Ethio Fm 107.8
20.3K subscribers
11K photos
18 videos
4 files
2.34K links
በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!
Download Telegram
የሃይማኖት አባቶች ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡


በመልዕክታቸውም÷ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የፍቅር እና የትህትና መሠረት በመሆኑ ክርስቲያን ምዕመኑ ርስበርስ በመፋቀር እና በመዋደድ በተግባር ሊተረጉመው ይገባል ሲሉ የሃይማኖት አባቶች አሳስበዋል፡፡


እግዚአብሔር ሰው ሆኖ ወደዚች ምድር መምጣቱ ለሰው ልጅ ያለውን ፍቅር ማሳያ በመሆኑ እኛም እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ያሳየውን ፍቅር ማሳየት ይገባናል ብለዋል።


ርስበርስ መዋደድ በሰላምና በፍቅር መኖር አምላካዊ ትእዛዝ ነውና በመንፈሳዊና አለማዊ የስራ ሃላፊነት የምንገኝ ሰዎች የእግዚአብሔር ትእዛዙን ማክበር ግዴታችን ነው ብለዋል።


በዓሉ የትህትና እና የፍቅር በዓል እንደመሆኑ ክርስቲያን ምዕመኑ በተለያየ ምክንያት የተቸገሩ ወገኖችን በማሰብ እና ካለው በማካፈል በዓሉን አብሮ ማሳለፍ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።


ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን


ታህሳስ 28 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡


ይህ በዓል መለያየት የጠፋበት፣ ኅብረትና አንድነት የጸናበት፤ መለኮትና ሥጋ፣ ህያውና ሟች፣ ዘላለማዊና ጊዜያዊ፣ ፈጣሪና ፍጡር፣ ሰማያዊና ምድራዊ፣ ምሉዕና ውሱን፣ በተዋሕዶ አንድ ሆነው አዲስ የምሥራች የተበሰረበት መሆኑን አንስተዋል፡፡

የልደቱ ብሥራት እረኞችን ከሜዳ፣ ሰብአ ሰገልን ከሩቅ ከምሥራቅ ወደ አንድ አምጥቷል፤ ሰዎችን ከምድር ጠርቷል፤ መላእክትን ከሰማይ አውርዷል ነው ያሉት።


ኢትዮጵያውያን የነገዋን ኢትዮጵያ የተሻለች ለማድረግ ከዚህ የልደት ታሪክ ብዙ ትምህርት ብንወስድ ይጠቅመናል፤ ዛሬ እዚህም እዚያም የምናየው የመለያየትና የመጠፋፋት አባዜ የባህሪያችን አይደለም፤ የማናችንም ማንነት መገለጫ አይደለም።

ይህ የተዘራብን ክፉ ዘር ውጤት ነው፤ የውስጥ የውጭ ባዳ አንድ ሆነው የዘሩብን ዘር ውጤት ነው፤ ያለንበት ዘመን ዘሩ የተዘራበት ጊዜ አይደለም ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ።


የጠላታችን ዓላማ አንዳችንን ጠቅሞ ሌላችንን መጉዳት ሳይሆን ሁላችንንም ማጥፋት ነው። ዲያብሎስ መጀመሪያ አዳምና ሔዋንን አካሰሰ። ቀጥሎ ሰውን ከፈጣሪው ነጣጠለ። ከዚያ ሰውን ከመኖሪያው ከገነት አፈናቀለ።

እሾህና አሜከላ እንዲበቅል አድርጎ ሰውንና ምድርን አቆራረጠ። ቃየልን በአቤል ላይ አስነስቶ አስገደለው። ጠላታችን አንዱን ሕዝብ ከሌላው በማጋጨት አይቆምም፤ አንዱንም ሕዝብ እርስ በርሱም ያባላዋል።


ክልልን ከክልል፣ ዞንን ከዞን፣ ወረዳን ከወረዳ፣ ጎጥን ከጎጥ፣ ቤተሰብን ከቤተሰብ፣ ባልን ከሚስት፣ ልጆችን ከወላጆች እያባላ ዓለምን ሁሉ የግጭትና የጠብ ዐውድማ ማድረግ ነው ምኞቱ።

ስለዚህ ቆም ብለን እናስብ። መንገዱ ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ የሚበጅ፣ ለሁላችንም በቅቶ የሚተርፍ፣ አዲስ ማንነትን ይዘን እንደገና መወለድ ነው። ታሪክ ማለፉ አይቀርም። ታሪክ መለወጡም አይቀርም።

ቁም ነገሩ የታሪክ ተከሳሽና ተወቃሽ ወይንስ ተዘካሪና ተሞጋሽ እንሆናለን? የሚለው ነው። ከሩቅ መጥተው መሲኹን እንደተገናኙት ጠቢባን ሰብአ ሰገል ታሪክ እንሠራለን ወይስ እንደ ሄሮድስ ታሪክን ለማጥፋት በንጽሐን ላይ ሰይፍ እናነሣለን? የሚለው ነው።


እንደ ቅዱሳን መላእክቱ ለአዲስ ታሪክ አዲስ የምሥራች እናበሥራለን ወይስ እንደ ዘመኑ የአይሁድ ልሂቃን ባለፈው ታሪክ ላይ ተተክለን የቀረበልንን ዕድል በንቀት እንገፋለን? የሚለው ነው።

የእነዚህን ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ ማግኘት፣ ኢትዮጵያ በአዲስ ልደት መንገድ እየተጓዘች የጌታችንንና የመድኃኒታችንን ልደት እንድታከብር ባለ በቂ ምክንያት ያደርጋታል ብለዋል።


ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ታህሳስ 28 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ህብረተሰቡ በበዓል ወቅት ከእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች እንዲጠነቀቅ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

ኮሚሽኑ በዓሉን አስመልክቶ ከእሳትና የኤሌክትሪክ ሀይል ፍጆታ መጨመርና ሰፊ የመዝናናት እንቅስቃሴ አንጻር ሊከተል የሚችለዉን የእሳት ቃጠሎና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ከወዲሁ ትኩረት በመስጠት ለመከላከል እንዲቻል ከጥንቃቅ ጉድለት የሚመጡ አደጋዎችን ለማስቀረት ህብረተሰቡ የበኩሉን ጥንቃቅ እንዲያደርግ ነዉ መልዕክቱን ያስተላለፈዉ፡፡

በዚህም ህብረተሰቡ በመኖሪያ ቤትና ምግብ በሚያሰናዱ ተቋማት የጧፍ ፣ የጋዝና የኤሌክትሪክ ምድጃዎችን አግባብ ባልሆነ መንገድ ከመጠቀም እንዲቆጠብ መልዕክቱን ያስተላለፈ ሲሆን፣ የከሰል ምድጃ በቤት ዉስጥ በምጠቀምበት ጊዜ በርና መስኮት በመክፈት በቂ አየር እንዲኖር ማድረግና ስራችንንም ከጨረስን በኋላ ወደ ዉጪ በማዉጣት ቤቱ አየር እንዲገባዉ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አንስቷል፡፡


እሳት ስራ ላይ በሚዉልበት አከባቢ በቀላሉ ሊቀጣጠሉ የሚችሉ ተቀጣጣይ ነገሮችን ማራቅ፣ ማትም ሽቶና የመጥፎ ጠረን ማጥፊያ ወይም ተባይ ማስወገጃ ፍሊቶችን ከመርጨት መቆጠብ አስፈላጊ መሆኑን ያነሳዉ ኮሚሽኑ፣ በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሰሩ የተለያዩ መሳሪያዎች መሰኪያዎችን በአንድ ሶኬት ላይ ደራርቦ አለመጠቀም እንደሚገባ ገልጿል፡፡


ከበዓሉ መዝናናት ጋር ተያይዞ በየአከባቢዉ የሚዘጋጀዉ ካምፕ ፋየርም እሳት አደጋዎችን የሚያስከትል እንዳይሆን ህብረተሰቡ የበኩሉን ጥንቃቄ ማድረግ ፣ በተለይም ለእሳት አስጊ በሆኑ ተቋማትና በነዳጅ ዴፖዎች፣ በነዳጅ ማደያዎች እንዲሁም በመኖሪያ መንደሮች አከባቢ ጥንቃቅ ማድረግ አስፈላጊ ነዉ ብሏል፡፡

በተጨማሪም በዓሉን አስመልክቶ በሚደረገዉ መዝናናት በመጠኑም ቢሆን እንዲሁም መጠጥ ጠጥቶ መኪና ከማሽከርከር መቆጠብ ሊደርስ ከሚችለዉ የህይወትና ንብረት ዉድመት ራስን መጠበቅ መሆኑን ተገንዝቦ የጥንቃቄ እርምጃ መዉሰድ እንደሚገባዉ ነዉ ያስታወቀዉ፡፡


ህብረተሰቡ አቅሙ በፈቀደ መጠን እነዚህን የአደጋ መከላከል ጥንቃቄዎችን እያደረገ ከአቅም በላይ በሆኑ ሁኔታ እሳትና ሌሎች አደጋዎች ቢከሰቱ በአስቸኳይ የኮሚሽኑን ድጋፍ መጠየቅ ይኖርበታል ተብሏል፡፡


ኮሚሽኑ 24 ሰዓት ሙሉ ህብረተሰቡን ለማገልገል ዝግጁ መሆኑን ገልጾ፣ የእሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ቢከሰቱ አልያም ለአንቡላንስ አገልግሎት በ 939 ነጻ የስልክ ጥሪ መጠቀም እንደሚችሉ ገልጿል፡፡

በእስከዳር ግርማ
ታህሳስ 28 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
በነገው እለት ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ 9 ጊዜ መድፍ ይተኮሳል!

ነገ ታኅሣሥ 29 ቀን 2015 ዓ.ም የሚከበረውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ 9 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡


ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ታህሳስ 28 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
ርችት መተኮስ ክልክል ነው!


በማንኛው ሁኔታ ርችት መተኮስ ክልክል መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በዓሉን ምክንያት በማድረግ መድፍ እንደሚተኮስ ተገልፆል፡፡


የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ ታህሳስ 29 ቀን 2015 ዓ/ም ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ዘጠኝ ጊዜ መድፍ የሚተኮስ መሆኑን በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የሀገር መከላከያ የኪነ ጥበባት ስራዎች ዳይሬክቶሬት አስታውቋል፡፡

ፖሊስ በተለያዩ ጊዚያት ባደረገው ቁጥጥር የጦር መሰሪያ የሚያዘዋውሩ ህገወጦች በዓላትን ጠብቀው ርችትን ሽፋን አድርገው ልዩ ልዩ የጦር መሳሪዎችን እንደሚተኩሱ አረጋግጫለሁ ብሏል ፡፡

ከዚህ ቀደም በአንድንድ ቦታዎች በርችት ምክንያት ጥፋትን ያስከተሉ አደጋዎች ማጋጣማቸውን ፖሊስ አስታውሶ ለህብረተሰቡ ሰላምና እና ደህንነት ሲባል እንዲሁም ርችት መተኮስ ለጦር መሳሪያ ለሚያዘዋውሩ ህገወጦች ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር በመሆኑ ለህብረተሰቡ ሰላምና ደህነንት ሲባል ርችት መተኮስ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ህብረተሰቡ ርችት ባለመተኮስ አስፈላጊውን ትብብር እንዲሁም ርችት በመተኮስ የህብረተሰቡን ፀጥታ የሚያውኩ ሲያጋጥመው ለፖሊስ ሪፖርት እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልእክቱን አስተላልፏል።
በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ

በጥር ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ አዲስ የዋጋ ማስተካከያ መደረጉን የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከዛሬ ታኅሣሥ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ እስከ ጥር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ተግባራዊ የሚሆን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ክለሳ መደረጉን ተገልጿል።

በዚሁ መሠረት በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆነው የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ፦

ቤንዚን በሊትር - 61 ብር ከ29 ሣንቲም

ነጭ ናፍጣ በሊትር - 67 ብር ከ30 ሣንቲም

ኬሮሲን በሊትር - 67 ብር ከ30 ሣንቲም

ቀላል ጥቁር ናፍጣ - 49 ብር ከ67 ሣንቲም

ከባድ ጥቁር ናፍጣ - 48 ብር ከ70 ሣንቲም

የአውሮፕላን ነዳጅ - 67 ብር ከ91 ሣንቲም መሆኑን የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር ገልጿል።

የተደረገውን የዋጋ ማስተካከያ በሚመለከት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሕዝብ ማስታወቂያ እንዳዘጋጀ እና በዚሁ የሕዝብ ማስታወቂያ የተካተቱ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በዝርዝር ከነገው ዕለት (ጥር 01 ቀን 2015 ዓ.ም) ጀምሮ በሁሉም ክልሎች በሚገኙ ማደያዎች ሁሉ ተግባራዊ እንደሚሆን ገልጿል።

መንግሥት ያወጣው የታለመለት የድጎማ ሥርዓት አፈፃፀም ላይ አንዳንድ ሊስተካከሉ የሚገባቸው ክፍተቶች ቢኖሩትም ከጥር ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ በሚደረገው የዋጋ ክለሳ፣ ዝቅተኛ ገቢ ላለው ኅብረተሰብ የሚሰጠው ድጎማ እንዲጨምር መደረጉን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ገልጿል።

በዚሁ መሠረት በአንድ ሊትር ቤንዚን ሲሰጥ የነበረው ድጎማ ከብር 15.76 ወደ ብር 17.33 እንዲሁም የአንድ ሊትር ናፍጣ ድጎማ ከብር 19.02 ወደ ብር 22.68 ከፍ እንዲል መደረጉ ተገልጿል።
በቅርቡ ይመረቃል!

የኢትዮጵያ እና ቻይና የግንባታ ሙያተኞች አሻራ ያረፈበት የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል ዋና ጽሕፈት ቤት ህንፃ በቅርቡ ይመረቃል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የተገነባው የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል ዋና ጽሕፈት ቤት ህንፃ በ90 ሺሕ ሜትር ስኩዌር መሬት ስፋት ያረፈ ሲሆን የህንፃው ግንባታ ብቻ በ40 ሺሕ ሜትር ስኩዌር ላይ ያረፈ ነው፡፡

ህንፃው የድንገተኛ ህክምና ክፍል፣ የመረጃ ማዕከል፣ ላቦራቶሪ፣ የስልጠናና የስብሰባ አዳራሾችን እና ሌሎች ተግባራትን ለማከናወን የሚረዱ ማዕከላትን ያቀፈ መሆኑም ተገልጿል፡፡
Audio
የዛሬው የኢትዮ ማለዳ ዜናዎቻችን
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
የሸገር ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ተመሰረተ።

በምስረታውም፥ አቶ ቃበቶ አልቤን የሸገር ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አድርጎ ሰይሟል።

ወይዘሮ ጸሐይ ደበሌ ደግሞ ምክትል አፈ ጉባዔ ሆነው ተሰይመዋል፡፡

ምክር ቤቱ በማስቀጠልም ተሾመ አዱኛን የከተማዋ ከንቲባ አድርጎ ሾሟል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥር 1ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
ለአረንጓዴ ልማት የተተው ቦታዎች በህገ-ወጦች እየተወረሩ ነው ተባለ፡፡


በጋራ መኖሪያ ቤቶች ለአረንጓዴ ልማት የተተው ቦታዎች በሕገወጥ መንገድ እየተወረሩ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ይህንን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ቢሮ የሕግ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ሽፈራው ናቸው፡፡

ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ለአረንጓዴ ልማት የተተው ቦታዎች በግለሰቦች እየተወረሩ መሆኑን፣ በታችኛው ዕርከን የሚገኙ አመራሮችም የግብር ደረሰኝ እየሰጧቸው ያላግባብ ቦታዎቹ እየተሰጡ መሆናቸው ነው የተገለጸው፡፡

የቤቶች ልማት ቢሮ በዚህ ጉዳይ ሁለትና ሦስት ቦታዎች ላይ ችግር እንዳጋጠመው በመግለጽ፣ ለአረንጓዴ ልማት የሚውሉ ቦታዎች ላይ የባለቤትነት ጥያቄዎች መበራከታቸውም ታውቋል፡፡

ቦታዎቹን በሕገወጥ መንገድ ወስደው በክረምት ወቅት ጤፍ የሚዘሩ ግለሰቦች መኖራቸውን የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ የፍትሕ ቢሮው በጉዳዩ ላይ በቂ ትኩረት ማድረግ አለበት ሲሉም አሳስበዋል፡፡

ለአብነትም በአያት አካባቢ 10,000 ካሬ ሜትር ለአረንጓዴ ልማት የተተው ቦታዎች በግለሰቦች መያዛቸው መነገሩን የሪፖርተር ዘገባ ያመለክታል፡፡

ለእነዚህ ችግሮች መፍትሔ ለመስጠት ለአረንጓዴ ልማት ክፍት የተደረጉ ቦታዎችን የሚያስተዳድረው አካል ይዞታው በሥሩ እንደሚገኝ የሚገልጽ ማስረጃ እንደሚያስፈልግ ጠቁመው፣ ማስረጃው በሌለበት ግን ትክክለኛ ፍትሕ ለመስጠት አስቸጋሪ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አንዳንድ ጊዜ እውነታው ሌላ ሆኖ በቂ ማስረጃ ባለመኖሩ፣ ፍርድ ቤቶች በተቃራኒው የሚፈርዱበት ሁኔታ እንዳለም ተመላክቷል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥር 1ቀን 2015 ዓ.ም
በአገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ተደረገ፡፡

በነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን ተከትሎ ከጥር 1 ቀን 2015 (ዛሬ) ጀምሮ በአገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ መጠነኛ የታሪፍ ማሻሻያ መደረጉን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ማሻሻያው በጀረጃ 1፣ ደረጃ 2 እና በደረጃ 3 ተሸከርካሪዎች ላይ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፤ በአስፋልት እና በጠጠር መንገድ ላይ የሚኖራቸውን እንቅስቃሴ ታሳቢ ያደረገ ነው ተብሏል፡፡

የአገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪዎችና ረዳቶች በተቀመጠው ታሪፍ ብቻ በማስከፈል አገልግሎት እንዲሰጡ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

ሕብረተሰቡም ይህን አውቆ ከታሪፍ በላይ የሚጠይቁ አካላትን ለትራንስፖርት ተቆጣጣሪዎች እንዲሁም በየደረጃው ለሚገኙ የሕግ አስከባሪ አካላት ሪፖርት በማድረግ ሕግ የማስከበሩ አካል እንዲሆንም የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ጠይቋል፡፡

በአባቱ መረቀ
ጥር 01 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን 5 ሚሊየን ሊትር የፓልም ዘይት እያሠራጨ እንደሚገኝ ገለጸ፡፡


ኮርፖሬሽኑ በአገር ውስጥ የሚታየውን የዘይት ምርት ዋጋ ንረትና አቅርቦት እጥረት ለመቅረፍ በመንግሥት በተላለፈው ውሳኔ ከተገዛው ውስጥ የ5 ሚሊየን ሊትር የፓልም ዘይት ሥርጭት እያከናወነ እንደሚገኝ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡


ጅቡቲ ከሚገኘው ጎልደን አፍሪካ የተባለ የምግብ ዘይት አምራች ኩባንያ በኮርፖሬሽኑ በኩል ተገዝቶ የቀረበው ይህ ምርት፤ ኮርፖሬሽኑ በአጠቃላይ ውል ከተፈራረመበት 21.5 ሚሊየን ሊትር የዘይት ምርት ከታኅሣሥ 21 ቀን 2015
ጀምሮ በተካሄደው የመጀመሪያ ዙር የምርት ሥርጭት 2 ነጥብ 4 ሚሊየን ሊትር የሚጠጋ ዘይት በኮርፖሬሽኑ የምርት
ማከፋፈያ ማዕከላት አማካኝነት በባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ ጋምቤላ፣ ጅማ፣ ድሬዳዋ እና አዲስ አበባ ከተሞች ተሠራጭቷል ብሏል፡፡


የዘይት ምርቱ መንግሥት ባወጣው የዋጋ ተመን መሠረት በሸማቾች የኅብረት ሥራ ማኅበራትና በተፈቀደላቸው አቅራቢዎች አማካኝነት ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር በተላለፈው ኮታ መሰረት ለኅብረተሰቡ በተመጣጣኝ
ዋጋ እየቀረበ እንደሚገኝም ኮርፖሬሽኑ ተናግሯል፡፡


ቀሪው ዘይት በተከታታይ ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት የሚሰራጭ መሆኑንም የኮርፖሬት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጨምሮ ገልጿል፡፡


ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥር 01 ቀን 2015 ዓ.ም