Ethio Fm 107.8
19.4K subscribers
5.79K photos
16 videos
4 files
2.26K links
በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!
Download Telegram
ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ቀረጥና ታክስ በማጭበርበር የምግብ ዘይትና ጫማ ከውጪ ሊያስገቡ የሞከሩ ነጋዴዎች ተያዙ።

በንግድ ማጨበርበር ሊታጣ የነበረ ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ቀረጥና ታክስ ሊሰበሰብ መሆኑንም የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው በአዳማ እና ሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በድምሩ ከውጭ የገቡ የምግብ ዘይትና ጫማ መከፈል የነበረበት እና በተሳሳተ ዕቃ መግለጫ መንግስት ሊያጣው የነበረ 16 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ቀረጥና ታክስ ተደርሶበት እንዲሰበሰብ መወሰኑን ገልጧል፡፡

በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ከቀረጥ ነፃ ወደ ሀገር እንዲገባ የተፈቀዱ የምግብ ፍጆታዎች ቢኖሩም ፤ በአዳማ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ከተፈቀደላቸው ታሪፍ ቁጥር ውጪ 14 ሚሊዮን ብር 508 ሺህ 328 ብር ከ 28 ሳንቲም ፤ ቀረጥና ታክስ አጭበርብረው ሊያስገቡ ሲሞክሩ ተደርሶባቸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በሞጆ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት በዲክላራሲዮን ቁጥር 4-27474/20 የተመዘገበ ዕቃ አስመጭው ቀረጥና ታክስ ከፍሎ በገቢ ዕቃ አወጣጥ በኩል በዝቅተኛ የስጋት ደረጃ ለእቃው መልቀቂያ ከተሰጠው በኃላ በኢንተለጀንስ በኩል በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ቀደም ሲል ከተገለፀው እቃ ልዩነት ተገኝቷል ብሏል ሚኒስቴሩ::

በዚህ የእቃው አገላለፅ ችግር ምክንያት ሊጭበረበር የነበረ ብር 1 ሚሊዮን 705 ሺህ 473 ብር ከ 30 ሳንቲም እንዲከፈል ተደርጓል ተብሏል ::

በሔኖክ አስራት
ሕዳር 3 ቀን 2013 ዓ.ም
በአሶሳ ከተማ ዛሬ ረፋድ ለሽብር ስራ ሊውል ይችላል በሚል ተጠርጥሮ በፖሊስ የተያዘው በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ቆጠራው እስካሁን አልተጠናቀቀም።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አብዱላዚዝ ሙሀመድ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት የህወሀት ቡድን ተላላኪዎች በክልሉ ከፍተኛ የጥፋት ሴራ ደግሰው ቢንቀሳቀሱም አስቀድመን እርምጃ በመውሰዳችን የታሰበውን ሴራ አክሽፈናል ብለዋል፡፡

በክልሉም የተለያዩ ከተሞች የሽብር ተልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ ግለሰቦች ዛሬ ረፋድ በአሶሳ ከተማ በሚሊዮን የሚገመት ገንዘብ መያዙ የተገለጸ ሲሆን ትክክለኛውን የገንዘብ መጠን ለማወቅ ቆጠራ ላይ መሆናቸውንም ኮሚሽነር አብዱልአዚዝ ነግረውናል።

ይህ ገንዘብ ከመቀሌ መላኩን የተናገሩት ኮሚሽነሩ የህወሃት ቡድን በውጊያ ላይ ሆኖም ሽብር ከመፍጠር ወደ ኋላ እንደማይል ማሳያ ነውም ብለዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በህግ ጥላ ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ ለሽብር ተልዕኳቸው ማስፈጸሚያ በሚል ወደ አሶሳ የተላከው እና በፖሊስ እጅ የሚገኘውን የገንዘብ መጠን ለማወቅ ከዛሬ ረፋድ ጀምሮ ቆጠራ ላይ ነን ቆጠራው ሰልችቶናል ብለውናል።

እስካሁን ባለን ቆጠራ እና ግምት የተያዘው ገንዘብ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ሊሆን እንደሚችል እና ቆጠራው እንዳለቀ መረጃውን ለህዝብ ይፋ እናደርጋለን ሲሉም ነግረውናል።

በደረሰ አማረ
ሕዳር 3 ቀን 2013 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ ትርምስ ለመፍጠር የህወሃት ቡድን ያሰማራቸው 242 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም የህወሃት ጁንታ ቡድን ያሰማራቸው 242 ግለሰቦች በከተማዋ ትርምስ ለመፍጠር ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮሚሽነር ጌቱ ገልጸዋል፡፡

ግለሰቦቹ 18 ያህል ቦምብ፣ 2 ፈንጂ፣ ላውንቸር ፣ ከ174 በላይ ሽጉጥና ከ4 ሺህ በላይ ጥይቶችና 4 ወታደራዊ የጦር ሜዳ መነጽሮችም በጥፋት ሃይሉ እጅ የተለያዩ አካባቢዎች በቁጥጥር ስር እንደዋለም ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል።

በተጨማሪም 23 የረጂም ርቀት መገናኛ ሬድዮ በሱር ኮንስትራክሽን በተደረገ ብርበራ ማግኘቱን ኮሚሽነር ጌቱ በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም 350 የተለያዩ ሃገራት ሲም ካርዶች ከአንድ ግለሰብ የተገኙ ሲሆን 7 የተለያዩ ሃገራት ፓስፓርት፣ 74 የተለያዩ የደንብ ልብሶችና የውጭ ሃገር ስልክ መጥለፊያ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል፡፡

ከወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ጋር ተያይዞ በከተማዋ ምንም አይነት ችግሮች እንዳይከሰቱ ህብረተሰቡ አካባቢውን በንቃት ከመጠበቁ በተጨማሪ መረጃና ጥቆማ በመስጠት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን አስቀድሞ በማምከን እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ኮሚሽነር ጌቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ሕዳር 3 ቀን 2013 ዓ.ም
የፌደራል ፖሊስ 14 የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎችን ከስራ አገደ።

ፌዴራል ፖሊስ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ አንዳንድ የግል የጥበቃ ኤጀንሲዎች የተቋቋሙበትን የመንግሥት እና የግል ተቋማትን የመጠበቅ ዓላማን ወደ ጎን በመተው ከቀጠሯቸው የጥበቃ አባላት መካከል ለሌላ እኩይ ተግባር የመረጧቸውን በመመልመል፣ ለተቋም ጥበቃ የተሰጣቸውን የጦር መሣሪያ በማስታጠቅ እና በማሰማራት በሕዝብ እና በመንግሥት ተቋማት እንዲሁም በተለያዩ አካላት ላይ ጥቃት ለመፈፀም እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ተደርሶበታል።

ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎቹ በቀጠሯቸው የጥበቃ አባላት እና ተባባሪዎቻቸው ባንኮችን እና የተለያዩ ድርጅቶችን ሲዘርፉ እና ሲያዘርፉ መቆየታቸውንም በአብነት ጠቅሷል።

በዚህም ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ገንዘብ እና ንብረት መዝረፋቸውን እና እንዲዘረፍም ማድረጋቸውን ገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪም ተቋማቱን እንዲጠብቁበት የታጠቁትን በርካታ የጦር መሣሪያ ይዘው እንደጠፉም ተረጋግጧል ብሏል።

እነዚህ ከተልዕኮአቸው ውጭ እንደሚንቀሳቀሱ የተደረሰባቸው የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች ይህም አልበቃ ብሏቸው አሁን ባለው ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ በጁንታው የሕወሓት ወንበዴ የተሰጠውን ተልዕኮ ለመፈፀም የተለያዩ ግለሰቦችን ወደ ኤጀንሲዎቹ አስርገው በማስገባት እና የጦር መሣሪያ በማስታጠቅ በኅብረተሰቡ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ ጥቃት ለመፈፀም እያሴሩ መሆኑ ነው ፌዴራል ፖሊስ የገለጸው።

በመሆኑም ከታች የተዘረዘሩት የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች፦

1. ንስር የሰው ሃይል እና የጥበቃ አገ/ሃ/የተ/የግ/ማ
2. አጋር የጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ
3. ስብኃቱና ልጆቹ የንብረት አስ/ጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ
4. ሰላም ሴኩሪቲ ሶሉሽን ኃ/የተ/የግ/ማ
5. ኃይሌ ተክላይ እና ጓደኞቻቸው የጥበቃ አገልግሎት ህ/ስ/ማ
6. ክፍሌ ጎሳዬ ሃጎስ እና ወ/ገብርኤል የጥበቃ አገልግሎት ሽርክና /ማ
7. ዮናስ፣ ሮዛ እና መብርሂት የጥበቃ አገልግሎት ህ/ሽ/ማ
8. ሃየሎም እና ብርሃኔ የጥበቃ አገልግሎት ህ/ሸ/ማ
9. ደመላሽ፣ ሃፍቱ እና ጓደኞቻቸው የጥበቃ አገልግሎት ህ/ሸ/ማ
10. ህሉፍና ሃለፎም የጥበቃ አገ/ህ/ሽ/ማ
11. ዋልታ የጥበቃ የሰው ኃይልና ኮሚሽን ኃ/የተ/የግ/ማ
12. ሴፍ የጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ
13. አትላስ ጠቅላላ አገ/ኃ/የተ/የግ/ማ
14. ጎህ የጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ

ለሀገር እና ለዜጎች ሰላም እና ደህንነት ሲባል ሥራቸውን እንዲያቆሙ የተወሰነና እስከአሁን ባለው ሀገር የማተራመስ እና ሕገ-ወጥ ሥራቸው በህግ የሚጠየቁ መሆኑን ገልጿል።

ስማቸው የተገለጸው የጥበቃ ተቋማት በአስቸኳይ ሥራቸውን አቁመው ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ሪፖርት እንዲያደርጉም አሳውቋል።

በተጨማሪም ማንኛውም የግልም ሆነ የመንግሥት አካል ከነዚህ የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች ምንም ዓይነት ቅጥር እንዳይፈፅም የተከለከለ መሆኑን አሳስቧል።

በመጨረሻም የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎቹ ስር ተቀጥረው ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እየተወጡ ያሉ ሠራተኞችን በተመለከተ ተገቢውን ልየታ በማድረግ ማስተካከያ እስኪወሰድ ድረስ በተመደቡበት ቦታ የጥበቃ ሥራቸውን አጠናክረው እንዲሠሩ እና የሚጠብቋቸው የግል እና የመንግሥት ተቋማት ኃላፊዎችም በተሰጠው መግለጫ መሠረት ተገቢውን ቁጥጥር እና ክትትል እንዲያደርጉ ሆኖ የዕለት ተዕለት ሥራቸውን ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ የጦር መሣሪያ ቁጥጥርና የግል ጥበቃ ተቋማት ብቃት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት ሪፖርት በማድረግ ቀጣይ በሚሰጡ የሥራ መመሪያዎች ብቻ ሊሠሩ እንደሚገባ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አሳስቧል።

ኢትዮ ኤፍ ኤፍ የኢትዮጵያውያን
ሕዳር 3 ቀን 2013 ዓ.ም
ዶክተር ሙሉ ነጋ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ።

በፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ መሠረት በትግራይ ብሔራዊ ክልል የሚቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር አስመልክቶ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ማጽደቁ ይታወቃል።

በጸደቀው ደንብ መሠረት ዶ/ር ሙሉ ነጋ በክልሉ የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሰይመዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው የጊዜያዊ አስተዳደሩ አካል ሆነው፣ የክልሉን የመንግሥት አስፈጻሚ አካላትን የሚመሩ ኃላፊዎችን ፣ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመመልመል እንደሚሾሙ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በፌስቡክ ገጻቸው አስፍረዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ሕዳር 4 ቀን 2013 ዓ.ም
የአሜሪካ የምርጫ ደህንነት ባለሥልጣናት የትራምፕን የማጭበርበር ጥያቄ ውድቅ አደረጉ።

ይህንን ለማየት የተሰየመው ኮሚቴ እንዳስታወቀው “የትኛውም የድምፅ አሰጣጥ ስርዓት ድምፆችን መሰረዙን ወይም መጥፋቱን ፣ ድምፁን መቀየሩን ወይም በምንም መልኩ ተጠልፏል የሚል መረጃ የለም ነው ያለው፡፡

ባለፈው ሳምንት በተካሄደው ምርጫ ተሰናባቹ ፕሬዝደንት ትራምፕ ያለ ምንም ማረጋገጫ 2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ድምጽ እንዲጠፋ ተደርጓል የሚል ክስ ማቅረባቸውን ተከትሎ ነው ይህንን ተናገሩት፡፡

ትራምፕ የዴሞክራቱ ጆ ባይደንን አሸናፊትን እስካሁን አልተቀበለም፡፡

ውጤቱ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን የተነገረ ቢሆንም የተወሰኑ ቆጠራዎች ግን አሁንም እንደቀጠሉ ናቸው ፡፡

ቢቢሲ ተመራጩ ፕሬዝደንት ባይደን የአሪዞና አሸናፊ አድርጎ በመገመት 11 ተጨማሪ የምርጫ ኮሌጅ ድምጾችን ይሰጠዋል፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
ሕዳር 4 ቀን 2013 ዓ.ም
በሙስና የተማረረው ግብጻዊ ራሱ ላይ እሳት ለኮሰ።

ግብፃዊው ሰው በአገሪቱ መዲና ካይሮ በሚገኘው ታህሪር አደባባይ ላይ ነው ራሱ ላይ እሳት የለኮሰው፡፡

ግብጻዊው ሰው ሙስናን በመቃወምና በማጋለጡ ከስራ መባረሩን ፤ሀገሪቱ የዘራፊዎች ምድር መሆኗ በእጅጉ እንዳማረረውም በእሳት እየተለበለበ ተናግሯል፡፡

ሚዲል ኢስት አይ እንደዘገበው ግለሰቡ የክልል ባለስልጣናት ሲሰሩት የነበረውን ሙስናን በማጋለጡ ከባንክ ስራው እንደተባረር ተናግሯል ፡፡

ግለሰቡ በፌስቡክ የቀጥታ ስርጭት ላይ ህይወቱ መበላሸቱን እና ራሱንም ቤተሰቡንም ማስተዳደር እንዳልቻለ አምርሮ ነው የተተናገረው፡፡

ሀገሪቱ በጥቂት “የሌቦች” ቡድን እየፈረሰች ነው ብሏል ፡፡

በኃላም በስፍራው የደረሱት የደህንነት ሰዎች እሳቱን በቶሎ በማጥፋት ህይወቱን ታድገውታል፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
ሕዳር 4 ቀን 2013 ዓ.ም
የአፍሪካ ህብረት የጸጥታ ሃላፊዉ ገብረእግዚያብሄር መብራቱን ከሃላፊነት አነሳ፡፡

ሜጀር ጀነራል ገ/ሄር መብራቱ ከሃላፊነት የተነሱት የኢትዮጵያ መከላከያ ሚንስቴር የታማኝነት ችግር አለባቸዉ የሚል ቅሬታ ማቅረቡን ተከትሎ ነዉ ተብሏል፡፡

በዚህም የህብረቱ ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት የህብረቱን የጸጥታ ሃላፊ ከሃላፊነት ማንሳታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

በፈደራል መንግስትና በህዋህት ቡድን መካከል እየተደረገ ባለዉ ጦርነት ሜጀር ጀነራሉ ለህብረቱም ሆነ ለሃገራቸዉ ሃላፊነታቸዉን በሚገባ ለመወጣት ቁርጠኛ አይደሉም በሚል የመከላከያ ሚንስቴር ለህብረቱ ደብዳቤ መጻፉን ዘገባው ጠቁሟል።

በሙሉቀን አሰፋ
ሕዳር 4 ቀን 2013 ዓ.ም
በአዳማ እና በአዲስ አበባ ሁለት የገቢዎች ቢሮ ሰራተኞች ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተያዙ።

በአዳማ ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት አንድ ተጠርጣሪ ባለሙያ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ለመቀበል ስምምነት ወስዶ፣ የመጀመሪያውን ዙር ክፍያ ብር 5ዐዐ ሺህ ብር ሲቀበል እጅ ከፍንጅ ሆቴል ውስጥ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል፡፡

በምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በኦዲት የሥራ ሂደት ውስጥ የቡድን መሪና በዚሁ የሥራ ክፍል ስር አንድ ከፍተኛ ባለሞያ 5 ሚሊዮን ብር ለመቀበል ተስማምተው፤ የመጀመሪያውን ክፍያ ብር 2ዐ0 ሺህ ብር ሲቀበሉ ሁለቱም እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል፡፡

የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው እንደገለፁት በሁለቱም የገቢዎች ሚኒስቴር ቅ/ጽ/ቤቶች በተሳካው የሕግ ማስከበር ሥራ የግብር ከፋዮቻችን ሚና እጅግ በጣም የሚያኮራ ነበር፡፡

ስለሆነም በዚህ ስኬታማ ሥራ የተሳተፋችሁ አካላትን በሙሉ በራሴና በገቢዎች ሚኒስቴር ሥም ከልብ አመሰግናችኋለሁ ብለዋል፡፡

ሌሎች ግብር ከፋዮችና ሁሉም ኢትዮጵያውያን የራሳችሁና የሀገራችሁ ሀብት በግለሰቦች እንዳይዘረፍና መከፈል ያለበት ግብርም ሳይከፈል እንዳይቀር እንዲሁም የዜግነት ግዴታችሁን በመወጣት እንድትተባበሩና እንድንተጋገዝ ጥሪዬን ለማቅረብ እወዳለሁ ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ አክለውም የግብርን ፍትሃዊነት እና ህጋዊነት በማረጋገጥ ለጤናማ ኢኮኖሚ ዕድገት ሀገራዊ ሚናችንን ለመወጣት በተግባር እየሰራን እንገኛለን ፤ ወደፊትም አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

በሔኖክ አስራት
ሕዳር 4 ቀን 2013 ዓ.ም
Forwarded from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ወሳኒ እዋናዊ ጻውዒት ንህዝቢ ትግራይን ሓይልታት ጸጥታን
የተከዜ ሃይል ማመንጫ በቦንም ተመታ ተብሎ የተናፈሰው ወሬ ሀሰት መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ አስታወቀ።

ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ መረጃ ለህዝብ እያደረሰ የሚገኘው ይህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ በማህበራዊ ድረገጹ እንዳስታወቀው ተከዜ ሀይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ፣ ልክ እንደ ሌሎቹ የኃይል ማመንጫ ግድቦች ሁሉ በፌደራል መንግሥት የተገነባና የሚያስተዳድረውም የፌደራል መንግሥት ነው።

እሁድ ጥቅምት 29፣ 2013 ዕለት የህወሓት ሚሊሻ ግድቡን ለመጠበቅ የተሠማራውን የፌደራል ፖሊስ ኃይል ከሥራው ለማደናቀፍ ጥቃት ፈጽሟል።

የተጎዱት እና የተገደሉት ቁጥር ያልተረጋገጠ ቢሆንም፣ በሕይወት የተረፉት 11 የፌደራል ፖሊስ አባላት ለ14 ሰዓት ያህል በእግር ተጉዘው፣ ተራራዎችን አቆራርጠው ወደ ጎንደር ገብተዋል።

በቀጣዮቹ ቀናት የህወሓት አክቲቪስቶች በማኅበራዊ ሚዲያ አማካኝነት "ግድቡን ተቆጣጥረናል" የሚል መረጃ ማሰራጨታቸው ተስተውሏል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል የህወሓት ሚልሻዎች በማይካድራ በንጹሀን ዜጎች ላይ የፈፀሙትን ጭፍጨፋ አስመልክቶ ሪፖርት ባወጣበት በህዳር 3፣ 2013 ዕለት፣ የህዝብን የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየር የተከዜ ግድብ በቦንብ እንደተመታ የሚያትት ሆን ተብሎ የተቀናበረ፣ የሀሰት መረጃን ህወሓት በቴሌቪዥን አሰራጭቷል ብሏል።

ባለሁለት ክበብ ቅስት ያለው እና በውሀ የተሞላ ግድብ በቦንብ ቢመታ ሊያስከትል የሚችለው መጥለቅለቅ እና ጥፋት ማንም ሊገምተው የሚችለው መሆኑ የመረጃውን ሀሰተኛነት በቀላሉ ማረጋገጥ እንደሚቻል ይሄው ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ መረጃ የሚያቀብለው የመረጃ ተቋም አስታውቋል።

ተፈጥሯዊ ባህሪው ነውና፣ በህወሓት ውስጥ የሚገኘው የጽንፈኞች ቡድን በሀሰት ለማሳመን ጥረት ማድረጉን ይቀጥላል። ህወሓት የሀሰት መረጃ የማሠራጨት ዘመቻውን በትጋት መቀጠሉን ሁሉም ሰው እንዲገነዘብ በድጋሚ ለማሳሰብ እንወዳለንም ብሏል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ሕዳር 4 ቀን 2013 ዓ.ም
ፈረንሳይ በማሊ አንድ ከፍተኛ የአልቃይዳ መሪ መግደሏን አስታወቀች፡፡

የፈረንሳይ መከላከያ ሚንስትር ፍሎረንስ ፓርሊ ከደቂቃዎች በፊት በሰጡት መግለጫ በሰሜን ምስራቅ ማሊ በተካሄደ ዘመቻ በሰሜን አፍሪካ የአልቃይዳ ክንፍ ወታደራዊ መሪ ባህ አግ ሙሳ በሀገሪቱ ወታደሮች መገደላቸውን አስታውቀዋል፡፡

እኚህ የጂሃዳዊ እንቅስቃሴ መሪ በማሊ እና በዓለም አቀፍ ኃይሎች ላይ ለተፈጸሙ በርካታ ጥቃቶች ተጠያቂ ናቸው ተብሎ ይታሰባል፡፡

መከላከያ ሚንስትሯ ፓርሊ በሰጡት መግለጫ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ይህ ትልቅ ስኬት መሆኑን አመልክተዋል፡፡

በሰሜን አፍሪካ የአልቃይዳ ክንፍ ወታደራዊ መሪ ሙሳ በአሜሪካ የሽብርተኝነት ዝርዝር ውስጥ ከተቀሱ ሽብርተኞች መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡

ፈረንሣይ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ አማፅያንን ለመዋጋት ከ 5 ሺህ በላይ ወታደሮችን አሰማርታለች፡፡

እነዚህም ወታደሮች በማሊ ከፍተኛ እንቅስቃሴዎችን በማክሸፍ ሲሳተፉ ቆይተዋል፡፡

የፈረንሳይ ወታደሮች በዚህ ወር ብቻ በማዕከላዊ ማሊ ከ 50 በላይ ጂሃዲስተኞችን መግደላቸውን ዘ ዲፌንስ ፖስት ዘግቧል፡፡

በደረሰ አማረ
ጥቅምት 4 ቀን 2013 ዓ.ም
ወጋገን ባንክ የአዲስ አበባ ፖሊስ ያዝኩት ያለውን የጦር መሳሪያው በህጋዊ መንገድ ለባንክ ጥበቃ ስራ የገዛው መሆኑን አስታወቀ።

ከዛሬ ረፋድ ጀምሮ የተለያዩ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን በወጋገን ባንክ ተከዝኖ ተገኘ ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ስህተት መሆኑን ወጋገን ባንክ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል።

በ2011 ዓ.ም በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ፍቃድ አግኝተን የገዛነውን የጦር መሳሪያ ነው እየተጠቀምንበት ያለነው ሲሉ የወጋገን ባንክ ተጠባባቂ ፕሬዝደንት አቶ ክንዴ አበበ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

ከጋፋት ኢንደስትሪያል የተመረቱ 113 የጦር መሳሪያዎችን በሶስት ዙር ገዝተን ተረክበናል ብለዋል።

አሁን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር ለቅርንጫፎች ባንኮች ልናከፋፍል ስላልቻልን የጦር መሳሪያዎቹን በዋናው መስሪያ ቤት አስቀምጠናቸው በፍተሻ ወቅት ሲገኙ በጸጥታ አካላት እንደተወሰደባቸው አቶ ክንዴ አበበ ነግረውናል።

ባንኩ ጦር መሳሪያዎቹን ከሚመለከተው የመንግስት ተቋም ጋር ተነጋግረን ህጉን ተከትለን የገዛናቸው ናቸው ብሏል።

የጦር መሳሪያዎቹ በቅርብ ለተከፈቱትና አዲስ ለሚከፈቱ ቅርንጫፎቻችን ያዘጋጀናቸው ናቸው ሲሉም አክለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ነው እንግዲህ ዛሬ ጠዋት በመገናኛ ብዙሀን 73 የጦር መሳሪዎች ህገ ወጥ ናቸው መባሉን የሰማነው ያሉት አቶ ክንዴ መረጃውን ላወጣው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በደብዳቤ ጥያቄ አቅርበናል ብለዋል ነገር ግን መልስ ሊሰጠን አልቻለም ሲሉ ነግረውናል።

በመቅደላዊት ደረጀ
ሕዳር 4 ቀን 2013 ዓ.ም
በአዲስ አበባ የወደቀ ቦንብ እጃቸው ላይ የፈነዳባቸው ህፃናት ጉዳት ደረሰባቸው።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው በተለምዶ 02 ወይም ካፒቴን ደምሴ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ህፃናት ወድቆ ያገኙት ቦንብ እጃቸው ላይ ፈንድቶ ጉዳት እንደደረሰባቸው አሳውቋል።

በዚህ ጉዳይ ዝርዝር መረጃ ይሰጣል ተብሏል።
በአዲስ አበባ የሽብር አደጋዎችን ለማድረስ እቅድ የነበረው የህወሀት ቡድን የጸጥታ ሀይሉ ቁጥጥር ሲጠነክርበት በየቦታው የጣላቸው ቦንቦች ሊኖሩ እንደሚችሉ የፌደራል ፖሊስ አሳሰበ።

በመሆኑም ህብረተሰቡ የወደቁ ነገሮችን ሲያይ ለጸጥታ አካላት እንዲጠቁም እና ህጻናትን እንዲጠብቅ ኮሚሽኑ ጥሪውን አቅርቧል።

እስካሁን በአዲስ አበባ የህውሀት ቡድን በጣሉት ቦምብ አምስት ህጻናት ጉዳት እንደደረሰባቸው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አረጋግጧል፡፡

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው በተለምዶ 02 ወይም ካፒቴን ደምሴ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ህፃናት ወድቆ ያገኙት ቦንብ እጃቸው ላይ ፈንድቶ ጉዳት እንደደረሰባቸው አሳውቋል።

በዚህም መሰረት አራቱ ህጻናት መጠነኛ ጉዳት አስተናግደው የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ህክምና አግኝተው ወደ ቤተሰቦቻቸው ተቀላቅለዋል ተብሏል፡፡

አንደኛው ህጻን ግን ጉዳቱ ከፍተኛ ስለሆነ በሚኒሊክ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገለት እንደሚገኝ ነው የተነገረው፡፡

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊ አቶ ጄይላን አብዲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት የህውሀት ቡድን በአዲስ አበባ ሽብር ለመፍጠር ቢንቀሳቀስም ቁጥጥሩ ሲጠነክርበት ቦምቦቹን በየቦታው እየጣሉ በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

እስካሁን እነዚህ ቡድኖች በሁለት ቦታ በጣሉት ቦምብ ስድስት ሰው ላይ ጉዳት ደርሳልም ብለዋል አቶ ጄይላን፡፡

የህውሀት የጥፋት ቡድኖች በየቦታው ያሰማሯቸው ሰዎች በተለያዩ ቦታዎች የጣሉዋቸው ቦምቦች ሊኖሩ ስለሚችሉ አሁንም ወላጆች ለልጆቻቸው ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ተብሏል፡፡

በመሆኑም ህብረተሰቡ የተጣሉ እና የተቋጠሩ ነገሮችን በሚያገኝበት እና እየጣሉ የሚገኙ ሰዎችን በሚመለከትበት ጊዜ ለፖሊስ ጥቆማ መስጠት አለበት ተብሏል፡፡

ማንኛውም የከተማው ነዋሪ የተጣለ ነገር ከማንሳቱ በፊት በ991 እንዲሁም በነጻ የስልክ መስመር 011 111 01 11 ላይ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ደውሎ ማሳወቅ ይችላል፡፡

እንደዚሁም በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በ987 ወይም በቀጥታ የስልክ መስመር 011 551 80 00 ላይ ጥቆማቸውን ማድረስ ትችላላችሁ ተብሏል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሕዳር 6 ቀን 2013 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በኡጋንዳ ከሕወሐት ጋር በሽምግልና ውይይቶች ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ በተለያዩ የዜና አውታሮች የቀረበው መረጃ የተሳሳተ እና በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ግብረ ኃይል ያልተረጋገጠ ነው፡፡

የፌደራል መንግሥት በትግራይ ክልል የሕግ የበላይነትን ለማስከበር በቁርጠኝነት እየሠራ ይገኛል፡፡

የሚዲያ አካላት እንደ መሠረታዊ የጋዜጠኝነት አሠራር የኢትዮጵያን የሕግ የበላይነትን የሚመለከቱ ጥያቄዎችን ሁልጊዜ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ግብረ ኃይል ፕሬስ ሴክሪታሪያት በኩል እንዲያረጋግጡ ጥሪ እናቀርባለን ፡፡
በአዲስ አበባ ሸራተን ሆቴል አካባቢ የእሳት አደጋ ተከስቷል።

አደጋዉ ከደቂቃዎች በፊት ሸራተን ሆቴል ጫፍ ላይ ከዘውዲቱ ሆስፒታል አጠገብ ባለ አንድ ካፌ ላይ የተነሳ ሲሆን አደጋው በመዛመት ላይ ይገኛል።

የአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ሰራተኞች ወደ ቦታው አቅንተዋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ህዳር 7 ቀን 2013 ዓ.ም
የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን ከኮቪድ 19 ስጋት ጋር ተያይዞ ራሳቸዉን አገለሉ።

ቦሪስ ጆንሰን ራሳቸዉን ያገለሉት Lee ሊ አንደርሰን ከተባሉ የሀገሪቱ የፓርላማ አባል ጋር ለ30 ደቂቃ ያህል ዉይይት ካደረጉ በኋላ አንደርሰን ፖዚቲቭ ሆነዉ በመገኘታቸዉ ነዉ ተብሏል፡፡

ይሁንና ቦሪስ ጆንሰን እስካሁን ምንም አይነት የቫይረሱን ምልክት አለማሳየታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትሩ ከዚህ ቀደም በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተዉ ጽኑ ህሙማን ክፍል ሳይቀር ገብተዉ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ሮይተርስ

በተያያዘ ዜና በእንግሊዝ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ሙከራ በስፋት መስጠት ተጀምሯል፡፡

ጃንሰን በተባለዉ የቤልጀም ኩባንያ የተሰራዉ ይህ ክትባት፣ የጉንፋን አምጭ ተህዋሲያንን የዘረ-መል ማሻሻያ በማድረግ የኮቪድ 19 ተህዋሲን እንዲዋጋ ተደርጎ የተዘጋጀ ነዉ፡፡

በእንግሊዝ ለኮቪድ 19 ክትባት ከተሞከሩት ዉስጥም ይህ 3ኛዉ ነዉ፡፡

እንግሊዝ አሁን ወደ ሙከራ ያስገባችዉ ክትባት በ 6 ሽህ ሰዎች ላይ ነዉ የሚመከረዉ፡፡ዉጤቱን ለማወቅም በትንሹ ከ6 እስከ 9 ወራትን ሊወስድ ይችላል መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ሩሲያ ሰራሹ የኮቪድ 19 ክትባት እስከ 90 በመቶ ድረስ አስተማማኝ ነዉ ማለቷን ተከትሎ ሀገራት ቀድሞ ለመገኘት በእጃቸዉ ያሉትን የምርምር ዉጤቶች ሙከራ ላይ እያዋሏቸዉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በሙሉቀን አሰፋ
ሕዳር 7 ቀን 2013 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ባለፉት ሁለት ቀናት በደረሱ የእሳት አደጋዎች ከ200 ሺህ ብር በላይ ንብረት መውደሙ ተገለጸ፡፡

የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቅው ባሳለፍነው ቅዳሜ እና እሁድ አራት የእሳት አደጋዎች መከሰታቸውን አስታውቋል፡፡

የመጀመርያው የእሳት አደጋ የተከሰተው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ በአንድ መኖርያ ቤት ላይ የደረሰ የእሳት አደጋ ነው፡፡

በዚህ አደጋ 100 ሺህ ብር የሚጠጋ ንብረት አደጋ የደረሰበት ሲሆን ከሁለት ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን ንብረት ደግሞ ማዳን እንደተቻለ ነው የተገለጸው፡፡

ሁለተኛ አደጋ የደረሰው ደግሞ በኮልፌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሰባት በመኖርያ ቤት የደረሰ የእሳት አደጋ ነው፡፡

በዚህኛውም አደጋ ምክንያት ከአምስት ሺህ ብር በላይ በሚሆን ንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ከሶስት ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን ንብረት ደግሞ ማዳኑን ነው ኮሚሽኑ ያስታወቀው፡፡

ሌላኛው የእሳት አደጋ የደረሰው በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ወረዳ አራት በአንድ መኖርያ ቤት ላይ የደረሰ አደጋ ነው፡፡

ከዚህኛው አደጋ ጋር በተያያዘም 50 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ንብረት ከውድመት ማዳኑን ነው የገለጸው፡፡

አራተኛ አደጋ የደረሰው ደግሞ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሶስት የኮንስትራክሽን እቃዎች በተከማቹበት መጋዘን ውስጥ የተከሰተ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ነው፡፡

ከአደጋው 80 ሺህ ብር የሚሆን ንብረት የወደመ ሲሆን ከ800 ሺህ ብር በላይ የሚጠጋ ንብረት ደግሞ ማዳን እንደተቻለ ነው የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ሀላፊ አቶ ጉልላት ጌታነህ የነገሩን፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሕዳር 7 ቀን 2013 ዓ.ም
በኢትዮጵያ የተጀመረው ሕግ የማስከበር ስራ የአገሪቷን አንድነት በጠበቀ መንገድ እንዲካሄድ ሩሲያ አሳሰበች።

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መግለጫን ዋቢ አድርጎ ስፑትኑክ በድረገጹ ይዞት በወጣው ዘገባ የሩሲያ የረጅም ጊዜ ወዳጅ የሆነችው ጦርነቱ ኢትዮጵያ ግዛቷን እና አንድነቷን በማያናጋ መንገድ እንዲቋጭ ፍላጎት እንዳላት ገልጻለች።

ሚኒስቴሩ አክሎ እንዳለው ኢትዮጵያ የበርካታ ብሄሮች እና ሀይማኖቶች አገር እንደመሆኗ የፌደራል መንግስት እና የትግራይ ክልል የአገሪቱን አንድነት እና ዘላቂ ሰላም በጠበቀ መንገድ እንዲመክሩ በመግለጫው ጠቁሟል።

በኢትዮጵያ ከሳምንት በፊት የሰሜን ዕዝ ላይ በህዋሃት የደረሰበትን ጥቃት ተከትሎ የኢትየጵያ መንግስትም አጸፋውን በሃይል እርምጃ እየወሰደ ይገኛል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ጊዚያዊ የሽግግር መንግስት ማቋቋሙም ይታወሳል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ ባሳለፍነው አርብ የትግራይ ልዩ ሃይል ህገመንግስቱን በማስከበር ላይ ላለው የአገር መከላከያ ሰራዊት እጅ እንዲሰጡ የሰጡት የሶስት ቀናት ጥሪ ዛሬ ያበቃል።

የአገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ክልል ልዩ ሃይል እና ሚሊሻ በትናንትናው ዕለት የአላማጣ ከተማን እና ካባቢውን ሙሉ ለሙሉ ከትገራይ ልዩ ሃይል መቆጣጠራቸው ይታወሳል።

በጅብሪል ሙሃመድ
ሕዳር 7 ቀን 2013 ዓ.ም