የኢትዮጵያ መንግሥት የሚቆጣጠረው ብሔራዊ የቴሌቭዥን ጣቢያ የፌስቡክ ገጽ መጠለፉን አስታወቀ።
በመስቀል አደባባይ በመካሔድ ላይ የሚገኘውን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዓለ ሲመት በቀጥታ ሥርጭት እያስተላለፈ የሚገኘው የቴሌቭዥን ጣቢያው በፌስቡክ ገጹ የተለጠፉ መልዕክቶች የተቋሙ አለመሆናቸውን አስታውቋል።
ቴሌቭዥን ጣቢያው «የኢቢሲ ፌስቡክ ገጽ ስለተጠለፈ እየተላለፈ ያለው መልዕክት የተቋሙ አለመሆኑን እንገልጻለን» ብሏል።
በቴሌቭዥን ጣቢያው የተረጋገጠ የፌስቡክ ገጽ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በስድስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አደረጉ የተባለውን ንግግር የተመለከተ ይገኝበታል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት በምክር ቤቱ ሹመታቸውን ሲጸድቅ ያደረጉት ንግግር አልነበረም። መልዕክቶች ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ከገጹ ጠፍተዋል።
የቴሌቭዥን ጣቢያው በፌስቡክ የነበረውን የቀጥታ ሥርጭት ዘግየት ብሎ አቋርጧል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመርሐ ግብሩ ንግግር እያደረጉ ሲሆን ብሔራዊው የቴሌቭዥን ጣቢያ ሥርጭቱን በዩቲዩብ እያስተላለፈ እንደሚገኝ ዶቼቬሌ ነው የዘገበው።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም

ታሊባን 13 የሃዛራ ብሄረሰብ አባላትን መግደሉ ተገልጿል
ታሊባን አፍጋኒስታን ውስጥ ሥልጣን ከያዙ በኋላ ብዙም ሳይቆይ በማዕከላዊው ዴክኩንዲ ግዛት ውስጥ የ 17 ዓመት ታዳጊን ጨምሮ ቢያንስ 13 የሃዛራ ጎሳ አባላትን መግደሉን የአምንስቲ ኢንተርናሽናል አዲስ ሪፖርት አመልክቷል።
ነሃሴ 30 ቀን 300 የታሊባን ወታደሮች ከኮናጎ ወደ ክድር አካባቢ በመግባት ቢያንስ 11 የቀድሞ የአፍጋኒስታን ብሔራዊ ደህንነት ሀይሎችን እና 9 ከእነርሱ ጋር የነበሩ ሰዎችን መግደላቸው ማረጋገጡን አምንስቲ ገልጿል።
የሂዩማን ራይት ተባባሪ የሆኑት የእስያ ዳይሬክተር ፓትሪሺያ ጎስማን ለአልጀዚራ እንደተናገሩት አሁን በአፍጋኒስታን ያለው ነገር ያሰጋል፤ የበቀል ጥቃቶች ከፍተኛ ዋጋን ከማስከፈሉም በላይ ማቆሚያ የለውም ።
“ለተጎዱት ተራ የህብረተሰብ ክፍሎች ደህንነትን ማስጠበቅ ካልተቻለ ወይም ለወታደራዊ ምክንያቶች የግድ አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር የዜጎችን በኃይል ማፈናቀል ሕገወጥነት ነው ሲሉ ገልፀዋል።
አልጀዚራ
በረድኤት ገበየሁ
መስከረም 25 ቀን 2014 ዓ.ም

6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ መካሄድ ጀመረ
ም/ቤቱ በልዩ ስብሰባው የኢፌዴሪ ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ም/ቤቶች የጋራ መደበኛ ስብሰባ ያቀረቡትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ የቀረበን የድጋፍ ሞሽን እደመጠ ይገኛል፡፡
በተጨማሪም በልዩ ስብሰባው የፌዴራል መንግስት የአስፈፃሚ አካላት ሥልጣንና ተግባርን መወሰኛ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ያፀድቃል።
በመጨረሻም የሚኒስትሮችን ሹመት መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
መስከረም 26 ቀን 2014 ዓ.ም

6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ከተነሱ ጉዳዮች መካከል
• ክልሎች የፀጥታ ችግር ሲገጥማቸዉ የፌደራሉ መንግስት በፍጥነት ኃይል በማሰማራት የማረጋጋት ስራ መስራት አለበት ለዚህ ደግሞ እራሱን የቻለ በማእከል ደረጃ ኮማንድ ሊቋቋም ይገባል፡
• የፀረ ሙስና ኮሚሽ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት መሆኑ ግልፀኝነትን አያረጋግጥም፡፡
• በርካታ አንገብጋቢ አገራዊ ጉዳዮች ባሉበት ጠቅላይ ሚኒስትሩ 20 የሚሆኑ የፌደራል መስሪያ ቤቶችን እንዲቆጣጠሩ ስልጣን መሰጠቱ አግባብ አይደለም ተብሏል፡፡
• ለግብርና ሚኒስቴር የተለየ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል
• እንዲሁም ኢትዮጵያ በምግብ እራሷን እንድትችል መንግስት በትኩረት መሰራት አለበት፡፡
6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ እየተካሄደ ሲሆን
የሚኒስትሮች ሹመት ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር መወሰኛ ረቂቅ አዋጅ ላይ 22 ሚኒሲቴር መስሪያ ቤቶች ቀርበዋል ፡፡
1. ግብርና ሚኒስቴር
2. የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር
3. የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር
4. የማዕድን ሚኒስቴር
5. የቱሪዝም ሚኒስቴር
6. የስራና ክህሎት ሚኒስቴር
7. የገንዘብ ሚኒስቴር
8. የገቢዎች ሚኒስቴር
9. የፕላንና ልማት ሚኒስቴር
10. የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
11. የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር
12. የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር
13. የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር
14. የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር
15. የትምህርት ሚኒስቴር
16. የጤና ሚኒስቴር
17. የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር
18. የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር
19. መከላከያ ሚኒስቴር
20. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
21. የፍትህ ሚኒስቴር
22. የሰላም ሚኒስቴር
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
መስከረም 26 ቀን 2014 ዓ.ም
1. ግብርና ሚኒስቴር
2. የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር
3. የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር
4. የማዕድን ሚኒስቴር
5. የቱሪዝም ሚኒስቴር
6. የስራና ክህሎት ሚኒስቴር
7. የገንዘብ ሚኒስቴር
8. የገቢዎች ሚኒስቴር
9. የፕላንና ልማት ሚኒስቴር
10. የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
11. የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር
12. የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር
13. የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር
14. የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር
15. የትምህርት ሚኒስቴር
16. የጤና ሚኒስቴር
17. የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር
18. የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር
19. መከላከያ ሚኒስቴር
20. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
21. የፍትህ ሚኒስቴር
22. የሰላም ሚኒስቴር
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
መስከረም 26 ቀን 2014 ዓ.ም
ስማቸው ከታች የተዘረዘሩት ሚንስትሮች ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አማካኝነት ቀርበው፣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በ2 ተቃውሞ በ12 ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ በማግኘት ፣ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሀላ ፈፅመዋል።
1. አቶ ዑመር ሁሴን - ግብርና ሚኒስቴር
2. አቶ ደመቀ መኮንን - ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
3. ገብረ መስቀል ጫላ - የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር
4. ዶክተር ሊያ ታደሰ - የጤና ሚኒስቴር
5. አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ - የቱሪዝም ሚኒስቴር
6. ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል - የስራና ክህሎት ሚኒስቴር
7. አቶ አህመድ ሽዴ - የገንዘብ ሚኒስቴር
8. አቶ ላቀ አያሌው - የገቢዎች ሚኒስቴር
9. ዶክተር ፍጹም አስፋው- የፕላንና ልማት ሚኒስቴር
10. አቶ በለጠ ሞላ - የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
11. ዳግማዊት ሞገስ - የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር
12. ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ - የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር
13. ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ - የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር
14. ኢንጂነር አይሻ ሙሳ - የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር
15. ዶክተር ብርሃኑ ነጋ - የትምህርት ሚኒስቴር
16. ኢንጂነር ታከለ ኡማ - የማዕድን ሚኒስቴር
17. የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
18. አቶ ቀጄላ መርዳሳ - የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር
19. ዶክተር አብርሃም በላይ - መከላከያ ሚኒስትር
20. አቶ መላኩ አለበል - የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር
21. ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ - የፍትህ ሚኒስትር
22. አቶ ብናልፍ አንዱዓለም - የሰላም ሚኒስትር
23. የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር- ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ

"የተሾምኩበት በትክክለኛው ቦታ ነው፣ከዚህ ሃላፊነት ውጪ ቢሰጠኝ ኖሮ አልቀበልም ነበር” ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በፀደቀው የሚንስትሮች ሹመት የትምህርት ሚንስትር ሆነው የተሾሙት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የተሾምኩበት በትክክለኛው ቦታ ነው፣ከዚህ ሃላፊነት ውጪ ቢሰጠኝ ኖሮ አልቀበልም ነበር ብለዋል፡፡
ይህንን ሃላፊነት እንደማገልገል ከወሰድነው ከዚህ መስሪያ ቤት ውጪ ሌላ ሃላፊነት ቢሰጠኝ አልወስድም ነበር፡፡ ትምህርት በፍቅር የሚሰራ ስራ ነው፡፡የትምህርት ሚንስቴርም ትልቅ ተቋም ነው የተሰጠኝም ሃላፊነት ትልቅ ሹመት ነው በማለት ተናግረዋል፡፡
ሹመቱንም በዛሬው እለት እንደ ሌላው ሰው ነው የሰማሁት ያሉት ፕሮፌሰሩ፣እድሜ ዘመኔን በማስተማር ስራ ላይ ነው ያሳለፍኩት፣ምናልባት ፔዳጎጂ እንደመስፈርት ይቆጠር እንደሆነ አላውቅም ብለዋል፡፡
የአገሪቱን ቀጣይ እጣ ፈንታ ለመወሰን ሁለት ጉዳዮች ከግንዛቤ ውስጥ መግባት እንዳለባቸው ያነሱት ፕሮፌሰሩ እነዚህም የአገሪቱን ፖለቲካዊ ሁኔታ ማሻሻል እና ትውልዱን በትምህርት ማነፅ ነው ብለዋል። አክለውም ላለፉት 40 ዓመታት በችግር የተተበተበው የትምህርት ዘርፍ የሚጠበቅበትን መስራት አልቻለም ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ)፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮችን ነው የካቢኔያቸው አባላት አድርገው በዛሬው እለት ሾመዋል፡፡
በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) መሪ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስትር፤ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሊቀመንበር በለጠ ሞላ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር እንዲሁም የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ምክትል ሊቀመንበር ቀጄላ መርዳሳ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል፤ ቃለ መሃላም ፈጽመዋል፡፡
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
መስከረም 26 ቀን 2014 ዓም

“አሁንም ከመንግስት ጋር ለመስራት ዝግጁ ነን “ የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ
የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ አሁንም ከመንግስት ጋር ለመስራት ዝግጁ ነው፣ ነገር ግን ምን አይነት የሀላፊነት ቦታ ላይ እንደምንመደብ ቀድሞ ሊነገረን ይገባል ሲሉ የፓርቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር አብዱልቃድር አደም ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።
በዛሬው ዕለት በተካሄደው 6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ አመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር አብዱልቃድርን ለአዲስ አበባ ምክር ቤት የካቢኔ አባልነት ተጠይቀው ፓርቲያቸው እንዳልፈቀደ መናገራቸው አይዘነጋም።
ፓርቲያችሁ ያልፈቀደበት ምክንያት ምንድነው? ያልናቸው ፕሬዝደንቱ በመጀመሪያ የተነገረን በአጭር ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ በፓርቲያችን መመሪያ መሰረት እነሱ የመረጡትን ሰው ሳይሆን እኛ ለቦታው ይመጥናል ብለን ያመንበትን ሰው መመደብ እንዳለብን ስለሚደነግግ ነው ሲሉ መልሰዋል።
በተጨማሪም ከመንግስት ጋር መስራት አለብን ብለን በማመናችንም ባይቀበሉትም ሌላ ሰው እንደመደብን አሳውቀን ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን ይህንን በምክር ቤቱ አላነሱትም ብለዋል የፓርቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር አብዱልቃድር።
አሁንም ቢሆን ፓርቲያችን ከመንግስት ጋር ሊሰራ ዝግጁ መሆኑን እናሳውቃለን ፣ ነገር ግን ጥሪ ሲደረግልን ግልጽነት እንዲኖርና ትክክለኛውን ሰው እንድንመድብ ግለሰብን ሳይሆን ፓርቲውን በመምረጥ መሆን አለበት ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
መቅደላዊት ደረጄ

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እና አዲስ ለተቋቋሙ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ተጠሪ የሆኑ ተቋማት ዝርዝር ይፋ ሆነ፡፡
በዚሁ መሠረትም÷ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ ለስራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ለፍትህ ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ ተቋማት ዝርዝር ይፋ ሆኗል፡፡
ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪ የሆኑ አስፈጻሚ አካላት
1. ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣
2. የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት፣
3. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣
4.የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን፣
5. የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣
6.የቤተ መንግስት አስተዳደር፣
7. የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣
8. የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ፣
9. የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣
10. የፋይናንስ ደህነነት አገልግሎት፣
11. አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣
12. የኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለስልጣን፣
13. የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ፣
14. የሪፐብሊክ ጥበቃ ሀይል፣
15. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት፣
16. የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣
17. የፌደራል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣
18. የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን፣
19. የዕርቀ ሰላም ኮሚሽን፣ (በቀጣይ የሚስተካከል)
20. የአስተዳደር ጉዳዮች፣የወሰንና ማንነት ኮሚሽን (በቀጣይ የሚስተካከል)።
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተጠሪ የሆኑ አካላት
1. የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ፣
2. የግል ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ።
የአዳዲስ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እና ለሱ ተጠሪ የሆኑ አካላት
ሀ. የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ
1. የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢኒስትቲዩት፣
2. የግብርና ቴክኒክና ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ፣
3. የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት።
4. የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ አካላት
5. የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት፣
6. የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት፣
7. የአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ናቸው
ለ. ለፍትህ ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ
1. የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን፣
2. የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን፣
3. የፌዴራል ፍትህና ሕግ ኢንስቲትዩት፣
4. የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ አገልግሎት፣
5. የፌደራል ግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ናቸው::

“ያደረግሁት አስተዋጽኦ በፈታኞቹ ወቅቶችና ሰአታት ሀገሬን ቀና አድርጓታል ብዬ አምናለሁ፣በቀጣይ ሀገሬ በምትፈልገኝ አገልግሎት የምሰማራ ይሆናል”- ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ” ብለዋል
በኢትዮጵያ መንግስት አዲሱ ካቢኔ ውስጥ ያልተካተቱት የቀድሞው የውኃ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ አለመካተታቸው በርካቶችን እያነጋገረ ነው።
ይህንን አስመልክቶም ስለሺ በቀለ (ዶ/ር ኢ/ር ) በይፋዊ የፌስቡክ ገጻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል። በዚህም መሰረት “በቀጣይ አገሬ በምትፈልገኝ አገልግሎት የምሰማራ ይሆናል” ሲሉ የቀድሞው ሚኒስትር ተናግረዋል።
የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ሚኒስትር በመሆን ለተሾሙት ኢንጂነር አይሻ መሀመድ እና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሆነው ለተሾሙት ዶ/ር ኢ/ር ሃብታሙ ኢተፋም መልካም ምኞት አስተላልፈዋል።
ላለፉት አምሰት አመታት ሚኒስትር በመሆን በቅንነት፤ በታማኝነትና በሚችሉት ሁሉ ሀገራቸውን ማገልገላቸውንም ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል።
ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ “ብዙ አስቸጋሪ ጊዜያትንም አሳልፈናል፤ ግድባችንም በጥቂት ወራት ሀይል ያመነጫል፤ በዚህና በሌሎችም መስኮች ያደረግሁት አስተዋጽኦ በፈታኞቹ ወቅቶችና ሰአታት ሀገሬን ቀና አድርጓታል ብዬ አምናለሁ“ ሲሉም ነው መልዕክት ያስተላለፉት፡፡
በቀጣይ ኢትዮጵያ በምትፈልጋቸው አገልግሎት እንደሚሰማሩም አል-ዐይን ዘግቧል፡፡

ቻይናዊያን ተማሪዎች ለረጅም ሰዓት የምትበር ድሮን በመስራት ክብረ ወሰን ሰበሩ::
በቻይናዊያን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተሰራች መሳርያ አልባ ድሮን ያለ እረፍት ለረጅም ሰዓት የበረረች ድሮን በመባል የዓለም ክብረ ወሰንን ሰብራለች፡፡
ፌንግ አርዩ 3-100 የተሰኘችው ይህች በቤጂንግ የኤሮናቲክስ እና አስትሮናቲክስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተሰራች ድሮን ያለ ማቋረጥ ለ80 ሰዓት ከ46 ደቂቃ ከ35 ሴኮንድ በመብረር ነው ቀድሞ በቦይንግ ስር በሚተዳደረው ኦሪዮን በተሰኘ ተቋም በ80 ሰዓት፣ ከ2 ደቂቃ ከ52 ሴኮንድ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን ያሻሻለችው፡፡
የክንፍ ርዝማኔዋ 10 ሜትር የሆነው ድሮኗ በጋዝ ሞተር አማካኝነት የምትንቀሳቀስና ጠቅላላ ክብደቷም (የተሞላባትን ነዳጅ ጨምሮ) 60 ኪ.ግ ነው፡፡
ስያሜዋም የቻይና አቪዬሽን ኢንዱስትሪ አባት ከሚባሉት ከፌንግ ሩ የተወረሰ ነው፡፡
በረራው የተከናወነው ባሳለፍነው ግንቦት ወር በቻይና ሄናን ግዛት ውስጥ ነበር፡፡ ሆኖም ክብረ ወሰኑ ገና ባሳለፍነው እሁድ ነው በዓለም አቀፉ የኤሮናቲክስ ፌደሬሽን (FAI) እውቅና የተሰጠው፡፡
በበረራው ወቅት ድሮኗ በ300 ሜትር ከፍታ ላይ ስትጓዝ የነበረች ሲሆን በአየር ላይ እያለችም ምንም አይነት ተጨማሪ ነዳጅ እንዳይሞላላት ተከልክላ ነበር፡፡
እንደ ዩኒቨርሲቲው መረጃ ከሆነ ድሮኗን የሰራው የተማሪዎቹ ቡድን 25 ከተለያዩ የትምህርት ዘርፎች የተውጣጡ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን ያቀፈ ነው፡፡
የተማሪዎቹ አማካኝ ዕድሜም ከ20 ዓመት በታች እንደሆነ ሺኑዋ ዘግቧል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለከፍተኛ የመንግስት ሃላፊነት ቦታዎች ሹመቶች ሠጡ::
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት አቶ ተፈሪ ፍቅሬን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አድርገው በድጋሚ የሾሙ ሲሆን ለ4 ከፍተኛ የሃላፊነት መደቦችም በሚኒስቴር ማእረግ የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል፡-
1. አቶ አደም ፋራህ - በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ
2. አቶ ተስፋዬ ቤልጅጌ - በሚኒስትር ማዕረግ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ
3. ዶ/ር ስለሺ በቀለ - በሚኒስትር ማዕረግ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የህዳሴግድብ ዋና ተደራዳሪና አማካሪ
4. ዶ/ር ለገሰ ቱሉ - በሚኒስትር ማዕረግ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ
በተጨማሪም፡
- ዶ/ር ምህረት ደበበ - የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚዳንት፤
- አቶ ፍሰሃ ይታገሱ - የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ፤
- እንዲሁም አቶ አብዱራህማን ሩቤ - የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ተሹመዋል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
መስከረም 27 ቀን 2014 ዓ.ም