Ethio Fast News-ኢትዮ ፈጣን መረጃ
3.24K subscribers
219 photos
25 videos
12 links
ከእየአቅጣጫው ሁሉም ዜናዎች በአንድ ቦታ የሚያገኙበት አዲስ ቻናል ነው
Download Telegram
የመንግስት ሠራተኞች የቀን ውሎ አበል ክፍያ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1111/2018
የቀን ሰራተኛዋ የዋንጫ ባለቤት!

የደብረታቦር ተወላጇ ማስተዋል ካሳው፣ በቤተሰብ የአቅም ማነስ ምክንያት በርካታ ውጣ ውረዶችን አሳልፋለች። የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ባለመምጣቱ ተስፋ ሳትቆርጥ፣ በግልገል በለስ በሚገኘው በለስ ፓራዳይዝ ኮሌጅ በፋርማሲ ዲፕሎማ ትምህርቷን ጀመረች።
ማስተዋል የትምህርትና የመኖርያ ወጪዋን ለመሸፈን ከትምህርቷ ጎን ለጎን በፅናት የቀን ስራ እየሰራች ራሷን ታስተዳድር ነበር። ዛሬ ሐምሌ 4 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው ምረቃ ላይ 4.00 ሙሉ ውጤት በማምጣት የሁለት ሜዳሊያና የዋንጫ ተሸላሚ ሆናለች።
ቤተሰቦቿ በአቅም ማነስ ምክንያት በምረቃዋ ላይ መገኘት ባይችሉም፣ ደግ የሆኑ አከራዮቿና ጎረቤቶቿ ደስታዋን ተጋርተዋል። ኮሌጁም ለዚህች ብርቱ ጀግና እዚያው መድረክ ላይ የቋሚ ቅጥር ደብዳቤ በስጦታ አበርክቶላታል።
12🥰3
''እነ ትራምፕን ይዞ ለመጣ ወረታውን እከፍላለሁ'' ኢራን

​የኢራን አብዮታዊ ዘብ በዶናልድ ትራምፕ፣ በቤንያሚን ኔታንያሁ እና በሌሎች የምዕራባውያን መሪዎች ላይ ጠንካራ “የአደን” አዋጅ ማወጁን አስታወቀ።
​ከአብዮታዊ ዘቡ ጋር ግንኙነት ያለው “ሀምሻህሪ” ጋዜጣ፤ ትራምፕን፣ ማክሮንን፣ ስታርመርን እና ሌሎችንም መሪዎች የእስረኛ ልብስ አልብሶ የሚያሳይ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰራ ምስል “በቀል አይቀሬ ነው” በሚል ርዕስ ይፋ አድርጓል።
​የኢራን የበላይ መሪ አያቶላ አሊ ኻሜኔይ ያስተላለፉትን የቅጣት ጥሪ ተከትሎ የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው፤ በኢላማ ውስጥ የተካተቱት መሪዎችና ከፍተኛ ወታደራዊ ሹማምንት እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ በሰላም እንደማይኖሩና የበቀል እርምጃው በእርግጠኝነት እንደሚፈጸም ተገልጿል።
7👍4