Ethio Fast News-ኢትዮ ፈጣን መረጃ
3.24K subscribers
219 photos
25 videos
12 links
ከእየአቅጣጫው ሁሉም ዜናዎች በአንድ ቦታ የሚያገኙበት አዲስ ቻናል ነው
Download Telegram
ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አመራሮች ተደባደቡ

ይህ ፊልም/ትያትር አይምሰልህ❗️ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የብልጽግና አመራር ያለበትን አሁናዊ ቁመና ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ የመድረክ ላይ ድብድብ ነው። ሕዝቤ ወዴት አቅጣጫ እያመራ ነው🤔 የአመራር ትርጉም ያል'ገባው ሁሉ ነው እንዴ የተሰባሰበው? ለነገሩ አይፈረድባችሁም ፖለቲካ የትምህርት ደረጃ፣ የተሻለ ልምድና ዲሲፕሊን ስለማይ'ፈልግና የማ'ይም ማጠራቀሚያ ከረጢት (dust bin) ስለሆነ ብስለት ጎድሏ'ችሁ መድረክ ላይ መደባደብ ይዛችኃል። ይህን ነው ሕዝቡ ከእናንተ የሚወስደው...
10👎3
"... ዘላቂ ሰላምን እና ልማትን ለማረጋገጥ በሚደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል ሕዝቡ ፅንፈኞችንና ተላላኪወችን የሚሸከምበት ትክሻ እንደሌለው በተደረጉት ትልልቅ ሕዝባዊ የውይይት መድረኮች ያሳየበትን አቋሙንና የጀመረውን ትግል አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ እናቀርባለን፡፡

አሁንም ድረስ የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ወደጎን በመተዉ የክልላችንን ሰላም ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ ሃይሎችን የማንታገስና የመንግሥት ተቀዳሚ ተግባር የሆነዉን ሕግ የማስከበር ተግባር አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑንም ለማሳወቅ እንወዳለን።
በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም በሀሰተኛ መረጃዎች ሳይደናገሩ በሀገራችንና በክልሉ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍንና የማይቀረውን የልማትና የብልጽግና ጉዞ ለማረጋገጥ በምናደርገው ርብርብ የበኩላቸውን አወንታዊ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ
12
ሰበር

ቆላድባ ከተማ አዲስ የተሰራ አስፓልት ላይ መድሃኔዓለም ታይቷል የሚል ቪዲዮ መሠራጨቱን ተከትሎ መንገዱ ተዘጋ!

ጌታ ቆላድባ ከተማን እንደ እየሩሳሌም አብዝቶ እንደወደዳት አንድ የአካባቢው ተወላጅ መምህር የተናገሩ ሲሆን ተአምሩንም በተለያዩ ቁሳቁሶች ላይ በመገለጥ አብዝቶ እያሳየ ነው ብለዋል።

ቆላድባ ከተማ ከሳምንት በፊት ዛፍ ላይ ኪዳነምህረት ተገልጣለች በሚል የውይይት አጀንዳ ሆና እንደነበረ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደሞ አስፓልት ላይ መድሃኔዓለም ተገልጧል ተብሏል።
😁446🙏2
በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ አንድ ልዩና ብዙዎችን እያነጋገረ ያለ አደጋ ተከስቷል። አንድ የሲኖ ትራክ አሽከርካሪ በስራ ላይ የነበረን የትራፊክ ፖሊስ ሞተር ሳይክል በመግጨቱ በአካባቢው በነበሩ ተመልካቾችና በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል። እንደ እድል ሆኖ በትራፊክ ፖሊሱ ላይ የደረሰ ምንም አይነት አካላዊ ጉዳት ባይኖርም፣ የሞተር ሳይክሉ መገጨትና አደጋው የተከሰተበት ሁኔታ ግን አሽከርካሪውን ወደ ከባድ የህግ ፈተና ሊከተው እንደሚችል እየተነገረ ነው።
​ይህ አደጋ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መጋራት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የሰዎች ምላሽ ለሁለት የተከፈለ ሆኖ ታይቷል። ብዙዎች "የሲኖ ሹፌሩ አሁን ምን አይነት አስቸጋሪ ጊዜ፣ የገንዘብ ጫናና የህግ ጦስ ይጠብቀው ይሆን?" በማለት ለሹፌሩ ያላቸውን ስጋትና አዘኔታ እየገለጹ ይገኛሉ። በአንጻሩ ደግሞ በትራፊክ ፖሊሶች ላይ ባላቸው የግል ቅሬታ ወይም ቀደም ሲል በደረሰባቸው በደል ምክንያት "እሰይ፣ ይገባዋል" የሚሉ አስተያየቶችን የሚሰጡ ሰዎችም አልታጡም።
​ምንም እንኳን በመንገድ ላይ የሚከሰቱ አደጋዎች በንብረትም ሆነ በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ማድረሳቸው የሚቆጭ ቢሆንም፣ የዚህ አደጋ ሁኔታ ግን በህዝብና በትራፊክ ፖሊሶች መካከል ያለውን ግንኙነትና በህብረተሰቡ ውስጥ ያለውን ስሜት ፍንትው አድርጎ አሳይቷል። አደጋው በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ሳያደርስ በንብረት ላይ ብቻ ማለቁ የሚደሰትበት ቢሆንም፣ የሹፌሩ ቀጣይ እጣ ፈንታና የሚጠብቀው የህግ ተጠያቂነት ግን አሁንም የብዙዎች መወያያ ሆኖ ቀጥሏል።
​እናንተስ በዚህ አጋጣሚ ላይ ምን ትላላችሁ? አሽከርካሪው ካጋጠመው የህግ ተጠያቂነት አንጻር እንደ ማህበረሰብ ሊኖረን የሚገባው አመለካከት ምን መሆን አለበት?
14😁1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሙሉጌታ አምበርብር ውርደት 🤣🤣🤣
😁16🥱9👎43🔥1
«ከኢትዮጵያ ጋር ምንም የሚያገናኘን ነገር የለም። የህዝቡ ማህበረዊ ሰረት ተበጥሷል። የሚያገናኘን ነገር የፕሪቶሪ የሰላም ስምምነት ብቻ ነው። ስምምነቱ የማይተገበር ከሆነና ግዛታችን በሰላም የማይመለስ ከሆነ ትዕግስታችን እያለቀ ነው። ለዚህም በሃይል ለማስመለስ ተዘጋጅተናል»
አቶ ገብረ ገብረ ፃዲቅ
የሕውሓት ቃል አቀባይ በዎይን ሚዲያ የተናገረው
👎72
ማይምሪ ከተማ

በሰሜን ጎንደር ዞን ምስራቅ ጠለምት ወረዳ ለአራት ተከታታይ ቀናት የቀጠለ ወታደራዊ ግጭት መኖሩንና ሁኔታውን ለመቃወም በሚጠምሪ ከተማ ዛሬ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል።

እንደ መረጃው ገለጻ፣ የትግራይ ኃይሎች በምስራቅ ጠለምት ወረዳ በኩል የከፈቱት ጥቃት ዛሬ አርብ ጥር 22 ቀን 2018 ዓ.ም አራተኛ ቀኑን ይዟል።ግጭቱ በተለይም "ደጃች ሜዳ" የተባለችውን ከተማ ለመቆጣጠር ያለመ እንደሆነ ተጠቁሟል።

የማጠምሪ ከተማ የከተማ አስተዳደር መዋቅር ያላትና የምዕራብ ጠለምት ወረዳ ዋና መቀመጫ በመሆን የምታገለግል የአካባቢው ቁልፍ የንግድና የአስተዳደር ማዕከል ናት።

ግጭቱ በሁለቱ ወገኖች መካከል የተደረሰውን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን መረጃው ያመለክታል።


የትግራይ ኃይሎች በክልሎቹ መካከል ያለውን የተከዜ ወንዝ ወሰን አልፈው ጥቃት መፈጸማቸው "የስምምነቱ መፍረስ ማሳያ ነው" ሲል ሙሉነህ ዮሐንስ በጽሁፉ ገልጿል።

እስካሁን ድረስ ከፌደራል መንግሥትም ሆነ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በኩል በጠለምት አካባቢ ስላለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ የለም።
4
ይህ ሆነ❗️

በባህርዳር ከተማ

በ24/05/2018 ከምሽቱ 1:30 አካባቢ አንድን የቀበሌ 15 ወጣት አጋቾች ተከታትለው መንገድ በመዝጋት ሊያግቱት ሲሞክሩ ልጁም መኪና ይዞ ስለነበር የዋዛ አይደለምና ቢከተሉትም አጋቾች መድረስ ባለመቻላቸው ከፍጥነት በላይ እያሽከረከረ ስለነበር ቀበሌ 15 አዲሱ ገቢያ ህንፃ አካባቢ ሲደርስ በወቅቱ ፓትሮል ሲያደርጉ የነበሩ ፓሊሶችና የፀጥታ አካላት መሳሪያቸውን ፊት ለፊት በመደገን የታጋች ሙከራ የሚደረግበትንና የአጋቾች የተጠቀሙበትን መኪኖች ያስቆሟቸው ሲሆን።

ከዛም የማገት ሙከራ ከሚያደርጉት መኪና ላይ 3 ሰዎች ወረዱ ፣ሊታገት የነበረውም ግለብም ከመኪናው ወረደና ሊያግቱኝ እያባረሩኝ ነበር በማለት ፓትሮል ሲያደረጉ ለነበሩት ለፓሊሶች አስረድቶ የአካባቢው ማህበረሰብም ጉዳዩን ሊመለከት ተሰበሰበ

ሆኖም የአጋች ቡድኖቹ በጣም ወከባ ፈጠሩና አንዴ የፀጥታ አካል ነን አንዴ የፌደራል ፓሊስነን አንዴ የደህንነት አካል ነን በማለት ለማጭበርበር ቢሞክሩም ነገር ግን ፓሊሶቹም የዋዛ አልነበሩምና ሁሎችንም ወደ ጣቢያ ወሰደው ያሰሯቸው ሲሆን በማግስቱ ጧት ላይ ሲታዩ የሆነው ጉድ አሳዛኝ ሆነ ማለትም አጋች ሆነው የተገኙት የፀጥታ አካል ሁነው ተገኙ ከዚያም በማጣራት ሰንሰለታቸው 7 ደረሰና ታሰሩ በሁለተኛው ሊታገት የነበረው ቃሉን ሰጦ ከእስር ቤት ወጥቷል።

ነገር ግን የማገት ሙከራ ያደረጉት 3ቱ ግለሰቦች ጥብቅ ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል።

አጋቾች በወቅቱ ይዘዋት የነበሩት ተሽከርካሪ ነጭ ሊፋን/ ያሪስ ታልጋ ቁጥር ኮድ 2-አአ C 05451 የሆነች ተሽከርካሪ ነበረች ጠዋት ታጋቹን ለመጠየቅ ታስራ ያገኘናት ታጋቾች ይዘዋት የነበረች መኪና ኮድ 4 አማ 05451 ሁኖ/ተቀይሮ ስናየው በጣም ገረመንና በምን ቅፅበት ቀየሩት ብለን ተገረምን ድንገት ተሳስተን ይሆን ብለን በወቅቱ ፎቶ አንስተው ከነበሩ ሰወች ጠይቀን ስናየው ደጋግመን ብናየውም ትክክል ነበርን።
በመሆኑም 1ኛ/እንዴትና የት ቦታ የመኪናዋ ታልጋው ተቀየረ ምን አልባት ፓሊስ ጣቢያ ከገቡ በኋላ በገንዘብ አስቀይረውት ሊሆን ይችላል ብለን ዝም አልን ምክንያቱም በወቅቱ የነበረና ወከባ ሲፈጥሩ በነበረበት ወቅት ለማስረጃ ብሎ ቪድዮ ሲቀርፅ ለምን ፎቶ አነሳህ ብለው አንድ ቀን አስረውት በስልኩ የነበረውን መረጃ አጥፍተው ሰደዱት ይህስ ለምን ተደረገ? ፖሊስ ለምን ማስረጃውን መጠቀም አልፈለገም? ምን አልባት ከላይ እንደገለፅኩት ሀለት/2 አይነት ታልጋ መኖራቸው እንዳይታወቅ ይሆን?

ስለሆነም የምርመራ ውጤቱን ወደፊት የምናየው ሁኖ ነገርግን ለባህር ዳር ከተማ ለ1ኛ ፓሊስ ጣቢያ እንድትጠይቁልን የምንፈልገው
የማገት ሙከራ ያደረጉት የፀጥታ አካላት በወቅቱ ሲጠቀሙበት የነበረው ታልጋ ቁጥር ማን ቀየረው? በምን ቅፅበት ተቀየረ? ለምንስ ወንጀሉ ከተፈፀመበት አካባቢ በመሄድ ለማጣራትና ተጨማሪ መረጃ ማግኘች አልተቻለም? በእገታ ሙከራ ላይ እንዴት ህዝብ ደህንነቴን ይጠብቃል ብሎ የሚተማመንበት የፀጥታ አካል ሊሳተፍ ቻለ? የሚሉ ጥያቄዎች በስፋት እየተነሱ መሆኑን ዘጋቢያችን ከባህርዳር የላከልን መረጃ ይገልፃል።
18👍5🤓3
የባንክ ሂሳብ እግድ

ፍትህ ሚንስቴር የህውሃት ባለስልጣናት የባንክ ሂሳብ እንድታገድ ማዘዙ ተሰምቷል።በዝርዝሩ ውስጥ
📌ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል
📌 አቶ ጌታቸው አሰፋ
📌ዶ/ር አብርሃም ተከስተ
📌 ዶ/ር አዲስ አለም ባሌማ
📌ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር
📌 አቶ አማኑኤል አሰፋ
ከወታደራዊ አመራሮች፦
📌 ሜጀር ጀነራል ህንፃ ወልደጊዮርጊስ
📌 ሜጀር ጀነራል መአሾ በየነ
📌 ሜጀር ጀነራል ዮሐንስ ወልደጊዮርጊስ
📌 ብርጋዴር ጀነራል ምግበ ኃይለ
📌 ብርጋዴር ጀነራል አብርሃ ተስፋይ
📌 ብርጋዴር ጀነራል ጉዕሽ ገብሬ ይገኙበታል።
12
የአምባሳደር ዘውዴ ረታን "የኤርትራ ጉዳይ" መጽሐፍ በድጋሜ እያነበብኩት ነው። ከዋናው ጉዳይ በላይ ያስገረመኝ፣ በአማራ ላይ የተነዛው ጥላቻ በተባበሩት መንግሥታት 4ኛው ጉባኤ ላይ በጣሊያን ፕሮፓጋንዲስቶች መቅረቡ ነው። ኤርትራ ወደ እናት ሀገሯ ኢትዮጽያ እንዳትመለስ የሀሰት ትርክት መፈብረክ ነበረባቸው። እንዲህ ይላል: "ኢትዮጵያ በአማራ ዘር ተጨቁና የተያዘች ስለሆነ፣ የሰውን ልጅን መብትና እኩልነት ትቀበላላች ተብሎ አይጠበቅም..."። የጥላቻው መርዝ በፕሮጀክት መልክ በጣሊያን ተቀርጾ፣ በእነ ግብፅ ተኮትኩቶ፣ በአገር በቀል ነፃ አውጪ እንከፎች ስጋ ለብሶ፣ ከገማሽ ክፍለዘመን በኋላ ፍሬ አፍርቷል። በድንገት የተፈጠረ አንዳች ነገር የለም!

ገፅ: 222።
👍65
ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት የኤርትራ ገዥው ሥርዓት በሦስት የተለያዩ ግንባሮች ላይ የተደራጁ የሜካናይዝድ ክፍሎችን አሰማርቷል። የአሰማራሩ ሂደት ታንኮችን፣ የመድፍ ሥርዓቶችን እና ሞርታሮችን ያካተተ ሲሆን፤ በዋና ዋና የድንበር ኮሪደሮች ላይ እንደሚከተለው ሰፍረዋል፦

ግንባር 1፡ በዛላንበሳ ዚባን ህፃ መስመር
ታንኮች፦ 22 (የተለያዩ ዓይነቶች)

122 ሚሜ መድፍ፦ 3 ባትሪ

130 ሚሜ መድፍ፦ 1 ባትሪ

155 ሚሜ መድፍ፦ 1 ባትሪ

80 ሚሜ ሞርታር፦ 10

120 ሚሜ ሞርታር፦ 6

ግንባር 2፡ በራማ ኮሪደር
ታንኮች፦ 20 (የተለያዩ ዓይነቶች)

122 ሚሜ መድፍ፦ 2 ባትሪ

130 ሚሜ መድፍ፦ 1 ባትሪ

155 ሚሜ መድፍ፦ 1 ባትሪ

80 ሚሜ ሞርታር፦ 8

120 ሚሜ ሞርታር፦ 4

ግንባር 3፡ በባድመ፣ ማይ ኩህሊ፣ ዓዲ ፀፀር፣ ዓዲ አሰር እና ሽመልባ ኮሪደር
ታንኮች፦ 30 (የተለያዩ ዓይነቶች)

122 ሚሜ መድፍ፦ 4 ባትሪ

ምንጭ 👉Conflict zone

130 ሚሜ መድፍ፦ 2 ባትሪ

155 ሚሜ መድፍ፦ 2 ባትሪ

80 ሚሜ ሞርታር፦ 20

120 ሚሜ ሞርታር፦ 12
6
ምን አይነት ግዜ ላይ ደረስን????😴

የምትመለከቱት ግለሰብ በአሰንዳቦ ከተማ በ20 kg ማር ዉስጥ 8.5 kg ትልቅ ድንጋይ ጋር አስመዝኖ ሲሸጥ ተያዘ።የገዛዉ ሰዉ ወደ እቃዉ ሊገለብጥ ሲል ተይዟል።
4😁4
የባንኮች የአገልግሎት ዋጋ ጭማሪ አደረጉ

​ባንኮች በዲጂታል ባንኪንግ እና በብድር አገልግሎቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ ማድረጋቸውን ጀምረዋል። የዚህ እርምጃ ዋና ዋና ምክንያቶች እና ዝርዝሮች የሚከተሉት ናቸው፦

​1. የጭማሪው ምክንያት
የአደጋ ስጋት ፈንድ፦ መንግሥት በሀገሪቱ ለሚከሰቱ ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ አደጋዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ገቢ ለመሰብሰብ ባወጣው አዋጅ መሠረት ነው።

የመንግሥት ትዕዛዝ፦ ባንኮች ከደንበኞቻቸው ላይ ክፍያ በመሰብሰብ ለ"ኢትዮጵያ አደጋ ስጋትና ምላሽ ፈንድ" ገቢ እንዲያደርጉ ታዝዘዋል።

​2. የታዩ የጭማሪ መጠኖች (ለምሳሌ በአዋሽ ባንክ)
በብድር ላይ፦ ከማንኛውም ዓይነት ብድር ላይ 1% ጭማሪ።

በዲጂታል ባንኪንግ፦ በአገልግሎት ክፍያ ላይ 5% ጭማሪ።

የተፈጻሚነት ጊዜ፦ ከየካቲት ወር ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል።

​3. ሌሎች ተያያዥ ክፍያዎች
ኢትዮ ቴሌኮም፦ ዘንድሮ ብቻ ሁለት ጊዜ የዋጋ ማሻሻያ በማድረግ እስከ 700 ብር የሚደርስ ጭማሪ አድርጓል።

የመንግሥት ሠራተኞች፦ በአዲስ አበባ የአስተዳደሩ ሠራተኞች ከደመወዛቸው 0.5% እየተቆረጠባቸው ይገኛል።

የከተማ ነዋሪዎች፦ ከወርኃዊ የውኃ ክፍያ ጋር 5 ብር ለዚሁ ፈንድ ገቢ ያደርጋሉ።
📌 ምንም እንኳን በሕግ ደረጃ ከሠራተኛ ደመወዝ ላይ ማስገደድ አይቻልም የሚሉ ድንጋጌዎች ቢኖሩም፣ በተግባር ግን ክፍያው እየተሰበሰበ መሆኑን ዘገባው ይጠቁማል።
3👏1
አልጀዚራ ይፋ ያወጣው የ20 ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞችና የእስራኤል የጋዛ ድርጊት ውዝግብ አስነሳ

አልጀዚራ "ሊስኒንግ ፖስት" በተሰኘው ፕሮግራሙ ባደረገው ምርመራ፤ እስራኤል በጋዛ እየፈጸመች ያለውን የዘር ፍጅት ገጽታ ለመቀየር 20 ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞችን ጨምሮ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎችን ወጪ በመሸፈን አሳሳች ዘገባዎች እንዲሰሩ ማድረጓ ተጋልጧል።

📌 ከኢቢኤስ: ከአሚኮ፣ ኦቢኤን እና ኤንቢሲ ጨምሮ ከ10 የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን የተውጣጡ 20 ጋዜጠኞች በጉዞው ተካፍለዋል።

📌ጋዜጠኞቹ ባዘጋጇቸው ፕሮግራሞች የፍልስጤማውያንን ድምፅ ያላካተቱ፣ የጉዳቱን መጠን ያሳነሱ እና "ፍልስጤም የሚባል ሕዝብ እንደሌለ" የሚያስመስሉ ይዘቶችን ማሰራጨታቸው ተጠቅሷል።

📌 ጉዞው በእስራኤል መንግሥትና ለእስራኤል ቅርበት ባላቸው ተቋማት (እንደ ደቡብ አፍሪካው አይሁድ ቦርድ) የተመራና ወጪው የተሸፈነ ቢሆንም፣ አብዛኞቹ ጋዜጠኞች ግን የገንዘብ ምንጩን ሳይገልጹ ቀርተዋል።

📌 ጋዜጠኛ ዘካርያስ ዘላለም እና የዘርፉ ባለሙያዎች ድርጊቱን "የጋዜጠኝነት የሥነ-ምግባር ደንብ ጥሰት" እና እውነታን የማድበስበስ ሙከራ ሲሉ ነቅፈውታል።

📌 ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ከኬንያ፣ ሩዋንዳ፣ ሴኔጋል እና ደቡብ አፍሪካ የሚዲያ ባለሙያዎችና የሶሻል ሚዲያ አንቂዎች በተመሳሳይ መልኩ ተመልምለው እንደነበር ተገልጿል።

📌በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው ፕሬስ ካውንስል ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ፣ የሚመለከታቸው ጋዜጦች ይቅርታ እንዲጠይቁና የገንዘብ ምንጫቸውን እንዲገልጹ የወሰነ ሲሆን፣ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ግን እስካሁን ለቀረበባቸው ክስ ምላሽ አልሰጡም።
6👍2
ሁለቱ የ4ኪሎ ሚንስትሮች የቃላት ጦርነት ውስጥ ገቡ!

ጌታቸው ረዳ እና በለጠ ሞላ የሚኒስትሮች ምክርቤት አባል ሲሆኑ፤ አገኘሁ ተሻገር የሚመሩት ቢሮ ወልቃይት እና ራያን በተመለከተ በወሰነው ውሳኔ የቃላት ምልልስ እያደረጉ ነው።

ሚኒስትሩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔን ደግፈው ውሳኔው " የፕሪቶሪያ ስምምነትን ያከበረ ነው " ብለዋል።

የነ አቶ ጌታቸው ረዳን ፓርቲም " ከፕሪቶሪያ ስምምነት ያፈነገጠ " በሚል ወርፈዋል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ደብዳቤን ተከትሎ ምርጫ ቦርድ ያሳለፈው ውሳኔ ከፍተኛ ውዝግብ አስነስቷል።

የተለያዩ የትግራይ ፓርቲ አመራሮች እንዲሁም ጊዜያዊ አስተዳደሩ ውሳኔው አደገኛ እንደሆነ አሳስበው ካልተቀለበሰ " መዘዝ አለው " ብለዋል።

የቦርዱን ውሳኔ ከተቃወሙት አንዱ አቶ ጌታቸው ረዳ የስምረት ፓርቲ ፕሬዜዳንት ናቸው። የፓርቲያቸውን አቋም በማያያዝ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ሃሳባቸውን ገልጸዋል።

ይህን ተከትሎ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) የአቶ ጌታቸውን መልዕክት ስክሪንሹት በማያያዝ ተቃውመዋቸዋል።

" የምርጫ ቀጠናዎችን በተመለከተ መንግስት የወሰነው ውሳኔ ህጋዊ እና የፕሪቶሪያ ስምምነትን ያከበረ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ከፕሪቶሪያ ስምምነት ያፈነገጡ ህጋዊ የፖለቲካ ድርጅቶች ህግ እንዲያከብሩ እናሳስባለን " ሲሉም ገልጸዋል።

በዚሁ መልዕክታቸው የእነ አቶ ጌታቸውን ፓርቲ ከ " ፕሪቶሪያ ስምምነት ያፈነገጡ " ሲሉ ገልጸዋቸዋል።
14🔥2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
❝የጨፈ~ጨፍናቸው የጋዛ ህፃናት በአይነ ህሊናዬ እየመጡ መተናት አልቻልኩም እየተከተሉኝ ነው የፈፀምነው የግ¤ፍ ጥግ እረፍት ነስቶኛል። እንዲህ ሆኜ አልኖርም.....❞

በጋዛ ህፃናት ደም የአይምሮ ህመምተኛ የሆነችው የእስራኤል 🇮🇱 ወታደር

በመጨረሻ ጭንቅላቷን 🔫🔫 ዷዷዷዷዷ 🙊🙊🙊
17👎4
#Coffee

ዓለም አቀፍ የቡና ዋጋ ከነበረበት 4 ዶላር ወደ 2.8 ዶላር ዝቅ አለ።

የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን በገለጸው መሰረት፣ ባለፉት ሁለት ወራት የዓለም አቀፍ የቡና ዋጋ ከነበረበት 4 ዶላር ወደ 2.8 ዶላር ዝቅ ብሏል፡፡

እንዲሁም በቀጣይ እስከ ወደ 2.5 ዶላር ሊወርድ እንደሚችል መተንበዩ በዘርፉ ላይ ከፍተኛ ስጋት ማሳረፉን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

በመሆኑም፣ አቅራቢዎች እጃቸው ላይ ያላቸውን የቡና ምርት በፍጥነት ለገበያ እንዲያቀርቡ አሳስበዋል።

ባለስልጣኑ ይህን ያለው፣ ዓለም አቀፉን የቡና ገበያ ሁኔታ እና የኢትዮጵያን ቡና ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ በሰጠው መግለጫ ነው። ለዋጋው መቀነስ ግን ምክንያቱ በዘገባው አልተጠቀሰም። #EPA
1