Ethio Fast News-ኢትዮ ፈጣን መረጃ
3.24K subscribers
219 photos
25 videos
12 links
ከእየአቅጣጫው ሁሉም ዜናዎች በአንድ ቦታ የሚያገኙበት አዲስ ቻናል ነው
Download Telegram
ዛሬ በግ ተራ ሄድኩኝ የሆነ አርሶ አደር ሲያለቃቅስ ሰምቼ ጠየቁት እና እንዲህ አለኝ ።

ይሄውልህ ወደ ገብያ ስንገባ በአንድ በግ ግብር 25ብ፣ በበሬ 50 ብር፣ በጋሬ 50ብር፣ በአህያ 50ብር ወዘተ እንከፍላለን።

ከዛ ተመልከት ጋሼ አለና የአርሶ አደሩን የወጭ ዝር ዝር ደረሰኝ ከኪሱ አውጥቶ አሳየኝ። እኔም ከደረሰኙ ላይ ከታች እንደሚከተለው አወጣኋቸው።

በአፈር ማዳበሪያ ወጭ ከጥንድ በሬዎች አንዱን ነጥለን እየሸጥን ነው ምክንያቱም አንድ ኩንታል ዳብ ማዳበሪያ 11,000ብር ነው ዩሪያ ደግሞ 10,000ብር ነው አለ።

እነዚህን ወጭዎችን ግን እዩትና የትኞቹ ወጭዎች ለአርሶ አደሩ ዞረው ይደርሳሉ ስለሚለው እናውራ::

1. አማራ ልማት ማህበር = 200ብር
2. የጤና ልማት ፀረ ወባ ማህበር =200ብር
3. ለወቅታዊ ሰላም እና ደህንነት = 1000 ብር
4. የቀይ መስቀል ማህበር = 100 ብር
5. አማራ ሴቶች ማህበር = 20ብር
6. ጤና መድህን= 1600ብር
7. የስፖርት = 100 ብር
8. የመሬት ግብር = 55ብረ
9. ሰበካ ጉባዬ = 440 ብር

ድምር= 3715 ብር
6🤔4
ሰበር ዜና 🛑

#የመን በእስራኤል አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ #የቦምብ_ጥቃት መፈፀሟን ተከትሎ በአካባቢው ውጥረት ነግሷል።
ይህ ልማት ለአለም አቀፍ ደህንነት እና መረጋጋት ከፍተኛ ስጋት ይፈጥራል ተብሏል።
2😁2
ጉድ አምቦ

በአምቦ ከተማ በግልሰቦች የሚፈጸም ግፍና የነዋሪዎች ስጋት

በአምቦ ከተማ "ካሳዬ ቀነኒሳ" የተባለ ግለሰብ "120" ተብሎ በሚጠራ የማፊያ ቡድን በመታገዝ በዜጎች ላይ እጅግ አሰቃቂ ድብደባና ግፍ እየፈጸመ እንደሚገኝ የሚጠቁሙ መረጃዎችና ተንቀሳቃሽ ምስሎች ወጥተዋል። ግለሰቡ ሰዎች እንደ እንስሳ ሲደበድብ የሚያሳዩ ምስሎችን ራሱ እየቀረጸ የሚያሰራጭ ሲሆን፣ ድርጊቱንም ያለ ምንም ከልካይ በአደባባይና በዝግ ቤቶች ውስጥ እንደሚፈጽም ተመልክቷል።
የከተማው ነዋሪዎች በከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ ሆነው የሚከተሉትን ጥያቄዎች እያነሱ ይገኛሉ፦
* የአምቦ ከተማ አስተዳደርና ፖሊስ ይህ ሁሉ ግፍ ሲፈጸም የት ነበሩ?
* "120" የተባለው የማፊያ ቡድን እንዴት በከተማዋ መዋቅር ውስጥ ሊንቀሳቀስ ቻለ?
* ግለሰቡ በህግ ጥላ ስር ውሎ ለምን ተገቢው ምርመራ አይደረግበትም?
ይህ ድርጊት በአስቸኳይ በፌደራል ደረጃ ትኩረት አግኝቶ ህጋዊ እርምጃ ካልተወሰደ፣ በከተማዋ ሰላምና በነዋሪዎች ደህንነት ላይ ከፍተኛ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል ነዋሪዎች በስጋት እየገለጹ ይገኛሉ።
11
ታጋቾችን ለማስለቀቅ የተዘጋጀ 1.5 ሚሊዮን ብር በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች መወሰዱ ተገለጸ

በኦሮሚያ ክልል ከጎሃፅዮን ወደ ፍቼ ሲጓዙ በነበሩ የህዝብ አውቶብስ ተሳፋሪዎች ላይ የተፈጸመውን እገታ ተከትሎ፣ የታጋች ቤተሰቦች ታጋቾቹን ለማስለቀቅ ይዘውት የነበረው 1.5 ሚሊዮን ብር በመንግስት የጸጥታ አካላት እንደተቀማባቸው ታውቋል።

ባሎቻቸውና ዘመዶቻቸው የታገቱባቸው ሴቶች ወርቃቸውን በመሸጥና በመበደር ያሰባሰቡትን ገንዘብ ለአጋቾች ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ፣ በሰሜን ሸገር ዞን ደገም ወረዳ የሚገኙ የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ አካላት ገንዘቡን ቀምተው አስረዋቸዋል ተብሏል።

የጸጥታ አካላቱ እገታውን ማስቆምም ሆነ ታጋቾቹን ማስለቀቅ ባልቻሉበት ሁኔታ፣ በጭንቅ ላይ ያሉ የቤተሰብ አባላትን ማሰርና ገንዘብ መንጠቅ ፍጹም ስህተት መሆኑን የገለጹት ቅሬታ አቅራቢዎች፤ የታሰሩት ቤተሰቦችና ገንዘባቸው በአስቸኳይ ተለቀው የታጋቾችን ሕይወት እንዲታደጉ ጥሪ አቅርበዋል።
8
በራያ ቆቦ አካባቢ ውጊያ መቀስቀሱ ተሰምቷል።

👉ዛሬ ረቡዕ ​በራያ ቆቦ አካባቢ በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች እና የፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ መሆኑን የኢትዮ ፋስት መረጃ ምንጮች የገለፁ ሲሆን፣ በጉዳዩ ላይ የሌሎች ወገኖች ጣልቃ ገብነት ሊኖር እንደሚችል ተገምቷል።የህውሃት ታጣቂዎች ከሰሞኑ በእግር ወደ ወሎ ቀጣ እንድጓዙ ታዘው የነበረው ለዚህ ሳይሆን እንዳልቀረ ተነግሯል።

👉ግጭቱን ተከትሎ በአላማጣ፣ ጨርጨር እና ቢሶበርን ጨምሮ ሙሉ የራያ አካባቢዎች ከፍተኛ የድሮን እንቅስቃሴ በመታየቱ ህዝቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ተጠይቋል።

👉በሌላ በኩል በመጋለ አቅጣጫ የህውሃት ታጣቂዎች ስብስብ (እንቅስቃሴ) በስፋት መታየቱን ተከትሎ የአፋር ክልል የፀጥታ ኃይሎች በተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኝ ታውቋል።በአቅራቢያ የሃራ መሬት ኃይሎች መኖራቸው ተነግሯል።
3
ለወራት በሆርሙዝ ሰርጥ ተይዛ ቆይታ የነበረችው "MV ጊቤ" መርከባችን ወደ ጅቡቲ እየተመለሰች ነው::
ሳህለወርቅ ዘውዴ አዲስ ዓለም አቀፍ የተመድ ኃላፊነት ተሰጣቸው

ሹመት፦ የተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ የቀድሞዋን የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴን በምእራብ አፍሪካና ሳህል ቢሮ (UNOWAS) የዋና ስትራቴጂያዊ ገምጋሚ (Lead Strategic Reviewer) አድርገው መድበዋቸዋል።

ተልዕኮ እና ጉዞ፦ በቢሮው ገለልተኛ ስትራቴጂያዊ ግምገማ የሚያካሂዱ ሲሆን፤ መጀመሪያ ኒውዮርክ ከፀጥታው ምክር ቤት አባላት ጋር ከተወያዩ በኋላ ወደ ሴኔጋል ዳካር ያመራሉ።

የምርጫው ምክንያት፦ ቀደም ሲል በሴኔጋል፣ ማሊ እና ጊኒ አምባሳደር በነበሩበት ወቅት ያካበቱት ሰፊ ቀጠናዊ ልምድ እና ጥልቅ እውቀት ነው።

የመጀመሪያ ጊዜ፦ የተሰጣቸውን አዲስ ዓለም አቀፍ ኃላፊነት በዚህኛው ወር (ጁን) ማብቂያ ላይ በይፋ መረከብ ይጀምራሉ።
@ethiofastnew
9
የመንግስት ሠራተኞች የጡረታ መመሪያ!
******
1. ማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ በተቀጠረው በ60 ቀናት ውስጥ ለጡረታ በማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ መመዝገብ አለበት፡፡

2. የጡረታ አበል ለቀጣይ ተቀማጭ የሚሆነው ገንዘብ ከሠራተኛ 7% ሲሆን ከመንግስት ደግሞ 11% በድምሩ 18% ሆኖ ለፖሊስና ለመከላከያ ግን ከሠራተኛ 7% እና ከመንግስት 25% በድምሩ 32% ነው፡፡

3. ጡረታ የሚያስወጡ ምክንያቶች:-
1=በእድሜ ምክንያት 60 ዓመት ሲሞላው
2=በራሱ ፈቃድ
3=በጤና ጉድለት
4=በስራ ለይ በደረሰ አካል ጉዳት
5=በሞት ናቸው፡፡

4. የጡረታ አበል በውክልና የሚከፈለው:-
1= በእርጅና
2=በህመም
3= ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ
4= በትምህርት ወዳ ሌላ ቦታ በመሄድ
5=በእስራት ምክንያት ናቸው፡፡

5ኛ. የጡሮታ አበል በይርጋ የሚዘጋው:-
1=የጡረታ አበል ጥያቄ ሳይቀርብ ወይም የተወሰነለትን ጡረታ ሳይወስድ ከ5 ዓመት በላይ ከቆየ አይከፈለውም፡፡ በቀጣይ ከአመለከተበት ቀን ጀምሮ ይከፈለዋል፡፡
2=የዳራጎት ጡረታ ሳይጠየቅ ቀርቶ ወይም የተጠየቀውን 5 ዓመት ድረስ ሳይወስድ ከቆየ በይርጋ ይዘጋል (አይከፈልም)::

6. በእድሜ 60 ዓመት ሲሞላው ለሠራተኛው የሚሰጥ የጡረታ አበል ስሌት:-
* ከተቀጠረበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ዓመት ድረስ ያለው አገልግሎት በ30% ሲባዛ ከ10 ዓመት በላይ ያለው እያንደንዱ አገልግሎት ግን 1.25 ይባዛል፡:ለምሳሌ 28 አመት አገልግሎት ያለው ስሌት 10ዓመት×30% + 18ዓመት ×1.25= 30+22.5= 52.5% ነው፡፡ በዚህም መሠረት ለጡረታ የሚያዘው ደመወዝ የመጨረሻው የ36ወራት (3ዓመት) ብቻ ስለሆነ በ3ዓመቱ ሲከፈል የነበረው ደመወዝ 5,000 ቢሆን ጡረታው 52.5% ×5,000ብር = 2,625 ብር ጡረታ ያገኛል ማለት ነው፡፡

7. በጀማሪ ቅጥር ወቅት ቀንና ወር ሳይሞላ ዓ,ም ብቻ በህይወት ታሪክ ተሞልቶ ከተገኘ የጡረታ ቀንና ወር የሚያዘው በኢ/ያ አቆጣጠር ከሆነ ነሐሴ 30 ተብሎ ሲያዝ እ.ኤ.አ ከሆነ ታህሳስ 31 ቀን ተብሎ ይታሰባል፡፡

8. በረሱ ፍላጎት ጡረታ የመውጣት መብት እድሜው 55 ዓመት ሲሆንና 25 ዓመት አገልግሎት ሲኖረው ሆኖ ለፖሊስና ለመከላከያ ሠራዊት ግን ከሚወጡበት ዓመት 5ዓመት ቀድሞ መውጣት ይችላሉ ፡፡

9. የሟች ጡረታ የሚወርሱ ልጆች ከ18ዓመት በታች ወይም አካል ጉዳተኛ ልጅ ከሆነ 21ዓመት በታችና የሟች እናትና አባት ናቸው፡፡

10. ለጡረታ አበል ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ ማስረጀዎች:-
1=በህይወት ታሪክ የተሞላው መረጃ (ጡ1እና 2)
2=የሙከራና የቋሚ ቅጥር ደብደቤ
3= የጡረታ መለያ ቁጥር
4= የ36 ወራት የደመወዝ መረጃ
5= የዝውውር፣ የደረጃ ዕድገትና የደመወዝ ለውጥ የተደረገበት ደብደቤ
6= የጋብቻ እና የልጆች ማስረጃ
7= የባለጡረታ ወይም የወራሽ ፎቶ ግራፍ ናቸው፡፡
6
በደቡብ አፍሪካ ራሱን ለመከላከል ከባድ መሳሪያ የታጠቀው ኢትዮጵያዊ መነጋገሪያ ሆነ
​በደቡብ አፍሪካ የተቀሰቀሰውን የመጤ ጠል (Xenophobic) ጥቃት ለመከላከል፣ አንድ ኢትዮጵያዊ ነው የተባለ ግለሰብ ከባድ የጦር መሳሪያና ውሾችን ይዞ መታየቱ በማህበራዊ ሚዲያ ከፍተኛ ክርክር አስነስቷል።
​በርካታ ደቡብ አፍሪካውያን ድርጊቱን "የሽብርተኝነት ተግባር" በማለት ግለሰቡ በአስቸኳይ እንዲታሰርና ከሀገር እንዲባረር እየጠየቁ ይገኛሉ። በአንጻሩ የሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ዜጎች ግለሰቡ ንብረቱንና ህይወቱን የመከላከል ሙሉ መብት እንዳለው በመጥቀስ ድርጊቱን ደግፈውታል።
​በአሁኑ ወቅት በደቡብ አፍሪካ በተቀሰቀሰው ሰሞነኛ ሁከት የሁለት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የበርካታ ስደተኞች ህይወት ማለፉና ንብረት መውደሙ ይታወቃል።
👍65😁1
በ20 ዓመታት ልዩነት የ2.0 ዶክተሮች እናት 🔥

ይህ መታደልም መባረክም ነው። እናት በ20 ዓመታት ልዩነት እነዚያ ትናንሽ ልጆቿ ከተመሳሳይ ተቋም ዶክተር ሆነው ወጡላት። የቀድሞው የቦንጋ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጴጥሮስ ወልደጊዮርጊስ ቤተሰብ።
👍4
ማኑዋል መኪና መንዳት የአንጎልን የመሥራት ብቃት እንደሚያሳድግ አዲስ ጥናት አመለከተ
 
የማኑዋል መኪና አነዳድ ከተለመደው የመንዳት ልምድ ባለፈ ለአእምሮ ጤና ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው በጃፓን የተደረገ አዲስ ጥናት ጠቆመ። ጥናቱ እንደሚያመለክተው ማኑዋል መኪናዎችን ማዘወር ለአውቶማቲክ መኪናዎች ከሚሰጠው ትኩረት ይልቅ ለአንጎል የማስታወስ፣ ትኩረትን የመሰብሰብ እና ውሳኔ የመስጠት ብቃትን በከፍተኛ ሁኔታ ያነቃቃል።
 
ይህ ግኝት ይፋ የሆነው በጃፓኑ “ቤስት ካር ዌብ” (Best Car Web) የጋዜጠኝነት መድረክ ሲሆን፣ ጥናቱን ያካሄዱት ደግሞ በቶሆኩ ዩኒቨርሲቲ የልማት፣ እርጅና እና ካንሰር ምርምር ተቋም ፕሮፌሰር የሆኑት ርዩታ ካዋሺማ ናቸው። ፕሮፌሰሩ ቀደም ሲል በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈውን የኒንቴንዶ “ብሬይን ኤጅ” የአእምሮ ማሳያ ጨዋታዎች በስተጀርባ ያለውን የሳይንስ መሠረት ያዘጋጁ ታዋቂ የነርቭ ሳይንቲስት ናቸው። በሳቸው ምርምር መሠረት ማኑዋል መኪና በሚነዳበት ወቅት የሚፈለጉት ተከታታይ ተግባራት ከፍተኛ የእውቀት ተግባራትን የሚያከናውነውን የአንጎል የፊት ክፍል ያነቃቁታል።
 
የማኑዋል መኪና አሽከርካሪዎች ክላች መርገጥን፣ ማርሽ መቀየርን፣ የነዳጅ መቆጣጠሪያን (throttle) ማስተካከልን እና በተመሳሳይ ሰዓት የትራፊክ ፍሰቱን መከታተልን በአንድ ላይ ማቀናጀት ይጠበቅባቸዋል። ተመራማሪዎቹ እንዳረጋገጡት ይህ በአንድ ጊዜ በርካታ ሥራዎችን የመሥራት ሂደት አእምሮ ያለማቋረጥ ንቁ ሆኖ መረጃዎችን እንዲያሰላስል የሚያስገድደው በመሆኑ፣ ለአንጎል የፊት ክፍል ታላቅ የዕለት ተዕለት የስፖርት እንቅስቃሴ ሆኖ ያገለግላል።
 
6
የመንግስት ሠራተኞች የቀን ውሎ አበል ክፍያ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1111/2018