Ethio-Djibouti Railway S.C.
4.98K subscribers
1.83K photos
24 videos
7 files
67 links
Download Telegram
ጳጉሜ 3 ቀን 2016
ጅቡቲ

ክቡር ኢንጂነር ታከለ ኡማ በጅቡቲ ከሚገኙ የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር አ.ማ ሠራተኞች ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል፡፡ ሠራተኞቹ ለተቋሙ እድገት እያበረከቱ የሚገኘውን የላቀ ትጋት እና ቀጣይ መሻትን በተመለከተ ውጤታማ፣ አበረታች እና ገንቢ ሃሳብና አስተያየቶችን አቅርበዋል፡፡

ለኢትዮጵያና ጅቡቲ ወሳኝ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አስተዋፅኦ እያበረከተ የሚገኘው ኢትዮ ጁቡቲ ባቡር ይበልጥ መጠንከር እንዳለበት በውይይቱ ተነስቷል፡፡

የጅቡቲ የመሠረተ ልማትና ግብአት ሚኒስትር ክቡር ሀሰን ሁመድ ኢብራሂም እና የኢዲአር ቦርድ አባል መሐመድ ሮቤል ዳባር ለባቡር መሠረተ ልማቱ ግንባታ ላበረከቱት አስተዋፅኦ አድናቆት ተችሯቸዋል፡፡

ሁለቱ ወንድማማች ሀገራት ያላቸውን የዘመናት ትስስር በማጠናከር ለጋራ ዕድገትና ብልፅግና መረጋገጥ ኢትዮ ጂቡቲ የሚጫወተውን አዎንታዊ ሚና ማጉላት እንደሚያስፈልግ ተመላክቷል፡፡
የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር መስመርን ከስትራቴጂክ ወደቦች ጋር ለማገናኘት የሚደረገው ጥረት ቀጠናዊ ንግድን የመለወጥ አቅም እንዳለው ተጠቆመ፤
****
ጅቡቲ ጳጉሜ 4 ቀን 2016 ፡- ይህ የተጠቆመው ክቡር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከጅቡቲ የኢነርጂ እና የተፈጥሮ ሃብት ሚኒስትር ከሆኑት ክቡር ዮኒስ አሊ ጉዲ ጋር ተገናኝተው በመከሩበት ወቅት ነው፡፡

በውይይታቸ ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ በባቡር መሠረተ ልማት ከተሳሰሩበት ጊዜ ጀምሮ እያከናወኑት ያለው የንግድ ልውውጥ ለቀጠናው ምሳሌ መሆን የሚችል መሆኑን አንስተዋል፡፡

ክቡር ኢንጂነር ታከለ ኡማ አክለውም የኢትዮ ጅቢቲ ባቡር መስመርን ከስትራቴጂክ ወደቦች ጋር ለማገናኘት እየተደረገ ያለው ያላሰለሰ ጥረት እና ክቡር ዮኒስ አሊ ጉዲ እየሰጡ የሚገኘው አመራር የሚደነቅ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ይህም የቀጠናውን የንግድ እንቅስቃሴ እየለወጠ ነው ብለዋል፡፡

ሁለቱን ወንድማማች ሀገራት የኢኮኖሚ እድገት ከማሳደጉ በተጨማሪ የሀገራቱን ጠንካራ አጋርነት ይበልጥ የሚያጎለብት መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በአዋሽ ነዳጅ ዴፖ እና በጅቱቲ ሆራይዘን ተርሚናል መካከል የሚዘረጋውን የባቡር መስመር በታቀደለት ጊዜ አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት በቅርበት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡
አዳዲስ የሚዘረጉ የባቡር መሠረተ ልማቶች በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የነዳጅ ትራንስፖርት በማሻሻል የንግድ እና የኢኮኖሚ ዕድገትን እንደሚያሳድግ ተጠቁሟል፡፡
የወደብ እና የባቡር ትራንስፖርት ትስስርን በማሳለጥ የሎጂስቲክስ ዕድሎችን ማስፋት ይገባል"- ክቡር ኢንጂነር ታከለ ኡማ፤
****
ጳጉሜ 5 ቀን 2016 ጅቡቲ፡- የኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር አ.ማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ክቡር ኢንጂነር ታከለ ኡማ የወደብ እና የባቡር ትራንስፖት ትስስርን በማሳለጥ የሎጂስቲክስ ዕድሎችን ማሰፋት እንደሚገባ ገለፁ፡፡

ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህን ያሉት ከጅቡቲ ወደብ ባለስልጣን ፕሬዚዳንት አቡበከር ኦመር ሃዲ ጋር ተገናኝተው የወደብ እና የባቡር ትራንስፖርት ትስስርን ማሳለጥ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በመከሩበት ወቅት ነው፡፡

በዶራሌህ ኮንቴይነር ተርሚናል (DCT) በዶራሌህ ሁለገብ ወደብ (DMP) እና በሆራይዘን ተርሚናልስ መሃል ያለውን የባቡር ትራንስፖርት ትስስር ቀልጣፋና እንከን የለሽ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የአቅርቦት ስርዓትን፣ የመጨረሻ ማይል አስተዳደርን እና የአቅርቦት ሰንሰለትን አፈፃፀምን ማሻሻል ላይ ከጅቡቲ ወደብ ባለስልጣን ፕሬዚዳንት አቡበከር ኦመር ሃዲ ጋር በጥልቀት መክረዋል፡፡

"It is necessary to expand logistics opportunities by streamlining port and rail transport connections"—H.E. Engineer Takel Uma;
****
August 10, 2024, Djibouti: Chief Executive Officer of Ethio-Djibouti Railway s.c. H.E. Engineer Takele Uma stated that logistics opportunities should be expanded by streamlining port and rail transport links.
The CEO said this when he met with the President of the Djibouti Port Authority, Mr. Aboubaker Omar Hadi, and advised on the possibility of facilitating the connection of port and rail transport.

CEO H.E. Engineer Takele Uma stated that it will work hard to make the rail transport connection between Doraleh Container Terminal (DCT), Doraleh Multipurpose Port (DMP), and Horizon Terminals efficient and seamless.

In addition, H.E. Engineer Takele discussed extensively with the President of the Djibouti Port Authority, Abubakar Omar Hadi, on improving the delivery system, last mile management, and supply chain performance.
እንኳን ለ2017 አዲስ ዓመት በሠላም አደረሳችሁ፣አደረሰን!

Baga bara haaraa 2017tiin isin gahe, nugahe!

Bagu ilahay sanada cusub ee 2017 nabad inagu gaadhsiiyey


https://www.facebook.com/share/p/Ft9v9G3Dw4rbJAcY/?mibextid=WC7FNe