Ethio Fm 107.8
20.5K subscribers
7.8K photos
16 videos
4 files
2.31K links
በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው!!!
Download Telegram
ፓዮኒር  ዳያግኖስቲክ ሴንተር  ከዚህ ወር ጀምሮ ለሚያደርገው የጡት ካንሰር የምርመራ ዘመቻ የ50 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን አስታወቀ

ፓዮነር ዲያጎነስቲክ ሴንተር  በተቋሙ ለ7ተኛ ጊዜ በሚያደርገው የጡር ካንሰር የምርመራ ዘመቻን ለምርመራ ለሚመጡ ማህበረሰብ የ50 በመቶ  ቅናሽ እንዳደረገ ገልጿል።

ተቋሙ ዛሬ በዋና መስሪያ ቤቱ  በሰጠው  መግለጫም በየአመቱ የጥቅምት ወር  የጡት ካንሰር የምርመራ ዘመቻ እንደሚያደርጉ ያስታወቀ ሲሆን  የአሁኑንም  በጥቅምት ወር ላይ  ዘመቻው እንደሚካሄድ ነግረውናል።

የማሞግራፊ (የጡት ራጅ) ላይ የ50በመቶ ቅናሽ አላማውም እድሜያቸው ከ40 በላይ የሆኑ ሴቶች የጡት ካንሰር ቅድመ ልየታ ምርመራ በማድረግ በሽታው ስር ሳይሰድ በጊዜ ለማግኘትና የብዙዎችን ህይወት ለመታደግ እንደሆነም ተገልጿል።

በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የማሞግራፊ ስክሪኒግ በመጠቀም የካንሰር ደረጃው ያለብትን ጊዜ በጊዜ ማወቅ እንደሚቻልም ተገልጿል።

በኢትዮጵያ እንደ ሀገር የተመዘገበ  የጡት ካንሰር ታካሚ ቁጥር  ባይኖርም   ወደ 70 በመቶ የሚጠጋ በኢትዮጵያ የሚገኙ የጡት ካንሰር ታካሚዎች   ከፍተኛውን የካንሰሩን  ደረጃን  እንደሚይዙ ተመላክቷል።

ለአለም አሰፋ

መስከረም 23 ቀን 2017 ዓ.ም
ሩሲያ ለመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት ተጠያቂ አሜሪካ ናት ስትል ወቅሳለች።

እየተባባሰ ለመጣዉ የመካከለኛ ምስራቅ የግጭት ሁኔታ ዋሽንግተን ሀላፊነቱን መዉሰድ አለባት ሲሉ የሩሲያ ዉጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ገልፀዋል።

በትናንትናው እለት በሰጡት መግለጫ በአረብ ዲኘሎማሲያዊ ጉዳዩች እና በመካከለኛው ምስራቅ ባለዉ ዉጥረት ላይ ያተኮረ ነበር።

ቃል አቀባይዋ በመካከለኛዉ ምስራቅ ስላለዉ መጠነ ሰፊ የጥቃት ዘመቻ ትኩረት ባደረገዉ መግለጫቸዉ ሀገራቸዉ ሰላም ለማስፈን በአፅንኦት እንደምትመለከተው አስታወቀዋል።

በዚህ መግለጫቸዉ ላይ በፍልስጤም እና በእስራኤል ግጭት ላይ ያሉ ተሳታፊዎች ጦርነቱን እንዲያቆሙ ጠይቀዉበታል።

ማሪያ ዛካሮቫ በመግለጫቸዉ አግባብነት ያላቸውን የተባበሩት መንግስታት እና የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔዎችን መከተል እንደሚያስፈልግ ማመላከቱን ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል።

ቁምነገር አየለ

መስከረም 23 ቀን 2017 ዓ.ም
የፕርሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ ተጫዋቾች ኢና አሰልጣኞች እጩዎች ታውቋል።

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ 2024/25 የውድድር ዘመን የወርሀ መስከረም የወሩ ምርጥ ተጨዋች ስምንት እጩዎች ይፋ ተደርገዋል።


ሀርቬይ ባርንስ

ጋብሬል ማግሀሌስ

ሪያን ግራቨንበርች

ኮል ፓልመር

ኦሊ ዋትኪንስ

ሉዊስ ዲያዝ

ራውል ሂምኔዝ

ማክኔል

በእጩነት መቅረብ ችለዋል።


በአሰልጣኝ ዘርፍ ደሞ አምስት እጩዎች ይፋ ተደርገዋል።

በዚህም መሰረት :-

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ

አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ

አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ

አሰልጣኝ ማርኮ ሲልቫ

አሰልጣኝ አርኔ ስሎት

በእጩነት መቅረብ ችለዋል።

በጋዲሳ መገርሳ

መስከረም 23 ቀን 2017 ዓ.ም
የነገ የመስከረም 24 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 2025 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጥቅምት 2 እና 5 ከጊኒ ጋር ለሚያደርጋቸው ሦስተኛ እና አራተኛ የምድብ ጨዋታዎች አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ለ23 ተጫዋች ጥሪ አድርገዋል።

ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ከነገ መስከረም 24 ጠዋት ጀምሮ በጁፒተር ሆቴል ሪፖርት አድርገው በመሰባሰብ በአዲስ አበባ ከተማ ዝግጅት እንደሚጀምሩም ተገልጿል።

በጋዲሳ መገርሳ

መስከረም 23 ቀን 2017 ዓ.ም


ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcasWebsite https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
በሰሜናዊ ናይጄሪያ ካኖ አውራጃ፣ ካኑ ከተማ፣ የሸሪዓ ፖሊስ አቋማሪ የስፖርት ውርርድ ቤቶች ላይ ዘመቻ አካሄደ።

የሸሪዓ ፖሊስ ምክትል ኃላፊ ሙጃሂድ አሚኑዲን “በእስልምና ቁማር ክልክል ነው፤ ስለዚህ ቤቶቹ ዘግተናቸዋል” ብለዋል።

ይህ የሸሪዓ ፖሊስ ዘመቻ የተካሄደው ከሕብረተሰቡ እና ከነዋሪዎች ከፍተኛ ቅሬታ ለፖሊስ መቅረቡን ተከትሎ ነው።

በዚህ የመጀመሪያው ዙር ዘመቻ 30 የሚሆኑ የውርርድ ሱቆች ተዘግተዋል።

የሱቆቹ ባለቤቶች እና አቋማሪዎች ግን እስር አልገጠማቸውም። ሁለተኛ እንዳይለመዳቸው ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ወደ ቤት ተሸኝተዋል።

“ሒስባህ” የሚል ስም ያለው የሰሜናዊ ናይጄሪያ የሸሪዓ ፖሊስ ከዚህ በኋላ እንዲህ ዓይነት ድርጊት እንደማይታገስ ዝቷል።

የካና አውራጃ ዋና ከተማ ካኖ ትባላለች አብዛኛው ሕዝብ ሙስሊም ነው። በከተማዋ በዋናነት ሸሪዓ ሕግ ተግባራዊ ቢደረግም ዓለማዊ ሕግም ጎን ለጎን አብሮ ይሠራበታል።

በካኖ የቁማር ቤቶች እና ጭፈራ ቤቶች ክርስቲያኖች በሚበዙባቸው ሰፈሮች አገልግሎት መስጠት ይችላሉ።

ሆኖም ግን ሙስሊሞች ወደዚያ መሄድን ያዘወትራሉ ተብሎ ሲገመት በክርስቲያን ሰፈሮች የሚገኙ ቤቶች ላይም እርምጃ ሊወሰድባቸው ይችላል።

አሁን የውርርድ ቤቶች ዘመቻው ያተኮረው ግን ሙስሊሞች በሚኖሩበት ካኖ አካባቢ ብቻ ነው።

በናይጄሪያ የስፖርት ውርርድ ቤቶች በየአካባቢው በስፋት የሚገኙ ሲሆን፣ ግድግዳ ላይ ቴሌቪዥን በመስቀል ለተመልካች የፈረስ ግልቢያ እና የእግር ኳስ ውድድር እያሳዩ ደንበኞቻቸውን ያቋምራሉ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መስከረም 23 ቀን 2017 ዓ.ም
የአሜሪካው የስለላ ድርጅት (ሲአይኤ) ከቻይና፣ ከኢራን እና ከሰሜን ኮሪያ መረጃ አቀባዮችን ለመመልመል አዲስ እንቅስቃሴ መጀመሩ ታወቀ።

ድርጅቱ ማኅበራዊ ሚዲያዎቹን ተጠቅሞ ረቡዕ ዕለት በማንዳሪን (የቻይና)፣ በፋርስ (ኢራን) እና በኮሪያ ቋንቋዎች ባሠራጨው መልዕክት ፍላጎት ያላቸው ሰዎች ደኅንነቱ በተጠበቀ መልኩ ሊያገኙት እንደሚችሉ ገልጿል።

የዩክሬንን ወረራ ተከትሎ ሩሲያውያንን ለመመዝገብ ተመሳሳይ ቅጥር የተካሄደ ሲሆን፣ ሲአይኤ የምልመላ ሂደቱ የተሳካ እንደነበርም ገልጿል።

የሲአይኤ ቃል አቀባይ በሰጡት መግለጫ “በአምባገነን መንግሥታት ውስጥ የሚኖሩ ግለሰቦች ለሥራ ክፍት መሆናችንን እንዲያውቁ እንፈልጋለን” ብለዋል።

እንደ ኤክስ፣ ፌስቡክ፣ ዩቲዩብ፣ ኢንስታግራም፣ ቴሌግራም እና ሊንክዲንን በመሳሰሉ የማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር መድረኮች ላይ በወጡት የምልመላ መልዕክቶች ፍላጎት ያላቸው ሰዎች ስማቸውን፣ አድራሻቸውን እና ስልካቸውን አንዲያሰፍሩ ተጠይቀዋል።

ለመረጃ አቀባይነት ፍላጎት ያላቸው ሰዎች አስተማማኝ የሆኑትን ኢንክሪፕትድድ ቨርቹዋል ፕራይቬት ኔትወርኮች (ቪፒኤን) ወይም ድብቅ ሆኑ ድረ ገጾችን (ዳርክ ዌብ) በመጠቀም በይፋዊው የሲአይኤ ድረ-ገጽ በኩል ግንኙነት እንዲፈጥሩ መክሯል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መስከረም 23 ቀን 2017 ዓ.ም
የዛሬ የመስከረም 24 ቀን 2017 ዓ.ም የከሰዓት እና የምሽት ፕሮግራሞቻችን
የኢሬቻ በዓል ነማክበር ለሚጓዙ እንግዶች ከ1 ሺህ 457 በላይ ተሽከርካሪዎች ተዘጋጅተዋል ተባለ

የኢሬቻ በዓልን ለማክበር ወደ አዲስ አበባ እና ቢሾፍቱ ለሚጓጓዙ እንግዶች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ከ1 ሺህ 457 በላይ ተሽከርካሪዎች መዘጋጀታቸው ተገለጸ፡፡

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎትና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ጋር በመቀናጀት በዓሉን ለማክበር ወደ አዲስ አበባ እና ቢሾፍቱ ለሚጓዙ ተሳታፊዎች የትራንስፖርት እጥረት እንዳያጋጥም በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ÷ በአዲስ አበባ በአምስቱም መግቢያ በሮች ወደ በዓሉ ማክበሪያ ቦታ የሚያደርሱ ከአዲስ አበባ ሲቲ ባስ 907 የከተማ አውቶቡሶች፣ 400 የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አውቶቡሶች ተዘጋጅተዋል ብሏል፡፡

በቢሾፍቱ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓልም 150 ሀገር አቋራጭና መለስተኛ አውቶቡሶች መዘጋጀታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመልክቷል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መስከረም 24 ቀን 2017 ዓ.ም
የሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት የፊታችን ሰኞ ይካሄዳል

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡

በኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት አንቀፅ 58 ንዑስ አንቀፅ (2) እና በምክር ቤቱ የአሠራርና የአባላት የሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 24 ንዑስ አንቀፅ (1) መሰረት÷ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአንድ ዓመት የሥራ ጊዜ ከመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ መሆኑ ተደንግጓል፡፡

በድንጋጌው መሰረት የ6ኛው ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የተጠናቀቀ ሲሆን÷ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓትም የሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት በተገኙበት መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሠዓት ጀምሮ ይካሄዳል ተብሏል፡፡

በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት ለሁለቱ የፌደራል መንግሥት ምክር ቤቶች ዓመታዊ ሥራቸውን መጀመራቸውን በማብሰር የፌደራል መንግሥቱን ዓመታዊ ዕቅድ ያቀርባሉ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መስከረም 24 ቀን 2017 ዓ.ም
የነገ የመስከረም 25 ቀን 2017ዓ.ም የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  ፕሮግራሞቻችን