#ትርታዬ
256 subscribers
401 photos
8 videos
49 files
7 links
Best channel concerning love affairs,educational, funny & health tips...☞♂⇜♥️⇝♀
Download Telegram
አዲስ ነገር የለም
""""""""""""""""""""""
ከሰማዩ በታች የለም አዲስ ነገር፣
ጊዜ የገዛትን ታሪካዊት ምድር ጠይቋት ትናገር፣

ካንዱጋር ዳንኪራ ከሌላጋር ሀዘን፣
አንዱ ሲረጋጋ አንደኛው መባዘን፣
መጪ ስንቀበል ሌላው ተሰናባች፣
ተወለደ ሲባል እዛጋ ደሞ ሟች፣

የለም አዲስ ነገር ሆኖ እንጂ ለየቅል፣
ጊዜ ንጉስ ሆኖ አውርዶ ሲሰቅል፣
እኛም ሆነንለት ተጎናባሽ አሽከር፣
እንከተላለን ....
በመሬት ዙሪያላይ ይዞን ሲሽከረከር፤

በዚች በቆምኩባት ባለሁበት ምድር፣
የወለደ ሲሞት ያሳደገ ሲድር፣
ጥንዶች ሲጫዎቱ የፍቅር ጫዎታ፣
ያረገዘች ስትወልድ ያገባ ሲፈታ፣
አማኝ የገዳም ሰው ወይም በግልባጭ፣
ጠንባዛ ሰካራም አንቡላ አንጫላጭ፣
መፍትሄ ጠፍቶበት ኑሮ ያቀወሰው፣
አይቻለሁ ባይኔ ....
ጨርቁን ጥሎ ሲያብድ ጤነኛ ያልኩት ሰው፤

አዲስ ነገር የለም

ስጠይቅ እራሴን ....
ለምን እንደሆነ አንዱ አለፈ ሲባል ሌላው የሚተካ፣
ሲገባኝ እውነቱ ....
ክብ አለም መዞር ነው ሂዎት ማለት ለካ።
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫
ሰው ፈልጌ ሰው አጣሁኝ ፣
ደከምኩ እኔስ ሰለቸሁኝ ፣
ሰው ናፈቀኝ ሰው አማረኝ ፣
የማይከዳ የማያማኝ ፣
ተንኮል ክፋት የማይመኝ ፣
ሰው አክባሪ የማይረሳኝ ፣
ጊዜ ሲጥል የሚያነሳኝ ፣
በልቡ ውስጥ የሚያኖረኝ ፣
ሰው ፈልጌ ሰው አጣሁኝ ፣
ደከምኩ እኔስ ሰለቸሁኝ ።
...
ሰው ነው ብዪ የቀረብኩት ፣
በልቤ ውስጥ ያከበርኩት ፣
ሰላም ፍቅር ሰመኝለት ፣
ታምኝለት እያመንኩት ፣
ለካ አይደለም ተንኮለኛ ባዶ ፍቅር ፣
ሰላም አልባ ባዶ ህይወት ባዶ ነገር ፣
ባዶ ኑሮ ባዶ ሰላም ከንቱ ነገር ፣
ለህሊናው የማይሳሳ በክህደት የሰክረ ፣
ለሰው ክፉ የመከረ ፣
ሰው ፈልጌ ሰው አጣሁኝ ፣
ደከምኩ እኔስ ሰለቸሁኝ ።
...
ሰው ቀርቤ ሰው አምኝ ፣
ሰው ቢጥለኝ ሰው ቢከዳኝ ፣
የማይተወኝ የማይከዳኝ ፣
የማይሸሽኝ የሚያቀርበኝ ፣
አጣህ ብሎ የማይጥለኝ ፣
እያመንኩት የታመነኝ ፣
እየወደኩ የሚያነሳኝ ፣
እየደከምኩ የሚይጽናናኝ ፣
አለ ከአርያም...
እየነገርኩት የሚሰማኝ ።
የማይሰለች የማይድክም ፣
አለ ከላይ ከአርያም ፣
የፍጥረታት ሁሉ ሰላም ፣
አለ...
🏜🏜🏜🏜🏜🏜🏜🏜🏜🏜🏜🏜🏜🏜🏜
*የካፊያ ምች**

ሳልላክ ተልካ እንሂድ አለቺኝ
ካላጣችዉ ሰዓት ከቤት አስወጣቺኝ
ጥርቅም ዕቅፍ አርጋ በካፊያ ሳመቺኝ
የዕድሜ ልክ ልክፍቴን ያኔ አስለከፈቺኝ።

መብረቅ እየጮኸ ዝናብ እያካፋ
የኔ ልብ በሷ የሷ በኔ ጠፋ
የሰማዩ ባህር ቁልቁል ተንዶብን
ዉሃ ጠማኝ ዉሃ እየዘነበብን።

ጠፍቼ ስመለስ ከእቅፏ ስወጣ
በርዶኝ አተኮሰኝ እቤቴ ስመጣ
እያደር አደረ ከርሞ ከረመብኝ
የዘመን ሕመሜን ያን ዕለት ታመምኩኝ።

አሁን አሁን ታዲያ!
ደመናዉ ሲጠቁር ነጐድጓድ ሲያጓራ
ነፋስ ሲያስገመግም ክረምቱን ሊጣራ
ግንቦት ማለቂያ ላይ ይነሳል ህመሜ
ሲያቀብጠኝ በዝናብ በካፊያ ተስሜ፥
ምች ተሳልሜ።
🥱 ዝምተኛ ልቦች 🥱
      〰️〰️〰️〰️
(ጌትነት እንየው)

አምነው የወደዱ
ወደው የተካዱ
ተክደው የራዱ
ፍርሃት አንሸራቶ ቁልቁል የጣላቸው
የብቸኛ ልቦች የትነው መውደቂያቸው?
የትነው መድረካቸው?
ማነው አጃቢያቸው?
እንዴት ነው ምታቸው
የተካዱ ልቦች አጋር የራቃቸው
የሚያቀነቅኑት ምንድን ነው ዜማቸው?
የተመረኮዙት እምነት ታጥፎባቸው
ድንገት የወደቁ ፍቅር ያዳጣቸው
ሚስጥር የሚያጋሩት ሰው የበደላቸው
ብቸኝነት ሰርጎ ብቻ ያስቀራቸው
ዝምተኛ ልቦች ምን ይሆን ቋንቋቸው?
ከየት ነው ጥሪያቸው?
በየት ነው ጉዟቸው?
የት ነው መድረሻቸው?
እንደ ሰብአሰገል ጠቅሶ የሚመራቸው
የቃተቱ ልቦች የታል ኮከባቸው?
መቼም ከአምላክ ትንፋሽ ከውሃ ከአፈሩ
ከእምንት እና እውነት ከፍቅር ሲሰሩ
ዝምተኛ ልቦች ጥንቱን ሲፈጥሩ
ተገፍትረው ወድቀው
ደቀው እንዳይቀሩ
በተስፋ ጸንተው ነው ዘላለም ሊኖሩ::
🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊
እንኳን ለ አዲሱ ዓመት አደረሳችሁ !!
ዘመኑን 2016
💥የሠላም
💥💥የጤና
💥💥💥የፍቅር
💥💥💥💥የደስታ ያድርግልን💥
🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊
🌻🌻 መልካም 🌻🌻️
🌻🌻 አዲስ 🌻🌻
🌻🌻 ዓመት 🌻🌻️
🌻️🌹🌾🌻💐🌷🌻
🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊
( ሞትኩልሽ )
=============

ያቺ  ....
ያኔ እንዲያ ላመልካት
ያዳዳኝ መውደዴ
'ሞትኩልሽ' ያልኳት ልጅ
በህይወት አለች እንዴ ???

አወይ ጊዜ ዳኛ
አወይ ወረት ክፉ
ባልተሰጣቸው መስክ
ቀን ከሌት ሲለፉ
ስንቶች ረገፉ  !!!

😂😂😂😂😂😂😂😂😂
መቼ ነው?
አልቀናም ስላቸው
ከዋክብቱ ረግፈው ምድር ላይ ፈሰሱ፤
ወደ ላይ ሳንጋጥጥ
ፅጌረዳ አበቦች ሰማይ አለበሱ፤
(አንቺን ሊያስታውሱ...)
.
አላደምጥም ብዬ ጆሮዬን ብደፍነው፤
ተስለው መጡብኝ
ድምፅሽና ሳቅሽ ግዙፍ አካል ሆነው፤
.
እንዳላይሽ ፈራሁ!...
አይኖቼን ጨፈንኩኝ፤
ዳስሼ አገኘሁሽ ለየሁሽ ጉድ ሆንኩኝ፤
.
ከዚህ ሁሉ ጣጣ
ከትውስታሽ ሽሽት ካንቺ ልገላገል፤
በራሴ ጨክኜ ራሴንም ብገል፤
መግነዜን አሽትቼ
ጠረንሽን አገኘሁ ድጋሚ ተነሳሁ፤
መቼ ነው እንዴት ነው አንቺን የምረሳው?፤
...........
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
(ከልዑል ሀይሌ)
👁👁የወርቅ አይን👁👁

ፈገግታዬ ቢያምር ስስቅ ቢታይ ብሎ

ጥሪቱን አሟጦ ብድር ተቀብሎ

አንዲት የወርቅ ጥርስ ቢያስተክልም እሱ

ማን ሲስቅ ይያለት በዝቶበት ማልቀሱ።


የሚያየው ባያገኝ ሚያስተውለው ቢያጣ
             ዘወትር እያነባ

በጣም በማረር በሰው ልጆች ሴራ
             በሰው ልጆች ደባ

ማልቀሱ እንዲታወቅ እንባው እንዳይናቅ
                ሀሳቡን ለውጦ

ሊያስተክል አስቧል ሁለት የወርቅ አይኖች
                ወርቅ ጥርሱን ሽጦ።

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @https://t.me/ethiofikir2
#ከስምሽ_ምን_አለኝ_?

ካንቺ የነበረኝ ውል ቃሌን አፍርሼ
         ቆረጥኩኝ ለአንዴ
ለምንድነው ግና ስምሽን ስሰማው
የምደናበረው በሁሉም መንገዴ?

ቆረጠልኝ ያልኩት ፍቅሬን ሚያስታውሱ
ከደጃፌ ቆመው
ስምሽን ሚጠሩት ማናቸው እነሱ?
ለቃል ማሰሪያቸው አምኔታና ውሉ
ከመቼ ወዲህ ነው
          በስምሽ ሚምሉ?

እንጃ ብቻ
ስምሽን ሲያነሱ ደርሶ ይከፋኛል
ለምን?....
              ናፍቀሽኛል!

ደህና ነሽ ግን?

🏴‍☠️🏴‍☠️🏴‍☠️🏴‍☠️🏴‍☠️🏴‍☠️🏴‍☠️🏴‍☠️🏴‍☠️🏴‍☠️🏴‍☠️
https://t.me/ethiofikir2/
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Day 1...
Have a blessed day !!!!
ምን ያክል አጠፋሽ ?

አንቺ ያላውቅሽው  ምን ያክል አጠፋሽ
በንፁህ ልብ ላይ  እዳፊሽን ደፋሽ
ከሳቂታ ፊት ላይ  ፈገግታን አጠፋሽ


አንቺ ልብ ያላልሽው  ስንት አበባ ደረቀ
ስንት አበባ ረገፈ
ከቁብ ያልቆጠርሽ  የስንቱ ሞራል ተገፈፈ
ህልሙ ጨነገፈ

ምን ያክል አጠፋሽ ?


አንቺ ያላውቅሽው ምን ያክል አሳመምሽ 
ምን ያክልስ ገደልሽ
ማመን የሚችልን  ማፍቀር የሚችልን
ስንት ልብ አጎደልሽ
.........................ስንት ልብ አበደንሽ

ምን ያክል አጠፋሽ ?

በድን ያደረግሽው  ነፍሱን የነጠቅሽው
በመጠን ካወቅሽው
ምን ያክል አጠፋሽ  በየትኛው ልኬት
በምንስ ሰፈርሽው

ምን ያክል አጠፋሽ ?


ያንችን ሳቅ  ያንችን ጨዋታ ያንችን እብደት
ስንት ልብ አለመ ? 
           ስ
              ን
                 ት ልብ ከሰመ ?
ከእሷ ውጭ እያለ   የመውደድ የማፍቀር
ተስፋው አከተመ


ምን ያክል አጠፋሽ ?

¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤¤
👍2
Channel photo updated
ዝምታ ሲደመጥ

አቤት! ጩኸቱ ዝምታ
ጆሮ ጠልዞ ናላ ሲመታ
ከወዲያ ወዲህ ሲያላጋ
በሞገዱ ቋጥኝ ሲያናጋ
ነጎድጓድ ነው ነው ዝምታ
የገዛ ራስ ጉርምርምታ
የደምን ፋፋቴ ጉዘት
የልብን ህይወታዊ ዑደት
እንደጢስ አባይ ፏፏቴ ቅኝት
ሰማይ ሰቅሎ ዶሎ አዘቅት
ያኖጋዋል ሲያዳምጡት
በሁካታ ዉስጥን ሞልቶ
በፀጥታ ነፍስ ዘርቶ
ከአፅናፍ አፅናፍ አስተጋብቶ
እንኳንማ ጆሮ ቀርቶ
ይደመጣል ባይን ገብቶ
ነጎድጓድ ነው ዝምታ
የገዛ ራስ ጉርምርምታ
እንዳፍላ ጎርፍ ይነደፋል
ሳይቀዝፍ ያጓጉዛል
ታገር አገር ያዘልላል
ማሚቶ አለዉ ይመልሳል
ነጎድጓዱ ዝምታ
የገዛ ራስ ጉርምርምታ።
👍3
Mothers love....😘😘😘
አይ ገላ አባ ወረት

በምናብ ሸራ ላይ ፥ በሐሳቤ ሰሌዳ
በምኞቴ ጓዳ ፥ በፍትወቴ ሜዳ
ውብ ሰውነትሽን፥ አየሁ ተቀይዳ
በስጋ እሳት ላንቃ ፥ በቁም እስር ርዳ።

የአይኖችሽን ጨረር ፥ የከንፈርሽን ማር
የአንገትሽን መርዘም ፥ የእግሮችሽን ማማር
የዳሌሽን ደጀን ፥የሽንጥሽን ጅረት
በስጋዬ አሰስኩት ፥በገላ ዳበስኩት
አወይ ገላ ግፉ፥ አይ ስጋ አባ ወረት

የጉንጭሽ ላይ ስንቡክ ፥ የአንገትሽ ስር ከርቤ
ቀመስኩት ሁሉንም ፥ መች ቀረሁ ተርቤ
የቤትኾቨን ኖታ ፥ የሞዛርት ሙዚቃ
መች ይስተካከላል ፥ ከአንደበትሽ ሲቃ
አወይ ገላ ግፉ ፥ አይ ስጋ አባ ወረት
ይገኝ ይመስለዋል ፥ ለነብስ ህመም ደዌ
አንድ የስጋ መድኅን ፥ አንድ የስጋ ሽረት።

አይጥመኝ ሐር ልብ ፥ ለስላሳ የተባለ
ከሐር ጠጉርሽ በቀር ፥  ከአለንጋ ጣቶችሽ
አላውቅም በአለም ፥ ላይ የተስተካከለ።

ይፈሳል እንደ አዋሽ ፥ ሳቅሽ እንደ መልካው
እጅ እግር አጠረኝ ፥ ነብስሽን በየት ልንካው
ሁሉን ስዳስሰው ፥ ጠጉርሽን ስለብሰው
እንደ ጠበል ጠዲቅ ፥ ከንፈርሽን ስቀምሰው
ጣፋጭ እሳትሽን፥  እንደ ኩዳድ ሳርሰው
ገላን በገላ አቅም ፥ ስትጠግቢኝ ስጠግብሽ
ንገሪኝ አንችዬ ፣
ለዚህ ጥያቄዬ ፥ ምን መለሰ ልብሽ?

አወይ ገላ ግፉ፥ አይ ገላ አባ ወረት
ምኞት ሙሉ ሜዳ ፥ ምኞት ሙሉ በረት

በአፍ እንደወደድሽኝ ፥በአይን እንደዳበሽኝ
መአት ረግረግሽ ውስጥ ፥ያኔ እንዳሰጠምሽኝ
መዘንጋት የማያውቅ ፥ ፍቅሬ እሱን ለግሽኝ
ገል አፈሩ ይቅርብኝ ፥
ገል አፈሩ ይብቃኝ፣
ነብስሽና ነብሴ ሁለቱ ይጣመሩ፥
ፍቅር እንደዚያ እንዲቃኝ።

By ©እስራኤል
   
👍1👏1
🔥🔥እሳትና ውሀ🌊🌊

የታፈነ ውሀ በብረት ድስት ገብቶ

በጭቆና ሲኖር ነፃነቱን አጥቶ

     ስንት ስቃይ አይቶ
      ታጋሽ ሆኖ ሳለ

አንድ ጉልበተኛ እሳት የተባለ

ብረት ድስቱን ሊያግል እየተቀጣጠለ

ነበልባል ተላብሶ ድንገት ከተፍ አለ::
:
:
ቃጠሎ ንዳዱ ውሀው ሲበዛበት

የስቃዩ ማብቂያ ጊዜው ሲረዝምበት

ትግስቱ ተሟጦ የሚገነፍል ለት

        የእሳቱ ግለት
     ምን ያክል ቢከፋ

የታፈነው ውሀ በምሬት ሲደፋ

ሀያሉም ነበልባል አብሮት ነው ሚጠፋ::


▪️ ነገሮችን በትግዕስት ማለፍ ተገቢ ነው ግን ሁሉም ነገር ገደብ አለው። ይሄ ግጥም ገደብ እንዳለው ላልተረዱ ይድረስልኝ።

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

      
የትኛው ነሽ አንቺ

ፀደይ ነሽ መስከረም ?
ግማሽ መልክሽ አደይ ግማሽ መልክሽ አረም።
ግማሽ የሚቀጠፍ ግማሽ የሚነቀል ፣
የትኛውን ልመን ምንሽን ልቀበል፤
የተኛው ነሽ አንቺ ምህረት ወይስ በቀል?
ስምዖንን መስለሺኝ መስቀሌን ስትይዢ
ለአንድ ሠሞን ፍዳ፣
በየት ዞረሽ ሸጥሽኝ ለብቻ መከራ
ደግሞ እንደ ይሁዳ።


✍️©እስራኤል
  
👍4😁4👏3
አትንኩብኝ
////////////
ደግሞስ አትንኩብኝ
ማጣት ወንድሜን
ያሳየኝ የለም ወይ
ጥሩ ወዳጄን
ጥርሶች የለሰኑት
ድብቁ ማንነት
ምን እንደሚታሰብ
ማያሳይ ሰውነት
በዙሪያ የነበር
ጓድ ወዳጅ ዘመዴን
ማጣት መውደቅ መጥቶ
አጠራው መንገዴን
እሳት የቀመሰ
ደረቅ ጭድ ይመስል
በኔ ክፉ ጊዜ
ሲገለጥ ማስመሰል
ንግግር ሞላሁት
ልዝብ አንደበቴን
ጭራሽ አትንኩብኝ
እያልኩኝ ማጣቴን
ሁሉን ቢገልጥልኝ
አስመሳይ ወዳጄን
አትንኩብኝ አልኩኝ
ወደድኩት ውድቀቴን
ድንገት ቢያሳየኝ
የወዳጅ ጠላቴን
==========