Ethio Fm 107.8
20.4K subscribers
7.52K photos
16 videos
4 files
2.3K links
በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!
Download Telegram
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 13 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2022/23 በጀት ዓመት 88.7ቢሊዮን ተቀማጭ ማሰባሰቡን እና 13 ቢሊዮን ያልተጣራ ብር ማግኘቱን ባንኩ ገልጿል።

ባንኩ በ2022/23 በጀት ዓመት በስድስት ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ይህንን እንዳሳካ ዛሬ በሰጠዉ መግለጫ ገልጿል።
ከባንኩ ጠቅላላ እንቅስቃሴም 13 ቢሊዮን ያልተጣራ ብር ማግኘቱን ባንኩ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ አቢ ሳኖ የባንኩን የ6ወራት አፈፃፀም ያቀረቡ ሲሆን፣ በስድስት ወራት ዉስጥ ከተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ 88.7 ቢሊዮን ተቀማጭ መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን፣ የባንኩ አጠቃላንይ ተቀማጭ ሒሳብ በ2022 ከነበረበት 890.1 ቢሊዮን ወደ ብር 978.8 ቢሊዮን መድረሱን ገልፀዋል።

ብድር በማስመለስ በኩል በግሉ ዘርፍ እና በመንግስት ለሚካሄድ የልማት ፕሮጀክት 55.8 ቢሊዮን ብድር ተመላሽ መሰብሰብ ተችሏል ብለዋል።

የዉጭ ምንዛሬን በተመለከትም 1.7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር መሰብሰቡንና የዕቅዱን 11 በመቶ ማሳካት መቻሉን ገልፀዋል።


የገቢና ትርፍ አፈፃፀም ላይም በስድስት ወራት ዉስጥ ከተለያዩ ምንጭች 58.7ቢሊዮን ገቢ መገነቱ ተገልጿል።

በ2ኛ ሩብ ዓመትም የባንኩ ጠቅላላ ሀብተ 1.2 ትሪሊዮን መድረሱ የተለፀ ሲሆን በብር 60 ቢሊዮን አድጓል ተብሏል።

ባንኩ ተደራሽነቱን በማስፋት 55 ኣዳዲስ ቅርንጫፎችን የከፈተ ሲህን በዚህም የባንኩ ቅርጫፎች 1 ሺህ 879 የደረሱ ሲሆን፣130 አዲስ የሲቢኢ ኑር ወይም ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ማስጀመሩንና 1 ሺህ 815 ለዚህ አግልግሎት ክፍት የሆኑ መስኮቶች አዘጋጅቻለዉ ብሏል።

በዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት 8.8 ሚሊዮን የኤቲኤም የካርድ ተጠቃሚ እና 6.3 ሚሊዮን የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚ ደርሰናል ብለዋል።

ባንኩ የዲጂታል አማራጮች አማካይነት ከብር 1.3 ትሪሊዮን በላይ ክፍያዎች መፈፀማቸዉንም የባንኩ ፕሬዝዲንት አቢ ሳኖ ገልፀዋል።

በአቤል ደጀኔ
ጥር 25 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
ስለ ኮሌራ ወቅታዊ ሁኔታ---የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

በኢትዮጵያ ኮሌራ ወረርሽኝ ነሃሴ 1/2014 በኦሮሚያ ክልል በባሌ ዞን ዉስጥ በሃረና ቡሉክ ወረዳ የተከሰተ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ወረርሽኙ ወደ አጎራባች ወረዳዎች ፣ ዞኖች የተዛመተ ሲሆን በኦሮሚያ በባሌ ፣ ጉጂ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች 8 ወረዳዎች እና በሶማሌ ክልል ሊባን ዞን 2 ወረዳዎች ተዛምቶ በአጠቃላይ በ10 ወረዳዎች የሚገኙ 66 ቀበሌዎችን ለማካለል ችሏል፡፡

የኮሌራ ወረርሽኝ በታየባቸው ሁለቱ ክልልች በ 10 ወረዳዎች ዉስጥ ወደ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ይኖራሉ፡፡
ከተከሰተበት ቀን ከነሃሴ 1/2014 እስከ ጥር 22/2014 በኦሮሚያ ክልል በባሌ ዞን 6 ወረዳዎች እንዲሁም በሶማሊ ክልል በሊባን ዞን 2 ወረዳዎች የተከሰተ ሲሆን ለበሽታው መከሰት እና መስፋፋት እንደ ዋና ምክንያት የሚሆነው የንጹህ ዉሃ አቅርቦት እና የመጸዳጃ ቤት ሽፋን አነስተኛ የሆነባቸው ወረዳዎች ሲሆኑ ይበልጥ እንዲባባስ ያደረገው አከባቢው በድርቅ የተጎዳ መሆኑ ነው፡፡

ወረርሽኙን ለመቆጣጠር እና ለመከላከል እንዲሁም ወደ ሌሎች አከባቢዎች እንዳይስፋፋ በየደረጃዉ (በፌደራል፣ በክልል ፣ በዞን ፣ በወረዳ ፣ በጤና ተቋማት እና በማህበረሰብ) ደረጃ ባሉ የመንግስት ተቋምት እና አጋር ድርጅቶች ጋር በቅንጅት ጠንካራ የጋራ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል፡፡
የህክምና አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ 14 የኮሌራ ህክምና ማዕከሎች (Cholera Treatment Center/CTC) ተቋቁመዉ ሲያገለግሉ የቆዩ እና እያገለገሉ ያሉ ማዕከላት ሲኖሩ እነሱም በበርበሬ ፣ ብጊርጃ ፣ በጎሮ እና በኔንሴቦ ወረዳዎች የገኙበታል።
በመሆኑም በአሁኑ ወቅት በሀገራችን እየተከሰተ ያለውን የኮሌራ ወረርሽኝ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስቆም እንዲሁም የማህበረሰቡን የበሽታ ተጋላጭነት ለመቀነስ መንግስት ከአጋር የልማት ድርጅቶች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ስራዎችን እየሰራ በመሆኑ ወረርሽኙ የመዛመት አቅሙን በመቀነስ በሶማሊ ክልል ወረርሽኙ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ላይ ሲገኝ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል በባሌ ዞን 4 ወረዳዎች ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር መቻሉን ተረጋግጧል፡፡

@የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ከኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ አዋጅ
በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረው አስቸኳይ ምልዐተ ጉባኤ በኢትዮጵያ የኦሮሚያ እና የብሔር ብሔረሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስ በሚል በሕገ ወጥነት በቀድሞ ስማቸው አባ ሳዊሮስ የተባሉ ግለሰብ መሪነት ይህ መግለጫ እስከተሰጠበት ቀን ድረስ በተለያዩ ክልሎች እና የፌዴራል መንግሥት በሚመራቸው ቦታዎች ውስጥ በሚገኙ የቤተ ክርስቲያኗ አህጉረ ስብከት የሆኑትን ሥርዓተ አምልኮዋን የምትፈጽምባቸው በየመዋቅሩ የሚገኙ አስተዳደር ቢሮዎችን ከሕግ አግባብ ውጭ የቤተ ክርስቲያኗ እምነት ተከታይ ያልሆኑ ግለሰቦችን በማካተት በመንግሥት ልዩ ኃይል ድጋፍ በመውረር እና በመስበር የሕግ አግባብነት በሌላቸው እንዲሁም መብት እና ጥቅም ሳይኖራቸው በማሸግ ቤተ ክርስቲያን ላይ ወረራ እየተፈጸመባት የሚገኝ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ለመረዳት ችሏል፡፡
መንግሥትም ሰላም እና ደህንነትን ከማስጠበቅ ባለፈ የሕይወት እና የአካል ደህንነት መብትን እንዲሁም የመንቀሳቀስ መብትን በመገደብ ያለአግባብ ታግተው መቆየታቸውን ከሊቃነ ጳጳሳት ውስጥ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን ከዚህ ቀደም መግለጻችን የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ ድርጊታቸውም ሳይታቀቡ በጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 3፡30 አካባቢ የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑትን ብጹዕ አቡነ ያሬድን በሕገ ወጥ መልኩ የዜግነት መብታቸው ተጥሶ በደረቅ ሌሊት በማሰር እና በማዋከብ ከሀገረ ስብከታቸው ለቀው እንዲወጡ የተደረጉ ሲሆን እንዲሁም የተለያዩ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳትን ወደየ አህጉረ ስብከታቸው እንዳይሄዱ ማስፈራሪያ በመላክ የቤተ ክርስቲያችንን ክብር እና ልዕልና እጅጉን የሚጎዳ እና አሳዛኝ ድርጊት እየተፈጸመባት ይገኛል፡፡ በተጨማሪም የየሀገረ ስብከት ሥራ አኪያጆችንና ሠራተኞችን፤ አገልጋይ ካህናትንና ምእመናን በሕገ ወጥ መልኩ በማሰር እንደ መንግሥት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ባለመወጣቱ ቤተ ክርስቲያናችን እጅጉን አዝናለች፡፡
ከዚህም አልፎ መንግሥትም በቤተ ክርስቲያችን በኩል በተደጋጋሚ የተሰጠውን ማሳሰቢያ ችላ በማለቱ ምክንያት በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በሻሸመኔ ከተማ ሕገ ወጦቹ መንግሥትን ተገን በማድረግ የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በሕገ ወጥ መልኩ ወረራ ለመፈጸም ባደረጉት እንቅስቃሴ ቤተ ክርስቲያንችንን ለመጠበቅ በወጡ ምእመናን ላይ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ የአደባባይ የግድያ ወንጀል ተፈጽሟል፡፡ ሌሎች በቁጥር ያልታወቁ ምእመናንም ላይ ከፍተኛ እና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
ይህንንም ሕገ ወጥ ተግባር በተመለከተ ተገቢውን ሕጋዊ የሰላም እና የደህንነት ከለላ እንዲያደርጉ ለሚመለከታቸው የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት በተደጋጋሚ ማሳሰቢያ ቤተ ክርስቲያናችን ብትሰጥም ይህንን ማሳሰቢያ ወደጎን በመተው መንግሥት ሕገ ወጡን ቡድን በመደገፍ እና በማስፈጸም ከላይ የተገለጹትን አሳዛኝ ድርጊቶች በይፋ በአደባባይ ፈጽሟል፡፡
ስለሆነም የኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በጠራው አስቸኳይ ጉባዔ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል፡፡
1. በብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት እና የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች፤ የክፍል ኃላፊዎች፤ ካህናት፤ አገልጋዮች እና ምእመናን ላይ የተፈጸመውንና እና እየተፈጸመ ያለውን ሕገ ወጥ እስር እና ወከባ ቅዱስ ሲኖዶስ በፅኑ አውግዟል፤
2. በጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በሻሸመኔ ከተማ በደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን፤ ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ የወጡት ምዕመናን ላይ ጭካኔ በተሞላ ሁኔታ የተፈጸመው ሕገ ወጥ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና የተፈጸመው አሰቃቂ የሞት ድርጊትን ፍጹም ታወግዛለች፤ ተገቢውን ሲኖዶሳዊ እና ሃይማኖታዊ ጸሎት በማድረግ በሁሉም አጥቢያ ሥርዓተ ፍትሐት እንዲፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
3. ቅዱስ ሲኖዶስ በጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም ባስተላለፈው ውሳኔ እና በሰጠው መግለጫ መላው የቤተ ክርስቲያኒቱ ተከታዮች ጾመ ነነዌን ሙሉ የሱባዔ ጊዜ በማድረግ ጥቁር ልብስ ያለውን ትርጓሜ በመግለጥ እንድንሰነብት መግለጫ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡
3.1. ለዚህም ዝርዝር አፈጻጸም መመሪያ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ከጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 3 ቀናት በመላው ዓለም የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የምትገኙ ማናቸውም ካህናት እና ምዕመናን ሙሉ ጥቁር ልብስ በመልበስ በየአብያተ ክርስቲያናት እና በገዳማት ያለውን ሥርዓተ ጸሎት እንድትመሩ እና እንድትከታተሉ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
3.2. በየትኛውም እንቅስቃሴ ይህንን ጥቁር ልብስ በመልበስ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ንቁ በመሆን እንድትፈጽሙ፤ ሆኖም ግን ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ዓለም አቀፍ የጸሎትና የምህላ መርሐ ግብር ካወጀበት ቀን በኃላ በተለያዩ ከተሞች የጥቁር ልብስን ሆነ ተብሎ ከገበያ እንዲወጣ እየተደረገ መሆኑን በመረዳታችን ምዕመናን ያላችሁን ተመሳሳይ አልባሳት በመጠቀም የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔን በእንቅስቃሴያችሁ ሁሉ እንድትፈጽሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
3.3. በነዚህ ቀናት ውስጥ አገልግሎቱ በድምጽ ማጉያ እንዲከናወን እና የሙሉ ጊዜ ሆኖ በሰባቱ የጸሎት ሰዓታት እየተጠበቀ በተመሳሳይ ሰዓታት ለአምስት ደቂቃ ያህል በማያቋርጥ ደወል በመደወል የማስተጋባት ሥራ እንዲሠራ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
3.4. ይህንንም የየአህጉረ ስብከት፤ የወረዳ ቤተ ክህነት እና የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ሰበካ ጉባኤያት በመከታተል እንድታስፈጽሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
3.5. የአኃት አብያተ ክርስቲያናት፤ የኦርቶዶክስ ዓለም፤ እውነቱን የምታውቁና የምትደግፉ ማናቸውም ኃይማኖታዊም ሆነ ማህበራዊ ተቋማት እና ግለሰቦች የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ጥሪ በመደገፍ በአንድነት ትቆሙ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላፋለን፡፡
4. በነዚህ የጸሎትና የምሕላ ጊዜያት የደነደኑ ልቦች ወደ ልቦናቸው ተመልሰው የቤተ ክርስቲያኒቱን ጥሪ ሰምተው የማይፈጽሙ እንደሆነ
4.1. በየካቲት 5 ቀን 2015 ዓ.ም በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት እና ምእመናን ከጠዋቱ 11፡00 ጀምሮ በየአጥብያቸው በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት እስከ ጠዋቱ 1፡30 ድረስ ሥርዓተ ቅዳሴው ከተፈጸመ በኃላ ከጠዋቱ 2፡00 ላይ ሁሉም ገዳማት፣ አድባራት እና አብያተ ክርስቲያናት በተመሳሳይ ሰዓት ደወል በመደወል ምእመናን በሙሉ እስከ ጠዋቱ 2፡30 ድረስ እንዲሰባሰቡ በማድረግ ከየአጥቢያው በመነሳት የጥምቀተ ባህር ወይም የመስቀል አደባባይ ላይ ታቦተ ሕጉን በማክበር፤ በማጀብ በዝማሬ እና በእልልታ በአንድ ቦታ በመሰባሰብ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
4.2. የዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ዝርዝር አፈጻጸም መመሪያን በተመለከተ በአጭር ጊዜ ውስጥ የምናሳውቃችሁ መሆኑን አውቃችሁ ዝግጅት እንድታደርጉ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፡፡
5. ማንኛውም የመንግሥት የጸጥታ ኃይል ቤተ ክርስቲያን ያዘዘችውን ሰላማዊ ጥያቄ በሚከወንበት ማንኛውም የአገልግሎት ጊዜ ተግባራቱ ሰላማዊ መሆናቸውን በመገንዘብ ተገቢውን ጥበቃ የማድረግ ግዴታ እንዳለበት አውቆ እንዲያስፈጽም ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፤
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ
ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
በወቅታዊ ጉዳይ ከኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ፦


ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የተፈጠረው መለያየት ሰላማዊ በሆነ መንገድ፣ በውስጣዊ አሠራር መፈታት እንዳለበት መንግሥት ያምናል።


ሀገራዊ ተቋማት አንድነታቸውንና ጥንካሬያቸውን ጠብቀው እንዲዘልቁ ከዚህ በፊትም ሆነ ችግሮች በተፈጠሩ ጊዜ ሁሉ መንግሥት የሚጠበቅበትን ሲወጣ ቆይቷል። ይሄንን ጥረቱን አሁንም አጠናክሮ ይቀጥላል።

የተቋማቱን አንድነት የሚፈታተኑ ችግሮች ከውስጥ ሲነሡ በውይይትና በውስጣዊ አሠራር እንዲፈቱ ድጋፍ ሲያደርግ ነበር። በተጨባጭም ውጤት አምጥቷል።

ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የተፈጠረው መለያየት በሰላማዊ መንገድ በውይይትና በቤተ ክርስቲያኒቱ አሠራር መሠረት እንዲፈታ ሁሉም አካላት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት መወጣት ይኖርባቸዋል። የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ሁለቱን ወገኖች በማቀራረብ ችግሩ በሰከነ መንገድ እንዲፈታ ማድረግ አለባቸው።

አማኞች ችግሩን ከማወሳሰብና ለሌሎች አካላት መጠቀሚያ ከመሆን በመታቀብ ገንቢ ሚና ሊጫወቱ ይገባል። የጸጥታ አካላት የየአካባቢውን ሕዝብና የእምነት ተቋማት ሰላምና ጸጥታ ማስከበር ግዴታቸው ነው። ግጭት የሚያባብሱ አካላትንም ሥርዓት ማስያዝ አለባቸው። የሚዲያ አካላት ችግሩን የሚያባብሱ ነገሮችን ከማቅረብ መቆጠብ ይጠበቅባቸዋል። እንዲሁም መላው ሕዝብ ለችግሩ መፈታት የሚጠበቅበትን እንዲያደርግ መንግሥት ያሳስባል።

በሌላ በኩል እምነትና ብሔርን ተገን አድርገው ግጭት ለመፍጠር የሚያስቡ፣ ሀገር ለማፍረስ በተለያዩ መንገዶች ሞክረው ያልተሳካላቸው ኃይሎች፣ ችግሩ እንዲባባስና እንዳይፈታ ለማድረግ እየሠሩ መሆኑ ተደርሶበታል። መንግሥት ይሄንን ፈጽሞ አይታገሥም።

ችግሩን ለማባባስና በሕዝቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር፣ ብሎም ሀገርን ወደፈተና ለማስገባት በሚጥሩ አካላት ላይ መንግሥት ሕግ የማስከበር ሥራውን እንደሚሠራ በዚሁ አጋጣሚ ያሳውቃል።

ጥር 28 ቀን 2015 ዓ.ም

አዲስ አበባ

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ቅዱስ ሲኖዶስ በነነዌ ጾም የሚከናወነውን ሥርዓተ ጸሎት አስመልክቶ መግለጫ ሰጠ


በጾመ ነነዌ የሚከናወነውን ሥርዓተ ጸሎት አስመልክቶ ቅዱስ ሲኖዶስ አሁን መግለጫ ሰጥቷል፤ በዚህም የምእመናን ድርሻ ምን እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ሁሉም ምእመናን እና ምእመናት በጾመ ነነዌ በሦስቱም ቀናት ጥቁር ልብስ መልበስ፣ በጸሎት መርሐ ግብሩ ተገኝቶ ጸሎት መጸለይ እና የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እና የአባቶችን መልእክት ሰምቶ መተግበር እንደሚገባው ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል፡፡

የጸሎት መርሐ ግብሩም ጠዋት ኪዳን እና ምሕላ፣ ቅዳሴ፣ የሰርክ የዐውደ ምሕረት መርሐ ግብር እንዲሁም ማታ የቤተሰብ ጸሎት ናቸው፡፡

በመጨረሻም ምእመናን ለጸሎት ወደ ቤተ ክርስቲያን በሚሄዱበት ጊዜ ለጸሎት ከሚያስፈልጉ መጽሐፍት ውጪ ሌላም ምንም ዓይነት መፈክር ይዞ መምጣት የማይቻል መሆኑን አስረድተዋል።

ማኅበረ ቅዱሳን
ዛሬ በተጀመረው የህዝበ ውሳኔ ምርጫ ላይ በህግ ጥሰት የአንድ ምርጫ ጣቢያ ድምፅ አሰጣጥ ተቋርጧል::


ዛሬ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም በደቡብ ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች የህዝበ ውሳኔ ድምፅ እየሰጡ ሲሆን በአንድ የምርጫ ጣቢያ ሂደቱ ተቋርጧል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንዳስታወቀው በወላይታ ዞን ስር በሌ የምርጫ ማዕከል ‘ሶርቶ’ ቀበሌ ውስጥ የሚገኘው ሶርቶ 1 ምርጫ ጣቢያ ውስጥ የህግ ጥሰት መፈፀሙን አረጋግጫለሁ ብሏል።


በምርጫ ጣቢያው ድምፅ በመስጠት ሂደት ወቅት የቀበሌ አስተዳደር ሀላፊዎች በሶርቶ 1 ምርጫ ጣቢያ በመገኘት 105 የሚሆን የግለሰብ ጊዜያዊ መታወቂያዎችን ድምፅ ለመስጠት ለተሰለፋ ዜጎች በማደል ህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው ተገኝተዋል።


በዚህም የህግ ጥሰቱ እስከሚጣራ ድረስ ሶርቶ 1 ምርጫ ጣቢያ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱን እንዲያቋርጥ መወሰኑ ታውቋል።


ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ህዝበ ውሳኔው ያለ ምንም ሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲከናወን ጥሪ አቀረበ፡፡

ዛሬ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የሚገኙ ስድስት ዞኖች (ጋሞ፣ ወላይታ፣ ጎፋ፣ ጌዴኦ፣ ኮንሶ እና ደቡብ ኦሞ) እንዲሁም አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ አማሮ፣ ባስኬቶ፣ ዲራሼ እና አሌ) በሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔ የሰብአዊ መብቶችን ሁኔታ በሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች የሚከታተል የባለሞያዎች ቡድን ወደ ስፍራው ማምራቱን ገልጧል፡፡

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ እንዳሉት፣ ሕዝበ ውሳኔ የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከቶች ሰላማዊ በሆነ መንገድ የሚስተናገዱበት እና ዜጎች በሕዝባዊ ጉዳዮች የመሳተፍ መብታቸውን የሚተገብሩበት አንደኛው ሂደት መሆኑን ገልፀዋል።

ዶ/ር ዳንኤል አክለውም " ዜጎች ያለምንም መድሎ፣ ጫና እና ጣልቃ ገብነቶች በነጻነት ድምፅ መስጠት እንዲችሉ ሁሉም አካላት ግዴታቸውን እንዲወጡ” ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ኮሚሽኑ ከሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔ ጋር ተያይዞ ሰዎች ለሚገጥሟቸው የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች በነጻ የስልክ መስመር 7307 ላይ በመደወልም መረጃ እና ጥቆማዎችን ማድረስ እንደሚችሉም አስታውቋል፡፡

ዛሬ በተጀመረው የህዝበ ውሳኔ ምርጫ ላይ በህግ ጥሰት የአንድ ምርጫ ጣቢያ ድምፅ አሰጣጥ መቋረጡ መገለጹ ይታወሳል::

ምክንያቱ ደግሞ በምርጫ ጣቢያው ድምፅ በመስጠት ሂደት ወቅት የቀበሌ አስተዳደር ሀላፊዎች በሶርቶ 1 ምርጫ ጣቢያ በመገኘት 105 የሚሆን የግለሰብ ጊዜያዊ መታወቂያዎችን ድምፅ ለመስጠት ለተሰለፋ ዜጎች በማደል ህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው በመገኘታቸው መሆኑ ተነግሯል፡፡

በአቤል ደጀኔ
ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

"ከመንግስት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ" በሚል ርዕስ በጥር ፳፰ ቀን ፳፻፲ወ፭ ዓ/ም የመንግስት ኮምዩኒኬሽን የሰጠውን መግለጫ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ህዝብ ግንኙነት መምሪያ የተሰጠ መግለጫ።

በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በፍትሕ መንፈሳዊ እንዲሁም በሕገ ቤተክርስቲያን አንቀጽ ፲፱ ንኡስ አንቀጽ ፫ በተደነገገው መሠረት ጥር ፲፰ ቀን ፳፻፲ወ፭ ዓ.ም. ባካሄደው አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ በተፈጠረው ወቅታዊ የሃይማኖት፣ የቀኖና እና የአስተዳደራዊ ጥሰቶችን አስመልክቶ ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት ሕገ ወጥ ሲመተ ጵጵስና እና መፈንቅለ ሲኖዶስ ሙከራ በፈጸሙ ግለሰቦች ላይ ሃይማኖታዊ፤ ቀኖናዊ እና አስተዳደራዊ ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ የቤተ ክርስቲያናችን የበላይ አካል በኾነው ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጡ ውሳኔዎች እና መልእክቶች ተከታታይ መድረኮች በማዘጋጀት ስለ ተፈጠረው የሃገራችን ሕግ እና የሕገ ቤተ ክርስቲያን ጥሰት በቂ ግንዛቤ ሕዝባችን እንዲያገኝ በተደጋጋሚ ከቅዱስ ሲኖዶስ እና ከብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት አማካኝነት መግለጫ እና ማሳሰቢያ ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል።

ይሁንና "በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከመንግስት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ" በሚል ርእስ በጥር ፳፰ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም የሰጠውን መግለጫ አስመልክቶ፤ መግለጫው ያስቀመጣቸው ነጥቦች የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ክብር፤ ታሪክ፤ እና እውነታ ቸል በማለት በጉዳዩ ላይ የተሟላ መረጃ የሌላቸው ወገኖች የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲይዙ የሚያስችል መግለጫ በመኾኑ በመግለጫው አንኳር ነጥቦች ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ተከታዩን ምላሽ ሰጥቷል።

፩. በመግለጫው የመጀመሪያ አንቀጽ ላይ "ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የተፈጠረው መለያየት ሰላማዊ በሆነ መንገድ፣ በውስጣዊ አሠራር መፈታት እንዳለበት መንግሥት ያምናል" ያለውን በተመለከተ

፩.፩. እንደሚታወቅ በቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች መካከል የተፈጠረ መለያየት የለም። በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት በአባልነታቸው የሚታወቁ እና የቤተ ክርስቲያናችን አባቶች ተብለው እውቅና የሚሰጣቸው ነገር ግን አለመግባባት የፈጠሩ ብፁዐን አባቶች የሉም።

የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት የሰጠው መግለጫ፤ ብቸኛ ሕጋዊ ሰውነት ያላት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመንፈስ ቅዱስ በታች የቤተ ክርስቲያናችን የበላይ አካል የኾነው ቅዱስ ሲኖዶስ በቀኖናው መሠረት አውግዞ የለያቸውን ግለሰቦች አሁንም ሕጋዊ አካላት እንደኾኑ እና እውቅናም እንደሚሰጣቸው የሚያስረዳ መግለጫ ኾኖ ስላገኘነው ተገቢነት የሌለው ነው ብላ ቤተ ክርስቲያን ስለምታምን በመንግሥት ኮምዩኒኬሽን የተሰጠውን መግለጫ አትቀበለውም፤

፩.፪. ሰላማዊት የኾነች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የመጨረሻው የበላይ አካል በኾነው ቅዱስ ሲኖዶስ በውስጣዊ መንፈሳዊ እና አስተዳደራዊ አሠራሩ የሰጠውን የመጨረሻ ውሳኔ መንግሥት ያወጣው መግለጫ አሁንም የማይቀበለው መኾኑን የሚያመለክት ኾኖ አግኝተነዋል።

፩.፫. በመንግሥት መገናኛ ብዙኅን የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ድምጽ በማፈን አንድም መግለጫዎቿን እንዳይተላለፉ ከተደረገ በኋላ ይህንን የመንግሥት መግለጫ በእነዚሁ መገናኛ ብዙኅን እንዲተላለፍ በማድረግ ብዙኅኑ አድማጭና ተመልካች የተዛባ አረዳድ እንዲኖረው የሚያደርግ ይዘት ያለው መግለጫ መኾኑን ቤተ ክርስቲያን ትገነዘባለች፡፡

፪. በመግለጫው ሁለተኛ አንቀጽ ላይ "...የተቋማቱን አንድነት የሚፈታተኑ ችግሮች ከውስጥ ሲነሱ በውይይትና በውስጣዊ አሠራር እንዲፈቱ ድጋፍ ሲያደርግ ነበር" ያለውን በተመለከተ

፪.፩. በመግለጫው ከተጠቀሰው በተቃራኒ ቤተ ክርስቲያናችን ሕገ ወጥ ካለቻቸው ግለሰቦች እና ቡድኖች ጋር መንግሥት ጥምረት ፈጥሮ በመንቀሳቀስ ላይ መኾኑን በጥር ፳፯ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም. ቅዱስ ሲኖዶስ በሰጠው መግለጫ ማሳወቁ የሚታወስ ሲኾን፤ መንግሥት ከዚህ ድርጊቱ አለመቆጠቡን የሚያሳይ ሆኖ አግኝተነዋል፤

፪.፪. መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ እንደማይገባ በቃሉ የሚናገር ኾኖ ሳለ በተግባር ግን ይህ መግለጫ እስከ ተሰጠበት ሰዓት ድረስ መንግሥት የሕገ ወጦቹን ስብስቦች ድጋፍ ከመስጠት ድርጊቱ አለመቆጠቡ እና በምእመናን ላይ ግድያ እስከ መፈጸም፤ የቤተ ክርስቲያናቱን ቅጽር ተዳፍሮ ለሕገ ወጥ ቡድኖቹ በመሳሪያ የታጀበ ድጋፍ በመስጠት የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ቁልፍ ሰብሮ በማስወረር ጭምር የሚፈጽመውን ፍጹም ያልተገባ እና ሕገ ወጥ የኾነ ድርጊት ለአድማጭ እና ለተመልካች ኹሉ ግልጽ ኾኖ ሳለ፤ መግለጫው ከዚህ ቀደም ክቡር ጠቅላይ ሚንስትራችን ከሰጡት እና ቅዱስ ሲኖዶስ መስመር በመስመር ነቅሶ ስህተቶቹን በመግለጽ እንዲታረም ካሳሰበው በተቃራኒ የክቡር ጠቅላይ ሚንስትራችን የተሳሳተ መግለጫ ቅጥያ ኾኖ አግኝተነዋል።

፫. በመግለጫው ፫ኛ አንቀጽ ላይ "የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ሁለቱን ወገኖች በማቀራረብ.." ሲል የገለጸውን በተመለከተ
፫.፩. ቅዱስ ሲኖዶስ ለክቡር ጠቅላይ ሚንስትራችን በሰጠው ምላሽ ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው፤ መንግሥት ተወግዞ የተለየውን አካል ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋር እኩያ እና ትይዩ አድርጎ መመልከት መቀጠሉን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አሁንም እየታዘበች ትገኛለች።

፫.፪. ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቅጽሮቿ እየተደፈሩ እና ልዕልናዋ በመንግስት አጋዥነት እየተጣሰ ባለበት በዚህ ሰዓት መልስ ተሰጥቶበት የተዘጋውን የውስጥ አሠራር ጉዳይ ወደ ሽምግልና አውርዶ በማሳየት መግለጫውን ለሚሰሙ ኹሉ ግርታን የሚፈጥር ምሉዕ ምስል የማይሰጥና የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የተልዕኮ ምሰሶ በኾነው "ሽምግልና" በተባለ ክቡር ሃሳብ ላይ መዘባበት ኾኖ በማግኘታችን የተሰጠው መግለጫ ተገቢነት የሌለው ነው።

፬. በመግለጫው አራተኛ አንቀጽ ላይ ከተቀመጡ ሃሳቦች መሐል "...የጸጥታ አካላት የየአካባቢውን ሕዝብና የእምነት ተቋማት ሰላምና ጸጥታ ማስከበር ግዴታቸው ነው" እንዲሁም "... የሚዲያ አካላት ችግሩን የሚያባብሱ ነገሮችን ከማቅረብ መቆጠብ ይጠበቅባቸዋል" በማለት የገለጻቸውን ፍሬ ሐሳቦች በተመለከተ፤

፬.፩. በመግለጫው የተጠቀሰው ሀሳብ ልክነት ያለው ቢሆንም በተጨባጭ እየታየ ያለው ተግባር ግን ቅዱስ ሲኖዶስ በጥር ፳፯ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው መንግሥት ለሕጋዊቷ ቤተ ክርስቲያን የሕግ ጥበቃ እና ከለላ ከመስጠት ይልቅ በተቃራኒው ለሕገ ወጥ ቡድኖች በተግባር እየሰጠ ባለው ወገንተኝነት የምእመናንን ሕይወት እየነጠቀ እና የቤተ ክርስቲያናችንን ቅጽር በተደራጀ የጸጥታ ኃይል አጀብ እየደፈረ እና እያስደፈረ መኾኑን የካደ መግለጫ መሆኑን ቤተ ክርስቲያን በፍጹም ሐሳቧ ትረዳለች።
፬.፪. የመንግሥት መገናኛ ብዙኅን የቤተ ክርስቲያኒቱን የበላይ አካል የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ የሚሰጣቸውን መግለጫዎች እንዳይዘግቡ በተግባር እቀባ ያደረገው መንግሥታችን ሕሊናዊ እና ሕጋዊ ተግባራቸውን እየፈጸሙ በሚገኙ የሚዲያ አካላት ላይ የማስፈራሪያ መግለጫ በመስጠት የቤተ ክርስቲያናችን ድምጽ ይበልጥኑ ለማፈን በመንቀሳቀስ ላይ መኾኑን በገሃድ ያመላከተ መግለጫ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ ስለሆነም ፈጽሞ ተገቢነት የሌለው ተግባር ነው፡፡

፭. በመግለጫው ፭ኛ አንቀጽ ላይ "...ሀገር ለማፍረስ በተለያዩ መንገዶች ሞክረው ያልተሳካላቸው ኃይሎች፣ ችግሩ እንዲባባስና እንዳይፈታ ለማድረግ እየሠሩ መሆኑ ተደርሶበታል።" በማለት የተገለጸውን ፍሬ ሐሳብ በተመለከተ፡-

፭.፩. ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በማንኛውም ሁኔታ ሀገር የሚያፈርሱ ተግባራትን የምትጸየፍ፤ ዋነኛ ተልእኮዋም የሀገርን ሕልውና ማስቀጠል መኾኑን በተለያዩ የጦር ሜዳ ዐውዶች ላይ ታቦተ ሕጓን በማክበር ምእመናቶቿን ለትግል በመጥራት ጭምር የሀገርን ሕልውና ያስጠበቀች እና እያስጠበቀች ያለች መሆኗ የሚታወቅ ሲሆን መንግሥት በመግለጫው የገለጸው ዓይነት ተግባር ቢፈጸም የመጀመሪያ ተቃዋሚ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን መሆኗን በድጋሚ ማስታወስ ትወዳለች።

ለዚህም ማሳያዋ እያንዳንዱ እንቅስቃሴዋ ፍጹም ሰላማዊ እና የሕግ አግባብ እና መሠረትን ብቻ ተከትላ እየፈጸመች መገኘቷ ነው፡፡

፭.፪. ችግሩ እንዳይፈታና እንዲባባስ የሚፈልጉት ሀገር አፍራሽ ኃይሎች ሕገ ወጥ ቡድኖች መሆናቸውን መንግሥት ጠንቅቆ የሚያውቀውና ልዩ ድጋፍም የሚሰጠው መሆኑን ቤተ ክርስቲያን እያሳወቀች መንግሥትም ሕገ ወጦችን ከመደገፍ እና ከማገዝ ተግባሩ እንዲቆጠብ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በድጋሚ ታሳስባለች።

፭.፫. እንደ መግለጫው ከሆነ ችግሩ የሚፈታው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሕልውናዋን፣ ሕጋዊነቷን፣ ተቋማዊ ነጻነቷን እና ከመንግሥት ልታገኝ የሚገባውን የሕግ ከለላ አጥታ ከሕገ ወጥ አካላት እኩል ስትታይ መሆኑን መግለጫው በግልጽ ቋንቋ ያስቀመጠ መሆኑን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በጽኑ የምታወግዘው እና የምትቃወመው መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡

፮. በመግለጫው የመጨረሻ አንቀጽ ላይ "..ችግሩን ለማባባስና በሕዝቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር፣ ሀገርን ወደፈተና ለማስገባት በሚጥሩ አካላት ላይ መንግሥት ሕግ የማስከበር ሥራውን እንደሚሠራ በዚሁ አጋጣሚ ያሳውቃል" በማለት ያስቀመጠውን በተመለከተ፡-

፮.፩. ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን የበላይ አካል ከሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ አንስቶ እስከ ታችኛው የአስተዳደር መዋቅር አልፎም እስከ ተከታይ ምዕመኖቿ ድረስ የሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላም የሕዝቧ አንድነት እና የሕግ የበላይነት ጉዳይ ለድርድር እንደማታቀርብ በድጋሚ እያስታወስን ስልጣንን ተገን በማድረግ የቤተ ክርስቲያንችንን ሕጋዊ ጥያቄ በግድያ፤ በእስር፤ በማዋከብ እና በማስፈራራት ሊፈታ የማይችል ይልቁንም መንግሥት የተጣለበትን መንግሥታዊ ኃላፊነት ያለ አድሎ መፈጸም ሲችል ብቻ መሆኑን ቤተ ክርስቲያናችን ዳግም በጽኑ ቃል ለማሳሰብ ትወዳለች፡፡

በመጨረሻም መንግሥት ይህንን መግለጫ ሲያወጣ በጥር ፳፯ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም በሻሸመኔ ከተማ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች የተፈጸመውን ሕገ ወጥ፤ አስነዋሪ እና ጭካኔ የተሞላበት የአደባባይ ግድያ እና የሕዝብ ፍጅት ያልጠቀሰና ሐዘኑን እንኳን መግለጽ ያልቻለበትና ያላወገዘ መሆኑን ስንመለከት የመንግሥትን ግልጽ ሚና በቀላሉ ለመረዳት እንድንችል ያደርገናል።

ስለሆነም መንግሥት ሕገ ወጥ አካላትን ድጋፍ ከመስጠት እና የእነርሱ ልሳን ሆኖ በመቅረብ የቤተ ክርስቲያንን ክብር እና ልእልና ከሚያንኳስስ ሕገ ወጥ ድርጊት እንዲታቀብ እያሳሰብን ሕገ ወጡ ስብስቦች እየፈጸሙ ላሉት ድርጊትም የሰጠውን ድጋፍ እና እገዛ በይፋ ቤተ ክርስቲያንን ይቅርታ በመጠየቅ እንዲያቆም እናሳስባለን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

ጥር ፳፱ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
በተወረወረ ድንጋይ በ19 የፖሊስ አመራርና አባላት ላይ ከከባድ እስከ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፤የአዲስ አበባ ፖሊስ!

//////

የአዲስ አበባ ፖሊስ በማህበራዊ ትስሰር ገጹ ያሰፈረው መልዕክት የሚከተለው ነው፡-

ጠዋት በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ልዩ ዞን ድንበር በተለምዶ ፊሊዶሮ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሰላማዊ እንቅስቃሴን የማወክ ህገ ወጥ ድርጊቶች ተስተውለዋል።


በኦሮሚያ ልዩ ዞን ክልል ውስጥ በምትገኘው ቅድስት ልደታ ቤተክርስቲያን የተሰበሰቡ ከአዲስ አበባ ወደ ኦሮሚያ ገብተው የታሰሩብን ሰዎች ይፈቱልን በሚል ምክንያት በድንጋይ መንገድ በመዝጋት የፀጥታ ችግር እንዲከሰት ለማድረግ ሞክረዋል፡፡ ምንም አይነት የታሰረም ሆነ የተያዘ ሰው እንደሌለ በመግለፅ ፖሊስ የተዘጋው መንገድ እንዲከፈት ቢያሳስባቸውም ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡


ከፖሊስ በተጨማሪ የቤተክርስቲያኒቱ የሃይማኖት አባቶች እና ሌሎች ወጣቶች የታሰረ ሰው አለመኖሩን በማስረዳት መንገዱን ለማስከፈት የፀጥታ አካሉን እያገዙ በምክር እና በተግሳፅ የበኩላቸውን ጥረት ቢያደርጉም የተሰበሰቡት ሰዎች ከቦታው ለመንቀሳቀስ እና መንገዱ እንዲከፈት ፍላጎት አልነበራቸውም፡፡


ይሁን እንጂ የአዲስ አበባ ፖሊስ በብዙ መስዋዕትነት እና በህብረተሰቡ ትብብር የተረጋገጠው የከተማችን ሰላም እንዳይደፈርስ እና በህዝቡ መሐል ውስጥ ሆነው ግጭት እንዲፈጠር ግፊት የሚያደርጉ ግለሰቦች መኖራቸውን በማረጋገጥ ፍላጎታቸው እንዳይሳካ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በወቅቱ ተዘግቶ የነበረው መንገድ እንዲከፈትና ሰላማዊ እንቅስቃሴው እንዲቀጥል የማድረግ ስራ ሰርቷል፡፡

በዚህ ወቅት ግጭቱ እንዲፈጠር በግልፅም ሆነ በስውር ሲቀሰቅሱና በተባባሪነት ሲሳተፉ በነበሩ ሃይሎች በተወረወረ ድንጋይ በ19 የፖሊስ አመራርና አባላት ላይ ከከባድ እስከ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

ወቅታዊ ሁኔታን እንደምቹ ሁኔታን በመጠቀም የፀጥታ ሃይሉን በመተንኮስ በሚፈጠረው የፀጥታ መደፍረስ ድብቅ ፍላጎታቸውን ለማሳካት የሚሰሩ አካላትን ህብረተሰቡ ከመሃሉ ነጥሎ ሊያወጣቸው እና አሳልፎ ሊሰጣቸው እንደሚገባ የጠቀሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ እነዚህ አካላት የከተማችንን እና የነዋሪዎቿን ሰላም ከሚያደፈርስ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በጥብቅ አሳስቧል፡፡


ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
Audio
የዛሬው የኢትዮ ማለዳ ዜናዎቻችን

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/
onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
ኤርዶጋን የሶስት ወራት ጊዜያዊ አዋጅ አወጁ፡፡

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲብ ጣይብ ኤርዶጋን የመሬት መንቀጥቀጡ በደረሰባቸው አካባቢዎች ሶስት ወራት የሚቆይ አዋጅ ማወጃቸው ታውቋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ለተጎጂዎች አስፈላጊውን ሁሉ እየተደረገላቸው ይገኛል ያሉ ሲሆን ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

አሁንም የህይወት አድን ስራው በፍጥነት እየተከናወነ ይገኛልም ተብሏል፡፡

ሰኞ ረፋድ በቱርክ እና በሶሪያ ድንበር ላይ በደረሰው ርዕደ መሬት ከ4 ሺህ 300 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ።

የነፍስ አድን ሠራተኞች በርካታ ተጎጂዎችን እያገኙ መሆናቸውን ከግምት በማስገባት፣ የጉዳቱ መጠን ከዚህም ሊጨምር እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡

አደጋው በደረሰበት አካባቢ የሚገኙ በርካታ ሰዎች ወደ መኖሪያ ህንፃዎቻቸው ለመመለስ ስጋት እንዳለባቸውም ተነግሯል፡፡

ከርዕደ መሬቱ በኋላም በነበረው የመሬት መንቀጠቀጥ ሳይበገሩ አንዳንድ የነፍስ አድን ሠራተኞች በህይወት የተረፉ ሰዎችን ህይወት ለማዳን በባዶ እጃቸው ጭምር ፍርስራሾችን እየቆፈሩ ፍለጋቸውን ቀጥለዋል።

ርዕደ መሬቱ በቱርክ በሚገኙ ሦስት አየር ማረፊያዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ለዕርዳታ አቅርቦት ፈተና መፍጠሩን ሮይተርስ ዘግቧል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘም በቱርክ ሊግ ሊደረጉ የነበሩ ሁሉም ጨዋታዎች ላልተወሰነ ጊዜ መራዘማቸው ታውቋል፡፡

በቱርክ ድንበር ላይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስደተኞች በሚኖሩባት ሶሪያም ቢያንስ 1,400 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥር 30 ቀን 2015 ዓ.ም
Audio
የዛሬው የኢትዮ ማለዳ ዜናዎቻችን

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
በቱርክ እና ሶሪያ የሟቾች ቁጥር ከ 8 ሺህ አልፏል፡፡

ባሳለፍነው ሰኞ በደረሰዉ ርዕደ መሬት በቱርክ እና ሶሪያ የሟቾች ቁጥር ከ 8 ሺህ 7 መቶ በላይ ማለፉ ተገልጿል፡፡

የቱርክ የአደጋ መከላከል ኤጀንሲ እንዳስታወቀዉ በአገሪቱ የሟቾች ቁጥር ከ 6ሺህ በላይ ሆኗል፡፡

በሶሪያ ያለዉን የሟቾች ቁጥር ለማወቅ አስቸጋሪ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ነገር ግን የአገሪቱ የመንግስት ሚዲያ እንዳስታወቀዉ የሟቾች ቁጥር ከ 2ሺህ 5መቶ በላይ መድረሱን ነዉ ያስታወቀዉ፡፡

በመንግስት ቁጥጥር ስር ባሉ አካባቢዎች ላይ እስካሁን የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 1 ሺህ 2 መቶ ሀምሳ መድረሱን የሶሪያ የጤና ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡

በአሸባሪዎች ቁጥጥር ስር ባሉ ቦታዎች የሞቱ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ1ሺህ 2 መቶ 80 በላይ መድረሱን ዘ ዋይት ሄልሜት የተባለ የበጎ ፈቃደኞች ቡድን ገልጿል፡፡

በእስከዳር ግርማ
የካቲት 01 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሙከ ጡሪ ከተማ ላይ ወደ አዲስ አበበ የሚጓዙ ወጣቶች በፀጥታ ሃይሎች እየታሰሩ መሆኑ ተነገረ፡፡

ከሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ እና ከአማራ ክልል አካባቢዎች ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙ መንገደኞች ሙከ ጡሪ ከተማ ላይ በፀጥታ ሃይሎች መታሰራቸዉን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

መንገደኞቹ ለጣቢያችን እንደተናገሩት “ ወደ አዲስ አበባ አትገቡም በሚል የአካባቢዉ የፀጥታ አካላት ከመኪና በማስወረድ ለእስርና እንግልት ዳርገዉናል” ብለዋል፡፡
ከአማራ ክልል መርሃቤቴና ጃማ ተነስተዉ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዙ የነበሩ መንገደኞችንም ወደ ለሚ ከተማ እንዲመለሱ መደረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

የፀጥታ ሃይሎቹ አዲስ አበባ እንዳይገቡ መንገደኞቹን የከለከሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በጠራችዉ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ለመሳተፍ አስባችኋል በሚል እንደሆነም ታዉቋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 01 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast
Website https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።