Ethio Fm 107.8
19.6K subscribers
6.49K photos
16 videos
4 files
2.28K links
በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!
Download Telegram
የአላሰካ አየር መንገድ በረራ በአብራሪዎቹ ጸብ ምንክኒያት መዝግየቱ ተገለጸ።

ከዋሽንግተን ተነስቶ ወደ ሳንፍራንሲስኮ ሊበር የነበረዉ የአላስካ አዉሮፕላን ቦይንግ 737 በአብራሪቹ ፀብ ምክንያት ወደ ተርሚናሉ እንዲመለስና ተጨማሪ ሰአት እንዲዘይ መገደዱን አየር መንገዱ አስታውቋል ፡፡

ጸቡ ሲፈጠር ተሳፋሪዎች በአዉሮፕላኑ ውስጥ ሆነው ጉዟቸውን ሲጠባበቁ ነበር።

7፡05 የበረራ ሰአቱን ይጨርሳል የተባለዉ አዉሮፕላን ከታቀደለት ሰአት ዉጪ ሁለት ሰአት በመዘግየት 9፡34 በረራዉን አጠናቋል ነው የተባለው።

ካፒቴኑና የመጀመሪያ መኮንኑ ለምን በረራዉ ዉስጥ ጸብ እንደተፈጠሩ ግልጽ ምክንያት አልተነገረም።

አየር መንገዱ ግን ድርጊቱን የሙያ አለመግባባት በማለት ጉዳዩን ቀለል ለማድረግ መሞከሩን ሀፊንግተን ፖስት ዘግቧል።

በቤዛዊት አራጌ
ሐምሌ 16 ቀን 2014 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast
ዌብሳይት https://ethiofm107.com/
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
በኬንያ የድምጽ መሰብሰብ ሂደቱን ለማጨበርበር ሙከራ ያደረጉ ሶስት ባለሞያዎች በቁጥጥር ስራ ዋሉ፡፡

በኬኒያ ሊደረግ ከታሰበው ሃገራዊ ምርጫ ቀደም ብሎ በሚሰበሰበው ድምጽ ላይ የማጭበርበር ሙከራ ያደረጉ ሶስት ተጥርጣሪዎች በሃገሪቱ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ተነግሯል፡፡

የምርጫ ኮሚሽኑ እንዳስታወቀው፣ ተጠርጣሪዎቹ “ስማርት ማቲ” የተባለ የምርጫ ቴክኖሎጂ ድርጅት ሰራተኞች ናቸው፡፡
ኮሚሽኑ አክሎም በፈረንጆቹ ነሃሴ 9 ከሚካሄደው አጠቃላይ ምርጫ ቀደም ብሎ የተሰበሰበው ድምጽ በርካታ ትችቶች እየተሰነዘሩበት ይገኛል፡፡

ከዚህም የተነሳ ተጠርጣሪዎቹ ጥፋተኛ ሆነው የሚገኙ ከሆነ ከፍተኛ ቅጣት እንደሚጥብቃቸው ዘገባው አመላክቷል፡፡
በሌላ በኩል የተጠርጣሪዎቹ ለእስር መዳረግ በምርጫው ላይ ከፍተኛ የሆነ ውጥረትን ሊጨምር ይችላል የሚል ስጋቶች እየተሰሙ መሆኑ ተግልጿል።

በዚህ ድርጊት ላይ ተሳታፊ ናቸው ከተባሉ ሰዎች መካከል እንዱ የውጪ ሃገር ዜጋ ሲሆን፤ስለተቀሩት ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ግን የተባለ ነገር እንደሌለ የአልጀዚራ ዘገባ አመላክቷል፡፡

በመሳይ ገ/መድህን
ሐምሌ 16 ቀን 2014 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast
ዌብሳይት https://ethiofm107.com/
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
በሴቶች በ5ሺህ ሜትር ጉደፍ ፀጋይ የወርቅ ዳዊት ስዩም የነሃስ ሜዳሊያ አሸንፈዋል!

ለተሰንበት ግደይ 5ኛ ሆና አጠናቃለች::
Audio
የዛሬው የኢትዮ ማለዳ ዜናዎቻችን 18-11-14
የተሰረዘው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ በሁለት ሳምንታት ውስጥ ይወጣል ተባለ፡፡

ሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. በይፋ ዕጣ ከወጣበት በኋል የማጭበርበር ከባድ የሙስና ወንጀል ተፈጽሞበታል ተብሎ፣ ሙሉ በሙሉ እንዲሰረዝ የተደረገው የ20/80 እና የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ እንደሚወጣ ተገልጧል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ ሰሞኑን ለመገናኛ ብዙኃን እንዳስታወቁት፣ ትክክለኛ ቀኑን እርግጠኛ ሆኖ መናገር ባይቻልም፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ይወጣል፡፡

የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ በቅርብ ለማውጣት ሌላ ሶፍትዌር እንደሚጠቀሙና፣ ጥራቱ መረጋገጥ እንዳለበት ጠቁመው፣ ትንሽ መታገስ አስፈላጊ መሆኑንም ተናግረዋል።

ቤቱን የሚጠባበቀው ሕዝብ ለጥራት ቅድሚያ እንዲሰጥና አስተዳደሩም በጥራት ለመሥራት የሚችለውን ሁሉ ጥረትና ጥንቃቄ እንደሚያደርግ ጠይቀዋል።

ከንቲባዋ ወ/ሮ አዳነች በድርጊቱ የተጠረጠሩ 16 የሚደርሱ የአስተዳደሩ ሠራተኞችም በሕግ ቁጥጥር ሥር መሆናቸውንና ሌላም የሚመለከተው ሰው ካለም ሕግ የማስከበር ዕርምጃው ይቀጥላል፤›› ብለዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊን
ሐምሌ 18 ቀን 2014 ዓ.ም
ኬንያ ወደ ሶማሊያ በድጋሚ ጫት መላክ ጀምራለች፡፡

የኬንያዉ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የሶማሊያዉ አቻቸዉ ሀሰን ሼክ ሞሀመድ በጋራ ምክክር ካካሄዱ በኋላ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለዉ ድንበር ክፍት እንዲሆን ተስማምተዋል፡፡

በዚህም የንግድ ዝዉዉሩ እንዲፋጠን ባደረጉት ስምምነት መሰረት ኬንያ በድጋሚ ወደ ሶማሊያ የጫት ምርት መላክ ጀምራለች፡፡

የኬንያዉ ግብርና ሚኒስቴር በትናንትናዉ ዕለት ጫት የጫነ የጭነት አዉሮፕላን ወደ ሞቃዲሾ መብረሩን ገልጸዋል፡፡

ሶማሊያ በፈረንጆቹ 2020 ከኬንያ ጋር በተፈጠረ የባህር ድንበር ዉዝግብ ምክንያት ከኬንያ ምንም አይነት የጫት ምርት ወደ ሀገሯ እንዳይገባ ዕገዳ ጥላ ነበር ፡፡

ከሶማሊያዉ ፕሬዝዳንት ድጋሚ ወደ ስልጣን መምጣት በኋላ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለዉ ግንኙነት እየተሻሻለ የመጣ ሲሆን፣ የሀገራቱ ነባራዊ ሁኔታም ሰላማዊ እና የረገበ እንደሆነ ሲጂቲኤን አፍሪካ ነዉ የዘገበዉ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

ዌብሳይት https://ethiofm107.com/

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

በእስከዳር ግርማ
ሐምሌ 18 ቀን 2014 ዓ.ም
የቱኒዚያን ህገ-መንግስት ለማሻሻል ዜጎች ህዝበ ዉሳኔ መስጠት ጀምረዋል::

በቱኒዚያዉ ፕሬዝደንት ካይስ ሰኢድ የቀረበዉን አዲስ ህገ መንግስት መቀበል አለመቀበል ላይ ድምጽ መስጠት መጀመሩን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ሃገሪቱን ወደ አምባገነናዊ አገዛዝ ሊወስዳት ይችላል ያሉትን ሂደት፤ ህጋዊ ለማድረግ በሚደረገዉ ጥረት ላይ ብዙዎች አድማ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የፕሬዝዳንታዊ ስርአትን ለመፍጠር ምን ጊዜም አዲስ ህገ መንግስት ማስተዋወቅ የ ካይስ ፕሮጀክት አካል እንደነሆነ ነዉ የተነገረዉ፡፡

የህግ አዉጭዉ ምርጫ ምንም ይሁን ምን ፕሬዝደንቱ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የመመረጥ ከፍተኛ እድል እንዳላቸዉም አየተነገረ ነዉ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

ዌብሳይት https://ethiofm107.com/

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

በቤዛዊት አራጌ
ሐምሌ 18 ቀን 2014 ዓ.ም
ያለኝ የደም ክምችት ለአምስት ቀናት ብቻ የሚሆን ነዉ---የኢትዮጵያ ደምና ቲሹ ባንክ አገልግሎት፡፡

በአሁኑ ሰዓት በቀን ከ250 ዩኒት አስከ 300 ዩኒት ደም እየተሰበሰበ መሆኑን የኢትዮጲያ ደም እና ቲሹበ ባንክ ተናግሯል፡፡

ጊዜው የክረምት ወቅት እንደመሆኑ የደም መለገስ ተግባሩ በከፍተኛ ሁኔታ መቀዛቀዙን ነግሮናል፡፡

የዛሬ አመት በህግ ማስከበር ዘመቻው የነበረው አይነት መነቃቃት ዓለመኖሩ የኢትዮጵያ ደም እና ቲሹ ባንክ ም/ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሃብታሙ ታዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓትም በቀን ከ250 ዩኒት ደም እስከ 300 ዩኒት ደም እየተሰበሰበ ቢሆንም ወደ ክልል ከተሞችና ለመንግስት ሆስፒታሎች በዛው ልክ እየወጣ በመሆኑ ያለው ክምችት አገልግሎት ላይ ቢውል ከ5 በላይ አያገለግልም ነው ያሉት፡፡

የተከሰተዉ እጥረት እንደየ የደም አይነቱ የሚለያይ ቢሆንም ፕላትሌት የተሰኘው የደም አይነት የደም አይነት “O” እና የደም አይነት ‘’- O’’ መሆኑን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ቀደም ሲል ከነበረው የፆም ወቅት እና የበአል ወቅት በመሆኑ የደም ልገሳ ልምዱ መቀነሱን ከብሄራዊ ደም ባንክ የተገኘዉ መረጃ ያመለክታል፡፡

አሁን የደም እጥረቱ ያለመሻሻሉን ብሎም ክምችቱ ከ5 ቀን በላይ እንደማያገለግል ሰምተናል፡፡

በደም ባንክ የደም እጥረት ሲያጋጥም በየ ሆስፒታሎች ደግሞ የደም ፍላጎት ስለሚጨምርም በዚህ ፍጥነት አገልግሎት ማግኘት ያለባቸው ታካሚዎች መደራረብን ያመጣል ተብሏል።

ለዚህም ሲባል የደም ልገሳውን ህብረተሰቡ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡ ብሔራዊ የደም ባንክም በተለያዩ ቦታዎች ዘመቻዎችን በማድረግ ድንኳኖችንም በመትከል በጎ ፈቃደኞች ደም እንዲለግሱ የማድረግ ስራ እየሰራ መሆኑን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

በረድኤት ገበየሁ
ሐምሌ 18 ቀን 2014 ዓ.ም
በትግራይ ክልል በተለያዩ ዞኖች በግጭት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው የውሃ አውታሮች ተጠግነው አገልግሎት መስጠት ጀመሩ፡፡

በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምዕራብ እና ማዕከላዊ ዞኖች በግጭት ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ የውሃ አውታሮች ጥገና ተደርጎላቸው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታውቋል፡፡

በግጭት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን የውሃ አውታሮች ወደ ነበሩበት ለመመለስ÷ የውሃ ፓምፖች፣ ጄኔሬተሮች እና የውሃ ማጣሪያ ኬሚካሎችን በመለገስ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ መደረጉን የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ መረጃ ያመላክታል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

ዌብሳይት https://ethiofm107.com/

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።


ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 18 ቀን 2014 ዓ.ም
የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችንን ይከታተሉ፦


በዛሬው የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችን ( ከ12:30-2:30)


-ከቤት ሳንወጣና ስፖርታዊ ጉዳዮችን ትሰማላችሁ

- በመንገዳችን ላይ፦በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች የዘመሙ የኤሌክትሪክ ሀይል ተሸካሚ እንጨቶች በተለይም በህጻናት እና አረጋዊያን ህይወት ላይ አደጋ ደቅነዋል፤ ለምን? ከጥንቅሩ ትሰሙታላችሁ።

- ለጤናችን፦ በታሸጉ ምግቦች ውስጥ የሚገኘው ትራንስ ፋቲ አሲድ ብዙዎችን ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች እየዳረገ ይገኛል።

መፍትሄው ምን ይሆን? የባለሙያ ምክረ ሀሳብ ይዘንበታል።

- በፍተሻ ሰዓታችን፦ ሩሲያና አሜሪካ ኢትዮጵያን የግላቸው ለማድረግ በዛሬው ዕለት ይፋዊ ዘመቻ ይጀምራሉ።

የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ዛሬ አዲስ አበባ ይገባሉ።
የአሜሪካው ልዩ መልዕክተኛም በተመሳሳይ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ።

ሁለቱ አገራት በዚህ ወቅት ኢትዮጵያን ለምን መረጡ?

በዚህ ጉዳይ የህግና የፖለቲካ ባለሙያዎችን አስተያየት እንዲሁም የኤምባሲዎችን ምላሽ አካተናል፤ ጉዳዩን ፈትሸነዋል።


-በኢትዮ ገበያችን ፦
በከፍተኛ የዋጋ ንረትና በውጭ ምንዛሬ እጥረት እየተጨነቀች ለምትገኘው ሀገራችን ኢትዮጵያ መተንፈሻ መፍትሄው ይህ ነው ሲል የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን ጥናቱን ይፋ አድርጓል፤ ትሰሙታላችሁ።

-በዓለም ጉዳይ፦ በቱኒዝያ ህዝቡና መሪዋ የተለያየ ጉዞ ጀምረዋል።

የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ካይስ ሰኢድ ስልጣናቸውን ለማስጠበቅ ህገ መንግስቱ ይሻሻል እያሉ ነው፤
ብዙሀኑ ቱኒዚያዊያን ግን ይህን አይፈልጉም።

ህዝብና መንግስት በዚህ ልዩነት ውስጥ ሆነው ህገ መንግስቱን ለማሻሻል ድምጽ መስጠት ተጀምሯል፤ በትንታኔ አዘጋጅተንላችኋል።


-በኮሮና ቫይረስ የተጠቁት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ማገገማቸው ተነግሯል።

- በሳውዲ ዓረቢያ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ተጠቂዎች ተገኝተዋል።

- እንዲሁም ሌሎች አዳድስ የሀገር ውስጥና ዓለምዓቀፋዊ ጉዳዮችንም አሰናድተንላችኋል

እንድታደምጡ ተጋብዛችኋል።

ለአስተያየትዎ '6321' አጭር የጽሁፍ መልዕክት

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
# ኢትዮጵያና ሩሲያ

በዛሬዉ እለት የሩስያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ያደርጋሉ።
ላቭሮቭ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት ለማድረግ ነው ዛሬ አዲስ አበባ የሚገቡት።

በአዲስ አበባ ቆይታቸው ፦

- በኢትዮጵያ እና ሩስያ የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ፤
- ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ እና ሩስያ መካከል የተፈረሙ ስምምነቶች ላይ ይመክራሉ፤
- ከአፍሪካ ህብረት ኃላፊዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ላቭሮቭ በፈረንጆቹ 2018 ላይ ኢትዮጵያን ጎብኝተው እንደነበር አይዘነጋም፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

ዌብሳይት https://ethiofm107.com/

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 19 ቀን 2014 ዓ.ም
Audio
የዛሬው የኢትዮ ማለዳ ዜናዎቻችን 19-11-14
በበጀት ዓመቱ በ4.8 ቢሊየን ብር የሚደርስ የተለያዩ ዕቃዎች ግዥ ተፈጽሟል፡፡

በ2014 በጀት ዓመት ለፌዴራል ባለበጀት መስርያ ቤቶች እና ለመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች አገልግሎት ግዢ ተፈጽሟል ነው የተባለው፡፡
ለተቋማቶቹ የሚውሉ የጋራ መጠቀሚያ ዕቃዎችን በዓለም አቀፍ ግልፅ ጨረታ ዘዴ ግዥ መፈፀሙን የመንግስት ግዥ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው ሪፖርት ገልጿል፡፡

የተፈጸሙ ዕቃዎች ግዥን በተመለከተ ከ2013- 2015 የሚያገለግሉ የቢሮ ፈርኒቸር እንዲሁም ከ2014-2016 በጀት ዓመት የሚያገለግሉ የ5 ሎት (የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ የፕሪንተርና ፎቶ ኮፒ ማሽን ቶነሮች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች እንዲሁም ለመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የተሽከርካሪ ጎማ) ዕቃዎች የግዥ ሂደት ተጠናቆ በ4.8 ቢሊዮን ብር ለ46 አሸናፊ ድርጅቶች የአሸናፊነት ደብዳቤ መስጠቱም ተመላክቷከል፡፡

የተፈጸሙ ግዥዎች የገንዘብ መጠን ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ42 በመቶ ቅናሽ እንዳሳየም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ተጠቁሟል፡፡

በ2013 በጀት ዓመት የስንዴ ግዥዎች፣የኮቪድ መከላከያ መሳሪያዎች፣የኔትወርክ ዕቃዎች እና ቁጥራቸው ከፍ ያሉ ተሽከርካሪዎች ግዥ መፈጸም ዋነኛ የግዢው ገንዘብ መቀነስ ምክንያቶች ናቸው ተብሏል፡፡

በረድኤት ገበየሁ
ሐምሌ 19 ቀን 2014 ዓ.ም

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

ዌብሳይት https://ethiofm107.com/

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
እንደ ሰዉ የሚራመደዉ ዉሻ!

ዴክስተር ይባላል በአሜሪካ ኮሎራዶ የሚኖር የ 7 ዓመት ዉሻ ነዉ፡፡
የመኪና አደጋ በፊት እግሮቹ ላይ ጉዳት ካደረሰበት በኋላ፣ እራሱን እንደ ሰዉ መራመድ ያስተማረ ዉሻ በመሆኑ በአለም ዙሪያ ላሉ ሁሉ ማነቃቂያ የሆነ ዉሻ ነዉ ይሉታል፡፡

ገና ቡችላ ሳለ ከባለቤቶቹ ቤት አምልጦ በመዉጣት የትራፊክ መንገድ ላይ ገብቶ አደጋ ይደርስበታል፡፡ በጊዜዉ ባለቤቶቹ የፊት ለፊት እግሮቹ ከመጎዳታቸዉ በላይ መትረፉን ነበር የፈለጉት እና ለሌላዉ ጉዳቱ ብዙም ትኩረት አልሰጡትም ነበር፡፡

መንቀሳቀሻ እንዲሆነዉ ዊልቸር ገዝተዉ ቢያቀርቡለትም ዴክስተር ግን ለጥቂት ጊዜ ብቻ ነዉ የተጠቀመዉ፤ በሁለት የኋላ እግሮቹ በደንብ መራመድ እንደሚችል ከተረዳ በኋላ የሚያስቆመዉ አልተገኘም፡፡ ከዛ በኋላ በመንደር ዉስጥ አንገቱን ወዲያ እና ወዲህ እያዞረ እንደሰዉ መራመዱን ተያይዞታል፡፡ ለብዙዎችም አነቃቂ ነዉ ተብሎለታል፡፡

ዴክስተር በእግር እርምጃ ከቀን ቀን እየተሻሻለ እና ለዉጥ እያመጣ ነዉ፣ አሁን ላይ ያለማንም አጋዥ በመንደር ዉስጥ ይራመዳል፡፡ የመንደሩ ታዋቂም ሆኗል፣ ሰዎች እሱን ለማየት ከየቤታቸዉ መዉጣት ከጀመሩ ቆይተዋል፡፡
በብዙዎች ፊት ላይ ፈገግታን የሚጭረዉ ዴክስተር፣ ህይወት የቱንም ያህል ብትደቁሰንም ሁሌም ቢሆን ለመነሳት የተሻለ መንገድ እንዳለ ማሳያ ተደርጎ እየተጠቀሰ ነዉ ፡፡
አሳዳጊዉ ‹‹ ይችላል ብለን አላሰብንም ነበር፣ ነገርግን እንዲሞክር እድሉን ሳልሰጠዉ ልተወዉ አልፈለኩም ነበር›› ብላለች፡፡

የዴክስተር ጉዳይ ከብዙ በጥቂቱ የሚከሰት ቢሆንም ግን ልዩ አይደለም ሲል ሀሳቡን የሚያጠቃልለዉ ኦዲቲ ሴንትራል፣ ፌዝ የምትባል ሁለቱንም የፊት እግሮቿን ያጣች ዉሻ እራሷን በኋላ እግሮቿ መንቀሳቀስ አስተምራ ለብዙዎች አርአያ እና ምሳሌ በመሆኗ በስሟ ፋዉንዴሽን እንደነበራትም ያነሳል፡፡

በእስከዳር ግርማ
ሐምሌ 19 ቀን 2014 ዓ.ም
በኦሮሚያና ሶማሊያ ክልሎች በድርቅ የተጎዱ ሰዎች ትኩረት ሊሰጣቸዉ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አሳሰበ፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በሁለቱ ክልሎች የተከሰተውን ድርቅ እና ያደረሰውን ጉዳት ተከትሎ ከየካቲት 14 እስከ 29 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ በድርቁ በከፍተኛ ደረጃ ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብለው በተለያዩ አካላት በይፋ እውቅና የተሰጣቸው አካባቢዎች በመዘዋወር ያዘጋጀውን ባለ 50 ገጽ ሪፖርት ዛሬ ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት ክትትል የተደረገባቸው ቦታዎች በተደጋጋሚ ጊዜያት በድርቅ የሚጠቁ አካባቢዎች ቢሆኑም በዚህ ሪፖርት የተሸፈነው ወቅት የተከሰተው ድርቅ ከዚህ በፊት ከነበሩት አደጋዎች በተለየ መልኩ የተራዘመ ማለትም ከ 2 እስከ 4 የዝናብ ወቅቶች ያልዘነበበት እንዲሁም ሰፊ ቦታዎችን ያካለለ እንደሆነ የክትትሉ ግኝት ያሳያል፡፡ በመሆኑም ማኅበረሰቡ እንደ ከዚህ ቀደሙ ወደ ተሻሉ ቦታዎች ተዘዋውሮ ከድርቁ ተጽዕኖ ለማምለጥ አልቻለም ብሏል፡፡

በድርቁ ጉዳት ሳቢያ በተለይ በቂ ውኃና ምግብ ባለመኖሩ ሰዎች ለተለያዩ የጤና እክሎች ተዳርገዋል፡፡

በምግብ እጥረት ምክንያት ሰውነታቸው የከሳ፣ ሆዳቸውና እግራቸው ያበጠ በዚህም ታመው የተኙ ሰዎች አሉ ነዉ ያለዉ ኢሰመኮ፡፡

የጤና ግልጋሎት መስጫ ተቋማት በአካልም በኢኮኖሚም ተደራሽ አለመሆናቸውንም ክትትሉ አሳይቷል፡፡ የጤና ግልጋሎቶችን ለራሳቸው ማግኘት ለማይችሉ የድርቁ ተጎጂዎች የጤና ግልጋሎቶችን ተደራሽ በማድረግ ረገድ የተሠሩ ሥራዎች ውስን መሆናቸዉንም አንስቷል፡፡

በዚህ ምክንያት ተጋላጭ የሕብረተሰቡ ክፍሎች በተለይም አረጋውያን እና ሕፃናት ሕይወታቸው አደጋ ላይ ወድቋል።

በድርቅ ምክንያት ተፈናቅለው በተፈናቃይ ካምፖች ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች የሕዝብ ጤና አጠባበቅ ተግባራት አለመከናወኑ እና የተፈናቃዮችን ጤና አደጋ ውስጥ ሊከት የሚችል እንደ ወረርሽኝ የመሰለ በሽታ ተጋላጭነት ነበር፡፡ ይህም የድርቅ ተጎጂዎችን የጤና መብት ከማረጋገጥ አንጻር ክፍተት እንዳለ ያመላክታል ብሏል፡፡

በሁለቱም ክልሎች የቅድመ ጥንቃቄ እና የማሳወቅ ስራዎች አለመሰራታቸዉ የሚሰጠዉ መፍትሄ የዘገየ እንዲሆን አድርጎታል ብሏል

ኮሚሽኑ መንግሥት ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን በድርቁ ሳቢያ ለተፈናቀሉ ድጋፍ ፈላጊዎች ባሉበት ቦታ እርዳታ እንዲያገኙ እንዲያደርግ፣ እርዳታ የሚገኝበትን ቦታ እና ሁኔታ እንዲያሳውቅ እና ያለ በቂ መረጃ ለሚፈናቀሉ ሰዎች አፋጣኝ እርዳታ ለማድረግ የሚያስችል የመጠባበቂያ እርዳታ ዝግጁ እንዲያደርግ ጠይቋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 19 ቀን 2014 ዓ.ም

Twitter https://twitter.com/EthioFM


YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

ዌብሳይት https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
#ዉሻዎቻችሁን አስከትቡ!

በአዲስ አበባ የእብደት ዉሻ በሽታ ክትባት ተጀምሯል፡፡

በኢትዮጵያ የእብደት ዉሻ በሽታን በቀጣዮቹ ስምንት ዓመታት ለማጥፋትና ለመቆጣጠር በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ክትባት እየተሰጠ እንደሚገኝ የግብርና ሚንስቴር ተናግሯል፡፡

በሚኒስቴሩ የቬተርነሪ ፐብሊክ ሄልዝ ዳይሬክተር ዶክተር ሲሳይ ጌታቸው በሽታውን ለማጥፋትና ለመቆጣጠር የግንዛቤ ፈጠራ፣ የህዝብ ንቅናቄ ስራዎችና የውሾች ክትባት ዘመቻ ወሳኝ ነዉ ማለታቸዉን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።

በከተማዋ ባለቤት ያላቸውንና ባለቤት አልባ ውሾችን ለማስከተብ ስራዎች ተጀምረዋል፡፡

የክትባት ዘመቻው በሚፈለገው ልክ ውጤት እንዲያመጣ ውሻ ያላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች በሚቀጥሉት አምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውሾቹን በኃላፊነት እንዲያስከትቡም ሚንስቴሩ ተጠይቋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 19 ቀን 2014 ዓ.ም


Twitter https://twitter.com/EthioFM


YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

ዌብሳይት https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
#UPDATE

የሩሲያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ሰርጌይ ላቭሮቭ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን እንዲሁም ሌሎች የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የሩሲያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሚኖራቸው ቆይታ በሩሲያ እና ኢትዮጵያ መካከል ስላለው የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ላቭሮቭ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት ለማድረግ ነው ዛሬ አዲስ አበባ የገቡት ።

በአዲስ አበባ ቆይታቸው ፦
- በኢትዮጵያ እና ሩስያ የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ፤
- ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ እና ሩስያ መካከል የተፈረሙ ስምምነቶች ላይ ይመክራሉ፤

- ከአፍሪካ ህብረት ኃላፊዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ላቭሮቭ በፈረንጆቹ 2018 ላይ ኢትዮጵያን ጎብኝተው እንደነበር አይዘነጋም፡፡


ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 19 ቀን 2014 ዓ.ም


Twitter https://twitter.com/EthioFM


YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

ዌብሳይት https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
የሐምሌ 20 ቀን 2014 ዓ.ም የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችን ከያዛቸው ጉዳዮች መካከል፦


በዛሬው የኢትዮ ማለዳ የዜና ሰዓታችን ( ከ12:30-2:30)


-ከቤት ሳንወጣና ስፖርታዊ ጉዳዮችን ትሰማላችሁ

- በመንገዳችን ላይ፦በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ግን ብዙም ትኩረት ከማንሰጣቸው ጉዳዮች መካከል አንድ ለየት ያለ ሀሳብን ያነሳል።


- ለጤናችን፦ በአዲስ አበባ በሱስ ላይ ከሚሰሩ ማገገሚያ ማእከላት ወደ አንዱ አቅንተን ቅኝት አድርገን ልናካፍላቹ የወደድነውን አዘጋጅተናል።


- በፍተሻ ሰዓታችን፦ የኢታስ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች /አሽከርካሪዎች / ላይ ተደጋጋሚ የግድያ ወንጀሎች እየተፈጸሙ ነዉ።

የሟች ወገኖች ፍትህን ከመንግሥት እየጠበቅን ነዉ ይላሉ፤

የቴክኖሎጂው ባለቤቶችስ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ይላሉ ?

በፍተሻችን ተመልክተነዋል።


-በኢትዮ ገበያችን ፦የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎችን ቁጥር እያሳደገ ይገኛል፤ አማራ ክልል ደግሞ ከፍተኛ የማዕድን ክምችት ያለባቸው አካባቢዎችን ለይቻለሁ ብሏል።

ክልሉ በጥናቱ ምን ምን ማዕድናትን አገኘ? ከኢትዮ ገቢያችን ትሰሙታላችሁ።


-በዓለም ጉዳይ፦ የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሃሰን ሸይኽ ሙሐመድ ሰሞኑን በግብጽ ካይሮ ጉብኝት ላይ ናቸው።

ከግብፁ አቻቸው አልሲሲ ጋር የመከሩት ሃሰን በህዳሴው ግድብ ዙሪያ አስገዳጅ ስምምነት ይፈረም የሚል አቋም ይዘዋል የሚሉ ዘገባዎች እየወጡ ነዉ።

ለመሆኑ የፕሬዝዳንቱ ጉብኝት ከኢትዮጵያ አንጻር እንዴት ይታያል?

የእለቱ የዓለም አቀፍ ትንታኔያችን ትኩረት አድርጎበታል።


- እንዲሁም ሌሎች አዳድስ የሀገር ውስጥና ዓለምዓቀፋዊ ጉዳዮችንም አሰናድተንላችኋል።

እንድታደምጡ ተጋብዛችኋል።

ለአስተያየትዎ '6321' አጭር የጽሁፍ መልዕክት

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን