Ethio Fast News-ኢትዮ ፈጣን መረጃ
3.24K subscribers
219 photos
25 videos
12 links
ከእየአቅጣጫው ሁሉም ዜናዎች በአንድ ቦታ የሚያገኙበት አዲስ ቻናል ነው
Download Telegram
ሳህለወርቅ ዘውዴ አዲስ ዓለም አቀፍ የተመድ ኃላፊነት ተሰጣቸው

ሹመት፦ የተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ የቀድሞዋን የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴን በምእራብ አፍሪካና ሳህል ቢሮ (UNOWAS) የዋና ስትራቴጂያዊ ገምጋሚ (Lead Strategic Reviewer) አድርገው መድበዋቸዋል።

ተልዕኮ እና ጉዞ፦ በቢሮው ገለልተኛ ስትራቴጂያዊ ግምገማ የሚያካሂዱ ሲሆን፤ መጀመሪያ ኒውዮርክ ከፀጥታው ምክር ቤት አባላት ጋር ከተወያዩ በኋላ ወደ ሴኔጋል ዳካር ያመራሉ።

የምርጫው ምክንያት፦ ቀደም ሲል በሴኔጋል፣ ማሊ እና ጊኒ አምባሳደር በነበሩበት ወቅት ያካበቱት ሰፊ ቀጠናዊ ልምድ እና ጥልቅ እውቀት ነው።

የመጀመሪያ ጊዜ፦ የተሰጣቸውን አዲስ ዓለም አቀፍ ኃላፊነት በዚህኛው ወር (ጁን) ማብቂያ ላይ በይፋ መረከብ ይጀምራሉ።
@ethiofastnew
9
የመንግስት ሠራተኞች የጡረታ መመሪያ!
******
1. ማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ በተቀጠረው በ60 ቀናት ውስጥ ለጡረታ በማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ መመዝገብ አለበት፡፡

2. የጡረታ አበል ለቀጣይ ተቀማጭ የሚሆነው ገንዘብ ከሠራተኛ 7% ሲሆን ከመንግስት ደግሞ 11% በድምሩ 18% ሆኖ ለፖሊስና ለመከላከያ ግን ከሠራተኛ 7% እና ከመንግስት 25% በድምሩ 32% ነው፡፡

3. ጡረታ የሚያስወጡ ምክንያቶች:-
1=በእድሜ ምክንያት 60 ዓመት ሲሞላው
2=በራሱ ፈቃድ
3=በጤና ጉድለት
4=በስራ ለይ በደረሰ አካል ጉዳት
5=በሞት ናቸው፡፡

4. የጡረታ አበል በውክልና የሚከፈለው:-
1= በእርጅና
2=በህመም
3= ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ
4= በትምህርት ወዳ ሌላ ቦታ በመሄድ
5=በእስራት ምክንያት ናቸው፡፡

5ኛ. የጡሮታ አበል በይርጋ የሚዘጋው:-
1=የጡረታ አበል ጥያቄ ሳይቀርብ ወይም የተወሰነለትን ጡረታ ሳይወስድ ከ5 ዓመት በላይ ከቆየ አይከፈለውም፡፡ በቀጣይ ከአመለከተበት ቀን ጀምሮ ይከፈለዋል፡፡
2=የዳራጎት ጡረታ ሳይጠየቅ ቀርቶ ወይም የተጠየቀውን 5 ዓመት ድረስ ሳይወስድ ከቆየ በይርጋ ይዘጋል (አይከፈልም)::

6. በእድሜ 60 ዓመት ሲሞላው ለሠራተኛው የሚሰጥ የጡረታ አበል ስሌት:-
* ከተቀጠረበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ዓመት ድረስ ያለው አገልግሎት በ30% ሲባዛ ከ10 ዓመት በላይ ያለው እያንደንዱ አገልግሎት ግን 1.25 ይባዛል፡:ለምሳሌ 28 አመት አገልግሎት ያለው ስሌት 10ዓመት×30% + 18ዓመት ×1.25= 30+22.5= 52.5% ነው፡፡ በዚህም መሠረት ለጡረታ የሚያዘው ደመወዝ የመጨረሻው የ36ወራት (3ዓመት) ብቻ ስለሆነ በ3ዓመቱ ሲከፈል የነበረው ደመወዝ 5,000 ቢሆን ጡረታው 52.5% ×5,000ብር = 2,625 ብር ጡረታ ያገኛል ማለት ነው፡፡

7. በጀማሪ ቅጥር ወቅት ቀንና ወር ሳይሞላ ዓ,ም ብቻ በህይወት ታሪክ ተሞልቶ ከተገኘ የጡረታ ቀንና ወር የሚያዘው በኢ/ያ አቆጣጠር ከሆነ ነሐሴ 30 ተብሎ ሲያዝ እ.ኤ.አ ከሆነ ታህሳስ 31 ቀን ተብሎ ይታሰባል፡፡

8. በረሱ ፍላጎት ጡረታ የመውጣት መብት እድሜው 55 ዓመት ሲሆንና 25 ዓመት አገልግሎት ሲኖረው ሆኖ ለፖሊስና ለመከላከያ ሠራዊት ግን ከሚወጡበት ዓመት 5ዓመት ቀድሞ መውጣት ይችላሉ ፡፡

9. የሟች ጡረታ የሚወርሱ ልጆች ከ18ዓመት በታች ወይም አካል ጉዳተኛ ልጅ ከሆነ 21ዓመት በታችና የሟች እናትና አባት ናቸው፡፡

10. ለጡረታ አበል ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ ማስረጀዎች:-
1=በህይወት ታሪክ የተሞላው መረጃ (ጡ1እና 2)
2=የሙከራና የቋሚ ቅጥር ደብደቤ
3= የጡረታ መለያ ቁጥር
4= የ36 ወራት የደመወዝ መረጃ
5= የዝውውር፣ የደረጃ ዕድገትና የደመወዝ ለውጥ የተደረገበት ደብደቤ
6= የጋብቻ እና የልጆች ማስረጃ
7= የባለጡረታ ወይም የወራሽ ፎቶ ግራፍ ናቸው፡፡
6
በደቡብ አፍሪካ ራሱን ለመከላከል ከባድ መሳሪያ የታጠቀው ኢትዮጵያዊ መነጋገሪያ ሆነ
​በደቡብ አፍሪካ የተቀሰቀሰውን የመጤ ጠል (Xenophobic) ጥቃት ለመከላከል፣ አንድ ኢትዮጵያዊ ነው የተባለ ግለሰብ ከባድ የጦር መሳሪያና ውሾችን ይዞ መታየቱ በማህበራዊ ሚዲያ ከፍተኛ ክርክር አስነስቷል።
​በርካታ ደቡብ አፍሪካውያን ድርጊቱን "የሽብርተኝነት ተግባር" በማለት ግለሰቡ በአስቸኳይ እንዲታሰርና ከሀገር እንዲባረር እየጠየቁ ይገኛሉ። በአንጻሩ የሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ዜጎች ግለሰቡ ንብረቱንና ህይወቱን የመከላከል ሙሉ መብት እንዳለው በመጥቀስ ድርጊቱን ደግፈውታል።
​በአሁኑ ወቅት በደቡብ አፍሪካ በተቀሰቀሰው ሰሞነኛ ሁከት የሁለት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የበርካታ ስደተኞች ህይወት ማለፉና ንብረት መውደሙ ይታወቃል።
👍65😁1
በ20 ዓመታት ልዩነት የ2.0 ዶክተሮች እናት 🔥

ይህ መታደልም መባረክም ነው። እናት በ20 ዓመታት ልዩነት እነዚያ ትናንሽ ልጆቿ ከተመሳሳይ ተቋም ዶክተር ሆነው ወጡላት። የቀድሞው የቦንጋ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጴጥሮስ ወልደጊዮርጊስ ቤተሰብ።
👍4
ማኑዋል መኪና መንዳት የአንጎልን የመሥራት ብቃት እንደሚያሳድግ አዲስ ጥናት አመለከተ
 
የማኑዋል መኪና አነዳድ ከተለመደው የመንዳት ልምድ ባለፈ ለአእምሮ ጤና ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው በጃፓን የተደረገ አዲስ ጥናት ጠቆመ። ጥናቱ እንደሚያመለክተው ማኑዋል መኪናዎችን ማዘወር ለአውቶማቲክ መኪናዎች ከሚሰጠው ትኩረት ይልቅ ለአንጎል የማስታወስ፣ ትኩረትን የመሰብሰብ እና ውሳኔ የመስጠት ብቃትን በከፍተኛ ሁኔታ ያነቃቃል።
 
ይህ ግኝት ይፋ የሆነው በጃፓኑ “ቤስት ካር ዌብ” (Best Car Web) የጋዜጠኝነት መድረክ ሲሆን፣ ጥናቱን ያካሄዱት ደግሞ በቶሆኩ ዩኒቨርሲቲ የልማት፣ እርጅና እና ካንሰር ምርምር ተቋም ፕሮፌሰር የሆኑት ርዩታ ካዋሺማ ናቸው። ፕሮፌሰሩ ቀደም ሲል በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈውን የኒንቴንዶ “ብሬይን ኤጅ” የአእምሮ ማሳያ ጨዋታዎች በስተጀርባ ያለውን የሳይንስ መሠረት ያዘጋጁ ታዋቂ የነርቭ ሳይንቲስት ናቸው። በሳቸው ምርምር መሠረት ማኑዋል መኪና በሚነዳበት ወቅት የሚፈለጉት ተከታታይ ተግባራት ከፍተኛ የእውቀት ተግባራትን የሚያከናውነውን የአንጎል የፊት ክፍል ያነቃቁታል።
 
የማኑዋል መኪና አሽከርካሪዎች ክላች መርገጥን፣ ማርሽ መቀየርን፣ የነዳጅ መቆጣጠሪያን (throttle) ማስተካከልን እና በተመሳሳይ ሰዓት የትራፊክ ፍሰቱን መከታተልን በአንድ ላይ ማቀናጀት ይጠበቅባቸዋል። ተመራማሪዎቹ እንዳረጋገጡት ይህ በአንድ ጊዜ በርካታ ሥራዎችን የመሥራት ሂደት አእምሮ ያለማቋረጥ ንቁ ሆኖ መረጃዎችን እንዲያሰላስል የሚያስገድደው በመሆኑ፣ ለአንጎል የፊት ክፍል ታላቅ የዕለት ተዕለት የስፖርት እንቅስቃሴ ሆኖ ያገለግላል።
 
6
የመንግስት ሠራተኞች የቀን ውሎ አበል ክፍያ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1111/2018
የቀን ሰራተኛዋ የዋንጫ ባለቤት!

የደብረታቦር ተወላጇ ማስተዋል ካሳው፣ በቤተሰብ የአቅም ማነስ ምክንያት በርካታ ውጣ ውረዶችን አሳልፋለች። የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ባለመምጣቱ ተስፋ ሳትቆርጥ፣ በግልገል በለስ በሚገኘው በለስ ፓራዳይዝ ኮሌጅ በፋርማሲ ዲፕሎማ ትምህርቷን ጀመረች።
ማስተዋል የትምህርትና የመኖርያ ወጪዋን ለመሸፈን ከትምህርቷ ጎን ለጎን በፅናት የቀን ስራ እየሰራች ራሷን ታስተዳድር ነበር። ዛሬ ሐምሌ 4 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው ምረቃ ላይ 4.00 ሙሉ ውጤት በማምጣት የሁለት ሜዳሊያና የዋንጫ ተሸላሚ ሆናለች።
ቤተሰቦቿ በአቅም ማነስ ምክንያት በምረቃዋ ላይ መገኘት ባይችሉም፣ ደግ የሆኑ አከራዮቿና ጎረቤቶቿ ደስታዋን ተጋርተዋል። ኮሌጁም ለዚህች ብርቱ ጀግና እዚያው መድረክ ላይ የቋሚ ቅጥር ደብዳቤ በስጦታ አበርክቶላታል።
12🥰3
''እነ ትራምፕን ይዞ ለመጣ ወረታውን እከፍላለሁ'' ኢራን

​የኢራን አብዮታዊ ዘብ በዶናልድ ትራምፕ፣ በቤንያሚን ኔታንያሁ እና በሌሎች የምዕራባውያን መሪዎች ላይ ጠንካራ “የአደን” አዋጅ ማወጁን አስታወቀ።
​ከአብዮታዊ ዘቡ ጋር ግንኙነት ያለው “ሀምሻህሪ” ጋዜጣ፤ ትራምፕን፣ ማክሮንን፣ ስታርመርን እና ሌሎችንም መሪዎች የእስረኛ ልብስ አልብሶ የሚያሳይ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰራ ምስል “በቀል አይቀሬ ነው” በሚል ርዕስ ይፋ አድርጓል።
​የኢራን የበላይ መሪ አያቶላ አሊ ኻሜኔይ ያስተላለፉትን የቅጣት ጥሪ ተከትሎ የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው፤ በኢላማ ውስጥ የተካተቱት መሪዎችና ከፍተኛ ወታደራዊ ሹማምንት እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ በሰላም እንደማይኖሩና የበቀል እርምጃው በእርግጠኝነት እንደሚፈጸም ተገልጿል።
7👍4