Ethio Fm 107.8
19.2K subscribers
5.5K photos
16 videos
4 files
2.24K links
በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!
Download Telegram
100 ዘመናዊ የህዝብ ትራንስፖርት አውቶብሶች በዛሬው እለት ወደ ስራ መግባታቸው ታውቋል።


ከንቲባ አዳነች አቤቤ የህዝቡን የትራንስፖር ችግር እና የመንገድ ችግሮችን ለመቅረፍ ከተማ አስተዳደሩ በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል።

200 ቀሪ አውቶብሶች በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንደሚገቡም ተናግረዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ሞትኩ አስማረ በተለይ በከተማዋ የሚስተዋለውን የትራንስፖርት ችግር እና ትራንስፖርት ለማግኘት የሚስተዋሉ ረጃጅም ሰልፎችን ለመቅረፍ በእቅድ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።


አውቶብሶቹ ዘመናዊ ቴክኖሎጅ የተገጠመላቸው ሲሆኑ፥ ለአብነትም መስማት ለተሳናቸው መንገደኞች በምልክት እንዲግባቡ የሚያስችሉ ቴክኖሎጅዎች ተገጥመዋላቸዋል መባሉን የኤፍ ቢ ሲ ዘገባ ያመለክታል።


በተጨማሪም የደህንነት ካሜራ እና መሰል ቴክኖሎጅዎች መኖራቸው ተመላክቷል።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትሩ አለሙ ስሜን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።


የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ ከተማ አስተዳደሩ ያቀረባቸው ዘመናዊ አውቶብሶች በከተማው የሚስተዋለውን የትራፊክ መጨናነቅ በመቀነስ ረገድ የማይተካ ሚና አላቸው ብለዋል።

ይህን ተሞክሮ ወደ ሌሎችም አካባቢዎች ለማዳረስ እንደሚሰራም ጠቁመዋል።


አውቶብሶቹ 3 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ወጪ እንደተደረገባቸው ተገልጿል።


ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 04 ቀን 2015 ዓ.ም
በስመ አብ፤ ወወልድ፤ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ
በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ወቅታዊ ጉዳይ ከመንግሥት ጋር
እየተደረገ ስለሆነው ውይይት እና የካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊደረግ ስለታሰበው ሰላማዊ
ሰልፍ አስመክቶ የተሰጠ መግለጫ

ሮሜ ፭፤፫-፬ “ መከራ ትእግስትን እንዳያደርግ፤ ትእግስትም
ፈተናን፤ ፈተናም ተስፋን እንዳያደርግ እያወቅን በመከራችን
ደግሞ እንመካለን”

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን!
በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቅርቡ ከቤተ ክርስቲያናችን
ሃይማኖታዊ፤ ቀኖናዊ እና አስተዳደራዊ ሥርዓት ፍጹም ሕገ
ወጥ በሆነ መንገድ በመደራጀት የቤተ ክርስቲያንን መብትና
ጥቅም የጎዳ ተግባር መፈጸሙ ይታወሳል፡፡ የተከበረውን
የአበው ሐዋርያዊ ሢመተ ኤጲስ ቆጶስነት ሥርዓት
በመፈጸማቸው ምክንያት በተፈጠረው የቤተ ክርስቲያንን
ሉዓላዊ ክብርና ልዕልና የማቃለል፣ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ
ውለታ የዘነጋ፣ ሕልውናዋን እና አንድነቷን ለመናድ የተደረገ
ከፍተኛ ጥቃት በመፈጸሙና መንግሥትም የቤተ
ክርስቲያናችንን ሕግና ሥርዓት፣ እንዲሁም ተቋማዊ ሕልውና
እንዳያስከብር እና እንዳያከብር በተደጋጋሚ ሲጠይቅ ቆይቷል፡፡
ከዚህም ውስጥ ቅዱስ ሲኖዶስ በየካቲት ፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
ባወጣው መግለጫ መንግሥት በዚሁ አካሄድ ሕግ እየጣሰ እና
የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር እና ልእልና እያዋረደ የሚቀጥል
ከሆነ ቤተ ክርስቲያን መንግሥት የጣሰውን ሕግ መሠረት

በማድረግ መብቷን ለማስከበር እስከ አሁን ድረስ ፍጹም
ሰላማዊ የሆነውን እንቅስቃሴዋን አድማሱን በማስፋት በየካቲት
፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለማድረግ ያቀደችውንና ያሳወቀችውን ሀገር
አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ያለማንም ከልካይነት
በራሷ አደባባይ የምታከናውን መሆኑን ስታሳውቅ ቆይታለች፡፡
በዚሁ መሠረት መንግሥት ቅዱስ ሲኖዶስ በመግለጫው
የሰጠውን ቀነ ገደብ ከግምት ውስጥ በማስገባትና ጥሪውን
በመቀበል በየካቲት ፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለአስቸኳይ ውይይት
ዝግጁ መሆኑን በተመረጡ የሀገር ሽማግልዎች አማካኝነት
መልእክቱ ሲደርሰን ካለው ወቅታዊ የሰላም እና ጸጥታ ሁኔታ
አንጻር ጥሪውን በመቀበላችን በብፁዕ ወቅዱስፓትርያርክ
የተመራ አሥራ ሁለት ብፁዓን ሉቃነ ጳጳሳት ፣ የኢፌዴሪ
ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣
ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የሀገር
ሽማግልዎች በተገኙበት ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በውይይቱም የተነሱት ነጥቦች በዋንኛነት ቤተ ክርስቲያን
ሃይማኖታዊ፤ ቀኖናዊ እና አስተዳደራዊ ሕግን መሠረት ባደረገ
መልኩ ጠብቃ የምትሠራ እና ከዚህ ውጭ ምንም አይነት
ድርድር የልለው መሆኑን ገልጻለች፡፡ በዚህም መነሻ መንግሥት
የቤተ ክርስቲያንን አቋም በመቀበል ወደፊትም የቤተ
ክርስቲያንን አንድነት እና ሉዓላዊነትን በጠበቀ መንገድ
እንደሚሠራ አረጋግጧል፡፡
በዚህ የፈተና ጊዜ ውስጥ የቅዱስ ሲኖዶስን መመሪያ በመቀበል
ራስን የቤተ ክርስቲያን ሕልውና መስዋእት አድርጎ በማቅረብ፤
በክርስቶስ ደም የከበረችውን ቤተ ክርስቲያንን የመጠበቅ እና
የማስጠበቅ ከጸጉር መላጨት እስከ ገመድ መታጠቅ በእንባና
በዋይታ መላው ሕዝበ ክርስቲያን ሀዘናችሁን የገለጻችሁበት

መንገድ የቤተ ክርስቲያን ሕልውና ማስጠበቅ መሠረት ሆኗል፡፡
በዚህም ሂደት ሕይወታቸውን በሰማእትነት፤ አካላችሁን ለአካል
ጉዳት፤ ኑሯችሁን ለፈተና ፤ ለስደት፤ ለእንግልት እንዲሁም
ለእስራት አሳልፋችሁ የሰጣችሁ ልጆቻችን ቅዱስ ሲኖዶስ
ሁልጊዜም ውለታችሁን ሲያስታውስ የሚኖር ሲሆን የጉዳት
ሰለባ ለሆኑቱም መንግሥት የድርጊቱን ፈጻሚዎች ለይቶ በሕግ
አግባብ ተጠያቂ እንደሚያደርግ እና አሁን ላይ እስር፤ ወከባ፤
እንግልት እየተፈጸመባቸው ያለት ብፁዓን ሉቃነ ጳጳሳት፤
የሀገረ ስብከት ሠራተኞች፤ አገልጋይ ካህናት እና በተለያዩ
አደረጃጀቶች የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱን ልጆች ችግሩ
በአስቸኳይ እንዲቆምና የታሠሩትም እንዲፈቱ፤
አገልግልታቸውን በሰላምና በነጻነት መስጠት እንዲችሉ
ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
በትናትናው እለት ከመንግሥት ጋር ባደረግነው ውይይት
መንግሥት የቤተ ክርስቲያኒቱን አቋም ሙሉ በሙሉ የተቀበለ
ቢሆንም ይህንን ለማስፈጸም የሚያስችል የአፈጻጸም የድርጊት
ጊዜ የሚያስፈልግ በመሆኑ እሁድ የካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
እንዲካሔድ የተወሰነው ሀገር ዓቀፍ እና ዓለም አቀፍ የአደባባይ
ሰላማዊ ሰልፍ ለተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ቅዱስ ሲኖዶስ
ወስኗል፡፡
በዚሁ እለትም ሕዝበ ክርስቲያኑ ሁለም በየአጥቢያችሁ
በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ዓውደ ምሕረት ላይ ባለመቅረት
የተለመደውን የእለተ ሰንበት የሥርዓተ ቅዳሴ፤ የጸሎት፣
የምሕላ እና የትምህርተ ወንጌል ከወትሮው በተለየ የመንፈሳዊ
ሥርዓት በማከናወን እንድታሳልፉ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
የተከበራችሁ ውድ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን፤

ቅዱስ ሲኖዶስ በየካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም የጠራውን ሀገር
አቀፍና ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ለተወሰኑ ቀናት
እንዲተላለፍ ያደረገው የአቋም ለውጥ አድርጎ ሳይሆን
አስቀድማ ቤተ ክርስቲያናችን በሮቿን ለሰላም ክፍት በማድረግ
ባስተላለፈችው ጥሪ እና በአስቀመጠችው ቀነ ገደብ መሠረት
በመንግሥት በኩል ወዲያውኑ ችግሩን ለመፍታት ፍላጎት
በማሳየቱ ምክንያት ብቻ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
ነገር ግን መንግሥት የገባውን ቃል እና የወሰነውን ውሳኔ
የማይፈጽም ከሆነ መንፈሳዊ ተጋድሏችን የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ይህ ሂደት በባህሪው ረዥም ተጋድል እና ጽናት የሚጠይቅ
በመሆኑ እስከ አሁንም በፍጹም አንድነት እና መደማመጥ
የቅዱስ ሲኖዶሱን ድምጽ እየሰማችሁ በአንድነት እና በሕብረት
እንደቆማችሁት ሁሉ ወደፊትም የቅዱስ ሲኖዶስን ድምጽ
በትጋት እንድትጠብቁ እያሳሰብን በሕግ የተያዙት ጉዳዮችም
የሕግ ሂደታቸውን ተከትለው የሚቀጥሉ መሆኑን እና እኛም
በልዩ ሁኔታ የምናውቃቸው መሆኑን እንገልጻለን፡፡
መንግሥትም የቤተ ክርስቲያንን ጥሪ ተቀብሎ የውይይት
መድረክ በማዘጋጀት የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በማክበር
በውሳኔው መሠረት የሚፈጸም መሆኑን ስላረጋገጠልን ቤተ
ክርስቲያን ታመሰግናለች፡፡
በተጨማሪም በዚህ የፈተና ወቅት በየደረጃው የምትገኙ በሀገር
ውስጥ እና በመላው ዓለም የምትገኙ የቤተ ክርስቲያናችን
የሥራ ኃላፊዎች፤ ሉቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ መነኮሳት፤
አገልጋይ ካህናት፤ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች፤ ልዩ ልዩ
የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ ማህበራት እና መላው
ምእመናንና ምዕመናት እንዲሁም ከቤተ ክርስቲያኗ ጎን
የቆማችሁ እና አጋርነታችሁን የገለጻችሁ የሃይማኖት

ተቋማት፤ የሕግ ባለሙያዎች፤ ግለሰቦች፤ የማህበረሰብ
አንቂዎች፤ የጥበብ ሰዎች፤ የሰብዓዊ መብት ተቋማት እና
በዚህ ሂደት ውስጥ ድጋፍ ስትሰጡ የነበራችሁ የተለያዩ አካላት
ቤተ ክርስቲያን እያመሠገነች ወደፊትም ልዩ ዕውቅና የምትሰጥ
መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
በመጨረሻም ቅዱስ ሲኖዶስ በጀመረው ፍጹም ሰላማዊ ና ሕጋዊ መንገድ ከመንግሥት ጋር የደረስንበትን ውጤት በየጊዜው የምናሳውቃችሁ ስለሆነ እንደዚህ ቀደሙ ፍፁም በሆነ
መንፈሳዊ ጨዋነት የቅዱስ ሲኖዶስን መልእክት እንድትጠባበቁ፤ አሁንም ቢሆን ያለመዘናጋት ቤተ
ክርስቲያናችሁን በጥብቅ ሁኔታ እንድትጠብቁ እና ቤተ
ክርስቲያናችሁ ላይ የሚያጋጥሙትን ችግሮች ሁሉ በተዋረድ
ላለው መዋቅራችሁ እንድታሳውቁ አባታዊ መልእክታችንን
እናስተላልፋለን፡፡
ያዕቆብ መልእክት ፩፤፪-፫ “ወንድሞቼ ሆይ የእምነታችሁ
መፈተን ትእግስትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፤ ልዩ ልዩ
ፈተና ሲደርስባችሁ እንደሙሉ ደስታ ቁጠሩት”
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
የካቲት ፬ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የኢትየጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ባለፉት ስድስት ወራት የነበረው የስራ አፈጻጸም ከ90 በመቶ በላይ መሆኑን ገለጸ።

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽ ስራዎች ኮርፖሬሽን የስድስት ወራት አጠቃላይ የሥራ አሰፈፃፀም 90.3 ደርሶል ሲል ዛሬ በሰጠው መግለጫ ገልፃል፡፡

ኮርፖሬሽኑ የግማሽ ዓመት የገቢ መጠኑ 3.20 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ዮናስ አያሌው ገልፀዋል፡፡

የ2015 በጀት ዓመት የስድስት ወር አፈፃፀሙ ያቀረቡት ኢ/ር ዮናስ በተጠቀሰወስ በጀት ዓመት 30 የህንፃ ግንባታ ፕሮጀክቶች፣23 የመንገድና ድልድልይ ግንባታ ፕሮጀክቶች፣ እና 8 የውሃ ኃብት ልማት ግንባታ ፕሮጀክቶች በአጠቃላይ 62 ፕሮጀክቶች ከ45.2 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ የኮንትራክት ዋጋ እየተከናወነ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

የህነፃ ግንባታ ፕሮጀክት የስራ አፈፃፀም 107 በመቶ፣የመንገድና ድልድይ ግንባታ ፕሮጀክት 67.9 በመቶ የውሃ ኃብት ልማት ፕሮጀክት 99 በመቶ እንዲሁም የቤት ልማት ግንባታ ፕሮክቶች የስራ አፈፃፀም 87.37 በመቶ እንደሆነም ተገልፃል፡፡

እንደ ኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፋፃሚ ገለፃም ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 599.5 ኩንታል የግብርና ምርት ማምረቱን ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን በርካታ የሪፎርም ስራዎች እያከናወነ እንደሚገኝና የለውጥ አምጪ መሳሪያዎችን እንደ አይ ኤስ ኦ እና ካይዘን ትግበራ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ተገልፃል፡፡

በአቤል ደጀኔ

የካቲት 04 ቀን 2015 ዓ.ም
ይቅርታ ጠይቀዋል!

በሕገ ወጡ ቡድን የጵጵስና ልብስ አልብሶ ሾሜዎታለሁ ካላቸው መነኮሳት መካከል ከኢየሩሳሌም የመጡት አባ ንዋየሥላሴ አክሊሉ ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጠውን ዕድል በመጠቀም በመንበረ ፓትርያርክ በመገኘት አስኬማቸውንና አርዌ በትሩን ለሕጋዊዋ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሢኖዶስ በማስረከብ ቤተክርስቲያንንና ምእመናንን ይቅርታ ጠይቀዋል።


በይቅርታ ደብዳቤያቸውምሰሞኑን በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ከቅዱስ ሲኖሱ እውቅና ውጪ አዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ሲካኼድ ከኢየሩሳሌም መጥቼ ከተሾሙት አንዱ ነበርኩ።

በዚህ ምእመናንን ባሳዘነ ቅዱስ ሲኖዶስ ቃለ ውግዘት ባስተላለፈበት ሕገ ወጥ ሢመት ውስጥ ባለማወቅና ነገሩን ሳላጣራ የገባሁበት በመሆኑ በእጅጉ የተጸጸትኩና በዚህም ተግባር ያዘንኩ መሁኑን በይቅርታ ልብ ለመግለጥ እወዳለሁ።

በመሆኑም በዛሬው እለት ቅዱስ ሲኖዶስ በሠየመው አቀራራቢና በይቅርታ ኮሚቴ አማካኝነት በቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ መሠረት በተከፈተው የይቅርታና የምሕረት በር ወደ እናት ቤተክርስቲያኔ እና የመንፈስ ቅዱስ አባቶቼ እንዲሁም ምእመናን ለይቅርታ የቀረብኩ ስለሆነ ቋሚ ሲኖዶሱ በምልዓተ ጉባኤው ውሳኔ መሠረት ይቅርታዬን በአባትነት መንፈስ ይቀበለኝ ዘንድ በታላቅ ትህትና እጠይቃለሁ ብለዋል ።

@EOTC TV
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማው ለሚገኙ የተለያዩ ተቋማት አመራሮች አዲስ የጥቅማ ጥቅም መመሪያ ማጽደቁ ተሰምቷል፡፡

መመሪያው በከተማ አስተዳደሩ ስር ያሉ ቢሮዎች ፣ኤጀንሲዎች ፣ ክፍለ ከተማ እና ወረዳ ውስጥ ያሉ አመራሮችን የሚያጠቃልል መሆኑንም ተነግሯል።
የጥቅማ ጥቅም መመሪያው ከታክስ ነጻ የሆነ ክፍያን፣ ቤት ለሌላቸው አመራሮች ቤት መስጠትን እንዲሁም ቤት ላላቸው አመራሮች የቤት እድሳት ወጪን መሸፈን እንዲሁም የተለያዩ ቁሳቁሶችን ማቅረብን ያካትታል። ሆኖም የጥቅማ ጥቅም መመሪያ ከአመራር ውጭ ያሉ የበታች ፈጻሚዎችን አይመለከትም ተብሏል።

በብር ተሰልቶ የሚከፈለውና ከታክስ ውጭ ሆኖ በተለያየ እርከን ላሉ አመራሮች የሚሰጠው ጥቅማ ጥቅም ከፍተኛው በወር 15 ሺህ 200 ብር ሲሆን ዝቅተኛው ደግሞ 5 ሺህ 800 ብር መሆኑን የዋዜማ ሬድዮ ዘገባ ያመለክታል።
ከዚህ ቀደም ለአመራሮች በጥሬ ገንዘብ የሚሰጠው ከፍተኛው ድጎማ ስምንት ሺህ ብር አካባቢ ሲሆን ዝቅተኛው ደግሞ ሁለት ሺህ ብር ገደማ ነበር። በጥሬ ገንዘብ ይሰጥ የነበረው ጥቅማ ጥቅም አሁን ላይ በእጥፍ አድጓል።

ለአመራሮች እንዲሰጥ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በጸደቀው መመሪያ ውስጥ የተካተቱት የማይመለሱ ላፕቶፕ ኮምፒውተር ፣ ሞባይል ስልክ እዲሁም የቤት እድሳት ወጪዎች ይገኙበታል ተብሏል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 06 ቀን 2015 ዓ.ም
በተርክዬ የማቾች ቁጥር ከ33ሺህ በላይ ደረሰ፡፡

በተርክዬ ከሳምንት በፊት በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የማቾች ቁጥር ከ33 ሺህ በላይ መድረሱ ታውቋል፡፡

እስካሁን ድረስ በቱርክዬ 29ሺህ 600 ያህል ዜጎች የሞቱ ሲሆን በጎረቤቷ ሶርያ ደግሞ 4ሺህ 500 ዜጎች መሞታቸው ነው የተገለጸው፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንዳስታወቀው ከመሬት መንቀጥቀጡ ጋር በተያያዘ በሶሪያ እስከ 5 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል፡፡
ባሁኑ ሰአትም 900 ሺህ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚፈልጉም ነው ያስታወቀው፡፡

አደጋው በደረሰበት ጋዚያንቴፕ አቅራቢያ የሚኖሩ ሶርያዊያን እጅግ በከፋ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አመልክቷል፡፡
ጋዚያንቴፕ የተባለችው የቱርክ ግዛት፣ ከሶርያ ጋር የምትዋሰን ሲሆን በአካባቢው የሶርያ አማጺያን የሚንቀሳቀሱበት ነው፡፡
በዚህም ምክንያት ሰብአዊ እርዳታ የማድረሱን ስራ እጅግ ከባድ እንዳደረገው ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

የካቲት 06 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast
Website https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆኗል፡፡



የትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡትን ከግምት ውስጥ በማስገባት እና በተመሳሳይ ሁኔታ ፈተናው የተሰጠበትን አግባብ እና ሌሎች ጉዳዮችን ከግምት በመውሰድ ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚያገለግል የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) እንዲተገበር መወሰኑ ይታወቃል።


በዚሁ መሰረት በ2015 የትምህርት ዘመን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው በ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎችን አነስተኛ የመግቢያ ውጤት መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ ነገር ግን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የ Remedial ፕሮግራም ተጠቃሚዎች ይሆናሉ ተብሏል።


1. በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30% ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣ 180 ከ 600 እና 150 ከ 500) የተቆረጠ መሆኑን።

2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት(ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉት የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ ይሆናል ተብሏል።


ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 06 ቀን 2015 ዓ.ም
የአፍካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በሰላም ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል…የአዲስ አበባ ፓሊስ

የህብረቱ ጉባኤ ያለአንዳች ችግር በሰላም እንዲጠናቀቅ ሰፊ ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮምሽን አስታውቋል፡፡
የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮምሽን የህዝብ ግንኙነት ዳሬክቶሬት ዳሬክተር ም/ኮ ማርቆስ ታደሰ ለኢትዮ ኤፍኤም እንደተናገሩት፣ ፓሊስ የህበረቱ ጉባኤ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ሰፊ ስራዎች መስራታቸውን ነግረውናል፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ባለፉት ቀናትም ወታደራዊ የተግባር ልምምዶች ተካሂደዋል ብለዋል፡፡
የእንግዳ ማረፊያዎችን ጨምሮ ከፀጥታ፤ከትራፊክ እና ከወንጀል አንፃር ሊያጋጥሙ የሚችሉ ሁኔታዎችን በማጥናት፣ የሞተር ሳይክል እና ሌሎችም ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች ገደብ ሊጣልባቸው እንደቻለ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ የእንግዳ ማረፊያ ባለቤቶች በዚህ ወቅት የሚቀበሏቸውን እንግዶች ማንነት አስቀድሞ ማወቅና ህብረተሰቡንም አካባቢውን ነቅቶ መከታተል እንዳለበት፣የሚያጠራጥሩ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙም ለአካባቢ ፓሊስ መጠቆም እንደሚገባም አስታውቀዋል፡፡

ለእንግዶች ቅድሚያ በመስጠት የትራፊክ ፓሊስ አባሎችን ትእዛዝ በማክበር፤ በጉባኤው ሊዘጉ የሚችሉ መንገዶችን ታሳቢ በማድረግ ህብረተሰቡ ቀና ትብብር እንዲያደርግም ጥሪ ቀርቧል፡፡

በየውልሰው ገዝሙ

የካቲት 06 ቀን 2015 ዓ.ም
አሜሪካ ዜጎቿ በአስቸኳይ ሩሲያን ለቀው እንዲወጡ አስጠነቀቀች፡፡

አሜሪካ ዜጎቿ ከሩሲያ በፍጥነት ለቀው እንዲወጡ ያሳሰበችው በሩሲያ ያሉ የህግ አስከባሪዎች እየተፈፀመ ነው በተባለው የዘፈቀደ አስር እና የማዋከብ ድርጊት መሆኑን ገልፃለች፡፡

በሞስኮ የሚገኘው የአሜሪካ ኢንባሲ ዜጎች በፍጥነት የሩሲያን ምድር ለቀው መውጣት አለባቸው ብሏል፡፡
የአሜሩካ ኢንባሲ እንደሚለው ከሆነ ዜጎች ያለአግባብ ታስረውብኛል እንዲሁም በሚስጥር ችሎት ያለ ማስረጃ ጥፋተኛ እየተባሉ ዘብጥያ እየወረዱ ስለሆነ በአስቸኳይ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ሲል ተናግሯል፡፡

የክሪምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ በበኩላቸው እንዲህ ያለ ነገር ከዚህ ቀደምም የተደረገ ነው ምንም አዲስ ነገር የለውም ብለዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ
የካቲት 06 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast
Website https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ጎፋ ገብርኤል ጀርባ የተነሳዉ እሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዉሏል።


ዛሬ የካቲት 6 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 9:20 ሰዓት ላይ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ወረዳ 6 ጎፋ ገብርኤል ቤተክርስታያን ጀርባ ያገለገሉ አሮጌ ጎማዎች ላይ የተነሳዉ የእሳት ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ዉሏል።


የእሳት አደጋዉ ከጎፋገብርኤል ቤተክርስቲያን ጀርባ በሚገኝ ጋራዥ አጠገብ ባለ ክፍት ቦታ የተከማቸ አሮጌ ጎማ ላይ ከደረሰዉ ጉዳት ዉጪ በቤተ ክርስቲያኑ ላይም ሆነ በሰዉ ላይ ምንም ጉዳት አልደረሰም ተብሏል።

በየውልሰው ገዝሙ
የካቲት 06 ቀን 2015 ዓ.ም