Ethio Fm 107.8
20.2K subscribers
7.22K photos
16 videos
4 files
2.29K links
በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!
Download Telegram
ብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ በአዲስ አበባ ከተማ ይካሄዳል፡፡ ጉበኤውን ተከትሎ የሚከናወኑ ልዩ ልዩ ተግባራት ስኬታማ ሆነው እንዲጠናቀቁ ለማስቻል የፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ ፡፡

ከዛሬ መጋቢት 2 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ መጋቢት 4 ቀን 2014 ዓ/ም ከተማችን አዲስ አበባ አንደኛውን የብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ እያስተናገደች ትገኛለች፡፡ ጉባኤውን ተከትሎ መጋቢት 2 ቀን እና መጋቢት 5 ቀን 2014 ዓ/ም በአዲስ አበባ ልዩ ልዩ ፕሮግሞች ይካሄዳሉ፡፡

ጉባኤው እና ተያያዥ ጉዳዮች በስኬት እንዲጠናቁ የፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል፡፡

በዚህ መሰረት መጋቢት 2 ቀን 2014 ዓ/ም ምሽት አራት ኪሉ አካባቢ የሚካሄደው ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ አራት ኪሎ የሚወስዱ መንገዶች
 ከፍል ውሃ ወደ ሸራተን ሆቴል
 ከኦርማ ጋራዥ በሸራተን ሆቴል ወደ ንግድ ማተሚያ
 ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ ኮንሰን
 ከአምባሳደር መናፈሻ ወደ ሸራተን ሆቴል

በተመሳሳይ መጋቢት 5 ቀን 2014 ዓ/ም የሚካሄደው ተመሳሳይ ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ወደ አራት ኪሎ የሚውስዱ መንገዶች፡-
 ከቀበና በቤልኤር ወደ አራት ኪሎ የሚወስደው መንገድ ቤልኤር መብራት
 ከስድስት ኪሎ ወደ አራት ኪሎ የሚወስደው መንገድ ቅድስተ ማርያም ትራፊክ መብራት
 ከፒያሳ በሰባ ደረጃ ቅድስተ ማርያም የሚወስደው መንገድ አራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ቢሮ
 ከቴዎድሮስ አደባባይ በእሪ በከንቱ ወደ አራት ኪሎ የሚወስደው መንገድ እሪ በከንቱ መብራት
 ከአዋሬ ገበያ በጥይት ቤት አራት ኪሎ የሚወስደው አዋሬ አደባባይ
 ከኮንሰን ወደ ፓርላማ የሚወስዱት መንገዶች በተጠቀሱት ቀናት ዝግጅቶቹ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቁ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትእዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል፡፡
8 ነፍሰጡር እናቶች በሕክምና ማጣት ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በሪፖርቱ ገለጸ፡፡

በአማራ ክልል መቄት ወረዳ ሸሆድ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በደረሰበት ዘረፋ እና ውድመት ምክንያት አገልግሎት መስጠት በማቆሙ በወረዳው 8 ነፍሰጡር እናቶች በሕክምና ማጣት ሕይወታቸው ማለፉን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ በአማራ እና በአፋር ክልሎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ ባወጣው ሪፖርት በአጠቃላይ 749 ያህል ዜጎች መሞታቸውን ገልጿል፡፡

አሸባሪው የህውሃት ቡድን በክልሉ በጤና እና በትምህርት ተቋማት ላይ በደረሰው ዝርፊያ፤ ውድመት እና ቃጠሎ የአካባቢው ነዋሪዎች የጤና እና ትምህርት አገልግሎት ማግኘት እንዳይችሉ ያደረገ ሲሆን፣ ነፍሰጡር እናቶች በሕክምና እጦት ሕይወታቸው አልፏል ሲል በሪፖርቱ አስታውቋል፡፡

የሕክምና ተቋማት በመውደማቸው እና በመዘረፋቸው በቂ ሕክምና ለማግኘት ሳይችሉ ሕይወታቸው ያለፈ ሕፃናትም አሉ ተብሏል።
በአማራ እና በአፋር ክልሎች የአሸባሪው የህውሀት ሀይሎች ባደረጉት የቡድን የአስገድዶ መድፈር ጥቃት በ100ዎች የሚቆጠሩ ሴቶች የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ እንዳስታወቀው ተጎጂዎች የደረሰባቸው ወሲባዊ ጥቓት በማህበረሰቡ ከታወቀ ሊደርስባቸው የሚችለውን መድሎ እና መገለል በመፍራት ብዙውን ጊዜ ጉዳታቸውን ለመናገር የማፈልጉ በመሆናቸው የጥቃቱ ስፋት በሪፖርቱ ከተጠቀሰው በላይ ሊሆን የሚችልበት አጋጣሚ ሰፊ ነው ሲል በዛሬው እለት ይፋ ባደረገው ሪፖርት አስታውቋል፡፡

መጋቢት 02 ቀን 2014 ዓ.ም
ሔኖክ ወልደገብርኤል
ቻይና ታይዋንን በምንም አይነት ሁኔታ ለመደገፍ የሚሞክር ካለ ጣጣውን ይሸከማል ስትል ዛተች፡ ፡

ለዘመናት ፣ ሉአላዊ ግዛቴ ነሽ ፣ የለም ራሴን የቻልኩ ሃገር ነኝ በሚል ሲነታረኩ የቆዩት ታይዋን እና ቻይና አሁን ወደየለት ቀውስ እንዳያመሩ ተሰግቷ፡፡

ቻይና ለታዋን በምንም አይነት ሁኔታ በተለይ ከጦር መሳሪያ ጋር የተያያዘ ድጋፍ አደርጋለው ያለ አፀፋው የከፋ ይሆንበታል ብላለች፡፡

የቻይና የመከላከያ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ኮሎኔል ታን ኪፊይ የታይዋን ጉዳይ የሃገር ውስጥ ጉዳይ ነው ሲሉ የተደመጡ ሲሆን በውስጣዊ ጉዳዮቻችን የማንንም ጣልቃ ገብነት አንሻም በማለት አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

ሃገራችን ሉአላዊ ግዛቷ ከሆነችው ታይዋን ጋር የምታደርገውን ውህደት አደናቅፋለው ላለ አካል ውጤቱ እጅግ አስከፊ ይሆናል ማለታቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

አብድልሰላም አንሳር
መጋቢት 05 ቀን 2014 ዓ.ም
ታዋቂው አሜሪካዊ ጋዜጠኛ በዩክሬንያ መገደሉ ተሰማ

ዝነኛው የጦርነት ጋዜጠኛና ቪዲዮግራፈር አሜሪካዊው ብሬንት ሬናውድ ትናንት በዩከሬን ኢርፔን በምትባል ቦታ ተተኩሶበት ተገድሏል፡፡

የቀድሞ ሰራተኛው እንደነበር የገለፀው ኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጠኛውን ወደ ዩክሬን ለስራ እንዳላከው አሳውቋል፡፡

ከዚህ ዝነኛ አሜሪካዊ ጋዜጠኛ ሞት በስተጀርባ ያለው ነገር ገና ያልጠራ ቢሆንም ቦታው የሩሲያና የዩክሬን ሀይሎች የሚዋጉበት የጦርነት ቀጠና መሆኑ ይታወቃል፡፡
RT News

ሔኖክ አሥራት
መጋቢት 05 ቀን 2014 ዓ.ም
ህገወጥ ናቸው ተብለው የተከለከሉ 21 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የሲጋራ ምርቶች ገበያ ላይ ሲሸጡ ተገኙ

በህገወጥ መንገድ ገበያ ላይ ሲሸጡ የተገኙና ግምታቸው 21 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ የሲጋራ ምርቶች እንዲወገዱ መደረጉን ሰምተናል

በሃገር ውስጥ ገበያ እንዳይሸጡ የተከለከሉ፤ በህገ ወጥ መንገድ በግለሰቦች ሱቆች ተገኝተው የተሰበሰቡ የሲጋራ ምርቶች እንዲወገዱ መደረጉን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምግብ እና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ነው የሰማነው።

ሻምላ እና ሬድ ስሜል የተባሉት የቱርክ እና የየመን ምርት የሆኑት እዚህ ሲጋራዎች በኮንትሮባንድ ገብተው በሱቆች ሲሸጡ እንደነበር እና በማህበረሰቡ ጥቆማ እንደተሰበሰቡ ተገልጿል።

ሲጋራዎቹ በይዘታቸው በጣም ከባድ ከመሆናቸው የተነሳ በውስጣቸው 250 የሰዎችን ጤና አደጋ ላይ የሚጥሉ ኬሚካሎች ከመያዙም በላይ፤70 በመቶ የሚሆኑት ተጠቃሚዎችን ለካንሰር በሽታ የሚመሩት ናቸው ብለዋል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምግብ እና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ትግስት በዳዳ ፡፡

አዲስ አበባን ከትንባሆ ጭስ ነጻ ለማድረግ እየሰራን ነው ብለዋል የከተማው ምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባስልጣን ምክትል ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ትዕግስት በዳዳ፡፡

መሳይ ገ/መድህን
መጋቢት 05 ቀን 2014 ዓ.ም
ቻይና በሩሲያና ዩክሬን ጉዳይ ላይ ግልጽ የሆነ አቋሟን እንድታሳዉቅ እፈልጋለሁ ብላለች፤አሜሪካ፡፡

የአዉሮፓ ህብረትና አሜሪካ በግልጽ ለዩክሬን የተለያዩ ወታደራዊ ቁሳቁሶች እና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ላይ ሲሆኑ ቻይና በአንጻሩ ድጋፏ ለሩሲያ መሆኑ ይነገራል፡፡

ከሰሞኑም የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ቁልፍ የጸጥታ አማካሪ ፤ ከቻይናዉ ፕሬዝዳንት ሽ ጅንፒንግ የቅርብ ሰዉ ጋር መምከራቸዉ ተነግሯል፡፡
ዋና አላማዉም ቻይና ያላት ድጋፍ ለሩሲያ እንደሆነ ቢታወቅም ይህን አቋማን በግልጽ እንድታሳዉቅ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ይህም አሜሪካ አንዱ በቻይናም ሆነ በሩሲያ ላይ ተጽዕኖ የማድረጊያ መንግድ አድርጋ ወስደዋለች ተብሏል፡፡
የቻይናዉ ፕሬዝዳንት ሽ ጅንፒንግ በሩሲያና ቻይና መካከል ያለዉ ግንኙነት ጠንካራና ሁሉንም ያካተተ ገደብ የለሽ ነዉ ሲሉ መደመጣቸዉ በአሜሪካ ዘንድ ስጋትን ፈጥሯል፡፡

ይህ አገላለጽ ወታደራዊ ድጋፍንም ሊጨምር ይችላል በማለት አሜሪካና የአዉሮፓ ህብረት አባል ሃገራት መሪዎች ስጋታቸዉን እየገለጹ ይገኛሉ፡፡
ለዚህም ይመስላል ቻይና ግልጽ የሆነ አቋሟን እንድታሳዉቅ አሜሪካ እየወተወተች የምትገኘዉ፡፡

ቢቢሲ
ሙሉቀን አሰፋ

መጋቢት 05 ቀን 2014 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጸጥታ ችግር ለመፍጠር የሞከሩ ተማሪዎች እና በግቢው ግጭት ለመፍጠር የሞከሩ አካላት ከፀጥታ ሃይሎች ጋር በቅንጅት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና÷ የጸጥታ ሁኔታውን ለማረጋገጥ ከከተማው የጸጥታ ሃ አካላት ጋር በመሆን አስፈላጊው ጥበቃ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

በዩኒቨርሲቲው የፀጥታ ችግር ለመፍጠር የሞከሩ ተማሪዎች እና በግቢው ግጭት ለመፍጠር የሞከሩ አካላት ከፀጥታ ሃይሎች ጋር በቅንጅት በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ጠቁመዋል፡፡

አሁን ላይም ዩኒቨርሲቲው መደበኛ የመማር ማስተማር ተግባሩ እንደቀጠለ መግለጻቸውን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
መጋቢት 05 ቀን 2014 ዓ.ም
አፍሪካ ኒውክለር ሀይል መገንባት አለባት ሲሉ ላውረንስ ፍሪማን ተናገሩ፡፡

በአፍሪካ የኢኮኖሚ እድገት ለማረጋገጥ ኒውከለር ሀይል መገንባት እንደሚያስፈልግ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ተመራሪ የሆኑት ላውረንስ ፍሪማን ተናገሩ፡፡

አሁኑ ሰአት በናይጄርያ እና በጋና ኒውክሌር ሀይል ለመገንባት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረጉ እንደሚገኙ የተናገሩት ላውረንስ በሁሉም ሀገራት መሞከር አለበት ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በአፍሪካ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ተመራማሪ የሆኑት ላውረንስ ፍሪማን በተለያዩ ጊዜያቶች በአፍሪካ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ጉዳችን እያነሱ ትንተናቸው እና የመፍትሄ ሃሳባቸው ሲያቀርቡ የምናውቃቸው ምሁር ናቸው፡፡

አሁን በአፍሪካ ሀገራት ኢኮኖሚው እድገት ያላሳየበት ዋነኛ ምክንያት የሀይል አቅርቦቱ እና አጠቃቀሙ ባለመመጣጠኑ ነው ብለዋል፡፡

የአፍሪካ ሀገራት ኢኮኖሚያቸው እና የህዝባቸውን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ቢያንስ 1ሺህ ጊጋ ዋት የሀይል አቅርቦት ሊኖራቸው ይችላል ሲሉ ምክራቸውን አቅርበዋል፡፡

አሁን በአህጉሪቱ ካለው የሀይል አቅርቦት አንጻር ሲታይ ይህንን ማሳካት እንደማይቻል የተናገሩት ላውረንስ ፍሪማን ሀገራቱ ፊታቸውን ወደ ኒውክለር ሀይል ማዞር አለባቸው ብለዋል፡፡

በአህጉሪቱ ናይጄርያ እና ጋና የሀይል አቅርቦታቸውን ለማሳደግ የኒውክለር ሀይል ለመገንባት እንቅስቃሴ መጀመራቸውንም በማህራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባወጡት ጹሁፍ አንስተዋል፡፡

በምእራብ አፍሪካ ትልቅ ኢኮኖሚ መገንባት የቻለችው ናይጄርያ ከደህንነት እና ከሰላም ጋር በተያያዘ ብዙ ጥያቄዎች ቢነሱባትም ጉዳዩን ከዳር ማድረስ ትሻለች ተብሏል፡፡

እንደዚሁም ጎረቤቷ ጋናም ልክ እንደ ናይጄርያ ሁሉ ኒውክለር ሀይል ለመገንባት ከአሜሪካ ጋር ድርድር እያደረገች እንደምትገኝ ነው ላውረስ የተናገሩት፡፡

ቀሪዎቹ የአፍሪካ ሀገራት የነዚህን ፈለግ መከተል አለባቸው የሚሉት ላውረንስ ጉዳዩ በትኩረት ሊመለከቱት ይገባል ብለዋል፡፡

ባሁኑ ሰአት የምእራባዊያን ሀገራት አሜሪካንን ጨምሮ በተወሰኑ የአፍሪካ ሀገራት የኒውክሌር ሀይል ለመገንባት ደፋ ቀና እያሉ እንደሚገኙ ነው የተናገሩት፡፡

በአፍሪካ ካለው የደህንነት እና የጸጥታ እጦት ጋር በተገናኝ አፍሪካ ኒውክለር ሀይል መገንባት የለባትም የሚሉ ምእራባዊያን ሀገራት እንዳሉም ነው ላውረንስ ፍሪማን የተናገሩት፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 05 ቀን 2014 ዓ.ም
የአልጄሪያው ፕሬዝዳንት መሰረታዊ ምግቦች ወደ ውጭ እንዳይላኩ እገዳ ጣለ፡፡

የአልጄሪያው ፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ቴቦዩን ሀገሪቱ ወደ ውጭ የምትልካቸውን መሰረታዊ የምግብ ምርቶች ከዛሬ ጀምሮ ወደ ውጭ እንዳይላኩ እገዳ መጣላቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ስኳር፣ ዘይት፣ ፓስታ እና ስንዴ እገዳው ካካተታቸው የምግብ ሸቀጦች መካካከል ይገኙበታል።

የፕሬዝዳንቱ ውሳኔ የታሸጉ የስጋ ምርቶችንም ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ይከለክላል ሲል የሃገሪቱ የዜና ወኪል ገልጿል።

የእገዳው ምክንያት ምን እንደሆነ ባይገለጽም፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩክሬን ግጭት ምክንያት እንደ ስንዴ ያሉ መሠረታዊ ምግቦች ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱ በሃገሪቱ ስጋት መፍጠሩ ተነግሯል፡፡

ስንዴን በብዛት ከዩክሬን ከሚያስመጡ ሃገራት ውስጥ አንዷየሆነችው ግብፅ ባለፈው ሳምንት ለሶስት ወራት ያህል ስንዴ፣ ዱቄት፣ ፓስታ እና ጥራጥሬ ለውጭ ገበያ እንዳይቀርብ መከልከሏ የሚታወስ ነው።

መሳይ ገ/መድህን
መጋቢት 05 ቀን 2014 ዓ.ም
የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ማለፊያ ነጥብ ይፋ ሆነ።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ ሳሙኤል (ዶ/ር) ለጋዜጠኞች የ12ኛ ክፍል መለቀቂያ ፈተና መቁረጫ ነጥብ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

በሁለት ዙር ለተሰጠው የመልቀቂያ ፈተና የተሰጠው የማለፊያ ነጥብ የተለያየ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም መሰረት በመጀመሪያ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ውጤት የሚከተለውን ይመስላል

በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 363 ለሴት 351 ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 351 ለሴት 339 ማለፊያ ነጥብ መሆኑ ተገልጿል።ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 300 ሆኗል።በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብም 380 ሆኖ መቆረጡ ተገልጿል።

በመጀመሪያው ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 300 ሆኗል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 264፣ ለሴት 254 ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 254፣ ለሴት 250 ማለፊያ ነጥብ ሆኖ ተቆርጧል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች ማለፊያ ነጥብ 250 መሆኑን እና በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 280 እንደሆነ ተገልጿል።

በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 250 ሆኗል።

በሁለተኛ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ውጤትም ይፋ የሆነ ሲሆን በዚህም መሰረት

በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 423 ለሴት 409 ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 410 ለሴት 396 ማለፊያ ነጥብ መሆኑ ተገልጿል።ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 350 ሆኗል።በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብም 443 ሆኖ መቆረጡ ተገልጿል።

በሁለተኛ ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ350 በላይ መሆኑ ተነግሯል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 317 ፣ ለሴት 305 ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 305፣ ለሴት 300 ማለፊያ ነጥብ ሆኖ ተቆርጧል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች ማለፊያ ነጥብ 300 መሆኑን እና በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 335 እንደሆነ ተገልጿል።

በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ 300 በላይ መሆኑም ተገለጿል።

ውጤቱ ለመጀመርያ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 እዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ከ500 የተያዘ መሆኑን እና በሁለተኛ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ700 እዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ከ600 የተያዘ መሆኑ ተገልጿል።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
መጋቢት 05 ቀን 2014 ዓ.ም
ሰበታ ከተማ መንታ መንገድ ላይ ቆሟል

በቤትኪንግ የኢትዮጲያ ፕሪምየር ሊግ በመወዳደር ላይ የሚገኘው ሰበታ ከተማ ከ15 ጨዋታ 9 ነጥቦችን በመሰብሰብ በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ተቀምጧል ፡፡

የፕሪምየር ሊጉ ሌሎች ቡድኖች ለሁለተኛ ዙር ዝግጅት እያከናወኑ ባሉበት በዚህ ወቅት ሰበታ ከተማ ድክመቱን ለማስተካከል ሁነኛ ጥረት እያደረገ አይደለም፡፡

የቡድኑ አስር ተጫዋቾች ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው በመግለጽ ቅሬታቸውን ለኢትዮጲያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስገብተዋል ፡፡

ገንዘቡ እስካልተከፈላቸው ድረስ ወደ ልምምድ እንደማይመለሱም አሳውቀዋል ፡፡

የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ አለማየሁ ምንዳ ከኢትዮ ስፖርት ጋር ባደረጉት ቆይታ የተፈጠረው ችግር እውነት መሆኑን አምነው መፍትሄ ለማግኘት ለክለቡ ቦርድ ጥያቄ ማቅረባቸውን እና ተጨማሪ በጀት እንዲፈቀድላቸው መጠየቃቸውን ተናግረዋል፡፡

ስራ አስኪያጁ ዘንድሮ ያልከፈሉት የሁለት ወር ደመወዝ ብቻ መሆኑን እና ተጫዋቾቹ እያነሱ ያሉት ክፍያ ዓምና የተጫዋቾች የደመወዝ ጣሪያ 50 ሺ ብር እንዲሆን ተወስኖ በነበረበት ወቅት ከጠረጴዛ ስር አድርገውት የነበረው ስምምነት ቀሪ ክፍያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ቀደም ሲል በውድድር ዘመኑ መጀመሪያ ለአጠቃላይ የውድድር ዘመኑ የክለቡ እንቅስቃሴ እንዲውል እስከ ዓመቱ መጨረሻ የሚበቃ ገንዘብ ተሰልቶ ወጪ ተደርጓል መባሉንም አስተባብለዋል፡፡

ክለቡ ያስቀመጠለቻውን ግብ ማሳካት አልቻሉም በሚል ከስራ የታገዱት አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ጉዳይ እልባት ሳያገኝ አዲስ አሰልጣኝ ስለመቅጠር እንደማያስቡም ተናግረዋል፡፡

ከጊዜያዊ አሰልጣኙ ብርሃን ደበሌ ጋር በቡድኑ ዙሪያ መወያታቸውን እና ያስፈልጋሉ የተባሉ ተጫዋቾችን መለየታቸውንም አሳውቀዋል ፡፡

ሆኖም አሁን ክለቡ የሚገኝበት የፋይናንስ ሁኔታ እንኳን አዳዲስ ተጫዋቾችን ለማስፈረም ይቅርና የያዛቸውንም ተጫዋቾች በቅጡ ማስተናገድ እንዳይችል እንደገደበው ተናግረዋል፡፡

የቡድኑ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ በቀጣዮቹ ቀናት ቦርዱ በሚወስነው ውሳኔ ላይ ተንጠለጠለ ይመስላል፡፡

አቤል ጀቤሳ
መጋቢት 06 ቀን 2014 ዓ.ም
በዚህ አመት 152ሺህ ተማሪዎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎችን እንደሚቀላቀሉ ተገለፀ።

የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ከወሰዱ ተማሪዎች ውስጥ 152ሺ 14 ተማሪዎች በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛው ፕሮግራም ምደባ እንደሚያገኙ ተገልጿል።

ይህም በአማካይ በአጠቃላይ በሁለቱም ዙር ፈተናውን 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ካመጡት ውስጥ 53 ፐርሰንት ያህል መሆኑ ተነግሯል።

በመንግስት ተቋማት ምደባ ከሚያገኙት ተማሪዎች ውስጥ 63ሺ 833 የሚሆኑት ሴት ተማሪዎች መሆናቸውም ነው የተገለፀው።

የዩኒቨርስቲ መግቢያ አነስተኛ ነጥብ እና ከዚያ በላይ ውጤት ያላቸው ሌሎች 135ሺ209 ተማሪዎች በተለያዩ አማራጮች ከፍተኛ ትምህርት መማር እንደሚችሉም ተነግሯል።

የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያን ፈተናን በሁለቱም ዙር የወሰዱ 598ሺ 679 ተማሪዎች ሲሆኑ ከዚህም ውስጥ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች 287ሺ 223 ናቸው።

የትምህርት ሚኒስቴር በሁለት ዙር የተሰጠውን የ2013ዓ.ም የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ውጤትን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
መጋቢት 06 ቀን 2014 ዓ.ም
በሃራችን ከሚሰራጩ የስልክ ምርቶች መካከል ከ 50 በመቶ በላይ የሚሆኑት በኮንትሮባንድ የሚገቡ መሆናቸውን ሰምተናል

አገልግሎት ላይ ካሉ የስልክ ምርቶች መካከል 60 በመቶ የሚሆኑ ወደ ሃገር የሚገቡት በህገ ወጥ መንገድ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት የኢኒስቲትዩት የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ፌጤ በቀለ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ዳይሬክተሩ እንዳሉት በስልክ መገጣጠም ስራ ላይ ተሰማርተው የሚሰሩ ወደ 30 የሚጠጉ ኩባንያዎች የነበሩ ቢሆንም፤በኮንትሮባንድ ንግድ ምክንያት ተዳክመው ሃያው ከስራ መውጣታቸውን ነግረውናል።

በአሁን ሰዓትም በዘርፉ ላይ የሚሰሩ 10 ኩባንያዎች ብቻ ናቸው ብለውናል፡፡

ከኮንትሮባንድ ንግድ በዘለለ፤ ከሃገር ውስጥ ግዢን መፈጸም አለመፈለግ እና የውጭ ምንዛሬ እጥረት ኩባንያዎቹ ከስራ እንዲወጡ እና እንዲዳከሙ ምክንያቶች ስለመሆናቸው ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

የኮንትሮባንድ ንግድ ሃገር ማግኘት ያለባትን ገቢ ጭምር እያሳጣት በመሆኑ፤ችግሩን ከወዲው ለመግታት ከጉሙሩክ ባለስልጣን ጋር በመቀራረብ እየሰራን ነው ብለዋል።

ማህበረሰቡ የሃገሩን ምርት መጠቀም እንዲችል የግንዛቤ ስራ በመስራት እና የምርት ጥራት ሂደቱን ለማሻሻል ተግባር ላይ ትኩረት አድርገው ከሚሰሩ የትምህርት ተቋማት ጋር ትስስር በመፍጠር እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ኢኒስቲትዩቱ በቅርቡ ስያሜውን “ ከብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩትነት” ወደ” ማንፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ እና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ምርምር እና ልማት ማእከል” በሚል እንደሚቀይር የኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፌጤ በቀለ፡፡

መሳይ ገብረ መድህን
መጋቢት 07 ቀን 2014 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ምግብን መሰረት ያደረገ የአመጋገብ መመሪያ ተዘጋጀ

በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ ምግብን መሰረት ያደረገ የአመጋገብ መመሪያ መዘጋጀቱን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል።

ጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ከሆነ መመሪያውን ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ፣ ከግብርናና ትምህርት ሚኒስቴር እንዲሁም ከተለያዩ የስነ-ምግብ ላይ ከሚሰሩ አጋር አካላት ጋር በመተባበር እንደተዘጋጀ ተነግሯል።

በዚሁ ምግብን መሰረት ያደረገ የአመጋገብ መመሪያን ይፋ ለማድረግ ከጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፤ ከትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ከግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴታ የሆኑት ዶ/ር ፍቅሬ ረጋሳ ተገኝተዋል።

በተጨማሪም የክልል ጤና ቢሮ ሃላፊዎች እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለሙያዎች እና በስነ-ምግብ ዙሪያ የሚሰሩ አጋር ድርጅቶች በተገኙበት ነው ይፋ የተደረገው።

ይህ መመርያ መዘጋጀቱ ምግብን እንዴት ማግኘት እንደሚቻልም የሚገልጽ መሆኑም የጤና ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል።

ይህን መመርያ ለማዘጋጀት የተለያዩ ሴክተሮች የተካተቱበት መሆኑን አንስተው ከ25 በላይ ከፍተኛ ባለሙያዎች መካፈላቸው አስታውቀዋል።

እርሳቸው እንዳሉት ከሆነ መመርያው ከአመጋገብ ጋር ለሚመጡ ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል ያስችላል ብለዋል።

በአፍሪካ የአመጋገብ መመርያ ካላቸው ስምንት አገሮች ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗንም ጠቅሰዋል ዶ/ር ሊያ፡፡

በዚሁ መድረክ ንግግር ያደረጉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ መመሪያው አስፈላጊነቱን በማንሳት በትምህርት ሚኒስቴርም አጋዥ የሆኑ ስራዎች መጀመራቸውን አንስተዋል።

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር እቅድ ከዚህ በኃላ የሚከፈቱ ሁሉም አዲስ ትምህርት ቤቶች የተወሰነ የእርሻ ቦታ እንደሚኖራቸው ተናግረዋል።

ይህ በመደረጉ ተማሪዎቹ የእርሻ ልምድ እንዲኖራቸው ከማድረግ ባሻገር ትምህርት ቤቱ በራሱ እንዲቆሙ የሚያደርግ መሆኑን ፕሮፌሰሩ ተናግረዋል።

ረድኤት ገበየሁ
መጋቢት 07 ቀን 2014 ዓ.ም
ዩክሬን አራተኛው የሩስያ ጄኔራል መገደሉን አሳውቃለች

ዩክሬን የ46 አመቱ የሩስያ ሜጀር ጀነራል ኦሌግ ሚትዬቭ በማሪፑል ጥቃት መገደሉን ተናግራለች፡፡

የዩክሬን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ባልደረባ ጌራሽቼንኮ ሚትዬቭ ባለፈው ማክሰኞ መሞቱን እና ሚትዬቭ በሶሪያ 150 ኛውን ብረት ለበስ ጦር ክፍል በመምራት ተዋግቷል፡፡

በጎዳዩ ላይ ከሩሲያ ምንም አይነት መረጃ እንዳልተገኘ ሲል አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ያይኔአበባ ሻምበል
መጋቢት 07 ቀን 2014 ዓ.ም
የ12ኛ ክፍል ፈተና የውጤት አያያዝና ማለፊያ ነጥብን በተመለከተ ትምህርት ሚኒስቴር ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጠ

የ2013 የ12ኛ ክፍል ፈተና የውጤት አያያዝ እና የማለፊያ ነጥብን በተመለከተ ትምህርት ሚኒስቴር ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

የ2013 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሁለት ዙር መሰጠቱ የሚታወስ ሲሆን፣ የውጤት አያያዝ እና የማለፊያ ነጥብም እንደየዙሩ የተለያየ ነው።

በዚህ መሠረትም በመጀመሪያው ዙር ተፈታኞች የሲቪክስ ትምህርት ፈተና ውጤት ያልተያዘ ሲሆን፤ ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ መሆኑን ተመላክቷል፡፡

ለመጀመሪያ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ 600፣ ለማህበራዊ ሳይንስ ከ 500፣ ለአይነ ስውራን ተፈታኞች ከ 400 ተይዟል፡፡

ለሁለተኛ ዙር ተፈታኞች ደግሞ ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ 700፣ ለማህበራዊ ሳይንስ ከ 600፣ ለአይነ ስውራን ተፈታኞች ከ 500 ባስመዘገቡት ውጤት መሰረት መያዙ ተገልጿል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
መጋቢት 07 ቀን 2014 ዓ.ም
ዋሽንግተን ለግብፅ F-15 ጄቶች ልታቀርብ ነው

የመካከለኛው ምስራቅ ከፍተኛ የአሜሪካ ጦር ጄኔራል ዩናይትድ ስቴትስ ለግብፅ ኤፍ-15 አውሮፕላኖችን እንደምትሰጥ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የማዕከላዊ ዕዝ ኃላፊ ጄኔራል ፍራንክ ማኬንዚ በኮንግረሱ ላይ ‘‘ረጅም ጠንካራ እና ኢላማውን በአግባቡ የሚመታ F-15 ልንሰጣቸው መሆኑ መልካም ዜና ነው'' ማለታቸው ተሰምቷል ፡፡

ማክኬንዚ በምን ያህል ጊዜ ወይም በቁጥር ስንት F-15 አውሮፕላኖች እንደሚሰጡ ዝርዝር መረጃ አልሰጡም።

ባለፈው ወር የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ለሀገሪቱ የሚሰጠውን 130 ሚሊዮን ዶላር በሰብአዊ መብት ስጋት ምክንያት ማቋጡን ማናገሩ የሚታወስ ነው፡፡

ማክኬንዚ በግብፅ ጎብኝት ማድረጋቸው ተከትሉ ግን ለግብፅ “በጣም ጠንካራ” ወታደራዊ እርዳታን እንዲሰጥ አፅንዖት በመስጠት ሲናገሩ ተደምጧል።

በሕዝብ ብዛት የምትታወቀው ግብፅ በአረብ ሀገራት ወሳኝ አጋር እና ቁልፍ ድምጽ ነች።

የአሜሪካ የጦር መርከቦች በስዊዝ ካናል በኩል እንዲያልፉ እና ለአሜሪካ ወታደራዊ አውሮፕላኖች ያለገደብ በረራ በመስጠትም ግብፅ ሚናዋ ከፍተኛ መሆነን የዋሽንግተን ወታደራዊ ባለስልጣናት ሲናገሩ ቆይተዋል።

ያይኔአበባ ሻምበል
መጋቢት 07 ቀን 2014 ዓ.ም
የሁውቲ ታጣቂዎች በየመን ለማካሄድ በታቀደው ድርድር ሳኡዲ አደራዳሪ መሆን አትችልም ብለዋል

ለአመታት በየመን እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ ስሟ በሰፊው የሚነሳው ሳኡዲአረቢያ የየመንን ሃይሎች ለማደራደር በሚደረገው ጥረት ምንም አይነት ድርሻ ሊኖራት እንደማይገባ አስታውቋል

ሁውቲ ይህን ያለው የድርድር ሂደቱ በሳኡዲ መዲና ሪያድ ለማድረግ መታቀዱን በመቃወም ነው

የሁውቲ አብዮታዊ ከፍተኛ ኮሚቴ ሊቀመንበር እንዳስታወቀው ከሆነ ሳኡዲ ከተዋጊዎች አንዷ ናትና ለማሸማገል አትችልም ብለዋል

በሳኡዲ የሚመራው ጦር ለአመታት በጦር ውርጅብኝ ያረሳትን የመንን መልሶ ለማቋቋም ድርድር ለማካሄድ ሳኡዲ አረቢያ የሁውቲ ታጣቂዎችን ለመጋበዝ አቅዶ ነበር

ድርድሩ እንዲካሄድ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም ድጋፉን ሲሰጥ መቆየቱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

አብዱልሰላም አንሳር
መጋቢት 07 ቀን 2014 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የተለያዩ ሹመቶ ችን ሰጡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል፡፡

በዚህ መሰረትም፡-
አቶ ፀጋ አራጌ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል።

እንዲሁም ዶክተር ንጉሴ ምትኩ የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤትያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
መጋቢት 07 ቀን 2014 ዓ.ም