረዋል፡፡
አሁን ላለዉ የምግብ ቀዉስ ምክንያት ከመሆን በተጨማሪ የሩሲያ ወታደራዊ ጥቃት፣ የአየር ንብረት ለዉጥ እና ኮሮና የምግብ ቀዉሱን እየጎዱ የነበሩ ጉዳዮችን የበለጠ እንዲባባሱ አድርጓቸዋል ብለዋል ዋና ጸሀፊዉ፡፡
ሩሲያ ፣ ዩክሬን እንዲሁም ቤላሩስ የምግብ እና ማዳበሪያ ግብዓቶች ዋና አምራቾች መሆናቸዉን የተናገሩት ዋና ጸሃፊዉ፣ ይህን አለመቀበል አንችልም ሲሉ መናገራቸዉን አር ቲ ኒዉስ ዘግቧል፡፡
በእስከዳር ግርማ
ግንቦት 12 ቀን 2014 ዓ.ም

‹‹የደህንነት ዕይታችን ሰፊ እና አካታች መሆን ይገባዋል›› የዉጭ ጉዳይ ኢንስቲትዪት፡፡
የደህንነት ዕይታችን ሰፊ እና አካታች መሆን እንዳለበት የዉጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የጥናትና ምርምር ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጃፋር በድሩ ናቸዉ ለኢትዮ ኤፍኤም የተናገሩት፡፡
የዉጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት‹‹ የብሄራዊ ደህንነት ስትራቴጂ ምንነት፣አቀራረጽና እና አስፈላጊነት›› በሚል ርዕስ የፖሊሲ ምክክር መድረክ በትናንትናዉ ዕለት አዘጋጅቶ ነበር፡፡
በዚህ መድረክ ላይ ሀገራችን ኢትዮጵያ በ1987 ዓ.ም የፌደራል ስርዓት ካዋቀረችበት ጊዜ አንስቶ በግልጽ የተጻፈ እና ከዉጭ ግንኙነት ፖሊሲ ጋር የተጣመረ የብሄራዊ ደህንነት ስትራቴጂ ነበራት የተባለ ሲሆን፤
ይህ ስትራቴጂ በሀገራችን የመንግስት ለዉጥ እስከተካሄደበት 2010 ድረስ እንደዋነኛ የዉጭ ግንኙነትና የብሄራዊ ደህንነት ፖሊሲና ስትራቴጂ ሆኖ ሲያገለግል መቆየቱ ተገልጿል፡፡
የዉጭ ግንኙነት ፖሊሲና ስትራቴጂ በአዲስ መልክ የተቀረጸና መሻሻል ተደርጎበት በመከለስ ላይ ያለ ቢሆንም፤ የሀገራችንን የብሄራዊ ደህንነት ፖሊሲና ስትራቴጂ አስመልክቶ ከዚህ በፊት የነበረዉና አሁን ላይ በመከለስ ላይ ያለዉም ቢሆን ‹‹ከዉጭ የሚመጣን ስጋት መከላከል››በሚል ዉስን ሀሳብ እና ተግባር ላይ የተወሰነ መሆኑ ተነስቷል፡፡
በሀገራችን የነበረዉ የደህንነት አረዳድ በጣም ጠባብ ነበር የሚሉት አቶ ጃፋር ብሄራዊ ደህንነታችንን ከመንግስት፣ ከተቋማት እና ከስርዓት ደህንነት ዉጭ ለይቶ አያይም ነበር ብለዋል፡፡
ሌላዉ ደግሞ የደህንነት ስትራቴጂያችን አካታች አልነበረም ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፣ ሁሉም የደህንነት ተቋማት ተሳትፈዉበት፣ ችግራቸዉንም ለይተዉ የብሄራዊ ደህንነታችን ላይ አደጋ ሊደቅን የሚችለዉ ይህ ጉዳይ ነዉ የሚለዉን ተነጋግረዉበት የተቀረጸ አይደለም ሲሉ ያክላሉ፡፡
ስለዚህ የህዝቡ ደህንነት ከመንግስት ተቋማት እና የሀገርን ሉዓላዊነት ከመጠበቅ ጋር አብሮ ታሳቢ ተደርጎ ይህ ስትራቴጂ መቀረጽ አለበት ያሉ ሲሆን ፤ ደህንነት ሲባል ከበሽታ፣ ከወረርሺኝ ፣ከተፈጥሮ አደጋዎች፣ ከድህነት ህዝቡን መጠበቅ እንዲሁም ሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ማስጠበቅንም ያካትታል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዉ ተናግረዋል፡፡