Ethio Fm 107.8
20.4K subscribers
7.52K photos
16 videos
4 files
2.3K links
በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!
Download Telegram
ከሰሞኑ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ያስተላለፉትን ዛቻ ተከትሎ ቻይናም ጠንከር ያለ ምላሽ እየሰጠች ትገኛለች፡፡


ባይደን ቻይና የተሳሳተ ውሳኔ በታይዋን ላይ እርምጃ ቢያስወስዳት፣ የምንሰስተው የጦር መሳሪያ አይኖረንም ሲሉ ዝተዋል፡፡

ባይደን በቀጠናዉ ሲያደርጉት የነበረዉን ጉብኝት አጠናቀዉ ከመውጣታቸው ቻይና በአይነቱ ልዩ እና በርካታ ወታደሮች የተሳተፉበት ወታደራዊ ልምምድ በታይዋን አቅራቢያ እያካሄደች ትገኛለች፡፡

የሃገሪቱ የጦር ሃይል ይህንን ያረጋገጠ ሲሆን ራስገዟ ታይዋን የኔ አካል ናት የምትለው ቻይና፣ ውህደቱን በአጭር ጊዜ ያለምንም ደምመፋሰስ እንዲካሄድ ፍላጎት እንዳለው የቻይና መንግስት በተደጋጋሚ ሲያሳውቅ ቆይቷል፡፡

ይህ ወታደራዊ ልምምድ በአየር እና በባህር ላይ የተካሄደ ሲሆን፣ በዚህ ፍጥነት ወደ ልምምድ የተገባው ለአሜሪካው ፕሬዝደንት ምላሽ ለመስጠት መሆኑ ተነግሯል፡፡

አሜሪካ፣ ሩስያ ዩክሬንን የወረረች እንደሆን የማትወጣዉ ችግር ዉስጥ ትገባለች ስትል ዛቻዎችን ስታሰማ ነበር፡፡
ዩክሬን ተወራ በርካታ ከተሞቿ ወድመው እና ሚሊየኖች ለስደት ተዳርገዉ እያለ አሜሪካ ከሩስያ ጋር ቀጥተኛ ወታደራዊ ግጭት ውስጥ ከመግባት እንደተቆጠበች ነው፡፡

በአብዱሰላም አንሳር

ግንቦት 18 ቀን 2014 ዓ.ም
ኢትዮጵያ የቻን ውድድር ማጣርያ ተጋጣሚዋን አውቃለች::

የ2022 የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ [ቻን] ውድድር በአልጄርያ አስተናጋጅነት ሲከናወን የማጣርያ ድልድልም በዛሬው ዕለት ወጥቷል።

በክፍለ አህጉራት ተከፍሎ የሚከናወነው ይህ የማጣርያ ውድድር ላይ፣ የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ [ሴካፋ] ሦስት ሀገራትን ወደ ዋናው ውድድር የሚያሳትፍ ሲሆን በወጣው ድልድል መሰረት ኢትዮጵያ በመጀመርያ ዙር ከደቡብ ሱዳን የምትጫወት ይሆናል። ይህን የማጣርያ ዙር ከተሻገረች ደግሞ ሩዋንዳን በሁለተኛው ዙር ትገጥማለች።

የጨዋታ ቀናትም የመጀመርያው ዙር የመጀመርያ ጨዋታ ከሐምሌ 15-17 ፣ ሁለተኛው ጨዋታ ከሐምሌ 22-24 ባሉት ቀናት ሲካሄድ የሁለተኛ ዙር የመጀመርያ ጨዋታ ከነሐሴ 20-22 ፣ ሁለተኛ ጨዋታ ከነሐሴ 27 እስከ 29/2014 እንደሚደረጉ ካፍ አስታውቋል።

የሀገር ውስጥ ሊግ የሚጫወቱ ተጫዋቾችን ብቻ የሚያሳትፈው ይህ ውድድር በኢትዮጵያ አቆጣጠር ጥር 2015 ላይ በአልጄርያ አስተናጋጅነት የሚካሄድ ሲሆን ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ በ2014 እና 2016 ውድድሮች ላይ ተሳታፊ እንደነበረች አይዘነጋም ።
ምንጭ፡- የኢትዮጲያ እግር ኳስ ፌደሬሽን

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ግንቦት 18 ቀን 2014 ዓ.ም
“ኢትዮ ፎረም” የተሰኘው የዩ ቲዮብ መገናኛ ብዙኃን አዘጋጅ የሆነው ያየሰው ሽመልስ ዛሬ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ገደማ በአዲስ አበባ የካ አባዶ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በጸጥታ ኃይሎች ተይዞ መወሰዱን ጠበቃው አቶ ታደለ ገብረመድሀን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ።

የሲቪል ልብስ ለብሰው ነበር የተባሉ አራት የጸጥታ ኃይሎች፤ ጋዜጠኛው ያየሰውን ወደ የካ አባዶ ፖሊስ ጣቢያ ወስደው ለትንሽ ጊዜ እንዳቆዩት የዓይን እማኞችን ጠቅሰው ጠበቃው አስረድተዋል።


የጸጥታ ኃይሎቹ ከቆይታ በኋላ ጋዜጠኛውን ወደ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ይዘውት መሄዳቸውንም ኢትዮጵያ ኢንሳይደር
ዘግቧል።

ያየሰው ምንም እንኳ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መስሪያ ቤት ወደሚገኝበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተወስዷል ቢባልም፤ ጠበቃውም ሆነ ቤተሰቦቹ እስካሁን ድረስ በአካል እንዳላገኙት ለማወቅ ተችሏል።

ምንጭ፡- ኢትዮጵያን ኢንሳይደር

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ግንቦት 18 ቀን 2014 ዓ.ም
በትራፊክ ግጭት አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡


ትላንት ሌሊት 10:00 ሰዓት ልዩ ስሙ 24 በሚባል አካባቢ በደረሰ የትራፊክ ግጭት አደጋ ሁለት ሰዎች ወዲያውኑ ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ሁለት ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በህክምና ላይ ይገኛሉ፡፡

የአደጋውን መንስኤ ፖሊስ በማጣራት ላይ ይገኛል፡፡

ምንጭ፡- የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅንመንት ኤጀንሲ

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 19 ቀን 2014 ዓ.ም
የቀድሞ የጋምቢያ ፕሬዝዳንት ያህያ ጃሜህ ክስ ሊመሰረትባቸው ነው።

የጋምቢያ መንግስት ‘በእውነት እና እርቅ ኮሚሽን’ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ያህያ ጃሜህ በስልጣን ላይ ከቆዩበት ጊዜ ጀምሮ በግድያ እና በሌሎች የተጠረጠሩ ወንጀሎች እንዲከሰሱ የቀረበውን ሀሳብ ተቀብሏል።

ጠቅላይ አቃቤ ህጉ እንደገለፁት ባለፈው አመት በእውነት እና እርቅ ኮሚሽን (TRRC) ሪፖርት ላይ የተቀመጡትን ከ1994 እስከ 2017 የተገኙ የመብት ጥሰት ጉዳዮችን ልዩ አቃቤ ህግ ይመለከተዋል ብለዋል።
"በእርግጠኝነት መናገር የምችለው የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጃሜህ ፍትህ እንደሚጠብቃቸው ነው" ሲሉም አክለዋል።

ገለልተኛው ኮሚሽን ጃሜህ እና ተባባሪዎቻቻዉ ግድያ እና አስገድዶ መድፈርን ጨምሮ በጋዜጠኞች፣ በቀድሞ ወታደሮች፣ በፖለቲካ ተቃዋሚዎች እና በሰላማዊ ሰዎች ላይ ለተፈጸሙ 44 ልዩ ወንጀሎች ተጠያቂ ናቸው ብሏል።
ጃሜህ እ.ኤ.አ. በ2016 በፕሬዚዳንት አዳማ ባሮው በምርጫ ተሸንፈው ወደ ኢኳቶሪያል ጊኒ ሸሽተው ሄደዋል።

“ፍትሕን ወይም የተወሰደውን ማንኛውንም ዓይነት እርምጃ ከብዙ ዓመታት መጠባበቅ በኋላ ለTRRC እና መንግሥት ምስጋና ይግባውና ዛሬ እውን ሆኖ በማየታችን እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ” ሲሉ ታዋቂው ጠበቃ አሚ ሲላ ተናግረዋል ።
የተጎጂ ቤተሰቦች ግን ወደዚህ ክስ ሂደት የተደረሰበት መንገድ አዝጋሚ እንደነበር ቅሬታ አቅርበዋል።

ጃሜህ ለፍርድ እንዲቀርቡ ኢኳቶሪያል ጊኒ ጃሜህን አሳልፋ ለመስጠት መስማማት ይኖርባታል።
ሁለት ሶስተኛው የጋምቢያ ፓርላማም ክሱን ማጽደቅ ይኖርበታል መባሉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

በእስከዳር ግርማ
ግንቦት 19 ቀን 2014 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ብቻ በየዓመቱ ከ10ሺህ በላይ ሰዎች በቲቢ በሽታ እንደሚያዙ ተነገረ፡፡

ሪች ኢትዮጲያ በ ‘USAID Urban TB LON Project’ አማካኝነት ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ እንደተገለጸዉ፣ በአዲስ አበባ በየዓመቱ ከ10ሺህ በላይ ሰዎች በቲቢ በሽታ ይያዛሉ፡፡

በመዲናዋ የቲቢ በሽታ መድሀኒት ከሚወስዱ ዜጎች መካከልም 40 በመቶ የሚያህሉት መድሀኒቱን በተለያዩ ምክንያቶች እንደሚያቋርጡ ነው የተነገረው፡፡
ታማሚዎቹ መድሀኒቱን የሚያቋርጡበት ዋነኛ ምክንያት ደግሞ የምግብ እጥረት ነው ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ በቀን 400 የሚደርሱ ሰዎች በቲቢ በሽታ ሲያዙ 52 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን ያጣሉ፡፡

በአለም የቲቢ በሽታ በከፍተኛ ደረጃ ከተጠቁ 30 አገራት መካከል ኢትዮጲያ አንዷ መሆኗም ተገልጿል።

በዚህም ሳቢያ በአንድ አመት ውስጥ ከ21 ሺህ በላይ የሚሆኑ የቲቢ ህሙማን ህይወት ያልፋል።

የአለም ጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያመላክተው ቲቢ በአመት 10 ሚሊዮን የሚገመት የአለምን ህዝብ እንደሚያጠቃ ተጠቁሟል።
ከዚህ ውስጥም በአመት 1.4 ሚሊዮን የሚጠጉ የቲቢ ህሙማን ህይወት ያለ፤ፋል ነው የተባለው።
በአብዛኛው በቲቢ በሽታ ከሚጠቁ የህብረተሰብ ክፍሎች ውስጥ ከ15 እስከ 54 ዓመት የሚሆነው የእድሜ ክልል ውስጥ የሚሆኑት መሆናቸዉም ተገልጿል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 19 ቀን 2014 ዓ.ም
በሃሰተኛ ገንዘብ ነዳጅ ቀድቶ ለማምለጥ የሞከረው አሽከርካሪ በትራፊክ አደጋ ህይወቱ አለፈ፡፡



በሃሰተኛ ገንዘብ ነዳጅ ቀድቶ ለማምለጥ የሞከረው አሽከርካሪ ከቆመ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ህይወቱ ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡

የትራፊክ አደጋው የደረሰው ትናንት ግንቦት 18 ቀን 2014 ዓ/ም ከሌሊቱ 6፡30 ሰዓት ገደማ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው ሚካኤል አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው ፡፡


የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 1- 30262 አ.አ የሆነ ተሽከርካሪ ከጀሞ 1 አቅጣጫ ወደ ሚካኤል አደባባይ እየተጓዘ 67 ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ ነዳጅ ማደያ ውስጥ ነዳጅ ሊቀዳ መግባቱን በአዲስ አበባ ፖሊስ የትራፊክ አደጋ ምርመራ ቲም ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ስጦታው ወልዴ ገልፀዋል፡፡


አሽከርካሪው ነዳጅ ከቀዳ በኋላ አምስት ባለ 100 መቶ ሀሰተኛ የብር ኖቶችን ለነዳጅ ማደያው ሰራተኛ ሰጥቶ በሚሄድበት ወቅት ነዳጅ ቀጂው የብሮቹን ትክክለኛነት በመጠራጠሩ ሊያስቆመው መሞከሩን ምክትል ኢንስፔክተር ስጦታው ጠቅሰዋል፡፡

አሽከርካሪው ግን በፍጥነት በማሽከርከር ለማምለጥ ጥረት ሲያደርግ መንገድ ዳር ቆሞ ከነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3A- 60203 አ.አ ከሆነ አይሱዙ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ህይወቱ ማለፉን ተናግረዋል፡፡

በወቅቱ አብረውት ተሳፍረው የነበሩ 2 ግለሰቦች ላይም ከባድ የአካል ጉዳት በመድረሱ ተጎጂዎቹ በህክምና ላይ እንደሚገኙ ምክትል ኢንስፔክተር ስጦታው ወልዴ አስረድተዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 19 ቀን 2014 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ለተጎዱ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋገጡ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በኢኳቶሪያል ጊኒ ማላቦ ከተማ እየተካሄደ ባለው በ15ኛው የአፍሪካ ህብረት የሰብአዊ ዕርዳታ እና ቃል ኪዳን ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ነው።

በጉባኤ ላይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ አጋሮች በመላው አህጉሪቱ የሚያደርጉትን የሰብዓዊ ድጋፍ ማሳደግ እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 20 ቀን 2014 ዓ.ም
ስዊድንና ፊንላንድ ከቱርክ በኩል የገጠማቸው ተቃውሞ ለውጥ እያሳየ እንደሚገኝ ዲፕሎማቲክ ምንጮች ገለጹ፡፡


ባሳለፍነው ሳምንት ሃገራቱ ለኔቶ አባልነት ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ ‹‹ እንዴት ተደርጎ!›› የሚል አቋም ይዛ የነበረችው ቱርክ፣ መለሳለስ አሳይታለች ተብሏል፡፡

ሄልሲንኪ እና ስቶኮልም በአንካራ ተቃውሞ ሳቢያ አባልነቱን ሊያጡ እንደሚችሉም ሲነገር ቆይቷል፡፡
ሃገራቱ ከሩስያ ሊቃጣብን ይችላል ያሉትን የጥቃት ስጋት መሸሸጊያ ይሆናቸው ዘንድ በማሰብ አባልነቱን ያቀረቡ ሲሆን፣ የቱርክንም ተቃውሞ ለማርገብ ብርቱ ዲፕሎማሲያዊ ስራዎችን ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡

ቱርክ ሃገራቱ የኩርድ ታጣቂዎችን በማስታጠቅ ለሉዓላዊነቴ ስጋት ሆነውብኝ ነበር ስትል የኖርዲክ ሃገራትን ትወነጅላለች፡፡
ስዊድንና ፊላንድ ደግሞ ውንጀላውን በይፋ ባያጣጥሉም፣ በዲፕሎማሲ ቻናሎቻቸው አንካራን ሰቅዘው በመያዝ ከአቋሟ እንድትለሳለስ አድርገዋል ተብሏል፡፡


ከሃገራቱ ባሻገር የፕሬዝደንት ሪሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን ቃል አቀባይ ከዲፕሎማቶቹ ጋር የነበረውን ቆይታ ‹‹አዎንታዊ›› ሲሉም ገልፀውታል፡፡
በውይይታቸውም ሃገራቱ የጦር መሳሪያ ዝውውር ቁጥጥር እንደሚደርጉ ይጠበቃል ሲል አር ቲ ዘግቧል፡፡

በአብዱሰላም አንሳር
ግንቦት 20 ቀን 2014 ዓ.ም
ኮንጎ በ11 ሰዎች ላይ የሞት ፍርድ ዉሳኔን አሳለፈች፡፡

ሰዎቹ የሞት ፍርድ ዉሳኔዉ የተላለፈባቸዉ ለአሸባሪ ቡድኖች የጦር መሳሪያ ሽያጭ ያከናዉናሉ በሚል ነዉ፡፡
ዉሳኔዉ ከተላለፈባቸዉ መካከልም 8ቱ ወታደሮች መሆናቸዉ ተነግሯል፡፡
በሃገሪቱ በርካታ የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን ፈጽሟል ለሚባለዉ ‹‹ሲኦ ዲኢ ሲኦ›› የተሰኘ የሽብር ቡድን መሳሪያ በመሸጥ ወንጀል ክስ ተመስርቶ፣ ካለፈዉ ወር ጀምሮ ሲካሄድ የነበረዉ የፍርድ ሂደት ፍጻሜዉን አግኝቷል፡፡

እኚህ ዜጎች በተጠረጠሩበት የጦር ወንጀል፣ እንዲሁም አመጽ በማነሳሳት ጥፋተኛ ሆነዉ መገኘታቸዉም ነዉ የተገለጸዉ ፡፡

በዚህም ፍርድ ቤቱ 8 ወታደሮች እና 3 ዜጎች ለአሸባሪ ቡድኑ መሳሪያ በመሸጣቸዉ የሞት ፍርድ ተበይኖባቸዋል፡፡

‹‹ህብረት ለኮንጎ እድገት›› በመባል የሚታወቀዉ ይህ አሸባሪ ቡድን፣ ፖለቲካዊ እና ሃይማኖታዊ ቡድን ሲሆን እራሱንም ‹‹ሌንዱ›› የሚባል ጎሳን መብት እና ጥቅም አስከባሪ ሀይል አድርጎ ይገልጻል፡፡

‹‹ሌንዱ›› እና ‹‹ሄማ ›› የአዉሮፓ ሰላም አስከባሪ ሃይሎች ወደ ቦታዉ በመግባት የሰላም ማስከበር ስራ እስኪሰሩ ድረስ፣ከፈረንጆቹ 1999 እስከ 2003 በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የሞቱባቸዉ የረጅም ጊዜ ቁርሾ ያለባቸዉ ጎሳዎች ናቸዉ፡፡

ይህ ቡድን ከመጣበት ከ2017 ጀምሮ ደግሞ በተለያዩ ንጹሀን ዜጎች ላይ የሚደርሱ ግድያዎችን ጨምሮ በርካታ ጥቃቶች ተባብሰዉ መቀጠላቸዉ ነዉ የተነገረዉ፡፡

የንጹህን ዜጎች ግድያ እና አስከሬኖችን በየቦታዉ ማግኘት የተለመደ ጉዳይ የሆነባት የዲሞክራቲክ ፐብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ ክፍል፣ ከ120 በላይ የታጠቁ ቡድኖች የከበቧት መሆኑን አልጄዚራ ዘግቧል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ግንቦት 20 ቀን 2014 ዓ.ም
#Update

በኮንጎ በተቀሰቀሰ ግጭት 72ሺህ ዜጎች ተፈናቅለዋል፡፡

በኮንጎ ምስራቃዊ ክፍል በመንግስት ሀይሎች እና ‹‹ኤም 23›› ተብሎ በሚጠራ አማጺ ቡድን መካከል ድጋሚ በተቀሰቀሰ ግጭት በአንድ ሳምንት ጊዜ ዉስጥ ብቻ 72ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸዉን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገልጿል፡፡

ከተፈናቀሉት ሰዎች መካከል 7ሺህ ያህሎቹ ወደ ጎረቤት ሀገር ኡጋንዳ መግባታቸዉን የገለጸዉ ድርጅቱ ፣የተቀሩት ደግሞ ወደ ‹‹ጎማ›› ወይም ባለፈዉ ዓመት ከእሳተ ገሞራ ሽሽት ለዜጎች መቆያ እንዲሆን በተሰራ መጠለያ ዉስጥ እንደሚገኙም አክሎ ገልጿል፡፡

‹‹ኤም 23›› በመባል የሚታወቀዉ ይህ አሸባሪ ቡድን ‹‹ቱትሲ›› በመባል የሚታወቅ ጎሳን ፍላጎት ለማስጠበቅ እራሱን የበላይ አካል አድርጎ የሾመ ሲሆን፣ ከ2012 እስከ 2013 ባለዉ ጊዜ ዉስጥ የሀገሪቱን ገጠራማ ክፍልም ተቆጣጥሯል፡፡

ምስራቃዊ ኮንጎ በ1994ቱ የሩዋንዳ ዘር ማጥፋት የተሳተፈዉን የሁቱ ሚሊሻ ቡድንን በመቃወም ሩዋንዳ እና ሌሎች ጎረቤት ሀገራት ቦታዉን ከወረሩበት ጊዜ አንስቶ ሰላሟን ተነጥቃለች፡፡

ኮንጎ ከአፍሪካ ቀዳሚ የሚባለዉ ቁጥር 5.6 ሚሊዮን የሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮች ያሉባት ሲሆን፣ ወደ 1.9 ሚሊዮን የሚሆኑት ተፈናቃዮች ደግሞ የሚገኙት አሁን ግጭቱ እየተካሄደ ባለበት ኪቩ ዉስጥ እንደሆነ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ግንቦት 20 ቀን 2014 ዓ.ም
ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ በፌደራል ፖሊስ አባላት ተያዘች።

" ሮሃ ሚዲያ " የተሰኘው የዩቲዩብ መገናኛ ብዙኃን መስራች እና ባለቤት የሆነችው መዓዛ መሐመድ ዛሬ ጠዋት በፖሊስ ተይዛ መወሰዷን የስራ ባልደረባዋ እና ጓደኛዋን ዋቢ አድርጎ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ " ዘግቧል።

የጋዜጠኛዋ እስር በኢትዮጵያ ከሰሞኑ በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር የዋሉ ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙኃን ሰራተኞችን ቁጥር 19 አድርሶታል።

ጋዜጠኛ መዓዛ የፌደራል ፖሊስ የደንብ ልብስ በለበሱ 2 ፖሊሶች እና የሲቪል ልብስ ባደረጉ 3 የጸጥታ ኃይሎች የተያዘችው በአዲስ አበባ ሰሚት ኮንዶሚኒየም ከሚገኝ የእርሷ መኖሪያ ቤት እንደሆነ ጋዜጠኛ ምስራቅ ተፈራ ገልጻለች።

የጸጥታ ኃይሎቹ መዓዛን ለ " ጥያቄ እንፈልጋታለን " በሚል ምክንያት ቢይዟትም ወዴት እንደሚወስዷት ለመናገር ፈቃደኛ እንዳልነበሩ ጋዜጠኛዋ ማስረዳቷን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር አስነብቧል።

ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ ከወራት በፊት ለእስር ተዳርጋ መፈታቷ ይታወሳል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 20 ቀን 2014 ዓ.ም
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ ሩፋኤል አካባቢ የእሳት አደጋ ተከስቷል፡፡

አደጋዉ የተከሰተዉ በአንድ የቢሮ እቃዎች ማምረቻ መጋዘን ዉስጥ መሆኑም ታዉቋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ሰራተኞችና 13 ተሸከርካሪዎች በቦታዉ ላይ የደረሱ ሲሆን፣ እሳቱን ለመቆጣጠር ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ በአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ የሆኑት አቶ ንጋቱ ማሞ ነግረዉናል፡፡

አካበባዉ በርካታ ቤቶች በተጨናነቀ መልኩ ተሰርተዉ የሚገኙበት በመሆኑ እሳቱን ለመቆጣጠር አስቸጋሪ እንዳደረገዉም ጨምረዉ ገልጸዋል፡፡

ከቀኑ 6፡30 አካባቢ በተከሰተዉ በዚህ የእሳት አደጋ እስካሁን ባለዉ መረጃ የተወሰኑ ሰዎች በጭስ የመታፈን አደጋ አጋጥሟቸዋል ተብሏል፡፡
አሁን ላይ የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር ገና ጥረት እየተደረገ ሲሆን ቀሪ መረጃዎችን እንደደረሱን የምናቀርብላችሁ ይሆናል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 20 ቀን 2014 ዓ.ም
“Nottingham Forest” ፕሪምየር ሊጉን ተቀላቀለ::

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ.ም
አፍሪካ አርም ዋርም የተባለው ተምች ወረርሽኝ በአማሮ ልዩ ወረዳ ተከሰተ

በተለያዩ የልዩ ወረዳው አካባቢዎች እየተከሰተ ያለው የተምች ወረርሽኝ በባለሙያዎች ዳሰሳ መረጋገጡን የአማሮ ልዩ ወረዳ የግብርና ፅ/ቤት ም/ሀላፊና የእርሻ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ከፍያለው አዱላ ለኤትዩ ኤፍ ኤም ተናረዋል፡፡

በተለይ በስድስት ቀበሌዎች ማለትም በቡኒት፣ በመዳይኔ፣ በዳይኬታና ወርካለ - ቦንጮ፣ በከሬዳ ተምቹ መከሰቱን ነግረውናል ፡፡

ለዚህ የተምች መከሰት ዋና ምክንያት በተያዘው በልግ ወቅት እየጣለ ያለው ዝናብ በመጠንም ሆነ በሥርጭት ያልተስተካከለ ከመሆኑ የተነሳ ለተለያዩ ተባዮችና ነፍሳት መከሰት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን እንደሆነ ም/ሀላፊ አቶ ከፍያለው አመላክቷል።

ተምቹ የመዛመት እድሉ ከፍተኛ በመሆኑ በሁሉም ቀበሌዎች የአሰሳና ቅኝት ሥራዎችን በማካሄድ የመከላከልና የመቆጣጠር ተግባራት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው፣ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች በመከላከል ዙሪያ ትኩረት እንዲሰጡም ጠይቀዋል፡፡

ከማሣ ውጭ እየተሳበ ስለሚመጣ ወደ ማሣ ሳይገባና ከአንዱ ማሣ ወደ ሌላ ሳይደርስ 50 ሣንቲ ሜትር ጥልቀትና ስፋት ያለ ቦይ በመቆፈር ተምቹን ህብረተሰቡ መከላከል እንዳለበት አቶ ከፍያለው አሳስበዋል።
ተምቹን ባለበት ለማቁም እና እንዳይዘመት ለማድረግ ጸረ- ተባይ መድሀኒቱ ወደ ወረዳ ማዕከል ደርሷል ብለዋል።
ከአቅም በላይ የሚሆን ከሆነ በፍጥነት ጸረ-ተባይ ኬሚካል በመርጨት ችግሩን መቆጣጠርና መከላከል እንደሚቻል የገለፁት ም/ሀላፊ፣ ካለው የጎንዮሽ ጉዳት አንጻር የኬሚካል ርጭቱ ግን የመጨረሻ አማራጭ መሆኑን አስረድተዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ.ም
በሱዳን በፀረ መፈንቅለ-መንግስት ተቃውሞ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 98 መድረሱ ተሰምቷል።

ከጥቅምት 25 ቀን 2014 ጀምሮ በጦር ኃይሎች አዛዥ አብዱልፈታህ አል ቡርሃን የሚመራውን ወታደራዊ አገዛዝ ተከትሎ በተካሄደው የፀረ መፈንቅለ መንግስት ተቃውሞ ላይ በተወሰደው እርምጃ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 98 መድረሱ ተገልጿል::

የህክምና ባለሙያዎች እንደገለፁት፣ ባለፈው ዓመት የተካሄደውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት በመቃወም የወጡ ሁለት ተቃዋሚዎችን፣ የሱዳን የጸጥታ ሃይሎች መግደላቸዉንና ይህም የሟቾችን ቁጥር ወደ 98 ከፍ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

ዶክተሮቹ እንደሚሉት በዋና ከተማዋ ካርቱም ውስጥ በተደረጉ ሰልፎች ላይ አንድ ተቃዋሚን በጥይት ከመቱት በኋላ ህይወቱ ማለፉን እና ሌላው በአስለቃሽ ጭስ ታፍኖ መሞቱን አስታውቀዋል።

እ.ኤ.አ.በ2019 ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ፣ ለሶስት አስርት አመታት የዘለቀው አገዛዝ ላይ ህዝባዊ ተቃውሞዎች መነሳታቸውን ተከትሎ በተካሄደ መፈንቅለ መንግስት ወደ ሲቪል አገዛዝ የሚደረገው ሽግግር እንዲጠናከር አድርጎታል።
ሱዳን በአልበሽር አስተዳደር ስር በነበረችበት ወቅት፣ ዓለም አቀፍ መገለል የደረሰባት ሲሆን፣ በተጨማሪም የመልካም አስተዳደር እጦት እና ለአስርት አመታት የዘለቀው ኢኮኖሚያዊ ውድቀት ሲያናጋት ቆይቷል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከአፍሪካ ህብረት እና ከኢጋድ ጋር በመሆን ቀውሱን ለመፍታት በሱዳን መንግስት የሚመራ ውይይት እንዲመቻች ግፊት ሲያደርግ መቆየቱ የሚታወስ ነው።

ነገር ግን የሲቪል ሃይሎች ከጦር ኃይሉ ጋር ወደ ድርድር ለመግባት ፈቃደኛ አልሆኑም፣በዚህም አብዱልፈታህ አል ቡርሃን የተባበሩት መንግስታት ተወካይ ቮልከር ፔርቴስን በሀገሪቱ ጉዳዮች ላይ "ጣልቃ ገብቷል" በማለት በተደጋጋሚ ሲከሱ ነበር ።

ሱዳን ከመፈንቅለ መንግስቱ በኋላ በአለም አቀፍ ደረጃ ይደረግ የነበረው ዕርዳታ በመቀነሱ ከባድ የሆነ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ እንደምትገኝ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ / AFP/ዘግቧል፡፡

በእስከዳር ግርማ
ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ.ም
ሱዳን ከመፈንቅለ መንግስት ወዲህ ተጥሎ የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አነሳች።

የሱዳን ወታደራዊ መንግስት ከስድስት ወራት በፊት በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ የጣለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አንስቷል እንደ ቢቢሲ አፍሪቃ ዘገባ።

የሀገሪቱ ገዥ የፀጥታና መከላከያ ምክር ቤት በወታደራዊ መሪው ጄኔራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን በተመራው ስብሰባ ላይ ነው ይህ ውሳኔ የተላለፈው ብሏል፡፡
ርምጃው ትክክለኛውን የውይይት ሁኔታ ለመፍጠር ያለመ ነው ብሏል።

በጥቅምት ወር ከተካሄደው መፈንቅለ መንግስት በኋላ በወታደራዊው መንግስት ላይ የሚካሄደው ተቃውሞ አሁንም ቀጥሏል።
በቅርብ ቀናት የጸጥታ ሃይሎች የተቃውሞ እንቅስቃሴ መሪዎችን ኢላማ በማድረግ በርካታ ተቃዋሚዎችን በቁጥጥር ስር አውለዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ.ም
ግብፅ የቀድሞ ፕሬዝዳንታዊ እጩን በ15 ዓመት አስራት ቀጣች::

የግብፅ የወንጀለኛ መቅጫ ፍርድ ቤት የቀድሞ ፕሬዚዳንታዊ እጩን ከከባድ የጉልበት ሥራ ጋር የ15 ዓመት እስራት ፈርዶባቸዋል፡፡

የ70 አመቱ እና በጠና የጤና እጦት የሚሰቃዩት አብደል ሞኒም አቡል ፎቱህ የሙስሊም ወንድማማችነት ቡድን ጊዜያዊ መሪ ማህሙድ ኢዛት ጋር የሀሰት ዜና በማሰራጨት እና አሸባሪ ቡድንን በመቀላቀላቸው ተከሰው እንደነበር ሚዲል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡

በዘገባው መሰረት ሁለቱም ከባድ ክሶች ናቸው።
አቡል ፎቱህ በፈረንጆቹ 2018 ከብሪታንያ ሲመለሱ ነበር ተይዘው ዘብጥያ የወረዱት፡፡
በለንደን በነበሩበት ወቅት የፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አል-ሲሲን አገዛዝ በመተቸት በርካታ የሚዲያ ቃለመጠይቆችን ሰጥተዋል።

ተከሳሾቹ በቅጣት ወሳኔ ላይ ይግባኝ ማለት ይችላሉ ሲል ሚዲል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ.ም
የድምጽ ብክለትን ለመከላከል አዲስ ህግ ሊወጣ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ እየታየ ያለውን ከመጠን በላይ የድምጽ ብክለት ለመከላከል አዲስ ህግ ሊወጣ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
ከዚህ በፊት በመዲናዋ የድምጽ ብክለት የሚከለክል ህግ ቢኖርም ተግባራዊ ማድረግ ላይ ክፍተቶች እንደነበሩ ነው የተነገረው፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ እንደተናገሩት፣ ከተማዋ በድምጽ የብጥብጥ እና የረብሻ ከተማ ከሆነች ሰነባብታለች ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በየመንገዱ በህገ-ወጥ መንገድ ከፍተኛ ድምጽ በመጠቀም፣ የንግድ ስራ የሚሰሩ ሰዎች የዜጎችን እና የከተማዋን ሰላም እየነሱ እንደሚገኙም ነው አቶ ጥራቱ በየነ የተናገሩት፡፡

አዲስ አበባ ለዜጎቿ እና ለእንግዶቿ የተመቸች ከተማ እንድትሆን፣ የሁሉንም እርብርብ ይጠይቃል ያሉት አቶ ጥራቱ፣ ሁሉንም ከህግ ጋር ማስኬድ ያስፍልጋል ብለዋል፡፡

በዓለማችን ካሉ ከተሞች አዲስ አበባ ከፍተኛ የድምጽ ብክለት ከሚያስተናግዱ ከተሞች መካከል ከቀዳሚዎቹ ዉስጥ እንደምትጠቀስ ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ከተማ አስተዳደሩ ውጤታማ እና ተግባራዊ የሚሆን አዲስ የድምጽ ብክልት የሚከለክል ህግ እያዘጋጀ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ.ም
"ባንኮች 1.8 ቢሊየን ብር ተመዝበረዋል" ተባለ፡፡


በባንኮች ላይ በሚፈፀሙ የማጭበርበር ወንጀሎች የተነሳ 1.8 ቢሊየን ብር የሚደርስ ምዝበራ በባለፉት አራት አመታት ማጋጠሙን የፍትህ ሚኒስቴር አስታዉቋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዛሬ ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓም በሸራተን አዲስ ይፋ ባደረገው ጥናት መሰረት፣ ከደረሰው ምዝበራ ውስጥ 50 ነጥብ 7 በመቶ ምዝበራው የደረሰው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ ነዉ መባሉን ሪፖርተር ጽፏል።

በመቀጠል ከፍተኛ ምዝበራ ያጋጠማቸው
* አቢሲኒያ ባንክ (328.9 ሚሊየን ብር)፣
*ኦሮሚያ ባንክ (161.8 ሚሊየን ብር) እና
* ወጋገን ባንክ (155.6 ሚሊየን ብር) ናቸው።

የፍትህ ሚኒስቴር ዲኤታ ፍቃዱ ፀጋ እንደተናገሩት በባንኮች ላይ የሚፈፀሙ የማጭበርበር ወንጀሎች የተለያየ መልክ የሚከተሉ በመሆናቸው የሚያደርሱት ቀውስና አደጋ ከፍተኛ ነው።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ተግባራዊ ይደረጋል የተባለዉ የህንጻዎች የውጭ ቀለም አጠቃቀም መመሪያ፣ ታሪካዊና በቅርስነት የተመዘገቡ ህንጻዎችን አይመለከትም ተባለ፡፡


በአዲስ አበባ የህንጻዎች የውጭ ቀለም አጠቃቀም መመርያ ተግባራዊ የማይሆንባቸው ህንጻዎች አሉ ተብሏል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የማስታወቂያ ፍቃድ መጠቀሚያ ዳይሬክተር አቶ ሔኖክ ረጋሳ፣ የህንጻዎች የውጭ ቀለም አተገባበር ተግባራዊ የማይሆንባቸው የህንጻ ግንባታዎች እንዳሉ ነግረዉናል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክልል ውስጥ በሚገነቡ የህንጻ ግንባታዎች ላይ የቀለም አጠቃቀም መመሪያው ተግባራዊ ከማይሆንባቸው ህንጻዎች መካከል ታሪካዊ የሆኑ እና በቅርስነት የተመዘገቡ ህንጻዎች በዋነኝነት ይጠቀሳሉ ነዉ ያሉት፡፡

እንደዚሁም በእምነት ተቋማት ለማምለኪያ አገልግሎት ብቻ እንዲውሉ በሚገነቡ ግንባታዎች፤በተጨማሪም አለም አቀፍ የቀለም ስታንዳርድ ያላቸው ማዕከላት ግንባታዎች፤ ዋና ዋናዎቹ ናቸው ብለዋል፡፡

የህንጻዎች የውጭ ቀለም አተገባበር ተግባራዊ ለማድረግ የዳሰሳ ጥናት መደረጉን የተናገሩት አቶ ሔኖክ፣ በዳሰሳው መሰረት በፒያሳ፣ በአራት ኪሎ፣ በለገሀር እና በሜሲኮ አካባቢ የሙከራ ስራ ይሰራል ብለዋል፡፡

መመሪያው አሁን ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ላይ ምክክር እየተደረገበት እንደሚገኝ ተገልጻል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ባዘጋጀው የህንጻ የውጭ ቀልም አተገባበር መመርያ ላይ የህንጻ ዲዛይን ባለሙያዎች እና አርኪቴክቶች ሀሳባቸውን የገለጹ ሲሆን፣ መመሪያው አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረው ባተጋባበሩ ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
ሪሌ እስቴቶች፡ ለአፓርትመንቶቻቸው ራሱን የቻለ አንድ ስታንዳርድ የህንጻ የውጭ ገጽታ ቀለም እንዲሁም በተናጠል ለተሰሩ ቤቶች አንድ ወጥ ስታንዳርድ የህንጻ ግንባታ ቀለም በማቅረብ ማፀደቅ ይኖርባቸዋል ተብሏል፡፡

የፀደቀው ስታንዳርድ ቀለምም በሁሉም የሪል እስቴቱ ሳይቶች ላይ ተፈጻሚ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ.ም