Ethio Fm 107.8
19.4K subscribers
5.81K photos
16 videos
4 files
2.26K links
በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!
Download Telegram
የማዕድን ሚኒስቴር የተፈጥሮ ጋዝና ነዳጅ የማፈላለግ ስራ ላይ ከተሰማራው ፖሊ ጂ ሲ ኤ ል ከተሰኘው ኩባንያ ጋር የገባውን ውል አቋረጠ።


የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ ከኩባንያው ጋር የነበረው ውል ከትናንት ጀምሮ የተቋረጠው ከረጅም ጊዜ ትእግስት እና ማስጠንቀቂያዎች በኋላ ነው ብለዋል።

በቀጣይም የነዳጅ ሀብቱን ወደ ስራ የሚያስገቡ አፋጣኝ ስራዎችን እንሰራለን ሲሉ የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 11 ቀን 2015 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል ለሚያካሄደው ሕዝበ ውሳኔ የ541 ሚሊዮን ብር የበጀት ጥያቄ አቀረበ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ውስጥ ለሚያካሂደው ሕዝበ ውሣኔ ማስፈጸሚያ የሚያስፈልገውን የ541 ሚሊዮን ብር
ተገማች በጀት ያቀረበው ለኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው።

ቦርዱ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር የሚገኙ ስድስት ዞኖች ማለትም የጋሞ፣ ጎፋ፣ ወላይታ፣ ጌዲዮ፣ ኮንሶና፣ ደቡብ ኦሞ ዞኖች እንዲሁም አምስት ልዩ ወረዳዎችን እነዚሁም የቡርጂ፣ አማሮ፣ ደራሼ፣ ባስኬቶ፣ አሌ ልዩ ልዩ ወረዳዎች ላይ ሕዝበ ውሳኔ እንደሚያካሄድ ይታወቃል።

ቦርዱ በተጠቀሱት ዞኖችና ልዪ ወረዳዎች ላይ ሕዝበ ውሣኔ በማደራጀት ውጤቱን እንዲያሳወቅ በፌዴሬሽን ምክር ቤት የተጠየቀው ነሐሴ 12 ቀን 2014 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ ሲሆን፤ በዚህም መሠረት ቦርዱ የሕዝብ ውሣኔውን ለማከናወን የሚያስፈልጉ ዝርዝር ተግባራትን በማካተት የድርጊት መርኅ ግብር አዘጋጅቶ አቅርቧል።

በሕዝበ ውሣኔው የድርጊት መርኅ ግብሩ ላይ የተጠቀሱትን አጠቃላይ ተግባራት ተፈጻሚ ለማድረግም የሚያስፈልገውን በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 11 ቀን 2015 ዓ.ም
“ ይፈለጋል “ ፊልም ከ15 ዓመት በኋላ ዳግም ለእይታ ሊቀርብ ነው።

በሰይፉ ፋንታሁን የተዘጋጀው ይህ ፊልም ከ15 ዓመት በሗላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአለም ሲኒማ ሊታይ ነው ተብሏል::

በእይታው የሚገኛውን ገቢ ደግሞ ለአዘጋጅና ተዋናይ ስዩም ተፈራ ለህክምና የሚውለው ይሆናል::
ተዋንያን :- ሠራዊት ፍቅሬ
:- ሰይፉ ፋንታሁን
:- አምለሰት ሙጪ
:- ደረጀ ሀይሌ
:- ቶማስ ቶራ
:- ሳምሶን ቤቢ
:- ፍቃዱ ከበደ
:- በላይነሽ አመዴ እና ሌሎችም አንጋፋ ተዋንያኖች የተሳተፉበት

በአለም ሲኒማ የሚታይባቸው ቀናቶች
⁃ መስከረም 12 ሀሙስ በ11:00 ሰአት
⁃ መስከረም 13 አርብ በ10:00 ሰአት
⁃ መስከረም 14 ቅዳሜ በ10:00 ሰአት ይታያል እንዲሁም
⁃ መስከረም 15 እሁድ ከቀኑ በ10:00 ሰአት በአለም ሲኒማ በልዩ ፕሮግራም ይታያል

የፊልሙ ሙሉ ገቢው ለአዘጋጅና ተዋናይ ስዩም ተፈራ ለህክምና እንደሚውል ተገልጿል።
ዛሬ ምሽት ከ3፡00 ሰዓት ጀምሮ ምሽቱን ከዲጄ ሔኒኬ ጋር ፕሮግራማችን ከተወዳጇ ድምጻዊት ሃሌሉያ ገ/ጻዲቅ ጋር “ተወዳጅ” ስለተሰኘዉ አዲስ አልበሟ እና ስለ አጠቃላይ የሙዚቃ ህይወቷ እንጨዋወታለን፡፡
Audio
የዛሬው የኢትዮ ማለዳ ዜናዎቻችን 12-01-15

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ዋና ክፍል ኀላፊ ተገደሉ::


የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ እንዳስታወቀው በባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ዋና ክፍል ኀላፊ የነሩት ኮማንደር ዋጋዉ ታረቀኝ ከአንድ ግለሰብ በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸዉ አልፏል።

ኮማንደሩ በፀጥታ በማስከበር ስራ ላይ በነበሩበት ወቅት ከምሽቱ 6፡00 ሰዓት አካባቢ በአንድ ግለሰብ በተተኮሰ ጥይት ተመትተዉ ለህዝብና ለሀገር ሲሰሩ መስዕዋት ሆነዋል ሲል የክልልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

ፖሊስ ኮሚሽኑ በኮማንደር ዋጋዉ ታረቀኝ ህልፈተ ህይወት የተሰማዉን ሀዘን ገልጾ ስርዓተ ቀብራቸው ዛሬ ረፋድ መፈፀሙን እስታውቋል።


ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 12 ቀን 2015 ዓ.ም
Audio
የዛሬው የኢትዮ ማለዳ ዜናዎቻችን 13-01-15

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ አምስት ሰዎች ተገደሉ፡፡

በትላንትናዉ እለት የሸኔ የሽብር ቡድን በወረዳው ባደረሰው ጥቃት አምስት ሚሊሻዎች መሞታቸውን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡
የአማሮ ልዩ ወረዳ የፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንፔክተር አራርሶ ነጋሽ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ በአካባቢው በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያሉትን ግድያዎች በመፈጸም ላይ ያሉት ከምዕራብ ጉጂ ገላና ወረዳ የሚነሱ የሸኔ ታጣቂዎች ናቸው፡፡

ትላንት የተከሰተው የጸጥታ ችግርም ጠንሳሾቹ እነርሱ መሆናቸው የገለጹት አራርሶ ነጋሽ፣ በወረዳው አሁንም ከፍተኛ የጸጥታ ችግር መከሰቱን ተናግረዋል፡፡

በትላንትናው እለት ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተውጣጡ አካላት በወረዳው ከዚህ በፊት የተከሰተውን የጸጥታ ችግር በተመለከተ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ለመምከር እያቀኑ በነበረበት ጊዜ ነው ጥቃቱ የደረሰው፡፡
በአካባቢው ከፍተኛ “የታጣቂዎች ክምችት” እንዳለ ከነዋሪዎች መስማታቸውንና ይህንኑም ዛሬ ወደ አካባቢው የተንቀሳቀሰው የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል እና የፌደራል ፖሊስ አባላት ማረጋገጣቸውን ነግረዉናል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
መስከረም 13 ቀን 2015 ዓ.ም
ሩሲያ ከዩክሬን በነጠቀቻቸዉ አራት ግዛቶች ህዝበ ዉሳኔ ማካሄድ ጀመረች፡፡

የሩሲያ ጦር ከዩክሬን በነጠቃቸዉ አራት ግዛቶች ህዝበ ዉሳኔ መጀመሩን የአገሪቱ መንግስት አስታዉቋል፡፡

ህዝበ ዉሳኔዉ የሚካሄደዉ በ ሉሃንስክ፤ ዶኔስክ፤ በኬርሶንና በዛፖርዢያ ግዛቶች ነዉ፡፡

ሂደቱ እስከ ቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ ድረስ እንደሚቀጥልም ሞስኮ አስታዉቃለች፡፡

ምዕራባዉያኑ ግን ህዝበ ዉሳኔዉን ለይስሙላ የሚደረግ ሲሉ አጣጥለዉታል፡፡

ሩሲያ ከስምንት አመት በፊት ከዩክሬ በወሰደችዉ ክረሚያ ግዛት ተመሳሳይ ህዝበ ዉሳኔ አድርጋ ማጠቃለሏ የሚታወስ ነዉ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።


በአባቱ መረቀ
መስከረም 13 ቀን 2015 ዓ.ም
ባህር ዳር ከተማ በጸሃይ ብርሃን የሚሰሩ የመንገድ ላይ መብራቶችን መገንባት ጀመረች፡፡


በከተማዋ በጸሃይ ብርሃን ወይም ሶላር ሲስተም የሚሰሩ እና 5 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ የመንገድ ላይ መብራቶችን ግንባታ እንደተጀመረ የከተማዋ ኮሙኒካሽን አስታዉቋል፡፡

ከሃያ አራት ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን ወጪ የሚደረገበት በከተማው አምስት ቦታዎች ላይ የመንገድ ላይ መብራቶችን ግንባታ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ዶክተር ድረስ ሳህሉ አስጀምረዋል።

ይህም የባህርዳር መንገዶችን ምንጊዜም መብራታቸው የማይጠፋ ለማድረግ ያስችላል ተብሏል፡፡


ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 13 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
ቤተክርስቲያኗ ምዕመኑ የመስቀል ደመራ በዓልን መንፈሳዊ ይዘቱን በጠበቀ መንገድ እና በክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር እንዲያከብር ጥሪ አቀረበች::


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ህዝበ ክርስቲያኑ የመስቀል ደመራ በዓልን መንፈሳዊ ይዘቱን በጠበቀ መንገድ እና በክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር እንዲያከብር መልዕክት አስተላለች።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የ2015 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓልን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው የመስቀል ደመራ በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም እንዲከበር ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

ለዚህም በቤተክርስቲያኗ በኩል የተለያዩ ኮሚቴዎች ተቋቁመው ከመንግስት የጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነም አስረድተዋል።

ህዝበ ክርስቲያኑ የመስቀል ደመራ በዓልን መንፈሳዊ ይዘቱን በጠበቀ መንገድ እና ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባርን በተላበሰ ሁኔታ እንዲከበር መልዕክት አስተላልዋል።
ምዕመኑ የመስቀል ደመራ በዓልን ለማክበር ወደ መስቀል አደባባይ ሲመጣ የቤተክርስቲያኗን ስርዓት የሚገልፅ አለባበስ ለብሶ መምጣት እንዳለበት ማሳሰባቸዉን ኢዜአ ዘግቧል።

በበዓሉ ላይ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው፣ ሃይማኖትን ከሃይማኖት የሚያጋጩ መልዕክቶችንና ዓርማዎችን ይዞ መግባት የተከለከለ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡
ብፁዕ አቡነ አብርሃም አክለውም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በዓሉ የፍቅር የሰላምና የአንድት እንዲሆን እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡

ህዝበ ክርስቲያኑ በዓሉን የተቸገሩትን በመርዳት፣የታመሙትን በመጠየቅ እንዲያከብርም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የድምፃዊት ሃሌሉያ ተክለፃዲቅ አዲስ አልበም ነገ ይለቀቃል

በቀድሞ ጃኖ ባንድ የምናዉቃት ተወዳጇ ድምፃዊት ሃሌሉያ ተክለፃዲቅ አዲስ የሰራችዉን "ተወዳጅ" የተሰኘ ሙሉ አልበም በነገው ዕለት ይለቀቃል።

የአልበሙን መለቀቅ በማስመልከት ዛሬ መስከረም 13 ቀን 2015 ዓ.ም ቦሌ በሚገኘዉ ቦስተን ዴይ ስፖ ሚድታወን ክለብ  ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።

ድምፃዊት ሃሌሉያ እንዲሁም በአልበሙ ላይ የተሳተፉት ዳዊት ተስፋዬ እና ኤንዲ ቤተ -ዜማ በጋራ በሰጡት ማብራርያ አልበሙ 13 ሙዚቃዎች የያዘ ሲሆን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ሶስት ዓመት ያህል ፈጅቷል።

ነገ መስከረም 14 ቀን 2015 ዓ.ም በኢንተርኔት የሚለቀቀዉ ይኸው አልበም  በቅርብ ደግሞ በሲዲ እንደሚለቀቅ ገልፀዋል። በተጨማሪም በቅርቡ በሀገር ዉስጥ እና በዉጭ ሀገራት ኮንሰርት ለማዘጋጀት ዕቅድ እንዳላት ድምፃዊት ሃሌሉያና ባልደረቦቿ ተናግረዋል ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 13 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos