Ethio Fm 107.8
20.4K subscribers
7.52K photos
16 videos
4 files
2.3K links
በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!
Download Telegram
የትግራይ ክልል የአየር መሥመር ለአገልግሎት ክፍት ሆነ።


በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የህግ ማስከበር ሂደትን ተከትሎ ተዘግቶ የነበረው የአየር ክልል ከዛሬ ታህሣሥ 5/2013 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ በሰሜን የኢትዮጵያ የአየር ክልል ውስጥ የሚያቋርጡ የአለም አቀፍ እና የሃገር ውስጥ የበረራ መስመሮች ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን እየገለጽን አገልግሎት መሥጠት የሚችሉ ኤርፖርቶች በረራ ማስተናገድ የሚችሉ መሆኑን ኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አስታውቋል::
ድላችን ይፋ ከሆነ በኋላ የህዝቡ ፈቃድ ይረጋገጣል ብለዋል ጆ ባይደን

የአሜሪካ ዲሞክራሲ ሲገፋና አደጋ ላይ እንዲወድቅ ለማድረግ ሲሞከር የነበረ ቢሆንም ፤ እውነተኛ፣ጠንካራና የማይበገር መሆኑን አስመስክሯል ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ የህዝቡን ፍቃድና የምርጫውን ውጤት ለመገዳደር እየሞከሩ ነው ያሉ ሲሆን አሁን ጊዜው ገፁን መግለጫ ነው ሲሉ ምክር ለግሰዋቸዋል፡፡

ነጩ ቤተ መንግስት ለመግባት ባይደን ከአሜሪካ የምርጫ ኮሌጅ ማረጋገጫ ማግኘት አለባቸው፡፡
የዲሞክራቱ ጆው ባይደን የህዳርን የምርጫ ፉክክር 306 ድምፅ በማግኘት ነበር 232 ድምፅ ያገኙትን ትራምፕ የረቷቸው፡፡
ውጤቱን መቀበል ያቃታቸው ፕሬዝዳንት ትራምፕ በትዊተር ገፃቸው ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዊሊያም ባርን ማሰናበታቸውን ገልፀዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ምርጫው ተጭበርብሯል ቢሉም ምንም ማስረጃ የለም ብለው ነበር ጠቅላይ አቃቤ ህጉ ::

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል ድረ ገጻችንን https://ethiofm107.com/ ይጎብኙ:: በሔኖክ አስራት
ታህሳስ 6 ቀን 2013 ዓ.ም
አሜሪካ ራሺያ ሰራሽ ሚሳዬል መከላከያ ስርአትሽ ውስጥ ተክለሻል ስትል ቱርክ ላይ ማዕቀብ ጥላለች::

አሜሪካ ራሺያ ሰራሽ ሚሳዬል መከላከያ ስርአትሽ ውስጥ ተክለሻል ስትል የኔቶ አጋሯ ቱርክ ላይ ማዕቀብ ጥላለች

አሜሪካ እንዳለችው የሩሲያ S-400 ሚሳኤል ከኔቶ ጋር የማይጣጣም ቴክኖሎጂ ሲሆን ከቀዝቃዛው ጦርነት በኋላ የኔቶ አባል ሀገራትና የኔቶ አባል ባለሆኑ ሀገራት መካከል የተመሰረተውን የአውሮፓ አትላንቲክ ወዳጅነት የሚጎዳና ስጋት ላይ የሚጥል መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ማዕቀቡ የቱርክን የመሳርያ ግዢ ማዕቀል ነው ኢላማ ያደረፈው፡፡
እርምጃው በቱርክና በሩሲያ በሚገኙ ባለስልጣናት ተወግዟል፡፡
አሜሪካ F-35 ከተባለው የተዋጋ ጄት ፕሮግራምም ቱርክን አስወጥታታለች፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል ድረ ገጻችንን https://ethiofm107.com/ ይጎብኙ::

በጅብሪል ሙሃመድ
ታህሳስ 6 ቀን 2013 ዓ.ም
የገቢዎች ሚኒስቴር በአምስት ወራት ውስጥ ከ126 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ በአምስት ወራት ውስጥ ከ126 ነጥብ ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ እና ከዕቅድ በላይ አፈጻጸም ማስመዝገቡን ተናግሯል፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ወ/ሮ ኡሚ አባጀማል የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ በተደረገ ርብርብ በያዝነው በጀት... https://ethiofm107.com/2020/12/15/የገቢዎች-ሚኒስቴር-በአምስት-ወራት-ውስጥ/
የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ህወሓትን ተክቶ ክልሉን ሊያስተዳድር ነው?
https://soundcloud.com/user-953568/6danppt6vbqe
ፑቲን በመጨረሻ ለባይደን የእንኳን ደስ አሎት መልዕክት አስተላልፉ

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጆ ባይደንን ዛሬ በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ በመሆናቸው ለጆን ባይደን ከስድስት ሳምንት በኋላ እና የምርጫ ኮሌጁ በይፋ የባይደንን አሸናፊነትን ባረጋገጠ ከአንድ ቀን በኃላ ነው የእንኳን ደስ አሉት መልዕክት ያስተላለፉት ፡፡

የምርጫው ውጤት ከታወቀ በጥቂት ቀናት ውስጥ ብዙ የዓለም መሪዎች አዲስ ለተመረጡት ፕሬዚዳንት ባይደን እንኳን ደስ አሉት ሲሉ ፣ ፑቲን ግን ለአሸናፊው የእንኳን ደስ አሉ መልእክት ከማስተላለፋቸው በፊት ኦፊሴላዊ ውጤቱን መጠበቁ “ትክክል” ነው ብለው በወቅቱ ተናግረዋል ብሏል ሲኤን ኤ ኤን በዘገባው ፡፡

ቭላድሚር ፖቲን ለተመራጮ ፕሬዝዳንት ስኬት ተመኝተዋል፡፡

በዓለም ላይ በአሁኑ ወቅት እየገጠሟት ያሉትን በርካታ ችግሮች እና ተግዳሮቶች ለመፍታት ልዩነቶች አሉ፡፡

ነገር ግን ለዓለም ደህንነት እና መረጋጋት ሲባል ይህንን ልዩ ሃላፊነት የሚሸከሙት ሩሲያ እና አሜሪካ እንደሚሆኑ እምነታቸውን ገልጸዋል ፡፡

ፑቲን “በእኩልነትና በጋራ መከባበር መርሆዎች ላይ የተመሠረተ የሩሲያ-አሜሪካዊ ትብብር የሁለቱም አገራት ህዝቦች እንዲሁም የመላው ዓለም ማህበረሰብ ፍላጎቶችን የሚያሟላ ነው” ብለዋል ፡፡

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ፑቲን "እኔ በበኩሌ ከእርሶ ጋር ለመተባበር እና ከእርስዎ ጋር ለመገናኘት ዝግጁ ነኝ" ብለዋል ፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
ታህሳስ 6 ቀን 2013 ዓ.ም
በአለማችን ጋዜጠኞችን በማሰር ግብፅ፤ሳውዲ አረቢያ እና ሶሪያ ቀዳሚ ሆነዋል።
ሪፖርተርስ ሳንስ ፍሮንትርስ (አር.ኤስ.ኤፍ) እንዳስታወቀው ቻይና ፣ ግብፅ ፣ ሳዑዲ አረቢያ ፣ ቬትናም እና ሶሪያ ለሁለተኛ ዓመት የጋዜጠኞች የወህኒ ቤት መሆናቸውን ቀጥለዋል ፡፡
ድርጅቱ በሪፖርቱ ዘንድሮ በእስር ላይ የሚገኙት የጋዜጠኞች ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ቁጥሩ በሁለት ...
https://ethiofm107.com/2020/12/15/4736/
የእንሰት አዘገጃጀትን የሚያዘምን ቴክኖሎጂ ወደ ስራ ሊገባ ነው

የተፈጠረው የእንሰት ማዘጋጃ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በተለይ የሴቶችን ጫና ከመቀነስና እንሰቱን በሚፍቁበት ወቅት ከሚያጋጥማቸው የጽንስ መቋረጥና የጀርባ ህመም እንደሚታደግ ታምኖበታል፡፡

የኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ፍሬው ደረጀ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ኢንስቲትዩቱ ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመሆን የእንሰት አዘገጃጀትን የሚያዘምን ቴክኖሎጂ ሰርቷል ብለዋል

እንደሚታወቀው ቆጮ(እንሰት) የሚፋቀው በባህላዊ መንገድ እግር ተሰቅሎ ነው ይሄን አድካሚ ሂደትም ይቀንሳል ተብሏል፡፡ ቆጮው ከተፋቀ በኋላም የመጭመቅ ሂደቱን የሚከውን መሳሪያም ተመራማሪዎቹ እንደፈጠሩ ሰምተናል፡፡

ቴክኖሎጂው በባህላዊ መንገድ ከሚዘጋጀው ቆጮ 45በመቶ ያህል ብክነትን ይከላከላል የሚሉት የኢንስቲቲዩቱ የህዝብና አለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ፍሬው ደረጀ ማሽኑ ጊዜ ቆጣቢ ስለመሆኑም ይናገራሉ፡፡

ከዚህ ቀደም በባህላዊ መንገድ ሲዘጋጅ 15ሰው ሆነው በአንድ ቀን ሊጨርሱት የሚችሉትን የቆጮ መፋቅ ስራ ቴክኖሎጂው ወደ 2ሰአት ያወርድላቸዋል ብለዋል፡፡

የእንሰት አዘገጃጀት ቴክኖሎጂውን ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ጋርም ለመስራት ዝግጁ ነን ሲሉ አቶ ፍሬው ደረጀ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

እንሰትን በደቡብ እና ደቡብ ምእራብ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚኖሩ ከ20 ሚሊዬን በላይ ዜጎች ለምግብነት እንደሚያውሉት መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
ታህሳስ 7 ቀን 2013 ዓ.ም
በመቅደላዊት ደረጀ
አንጋፋው የጥበብ ባለሙያ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ በ84 አመት እድሜአቸው ዛሬ ታህሳስ 7 ቀን 2013 ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመድ መፅናናትን ይመኛል።
ከነገ ጀምሮ ለአንድ ወር ወደ አንድነት ፓርክ የሚወስደው መንገድ በግንባታ ምክንያት ይዘጋል ተባለ፡፡

በታላቁ ቤተመንግስት ወደ አንድነት ፓርክ የሚወስደው መንገድ ግንባታ ሰለሚጀመር አሽከርካሪዎች አመራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

የታላቁ ቤተመንግስት አንድነት ፓርክን ያለ ትራፊክ መጨናነቅ መጎብኘት የሚያስችል የውስጥ ለውስጥ ዋሻ ግንባታ ምክኒያት ከነገ ህዳር08/2013 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ወር የሚቆይ የተወሰኑ መንገዶችን ዝግ እንደሚሆኑ ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

ለዚሁ ስራ ሲባል ለአንድ ወር የሚቆይ የተወሰኑ መንገዶችን የሚዘጉ ሲሆን ከሂልተን ሆቴል ተነስቶ ወደ ቀኝ የሚታጠፉ ተሸከርካሪዎች እና ከካሳንችስ ወደ 4 ኪሎ የሚያስወጣው መንገድ ከነገ ህዳር08/2013 ዓ.ም ጀምሮ የሚዘጋ በመሆኑ አሽከርካሪዎችም ኢንተርኮንትኔታል ሆቴል በንግድ ሚንስቴር በሂልተን ሆቴል ወደ 4 ኪሎ እና ከካሳንቺስ መለስ አካዳሚ ሴቶች አደባባይ አቧሬ አድርገው ወደ 4 ኪሎ መውጣት እንደሚችሉ ኤጀንሲው ገልጿል፡፡
ጃንሜዳ ለጥምቀት በዓል ማክበሪያ ዝግጁ እንዲሆን የከተማ አስተዳደሩ ላደረገው ትብብር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምስጋና አቀረበች ።

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጱህ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ እንዲሁም የተለያዩ ሀጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጃንሜዳ የጥምቀት ማክበሪያ ስፍራን ጎብኝተዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጱህ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ የከተማ አስተዳደሩ ጃንሜዳን ለጥምቀት በዓል እንዲደርስ ቃል በገባው መሰረት እዚህ ደረጃ ደርሶ በማየታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል ።
ጃንሜዳ ለበዓሉ ማክበሪያ ዝግጁ ለማድረግ ከምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጀምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ላደረጉት ትብብር በቤተክርስቲያኗ እና በህዝበ ክርስቲያኒቱ ስም አቡነ ማቲያስ ምስጋና አቅርበዋል ።
ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው የጥምቀት በዓል የሁሉም ኢትዮጵያውያን በዓል ፤የዓለም ቅርስ በመሆኑ ልንጠብቀው እና ልንንከባከበው ይገባል ብለዋል ።

በዓሉ የኢትዮጲያዊነት ባህል እና እሴት የሚጎላበት በመሆኑ የአካባቢው ወጣቾች ፣የስፖርት ቤተሰቡ እና አርቲስቶች ተባብረው ለበዓሉ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ወ/ሮ አዳነች ተናግረዋል ።

የዘንድሮው የጥምቀት በዓል ሀይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ በድምቀት እንዲከበር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸው ህዝበ ክርስቲያኑ ላሳየው ትዕግሥት እና ተሳትፎ ምክትል ከንቲባ አመስግነዋል ።
አንጋፋው የጥበብ ባለሙያ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ ማናቸው?

https://soundcloud.com/user-953568/cdxgwnvsyrtf
በመተከል እና በወለጋ በተደጋጋሚ ዜጎችን ከሞት መታደግ አለመቻል ለችግሩ የተሰጠው ትኩረት ማነስ ውጤት እንደሆነ ኢዜማ ገለፀ::

በንፁሃን ዜጎች ላይ በተለይ በሁለቱ አካባቢዎች በተደጋጋሚ እየደረሰ ያለው አሰቃቂ ግድያ ማቆሚያ ያልተገኘለት ለጉዳዩ ከተሰጠው የትኩረት ማነስ መሆኑ ልብ ሊባል እንደሚገባው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ ገልጧል::

በአለፉት ስድስት ወራት በተደጋጋሚ በነዚሁ ቦታዎች ላይ ከስብዕና ውጪ የሆኑ አሰቃቂ ድርጊቶች ንፁሃን ላይ የተፈፀመ ቢሆንም እንዳይደገሙ የተወሰዱ እርምጃዎች ችግሩን የሚመጥኑ አይደሉም ብሏል ፓርቲው፡፡

የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ ባልቻሉ በየደረጃው ያሉ ኃላፊዎች ላይ ተጠያቂነትን ማስፈን አልተቻለም ያለ ሲሆን ክቡር የሆነው የሰው ሕይወት በየቀኑ እየጠፋ፣ ቤተሰብ እየፈረሰ እና ማኅበራዊ ሰንሰለታችን እየተበጠሰ፣ በአካባቢው የሚኖሩ ዜጎች የፌደራልም ሆነ የክልል መንግሥታት በሕይወት የመቆየት ዋስትናን ሊሰጡን አይችሉም ብለው እንዲያምኑ የሚገደዱበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል ብሏል።

ድርጊቶቹ መደጋገማቸው፣ የፌደራልም ይሁን የክልል መንግሥታት እና የፀጥታ አካላት ንፁሃን ላይ የሚደርሱ አደጋዎች ከመድረሳቸው በፊት አስቀድሞ የመከላከል፣ አደጋዎቹ ሲከሰቱ ከባድ ጉዳት ሳያደርሱ የመቆጣጠር እንዲሁም ከደረሱ በኋላ አስተማሪ የሆነ እርምጃ የመውሰድ አቅማቸው ከፍተኛ ክፍተት እንዳለበት በግልፅ የሚያሳይ ነው ሲል ኢዜማ በመግለጫው አስቀምጧል።

ከአሁን በኋላ በምንም ምክንያት ተመሳሳይ ድርጊቶች መደገም እንደሌለበት ፓርቲው የገለፀ ሲሆን ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን በተደጋጋሚ ጥቃት የደረሰባቸው ዜጎች በመንግሥት ጨርሶ ተስፋ እንዲቆርጡ እና ደህንነታቸውን የመጠበቅ ኃላፊነት በራሳቸው እንዲወጡ በመግፋት ወደማንወጣው እና ታሪካዊ ጠባሳ ወደሚጥል አዘቅት ውስጥ ሊከተን የሚችል ከፍተኛ አደጋ እንደተጋረጠብን ሊታወቅ ይገባል ሲል አሳስቧል ፓርቲው፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በመተከል አና በወለጋ በጠፋው የሰው ሕይወት የተሰማዉን ጥልቅ ሐዘን በላከልን መግለጫ ገልጧል፡፡

በሔኖክ አሰራት
ታህሳስ 8 ቀን 2013 ዓ.ም
የህወሓት አመራሮች የሚገኙበትን ለጠቆመ የ10 ሚልዮን ብር ሽልማት ማዘጋጁትን የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት ማስታወቁን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ሌ/ጀነራል አስራት ዴኔሮ እንደተናገሩት የህወሓት አመራሮችን በአጭር ጊዜ በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ሽልማቱ መዘጋጀቱን ገልፀዋል።

በዚህም የመከላከያ ሠራዊት በህግ የሚፈለጉትን የህወሓት አመራሮች ያሉበትን ቦታ ለጠቆመ የ10 ሚሊዮን ብር ሽልማት እንደሚሰጥ አመልክተዋል።(ኢብኮ)

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል ድረ ገጻችንን https://ethiofm107.com/ ይጎብኙ::
ታህሳስ 9 ቀን 2013 ዓ.ም
የዛምቢያ መዲና ሉሳካ ከንቲባ ሰርጋቸውን በከተማዋ ስታዲየም ውስጥ ለማካሄድ አቅደዋል፡፡ ይህ እቅዳቸው ግን ውዝግብ አስነስቷል፡፡ ሀገሪቱ በኮሮናቫይረስ ወቅት እንዲተገበሩ ከደነገገቻቸው ህጎች መካከል ደግሞ ሰርጎች በ50 ሰዎች ....
https://ethiofm107.com/2020/12/18/4765/
ከትናንት ጀምሮ እየተካሄደ የሚገኘው የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ዛሬም እንደቀጠለ ነው፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስበስባውን ከትናንት ጀምሮ እያካሄደ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ዛሬም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መምከሩን ቀጥሏል፡፡ ኮሚቴው በተለያዩ ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያሳልፋል፤ አቅጣጫዎችንም ያስቀምጣል ተብሎ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከብልፅግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል ድረ ገጻችንን https://ethiofm107.com/ ይጎብኙ::

ታህሳስ 9 ቀን 2013 ዓ.ም
ዛሬ ረፋድ ላይ ቦሌ ኦሮሚያ ታወር አጠገብ እየተሰራ ካለ ህንጻ ላይ የወደቀ እንጨት እግረኞች ላይ ጉዳት አደርሷል፡፡

አራቱ ጓደኛሞች በህንፃው ስር ባለ የእግረኛ መንገድ ላይ እያለፉ ሳለ ነበር ከህንጻው ላይ የወደቀ እንጨት አግኝቷቸው አንዱን ለከፋ ጉዳት ሁለቱን ደግሞ ቀላል ጉዳት ያደረሰባቸው፡፡አንዱ ግን ከዚህ ጉዳት መትረፍ ችሏል፡፡

ሪፖርተራችን በስፍራው በመድረስ ከአይን እማኞች እንዳጣራው አሁን ጎዳት የደረሰባቸው ግለሰቡች ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡

በከተማችን እየተገነቡ ካሉ ይህንን መሰል ህንጻዎች ተገቢው ጥንቃቄ እየተደረገ ባለመሆኑ መሰል አደጋዎች ቁጥራቸው እየጨመረ መጥቷል፡፡
በመሆኑም የህንጻ አሰሪዎች አስፈላጊውን ጥንቃቂ በሚገነቡበት ህንጻ አከባቢ እንዲወስዱ የሚመለከተው አካል ጥብቅ ክትትል ይገባዋል፡፡

እግረኞችም በእነዚህ አከባቢዎች መንገድ ሲያቋርጡም ሆነ ሲጓዙ ፈጠን ብሉ መጓዝ አሊያም አማራጭ መንገድ መጠቀም ይገባቸዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል ድረ ገጻችንን https://ethiofm107.com/ ይጎብኙ::

ደረሰ አማረ
ታህሳስ 9 ቀን 2013 ዓ.ም