Forwarded from የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕዝብ ግንኙነት-Holy Trinity University PR
ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
✥✥✥ጾመ ጋድ እና ሰንበት✥✥✥
፩፦ ጾመ ጋድ በሰንበት ከዋለ ይጾማልን?
፪፦ ከቅዳሜ 7 ሰዓት ከእሁድ 2 ሰዓት ኣገናኝተን ጾመ ጋድ(ገሓድ) እንጾማለንን?
፫፦ በዕለተ በዓሉ የሚቆርቡ እንዴት ይጾማሉ?
መልስ፦
፩፦ ጾመ ጋድ በሰንበት ከዋለ በሰንበት ጾም ስለማይፈቀድ ከፍስክ ምግቦች (ሥጋ ዕንቁላል….) በመከልከል ሌላ ምግብ በመመገብ እንውላለን ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት ጾመ ገሓድ(ጋድ) በሰንበት ላይ ሲያርፍ እንደ ሌሎች የአዋጅ አጽዋማት ውስጥ እንዳሉ ሰንበታት ሰንበትነቱን በማይሽር መልኩ ይጾማል እንጂ ከምግብ በመከልከል መጾም አይገባም ለማለት ነው።
➙ የጥር 10 ስንክሳር "ወለእመ ኮነ በዓለ ልደት ወበዓለ ጥምቀት በዕለተ ሰኑይ ኢይትከሃል ከመ ይጹሙ በዕለተ ሰንበት ዳዕሙ ይትዓቀቡ እምነ በሊዕ ጥሉላተ" - "የልደትና የጥምቀት በዓልም ሰኞ ቀን ቢሆን በሰንበት ቀን ይጾሙ ዘንድ ኣይቻልም፤ ነገር ግን ጥሉላትን ከመብላት ይቆጠቡ" የሚለውን ነው። ስለዚህ ሰንበትም ሳይሽሩ ጾመ ጋድን ጠብቀው ያከብሩታል ማለት ነው።
፪፦ ከቅዳሜ 7 ሰዓት ከእሁድ 2 ሰዓት ኣገናኝተን ጾመ ጋድ(ገሓድ) እንጾማለን ለሚለው "ሰላም ዕብል ለጾመ ዕለት ዋሕድ" (የስንክሳሩ አርኬ) ከሚለው ጋር ይጋጫል ጾመ ጋድ ቅዳሜን እስከ 7 ቆተው ከበሉ በኋላ እንደገና የእሁድ 2ሰዓት ኣገናኝተው የሚጾሙት ሳይሆን «ለጾመ ዕለት ዋሕድ/ የኣንድ ዕለት ጾም» እንዳለው በልደት እና በጥምቀት ዋዜማ በኣንድ ዕለት ሊፈጽሙት የሚገባ ጾም እንጂ ሁለት ዕለትን በማገናኘት የምንጾመው አይደለም ። ለምሳሌ ሌሎች የኣዋጅ አጽዋማት ዕለታቱ ከአንድ በላይ ናቸው ጾመ ነነዌን ብንመለከት ሦስት ዕለታት ነው በእነዚህ ሦስት የጾም ዕለታት በየዕለቱ እስከ ዘጠኝ እየጾምን እየበላን ብናሳልፋቸውም አንዱን ጾመ ነነዌን ለመጾም ነው ሦስት ዕለት ይጹሙ ይላልና።
➙ በሰንበት ስለሚሆነው ጾም ሊቃውንት ከቀዳም ስዑር (ከሰሙነ ሕማማት ቅዳሜ) ሳያጠቃልል ስለቀሪው ቅዳሜ እና እሁድ በሃይማኖተ አበው ላይ በእሁድ ሰንበት ቅዳሴው እስከሚፈፀም መጾም እንደሚገባ ሲገልጽ ስለቅዳሜ ግን እጾማለሁ የሚል ቢኖር « አላ ጊዜ ዘይደሉ እስከ ስድስቱ ሰዓት ወእመ አኮ እስከ ሰብዓቱ/ እሰከ ስድስት ሰዓት እስከ ሰባት ሰዓት ድረስ » በማለት ገልጾልናል። (ይህ በቀድሞ ጊዜ የቅዳሜ ቅዳሴ አርፍደው ይጀምሩ ስለነበር ቅዳሴው እስከሚፈጸም ስድስት ሰዓት ይሆን ስለነበር ስድስት ሰባት ሰዓት ድረስ ተባለ እንጂ በቅዳሜ ጾም ይገባል ለማለት አይደለም )
በዚህ መሠረት ቅዳሜና እሁድም ቅዳሴው እስኪፈጸም ከምግብ መከልከል ይገባል እንጂ በሰንበት መጾም አይገባም።
➙ ጥምቀት ሰኞ ቢውል እንደሚታወቀው የጥምቀት ቅዳሴ የሚጀምረው እንደልደት እና ትንሳኤ ሌሊት 6 ሰዓት ሳይሆን ሊነጋጋ ሲል ወደ 10 ሰዓት ላይ የሚጀምር በመሆኑ ይህን ታሳቢ በማድረግ 18 ሰዓት አስልተው ከምግብ መከልከል ይገባል። በዚህም ሰንበትን ሻሩ አይባልም ጠዋት ተመግበዋልና ለመቊረብ ብለው ለ18 ሰዓት ከምግብ ተከለከሉ እንጂ ሰንበትን ሽረው ጾሙ ማለት አይደለም። ይቆየን

Telegram
ፍካሬ ሃይማኖት
ጌታችን ቅዱስ ቶማስን በልቡናው ውስጥ ያኖረውን ጥርጣሬና ጥያቄ ያርቅለት ዘንድ “ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን ” /ዮሓ ፳፥፳፯/ እንዳለው ሰው በሃይማኖት ያለውን ጥያቄ ጠይቆ ይረዳ ዘንድ ይገባል እንጂ ወደ ጥርጣሬ ወደ ክህደት መግባት ኣይገባውምና ይህም የቴሌግራም ማኅበር ስለሃይማኖታችን እንድንማማርበት የተከፈተ በመሆኑ ወደዚህ ማኅበር እናንተ እንድትሳተፉ ሌሎችንም እንደትጋብዙ ይሁን።
❤3👍1🙏1