Ethio unique tutorial
3.21K subscribers
1.19K photos
1 video
451 files
92 links
Well Come To Ethio unique tutorial

♀️Freshman Pdfs
♀️Mid and Final Exam
♀️Other Relevant materials.
♀️Dep't exam
➜department review
Our youtube channel
➜https://youtube.com/@ethiouniquetutorial?si=bMnwsw7S
Contact me for Support @Ethio_Supporter
Download Telegram
🇮 🇳 🇩 🇺 🇸 🇹 🇷 🇮 🇦 🇱
        🇨 🇭 🇪 🇲 🇮 🇸 🇹 🇷 🇾  🧪🔬**

📚 ኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ የሚለው የሳይንስ ዘርፍ በኢንዱስትሪያል ሂደቶች ውስጥ የኬሚካሎች እና የማተሚያ ሂደቶችን በመጠቀም ምርቶችን ለመፍጠር የሚያገለግል ነው። ይህ ዘርፍ በአሁኑ ጊዜ በብዙ የኢንዱስትሪ ዘርፎች ውስጥ እጅግ አስፈላጊ ሆኖ ይገኛል። ከፋብሪካዎች እስከ ፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪዎች ድረስ �ሻማ የሆነ ሚና ይጫወታል።

🌟 ታሪክ እና የአሁኑ ሁኔታ 
ኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ከኢንዱስትሪያል አብዮት ጋር ተያይዞ ተጀምሯል። በአሁኑ ጊዜ ደግሞ በቴክኖሎጂ እድገት ምክንያት በተለይም በኢትዮጵያ ውስጥ በፋብሪካዎች እና በማምረቻ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ እያደገ ይገኛል። �ሻማ የሆኑ የኬሚካል ምርቶችን ለመፍጠር እና ለማሻሻል የሚያገለግል ዘርፍ ነው።

🔮 የወደፊት እድሎች 
በወደፊቱ ኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ በተለይም በአረንጓዴ ኬሚስትሪ (Green Chemistry) እና በተቀናጀ ኬሚካል ምርቶች ላይ ትኩረት በመስጠት እየተሻሻለ ነው። ይህም ማለት በኢንዱስትሪያል ሂደቶች ውስጥ የአካባቢ ጥበቃን እና ዘላቂነትን ማስተዋል ነው።

🎯 ምን አይነት ተማሪዎች ይመቻሉ? 
- በኬሚስትሪ እና ሂሳብ ላይ ጠንካራ የሆነ ፍላጎት ያላቸው 
- በምርምር እና በፈጠራ ላይ ዝንባሌ ያላቸው 
- በትንታኔ እና ችግር መፍታት ላይ ጠንካራ የሆኑ 

📚 የትምህርት ዘመን እና ኮርሶች 
በኢትዮጵያ ውስጥ ኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ በብዙዎች ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በ5 አመት የትምህርት መርሃ ግብር ይሰጣል። ከዋናዎቹ ኮርሶች መካከል፦ 
- ኦርጋኒክ ኬሚስትሪ 
- ኢኖርጋኒክ ኬሚስትሪ 
- ፊዚካል ኬሚስትሪ 
- ኢንዱስትሪያል ሂደቶች 
- የኬሚካል ምህንድስና 
- የአካባቢ ኬሚስትሪ 
- የምርት ማስተዳደር 

🌟 የስፔሻላይዜሽን እድሎች 

በትምህርት ከመጨረሻ በኋላ ተማሪዎች በሚከተሉት ዘርፎች ላይ ሊያተኩሩ ይችላሉ፦ 
- ፋርማሲዩቲካል ኬሚስትሪ 
- አረንጓዴ ኬሚስትሪ 
- የኬሚካል ምህንድስና 
- የኢንዱስትሪያል ምርት ማስተዳደር 


💸 የትምህርት ክፍያ 
በኢትዮጵያ ውስጥ የኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ ትምህርት ወርሃዊ ክፍያ በዩኒቨርሲቲዎች ላይ በመሠረቱ ከ5,000 እስከ 10,000 ብር ይሆናል። በግል ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ደግሞ ከ10,000 ብር በላይ ሊሆን ይችላል።

💼 የስራ እድሎች እና ገቢ 
በኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ የተመረቁ ተማሪዎች በሚከተሉት ዘርፎች ላይ ስራ ማግኘት ይችላሉ፦ 
- ፋብሪካዎች ውስጥ እንደ ኬሚስት ወይም ምርት ማኔጅር 
- ፋርማሲዩቲካል ኩባንያዎች 
- የኬሚካል ምርት እና ምርምር ኢንዱስትሪዎች 
- የአካባቢ ጥበቃ ድርጅቶች 


በአማካይ ደሞዝ ከ8,000 እስከ 20,000 ብር ይሆናል። በተጨማሪም በግል ስራ ላይ በመዋዠቅ ተጨማሪ ገቢ ማግኘት ይቻ

ላል።
🚀 የራስ ስራ እድል 
አዎ። በኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ የተመረቁ ተማሪዎች የራሳቸውን የኬሚካል ምርት �ጣና �ሻማ ድርጅት መጀመር ይችላሉ። በተለይም በሳሙና፣ በመዳብ እና በሌሎች የቤት ንጥረ ነገሮች ምርት ላይ ማተኮር ይቻላል።

🌟 ዝነኛ ሰዎች 
በኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ ዘርፍ ዝነኛ የሆኑ ሰዎች እንደ ሊኒየስ ፖሊንግ (Linus Pauling) እና ፍሪትዝ ሃበር (Fritz Haber) ያሉ ሰዎች ይገኙበታል። እነዚህ ሰዎች በኬሚስትሪ ዘርፍ ውስጥ የታላቅ አስተዋጽኦ ያደረጉ ናቸው።
❤2
🎧JOURNALISM 🎤

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የጋዜጠኝነት ዘርፍ በሀገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ባህላዊ ለውጦች የተቀረፀ ልዩ ልዩ ፈተናዎች እና እድሎች ይገለጻል።

🎤የ journalism ትምህርት ማለት በጋዜጠኝነት መስክ ውስጥ ያሉትን መሰረታዊ መርሆዎች ፣ ችሎታዎች እና ልምዶች ለማስተማር የተዘጋጀ የትምህርት መርሃ ግብር ነው።ይህ ትምህርት ተማሪዎች በጋዜጠኝነት መስክ ውስጥ ለስኬት አስፈላጊ የሆኑትን መሰረታዊ ችሎታዎችን እንዲያዳብሩ እና ለሙያ ዝግጁ እንዲሆኑ ይረዳቸዋል።

🎧ትምህርቱ ምን ኮርሶችን ያካትታል❔

🎧የጋዜጠኝነት መርሆዎች፡- ይህ ኮርስ ጋዜጠኝነትን ለመረዳት አስፈላጊ የሆኑትን መሰረታዊ መርሆዎች፣ ታሪክ፣ እና ትክክለኛ የጋዜጠኝነት ልምዶችን ያስተምራል።

🎤የዜና ሪፖርታጅ፡- ይህ ኮርስ ተማሪዎች ዜናዎችን በትክክል እና በተጨባጭ እንዴት እንደሚሰበስቡ፣ እንደሚጽፉ እና እንደሚያቀርቡ ያስተምራል።

🎧የምርምር ጋዜጠኝነት፡- ይህ ኮርስ በጥልቀት በመመርመር እና በማረጋገጥ ላይ ያተኩራል። ተማሪዎች ውስብስብ ጉዳዮችን ለማጥናት እና ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት ያስፈልጋቸውን ችሎታዎች ይማራሉ።

🎧የጋዜጠኝነት ህግ እና ሥነምግባር፡- ይህ ኮርስ ተማሪዎች በጋዜጠኝነት መስክ ውስጥ ያለውን ህግ እና ሥነምግባር እንዲረዱ ያስችላቸዋል።

🎧የጋዜጠኝነት እና የህዝብ ግንኙነት፡- ይህ ኮርስ ተማሪዎች የጋዜጠኝነትን እና የህዝብ ግንኙነትን አጠቃላይ ግንኙነት እንዲረዱ ያስችላቸዋል።

🎧በተጨማሪም በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች በጋዜጠኝነት መስክ ውስጥ ልዩ ሙያዎችን የሚያቀርቡ ኮርሶችን ይሰጣሉ፣ እንደ፦

🎧የቴሌቪዥን ጋዜጠኝነት፡- ይህ ኮርስ ተማሪዎች ለቴሌቪዥን ዜናዎች ሪፖርታጅ እንዴት እንደሚሰሩ ያስተምራል።

🎧የሬዲዮ ጋዜጠኝነት፡- ይህ ኮርስ ተማሪዎች ለሬዲዮ ዜናዎች ሪፖርታጅ እንዴት እንደሚሰሩ ያስተምራል።

🎧የዲጂታል ጋዜጠኝነት፡- ይህ ኮርስ ተማሪዎች በዲጂታል መድረኮች ላይ ዜናዎችን እንዴት እንደሚያቀርቡ ያስተምራል።

🎧የፎቶ ጋዜጠኝነት፡- ይህ ኮርስ ተማሪዎች በፎቶግራፍ በኩል ዜናዎችን እንዴት እንደሚያቀርቡ ያስተምራል።

ግቢ ላይ ምን ያህል ዓመት ይወስዳል❔

Journalism ተምሮ ለመጨረስ ከ3-4 ዓመታት ይፈጃል

Graduate ካረኩ ቦኃላስ❔

🎧በJournalism ትምህርት graduate ካደረጋችሁ በኃላ የቴሌቪዥን, የሬድዮ እና ሌሎች የሕዝብ ግንኙነት ላይ ተቀጥራችሁ መስራት ትችላላችሁ

ክፍያዉስ እንዴት ነዉ❔

ክፍያው እንደ ተቋሙ ይለያያል:: ለምሳሌ:ለማጣራት እንደሞከርነው, ETV ላይ ሚሰሩ ጋዜጠኞች ከ30,000-40,000 ብር ይከፈላቸዋል

የት የት ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ይሰጣል❔

🎧በኢትዮጵያ ውስጥ የ journalism ትምህርት በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች ይሰጣል። አዲስ አበባ, ሐዋሳ, ባህርዳር, ዲላ ዩኒቨርሲቲዎች ዋና ዋናዎቹ ናቸው ::

🎧የ journalism ትምህርት በኢትዮጵያ በአዎንታዊ አቅጣጫ እየተንቀሳቀሰ ነው። በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች በጋዜጠኝነት መስክ ውስጥ ልዩ ትምህርት እየሰጡ ናቸው፣ እና በተማሪዎች መካከል ለጋዜጠኝነት ፍላጎት እየጨመረ ነው።

🎧በኢትዮጵያ ውስጥ የ journalism ትምህርት በተማሪዎች ላይ ትልቅ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው። ተማሪዎች በጋዜጠኝነት መስክ ውስጥ ስኬታማ ለመሆን አስፈላጊ የሆኑትን ችሎታዎች እያዳበሩ እና ለሙያ ዝግጁ እየሆኑ ናቸው። በተጨማሪም፣ የ journalism ትምህርት በኢትዮጵያ ውስጥ ለዴሞክራሲ እና ለነፃነት መስፋፋት አስተዋጽኦ ያደርጋል።
❤3
👨‍💻SOFTWARE ENGINEERING💻

🔑በኢትዮጵያ ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ ባለፉት ጥቂት አመታት በፍጥነት እያደገ ሲሆን በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ የቴክኖሎጂ መፍትሄ ፍላጎት መጨመር፣ የኢንተርኔት አገልግሎት መጨመር እና በቴክኖሎጂ የዳበረ ወጣት ህዝብ። በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የሶፍትዌር ምህንድስና ዘርፎች በጥልቀት:

1️⃣ትምህርታዊ

💻ኢትዮጵያ የኮምፒዩተር ሳይንስና ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ ፕሮግራሞችን የሚሰጡ ዩኒቨርሲቲዎችና የቴክኒክ ተቋማት ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መጥቷል። እንደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ጅማ ዩኒቨርሲቲ እና ሌሎችም ሶፍትዌር እንጂነሪንግ ትምህርትን በማቋቋም በንድፈ ሐሳብ እና በተግባራዊ ክህሎት ላይ ያተኮሩ ተቋማት አቋቁመዋል።

💻በ እትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ሶፍትዌር ኢንጂኔሪንግን ለመቀላቀል:-
   
➫GPA(50%)
➫EUEE result(20%) &
➫COC(30%).
🔑እነዚህ 3 ነገሮች ተደምሮላችሁ ዉጤታችሁ መመዘኛዉን ካሟላ ፊልዱን ትቀላቀላላችሁ።መመዘኛዉ ከዩኒቨርሲቲ ወደ ዩኒቨርሲቲ ልለያይ ይችላል።

👨‍💻ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግን ተምራችሁ ለመጨረስ ከ 4_5 ዓመታት ይፈጃል።



➫የስርዓተ ትምህርት ልማት፡ ስርአተ ትምህርቱ ብዙ ጊዜ Programming languages,software development, cloud computing,website development &Mobile app development ን ያካትታል።             
ይሁን እንጂ በአካዳሚክ ስልጠና እና በኢንዱስትሪ ፍላጎቶች መካከል ክፍተት ሊኖር ይችላል።ይህም የበለጠ ተግባራዊ እና የተግባር ስልጠና ጥሪዎችን ያመጣል።

➫የቴክኒክ ማሰልጠኛ ማዕከላት፡- ከዩኒቨርሲቲዎች በተጨማሪ ልዩ ልዩ የቴክኒክ ማሰልጠኛ ማዕከላት የክህሎት ክፍተቱን ለመቅረፍ በተወሰኑ ቴክኖሎጂዎች፣ ፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች እና ሶፍትዌር ዲቭሎፕመንት ልምዶች ላይ የአጭር ጊዜ ኮርሶችን ይሰጣሉ።

2️⃣የስራ ዕድሎች

💻በሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ ተመርቃችሁ ስራ ለማግኘት:-
  ➫ልምዳችሁ ላይ ጎበዝ መሆን  
      ይኖርባችኋል።ማለትም ዩኒቨርሲቲ
      ዉስጥ በሚትቆዩ ጊዜያት ዩኒቨርሲቲ
      ከሚሰጣችሁ ኮርሶች በተጨማሪ
      በራሳችሁ ፍላጎት በ ኦንላይን
      የተለያዩ programming
      languages መማር ይኖርባችኋል።

  ➫ግቢ ዉስጥም ብአንስ አንድ
        አዋጭ ፕሮጀክት ብትሰሩ
        ከተመረቃችሁ በኋላ ያንን ፕሮጀክት
        ለተለያዩ ኩባንያዎች በማሳየት በ
        ኩባንያዎቹ በ እጅግ ተፈላጊ
        ትሆናላችሁ።

   ➫መረጃን መሰብሰብ:-   

     🔑ልክ እንደ ተመረቃችሁ
     የተለያዪ የ ስራ ዕድሎች
     ማስታወቅያን የሚያወጡ
     ቻናሎችን በየ ቀኑ መከታተል
     ይኖርባችኋል ።

3️⃣የኢንዱስትሪ እድገት

💻በኢትዮጵያ የሶፍትዌር ኢንዱስትሪ ገና በጅምር ላይ ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ነው። ለዚህ እድገት አስተዋጽኦ የሚያደርጉ በርካታ ምክንያቶች-

➫የመንግስት ኢኒሼቲቭስ፡ የኢትዮጵያ መንግስት ቴክኖሎጂ ለኢኮኖሚ ልማት ያለውን ጠቀሜታ ተገንዝቧል። እንደ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ያሉ ተነሳሽነት በሴክተሮች ውስጥ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ማስተዋወቅ ነው።

➫ጀማሪዎች እና የኢኖቬሽን መገናኛዎች፡- እንደ አዲስ አበባ ባሉ ከተሞች የቴክኖሎጂ ጅምሮች መበራከታቸው ደማቅ ስነ-ምህዳር ፈጥሯል። እንደ ብሉሙን እና አይስአዲስ ያሉ የኢኖቬሽን ማዕከላት ለስራ ፈጣሪዎች እና አልሚዎች ድጋፍ ይሰጣሉ፣የፈጠራ ባህልን ያሳድጋል።

➫የውጪ አቅርቦት እና ፍሪላንሲንግ፡- ብዙ ኢትዮጵያውያን አልሚዎች በነጻ ሥራ ወይም በውጭ አገር ለዓለም አቀፍ ደንበኞች የማውጣት ፕሮጀክቶች ላይ እየተሳተፉ ነው። እንደ Upwork እና Fiverr ያሉ መድረኮች የሀገር ውስጥ ተሰጥኦዎች አለምአቀፍ ገበያዎችን እንዲያገኙ አስችለዋል።

💰ገቢዉስ ምን ያክል ነው?



👨‍💻ለማጠቃለል💻

🔑maths & physics ላይ ጎበዝ የሆናችሁ፣ለቴክኖሎጂ ያላችሁ አመለካከት ከፍተኛ ድጋፍ ካለዉ እና ከ theory ይልቅ calculation የሚያስደስታችሁ ልጆች ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግን ብትቀላቀሉ ዉጤታማ ትሆናላችሁ።
❤4
ለOTHERS

የስራ እድል እና ችሎታወችን የያዘች ፖስት እንደሚከተለው አቀርብላቹሃለሁ።

1) Horticultural Science

☑️Woreda, Zonal and regional ☑️agriculture sectors

☑️Land beautification, greenery

☑️Flower company

☑️Fruit farmers

☑️Vegetable farms

Coffee, tea, spice sector/

☑️industry

☑️Irrigation sectors

☑️Agro-processing sectors

🛑Self job creation (seedling preparation, floriculture, urban horticulture)

❗️Skills required: Good in any natural science subjects

2) Plant Science

☑️Kebele, woreda, Zone,

☑️regional office,

☑️NGOs,

☑️Research centers

☑️Wheat industry sectors

☑️Agro-processing

☑️Biodiversity institute

☑️Agro-processing parks

Universities

❗️Skills required: Good in any natural science subjects

3) Animal Science

☑️Woreda, Zone, regional

☑️Agriculture

☑️Trade and industry

☑️Cooperatives

☑️Research centers, pastoral office

☑️Agro-processing parks

☑️Private feedlots, export industry

☑️Hide and skin industry

☑️Universities

☑️Biodiversity institute

☑️NGOs

☑️Consultant

☑️Self job creation(fattening, poultry, dairy, beekeeping)

☑️Skills required: Good in any natural science subjects, biology

4) Food Science and Postharvest Technology

☑️Woreda, Zone, Regional office

☑️Agroprocessing industry

☑️Food industry

☑️Beverage industry

☑️Industrial parks

☑️NGOS

❗️Skills required: Good in chemistry, physics, Maths

5) Human Nutrition

☑️Woreda, Zone, Regional office

☑️Health centers (Hospitals)

☑️Agroprocessing industry

☑️Food industry

☑️Industrial parks (Yirgalem)

☑️NGOS (community nutrition )

☑️Food security experts

☑️Emergency

❗️Skills required: Good in chemistry, biology

6)Rural Development and Agricultural Extension

☑️Woreda, Zone, Regional office

☑️Cooperative and marketing office

☑️NGOs,

☑️Universities

☑️Research centers

☑️Food security expert

☑️Saving and credit associations

Any development projects

(Social sciences)

7) Agribusiness and Value chain management

☑️Woreda, Zone, Regional office

☑️Agroprocessing industry

☑️Food industry

☑️Industrial parks

☑️NGOS

☑️Banks,

☑️Saving and credit associations

(Good in Economics, statistics, management)

8) Agrieconomics

☑️Woreda, Zone, Regional office

☑️Industrial parks

☑️NGOS

☑️Agricultural inputs

☑️Research centers

☑️Universities

☑️Banks

❗️Saving and credit association

(Good in Economics, Maths, statistics)
❤6
ጠንካራ ሰው መሆንን ልመዱ
በሰዎች ለይ ጥገኛ አትሁኑ
ለምንም ነገር ስዎችን አትለምኑ
የምትኖሩት አንዴ ነው። ለሰው ባላችሁ
አትኑሩ: ቆራጥ መሆን ልመዱ ፍርሃት
መጋፈጥ ልመዱ ጠንክራችሁ ስሩ ደስታችሁን ከሰው ዘንድ አትፈልጉ
ለትንሹም ለትልቁም ማመስገን ልመዱ

መልካም ቀን 🙏
uniques
❤18🆒3
🎓ግቢ ውስጥ አዲስ ሊሆኑባቹህ የሚችሉ የግቢ ቃላቶች ውስጥ ጥቂቶቹን እንመልከት!

🍰 ካፌ-  ብዙሃኑ ተማሪ የሚጠቀምበት  የግቢው መመገቢያ ቦታ

🍔 ላውንጅ - ግቢ ውስጥ የሚገኝ ተማሪን ባመከለ መልኩ ክፍያ የሚያስፈልግ ካፌ ነገር ነው  ፤ ምግብና መጠጦቹ(ለስላሳ ፣ ትኩስ ነገር ምናምን) ጥራት ያላቸው እና በዋጋም በጣም ቅናሽ ናቸው።

🧑‍🎓 ችከላ- ጥናት

😭 ቴንሽን- ጭለላ ፣ ውጥረት፣ መረበሽ፣ መጨናነቅ

🥖 11  - ግማሽ እንጀራ በዳቦ ( የካፌ ምግብ ነው በተለይ እራት ላይ)

🍔 Non-cafe - የግቢውን ካፌ የማይጠቀሙ ተማሪዎች

🚀Space - ባዶ ክፍል ብዙውን ጊዜ መማሪያ ክፍሎችን ለንባብ ስንጠቀምባቸው ስፔስ ይባላሉ

🥩Therefore- የካፌ ስጋ  ( ስጋ ሲባል ግን ሰፍ እንዳትሉ ! እንደስሙ ነው ማለት ትንሽ ስጋ ጣል ጣል የተደረገበት ገራሚ መረቅ )


💵Cost -ካፌ ለማይጠቀሙ ተማሪዎች የሚሰጥ ወርሃዊ ክፍያ ፤ የሁሉም ማለት በሚቻል መልኩ ክፍያው ተመሳሳይ ነው።

📤Add and drop - በትምህርት ሂደት ውስጥ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ነገሮች ናቸው ፤ ይሰውራቹህና የሆነ ኮርስ ከፈላ(F) add and drop process ግድ ይሆናል

🪑ድድ ማስጫ- አላፊ አግዳሚውን ለማየት አመቺ የሆነ ቦታ ወይም መቀመጫ 

👮‍♂️ዛፓ - ጥበቃ ሰራተኞች

🎓 GC- ተመራቂ ተማሪዎች

🐒 Fresh፣ጦጣ ምናምን  - አዲስ ገቢ ተማሪዎች ( ግቢ ስትገቡ ፍሬሽ ምናምን እያሉ አዛ የሚያደርጓቹህ ብዙውን ጊዜ ሁለተኛ አመቶች ናቸው ሁሉም ሁለተኛ አመቶች ሳይሆኑ ፍሬሽነታቸውን ያልጨረሱት ወይም ገራሚ ፉገራ የተፎገሩት ናቸው

🍃በርጮሎጂስት- የፍየልን መኖ የሚጋፉ ጫት ቃሚዎች ማለት ነው

🍺ኦቨር- መጠጥ ቤት መሄድና ሰክሮ መምጣት

🫰ሻት - ይቅርባቹህ እንዳያስመልሳቹህ ብዬ ነው


🧦 ጥፊ- የዶርምን ላይፍ እንዳይረሳ ከሚያደርግ ግሩም ጠረኖች ውስጥ አንዱ ነው፤  የተለመደ የካልሲ ጭስ ነው::

🍔 Meal Card- የግቢው ካፌ ውስጥ ለመመገብ በግቢው የሚሰጣችሁ የመመገቢያ ካርድ።

JOIN: @ethio_unique_tutorial
❤5😭3
❗️ውጤት ይፋ የሚሆነው
ከሰኞ እስከ ማክሰኞ ባለው ጊዜ ነው

ውጤት ሲለቀቅ ለማየት የሚያስችሉ

1. result.eaes.et
2. result.neaea.gov.et
3.@ESSLCEResultBot
4. SMS 6284 ተጠቀሙ።


share: @ethio_unique_tutorial
ውድ ቤተሰቦቻችን እስካሁን ስለ ዉጤት ምንም አዲስ ነገር የለም:: እንደምታዩት "Results Not yet Released " ነው የሚለው:: ስለዚህ ተረጋግታችሁ ጠብቁ እኛ በየሰዓቱ እየተከታተልን ይፋ ሲሆን እናሳውቃችኋለን።

የኔትዎርክ ችግር ያለባቸው ተማሪዎችን በhttps://t.me/Ethio_unique_g ላይ ዉጤታቸውን በማየት እንተባበራለን::

እስከዛ ቻናላችንን ለክፍል ጕደኞቻችሁ ሼር እያደረጋችሁ ጠብቁ::

መልካም እድል!!!!!! 👍🙏♥️

JOIN: @Ethio_Unique_tutorial
--------------------------------------------
❤3🙏2
ውጤት እስካሁን አልተለቀቀም!!

የ12ኛ ክፍል ውጤት ጋር ተያይዞ ብዙዎች ጥያቄ እየጠየቁ ስለሆነ ዉጤት እስካሁን አለመለቀቁን እናሳዉቃለን::

‎​ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ወደ [ፖርታሉ] ገብተን ስንመለከት፣ "The 2018 result is not released" (የ2018 ውጤት አልተለቀቀም) የሚል መልእክት አለ።

‎​አዲስ መረጃ ወይም ለውጥ ካለ በቅርቡ በትክክለኛው ሰዓት እናደርሳችኋለን።
‎
‎​
👍7
#New

የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት የሚገለጽባቸው አድራሻዎች ይፋ ሆኑ።

ውጤት የሚገለጽባቸው ማስፈንጠሪያዎች፡-

· በድረ ገጽ፡ https://result.eaes.et
· ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram
· አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms

የውጤት መገለጫ ቀንና ሰዓት፡-

· ተፈታቹ ዛሬ ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

ቅሬታ የማቅረቢያ ሂደት፡-

· ቅሬታ ያላቸው ተፈታቹ በአካል መምጣት ሳያስፈልግ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ፡
https://result.eaes.et/complaint
· የማቅረቢያ ጊዜ፡ ከነሐሴ 19 እስከ 26/2012 ዓ.ም እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ።
· ምላሽም በተመሳሳዩ ማስፈንጠሪያ በኩል ይሰጣል።
❤2🙏1
የአምና የRemedial የመቁረጫ ነጥብ ፦

👉 የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 216

👉 የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 204

👉 ታዳጊ ክልል እና አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 198

👉 የማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 198

👉 ማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ዓይነስውራን ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 165

⭐ የዘንድሮዉ እስካሁን አለተገለፀም።አዲስ መረጃ ካለ የምናደርሳቹ ይሆናል።

About 2018 remedial መቁረጫ ነጥብ 👇
https://vt.tiktok.com/ZSVGXpXRS/


@Ethio_unique_tutorial
🙏4❤2
📢 የዩኒቨርስቲዎች የ ትዉልድ ደረጃ ምንድነው ?

የዩኒቨርስቲዎች የ ትዉልድ ደረጃ በ አመሰራርት የጊዜ ሂደት ዩኒቨርስቲዎችን በቅደም ተከትል እንደ አንጋፋነታቸው የማስቀምጥ ሂደት ነው።

ከተመሰረቱ ብዙ አመታትን ያስቆጠሩ ዩንቨርስቲዎች ብዙ ነገሮችን ያሟላሉ ተብሎ ስለሚታሰብ በብዙዎች ዘንድ ተመራጭ ያደርጋቸዋል።

📌ያው ምንም እንኳ የተሟላ ነገር ቢኖረውም ትንሽ ውጤት ለመስራት ያስቸግራል ፣የምትፈልጉትን ዲፓርትመንት በደንብ ካልሰገጣችኹ ለማግኘት ይከብዳል።

1st Generation
  📚 Addis Ababa University
  📚 Arba Minch University
  📚 Bahirdar University.
  📚 University of Gondar
  📚 Hawassa University
  📚 Haramaya University
  📚 Jimma University
  📚 Mekele University


2nd Generation
   📚 Dila University
   📚 Dire Dawa University
   📚 Jijiga University
   📚  Mede Melabo University
   📚 ASTU
   📚 Debra Markos University
   📚 Aksum University
   📚 Debra Birhan University
   📚 Wollega University
   📚Wollo University
   📚 Mizan Teppi University
   📚Mekdela Amba University
   📚 Ambo University
   📚 Semera University
   📚 Kotebe motrop. University

  3rd Generation
  📚Adigrat University
  📚Mattu University
 📚 Woldia University
  📚 Wolkite University
  📚Debratebor University
  📚 Wachamo University
  📚Assosa University
  📚AASTU University
  📚Arsi University
  📚Gambela University
  📚 Bulehora University
  📚Wolaita Sodo University

4th Generation
   📚Jinka University
   📚Bonga University
   📚Worabe University
   📚Injibara University
   📚Debark University
   📚Mekdela Amba University
   📚Raya University
   📚Dembidolo University
   📚Selale University
   📚Oda Bultum University
   📚 Borena University


🙏Join and share🙏
@ethio_unique_tutorial
❤6
➡️‎የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ — 2025

➡️የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች በሚሰጡት የአገልግሎት ጥራት በየአመቱ ደረጀ የ ሚቀመጥላቸው ሲሆን ከዚህ በታች እንደሚከተለው ተቀምጦላችኋል ።

ይህ መረጃ ቀጣይ University ለምትመርጡ የ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ያግዛችኋል 🙏

1 Addis Ababa University
2 University of Gondar
3 Bahir Dar University
4 Jimma University
5 Mekelle University
6 Hawassa University
7 Haramaya University
8 Adama Science and Technology University
9 Arba Minch University
10 Jigjiga University
11 Addis Ababa Science and Technology University
12 Ambo University
13 Dilla University
14 Unity University
15 Debre Berhan University
16 Wollo University
17 Debre Markos University
18 Wolaita Sodo University
19 Madda Walabu University
20 Worabe University
21 Wachamo University
22 Debre Tabor University
23 Wolkite University
24 Ethiopian Civil Service University
25 Arsi University
26 Samara University
27 Assosa University
28 Dire Dawa University
29 Wollega University
30 Mattu University
31 Mizan-Tepi University
32 Kotebe Education University
33 Adigrat University
34 Woldia University
35 Oromia State University
36 Bule Hora University
37 Aksum University
38 Bonga University
39 Rift Valley University
40 Oda Bultum University
41 Raya University
42 Injibara University
43 Selale University
44 Debark University
45 Kebri Dehar University
46 Gambella University
47 Mekdela Amba University
48 Dembi Dolo University
49 Jinka University
50 Borena University
51 Ethiopian Police University
‎ 
‎Source : UNIRANKS® — Top-Ranked Universities in Ethiopia - 2025)

🙏Join and share🙏

🔥🔥@ethio_unique_tutorial
❤‍🔥4
✅DILLA UNIVERSITY

"university of green land"


በውስጥ መስመር ስለ ዲላ ዩኒቨርስቲ እየጠየቃቹኝ ላላቹ fresh 😁( fresh መባላቹ ግድ ነው😍) ተማሪዎች ትንሽየ ገለፃ እንካቹ አልኳቹ

        ✅መገኛ
ዲ.ዩ በደ/ብ/ብ ክልል በ ጌዲኦ ዞን በዲላ ከተማ የሚገኝ ዩኒቨርስቲ ሲሆን ከመዲናችን አዲስ አበባ በ 360 km ርቀት ላይ ይገኛል።ከክልሉ ዋና ከተማ  ሀዋሳ ደግሞ በ 80km ርቀት ላይ ይገኛል።
ከ አዲስ አበባ ስትመጡ ሁለት አሪፍ 👌አማራጭ አላቹ
ቀጥታ ዲላ የሚወስዱ መኪኖችን መጠቀም አሊያም
ሀዋሳ ድረስ በባስ በመምጣት ከሀዋሳ ዲላ ሚኒባስ መጠቀም
ከ አ/አ ዝዋይ ድረስ 🛣highway  ስለሆነ ባሪፍ ሰዓት ዲላ ከች ትላላቹ መንገዱ 5 ሰዓት ይፈጃል ግን ከ አ/አ እንዳነሳሳቹ የምትደርሱበት ሰዓት ይለያያል
ግቢው አ/አ ድረስ ተማሪ ይቀበላል የሚባለው ነገር ውሸት ነው።ግን ዲላ መናሀሪያ ላይ ግን ይቀበላቹሀል
የግቢ ሁኔታ
ዲ.ዩ ከዋናው ግቢ ውጭ ሦስት ግቢዎች አሉት
          ✅ኦዳያ (ሠመራ)
አሴዴላ(በማለቅ ላይ ያለ አዲሱ ግቢ ሲሆን ምናልባትም በቅርቡ የተማሪዎች ቅበላን ሊቀላቀል ይችላል )
ሆስፒታል
      ✅ዋናው ግቢ
ዋናው ግቢ ጠበብ ያለ ቢሆንም ፅዱ ነው።ለዐይን የሚማርኩ ዛፎች እና አበቦች አሉ ግቢው ሙሉ በሙሉ በሚያስብል ደረጃ በዛፎች የተሸፈነ ነው።እዚህ ግቢ የደረሳችሁ freshoch 👌 ግቢው ውስጥ ያሉ አብዛኞቹ ህንፃዎች የመማሪያ ክፍሎች ሲሆኑ ዶርምተሪዎች ግን ኖርማል የምድር ቤቶች ናቸው ከሴቶቹ እና እንድ ህንፃ የወንዶች ሲቀር። ሽንት ቤቶች ብዙም እይነፉም ነገር ግን ከሌሎቹ ግቢዎች ይሻላል ። ሻወር🛀 እንደልብ ነው በተለይ  ጠዋት ወሳኝ ነው👌
      ✅ ኦዳያ(ሠመራ) ግቢ
በጣም ሠፊው ግቢ ሲሆን ከስፋቱ አንፃር ብዙ ዛፎች የሉትም። ከዶርም-ካፌ/ክፍል እንዲሁም ከዋናው በር ዶርም ያለው ርቀት በዛ ፀሀይ🌞🥵😡🥴 ለዚህ ፍቱን መድሀኒቱ ጥላ፤ ጥላ ወሳኝ ነው🌂 👌ግቢው ሙሉ በሙሉ ህንፃ ነው ። ከሙቀቱ ብዛት ግቢው የሚታወቀው ሠመራ በሚለለው መጠሪያ ነው።
          ✅ሆስፒታል ግቢ
ከDURH(dilla university referal hospital ) ውስጥ ይገኛል።ከስሙ እንደምንረዳው የጤና ትምህርቶች ብቻ ይሰጡበታል። ሻወሩ አሪፍ ነው ሽንት ቤቱን ግን አጠይቁኝ🥴
የአየር ሁኔታ
ዲላ ከ rift valley ከተሞች እንዷ እንደመሆኗ ትንሽ ሙቀት አለ።ነገር ግን አመቱን ሙሉ ዝናብ ነው ማለት ይቻላል። ስለዚህ ቀለል ያሉ ልብሶችን ብትይዙ መልካም ነው ባትይዙም ዲላ ልብስና ጫማ 👍እድሜ ለሞያሌ።የግቢዎችን የአየር ሁኔታ ስናይ
         ✅ዋናው ግቢ
ከሠመራና ከሆስፒታል ግቢ እንፃር ስናየው ከ ሆስፒታል ቀጥሎ ቀዝቃዛው ግቢ ነው።በዛፍ መሸፈኑ ነው እንጅ ከሰመራ ምንም አይለይም እንደውም ሁለቱን ግቢዎች የሚለያቸው ሚችሌ ወንዝ ነው።
        ✅  ኦዳያ (ሠመራ) ግቢ
ከላይ እንደፃፍኩላቹ የሙቀቱ ነገር 🥵 ውሀውም እንደዛውነው  ያለ እሳት የፈላ ነው።እንደ ዐይን 👁ብሌን የሚታዩ ዛፎች አሉት ወደ ዶርም አካባቢ ግን ጥቅጥቅ ያለ ዛፍ ነው ሙቀቱ ግን ያው ነው🤦‍♂️🙆‍♀️️
         ✅ሆስፒታል ግቢ
ይህ ግቢ ሰላም ያለው ግቢ ነው(ቴንሽን ስለሚበዛበት ግን ብዙ ተማሪዎች እይወዱትም ) ዛፍ የለዉም ነገር ግን ቀዝቃዛ ነው ። በጣምም ጠባብ ነው
የምግብ ሁኔታ
አብዛኛው ተማሪ  ምቾት ከማይሰጣቸው ነገሮች ውስጥ ካፌ ቀዳሚው ነው ብዙም አይመችም ስለዚህ ውድ freshochachn በሶ፣ኩኪስ፣ዳቦቆሎ፣ገብሥ ቆሎ፣ጭኮ(ለማታቁት ከ በሶ እና ከ ቅቤ የሚዘጋጅ ያበደ ምግብ ነው😋)እና ሌሎችንም ነገሮች መያዛቹን እንዳትረሱ ሚጥሚጣ እንኳን እዚሁ አለ።በሦስቱም ግቢ ተመሳሳይ ምግብ ነው የሚዘጋጀው
       🧆 ቁርስ 
ፍርፍር በዳቦ(ይህ ምግብ ሆስፒታ ግቢ አይታወቅም emergency food ነው ዳቦ ከለለ ማለት ነው)
ሩዝ በዳቦ😋(ሩዝ በ ዳቦ ውስጤ ነው)
መኮረኒ በዳቦ
ዳቦ በ 🧉ሻይ
ምሳ
ምሥር
ክክ
ሽሮ
ፓስታ
ራት
ምሥር
ክክ
ሽሮ
(.'.)(ዜርፎር 😋)በሳምንት ሶስት ቀን ማክሰኞ፣ሀሙስ፣እሁድ(በነዚህ ቀን ቀድማቹ ካፌ ካልተሰለፋችሁ ተበላቹ😁ዜርፎር ልትበሉ ገብታቹ ውሀ ብቻ ጠጥታችሁ ትወጣላቹ🥴)
ነገር ግን ዲላ የፍራፍሬ ሀገር እንደመሆኗ ማንኛውም ተማሪ ቀለል ባለ ዋጋ
🍌ሙዝ
🥑አቮካዶ
🍍አናናስ
በብዛት ግቢዎች በር ይሸጣሉ እነዚህን ገዝቶ  የካፌን ምግብ balance ማድረግ ይቻላል ከዚህ ውጭው  ደግሞ ግቢ ውሥጥም ውጭም  ያሉ ካፌዎች ስላሉ አሪፍ ነገር መጠቀም ይቻላል ግቢ ውስጥ ያሉት እስከ ሌሊቱ 6ሰዓት ይሠራሉ ያ ማለት ከ ችኬ መልስ 😋😍  ማታ 5 ሰዓት ውስጤ ነው😍።በተረፈ ከላይ ያልኳቹን ስንቅ እንዳትረሱ ሲሆን በሶ 10kg ዳቦ ቆሎ እና ገብስ ቆሎ 5kg  ያው ግማሹ የሲኒየር (የኛ) ነው 😋እናንተን በጉጉት እንድንጠብቃቹ ከሚያረጉን ነገሮች ዋናዎች ናቸው 😍
        ✅ዋናው ጊቢ
3-4ካፌዎች አሉ ግን ሁለቱ ብቻ ናቸው እስከ 6 ሰዓት የሚቆዩት።ውጭ መንቀሳቀስ የሚፈቀደው እስከ ከምሽቱ 1ሰዓት ነው። ዘቡላዎች ወጥ ባህሪ የላቸውም ስለዚህ በጊዜ መሰተሩ 👌 ላለመጨቃጨቅ።ከሰመራዎች ግን ይሻላሉ።
         ✅ ኦዳያ(ሠመራ)
በጣም ብዙ ካፌዎች አሉ አብዛኞቹ እስከ 6ሰዓት ይቆያሉ ነገር ግን አብዛኛው ተማሪ ውጭ ያሉ ካፌዎችን ተመራጭ ያደርጋሉ። ውጭ መንቀሳቀስ የሚፈቀደው እስከ ከምሽቱ 1ሰዓት ነው 1:01 ላይ እንኳን ዘቡላወች አይሰሟቹም ሀርድ ናቸው😡።
          ✅ሆስፒታል ግቢ ውስጥ ምንም አይነት ካፌ የለም😡🤔 ነገር ግን ውጭ እንደፈለጋቹ ነው።ግቢው የሰዓት ገደብ የለም 🙅‍♀️ እንደፈለጋቹ ነው።
ዲፓርትመንት
ዋናው የምትመጡበት ጉዳይ ትምህርት እንደመሆኑ ዩኒቨርስቲው  የሚሰጣቸውን ዲፓርትመንቶች ማወቅ ግድ ነው
ዋናው ግቢ
በውስጡ 3 schools አሉት
computational
Natural science
አፕላይድ ነገሮች
Agricultural
ለመቸከያ ስፔስ(ብዙም አይመከርም በተለይ  ለእህቶቻችን)
ሁለት ላይበራሪ አለው እስከ ሌሊቱ 8 ሰዓት ክፍት ነው(እንደልብ ቦታ ስለማይገኝ freshoch መደባደብ ነው የሚቀራቸው ኧረ እንደውም የተደባደበ አይጠፋም🤕 ዛቻማ normal ነው😂 ትንሽ ልናፈስ ብለቹ ከወጣችሁ ቁሞ ለሚያሠፍስፍ fresh ሰርግና ምላሹ ነው ስትመለሱ ራሱ አይስሰሟችሁም ስለዚ ስትወጡ ወንበራችሁን ይዛቹ ነው😂 )

    ይቀጥላል .......

Le dilla letemedebu adrsulgn

ለተማሪዎች ሼር አርጉላቸው👇👇
❤10
◦♻️ሀረማያ ዩንቨርሲቲ

መገኛ
፡ ሀረማያ :ከሀረር 17ኪ/ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ወይም ሀረር ከመግባታችን በፊት የ10ብር መንገድ ሲቀረን ያለች ከተማ ናት ሃረማያ ።🚍 ድሬም ቅርብ ናት የ150 ብር  መንገድ ብቻ

የአየር ሁኔታ፡ ብርዳማ ነው በተለይ ምሽት ላይ በጣም ይበርዳል ።ሀረማያ ሀሩር ነው ምናምን የሚባለውን አትስሙ በርግጥ አንዳንድ የሙቀት ወራት አሉ ግን ብዙውን ጊዜ ቅዝቃዜው ያመዝናል ፤ ስለዚህ ወፍራም ልብስ መያዝ ይኖርባቹሃል ።
ብርድ ልብስ ምናምን መሸከም ካልፈለጋቹህ ሀረማያ ልብስ እና አንዳንድ ሸቀጦች ርካሽ በመሆናቸው ግቢ ከገባቹህ በኋላ መሸመት ትችላላችሁ


በውስጡ ያሉ ግቢዎች ፡ አንድ ትልቅ ግቢ ሆኖ በውስጡ ግን ሶስት የተያያዙ subግብዎች አሉት በተጨማሪም ሀረር ከተማ ላይም ሌላ ግቢ አለው

Subግቢዎች

1 Main campus
👉All social departments
👉Computer science
👉Business
👉Economics
👉Natural computational science
👉Law
👉Teaching and
👉Agriculture....

2 Gandajay.........(Techno campus )
👉Engineering above second year
👉Food science

3 Station
👉Fresh Engineering students and
👉Veterinary

4 Hareri
👉Medicine
👉Health
👉Pharmacy

📶ግቢው ውስጥ አሪፍ የሚባሉት agri,law and computer science ናቸው ።


🍞🍚🍣ምግብ ቤቶች🍝🍔🍣
ምግብ ኢትዮ ውስጥ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ቀዳሚው ነው ማለት ይቻላል።


5⃣በሳምንት አምስት ቀን Therefore አለ

1⃣ ቀን ፓስታ

1⃣ ቀን ደግሞ መኮረኒ


     🔰ቁርስ

🍔ሳንድዊች
🍝አንድ ቀን ማርማራታ
🍣ሁለት ቀን ዳቦ በስጋ ፍርፍር
🍚አንድ ቀን በሩዝ
🍞አንድ ቀን አንድ 🍞 ዳቦ

  🔰Launch
Pasta....60-70birr
Frfr.........50-70birr
Shro........50_60birr
Tegabino...70_80birr
Buna.......15 birr
Shayi.......10 birr
Sandwich.....15-25birr



የጫት ነገር የማይሆንላቹህ አልያም ጫትን እንደ ምግብ የምትጠቀሙ ተማሪዎች ስለምትኖሩ ሌላ ግቢ ሄዳቹህ እሰጥ አገባ ውስጥ ከመግባትና ብሎም የዲሲፕሊን ኮሚቴ ጋር ከመጨቃጨቅ ሀረማያ ዩንቨርሲቲ ጎራ ብትሉ pis አለው። ( ጫት መቃም አይካበድም እንደ ህግ ግን ክልክል ነው )
አደራችሁን ከጫት ለመራቅ ሞክሩ ፤ በተለይ ለጫት አዲስ የሆንችሁና ምናልባትም ከነ ጭራሹ የማታውቁት ፍሬሽ ተማሪዎች ከተማው ላይ ባለው የጎላ የጫት ተጠቃሚነት እንዳትረበሹ ብሎም እንዳትሞክሩት ለማሳሰብ እወዳልሁ።

♻️[ Water ]

🚰የውሃ ችግር የለብንም ቢጠፋ ቢጠፋ እንኳ ካፌ አይጠፋም ስለዚህ ከካፌ መጠቀም ይቻላል ግን አይጠፋም
🚺
ለሴቶች በየ ብሎካችው ውሃ አለላቸው


ሀረማያ ዩንቨርሲቲ የሚመደብ  ሰው የብሄር ቀልድ ምናምን እንዳይቀልድ በጣም Serious ጉዳይ ነው ፤ ባሁኑ ሰዓት የትኛውም ግቢ የሚገባ ተማሪ ከዘረኝነት የፀዳ ካልሆነ  አዛ ነው። እኛ ጋር ግን ባስ ይላል   ብሄርተኝነት ምናምን ....F ነው ግሬዱ

በተረፈ  ዝርፊያና ሌላ አስጊ ሁኔታ የለም፤ለፍሬሽ ተማሪዎች ደግሞ ሰርቪስ ተዘጋጅቶ ይጠብቃቸዋል ።
❤11🤔2🙏2🤩1🆒1
#ሀዋሳ_ዩኒቨርሲቲ

አድራሻ  ❓

📚 ሃዋሳ ከአዲስ አበባ ቅርብ ርቀት ላይ የምትገኝ ውብ ከተማ የሲዳማ ክልል ፈርጥ ስትሆን የመናገሻ ከተማም ነች ።

2

የአየር ሁኔታ ❓

📚 ብዙ ግዝ በቀኑ ክፍለ ጊዜ ሞቃታማ ሁና አመሻሽ ላይ ደስ የሚል አየር አላት ፤ ከተማዋ በራሱ የሆነ ደስ የሚል ነገር አላት ።

የካንፓሶቹ ብዛት ❓

📚 በውስጡ ያሉ ግቢዎች ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በውስጡ ብዙ ግቢዎች ያሉ ሲሆን ከነሱም ውስጥም ጥቂቱን እንይ ፦


✅ Main campus
📍Location: Hawassa town (found on the enterance of the city)
       
   ዲፓርትመንት 💡

🎯 governance
🎯 Engineering
🎯 social others
🎯 art
🎯 architect
🎯 touris
🎯 hotel management
🎯  Sport
🎯 law
🎯 Computational science ..
               
✅ Techno campus ፦

📍Location:beside the main campus connected with the main campus though bridge ፦

                   ዲፓርትመንት

             -->  Engineering
             --> information system
            --> programming
            --> Enla,discrit,
           --> for engineering and computer science students until 3rd year wait here after that the student will be transfered to main campus..!

  ✅ Agri campus 
📍Location:  located on the middle o fthe city around piyasa

                 ዲፓርትመንት
              --> animal

✅ Yirgalem campus
📍Location: Yirgalem  town (near hawassa city..)

           ዲፓርትመንት

  🎯FB faculty of business -
  🎯 marketing management
🎯 logistic
🎯 Accounting
🎯 Cooperative
🎯  management
🎯economics 

✅ 5 Referral campus

📍Location:
located around the lake hawassa amazing view from the dorm nice sunset ...

              ዲፓርትመንት ፦

               --> Medicine
               --> HO
               --> nursing
               --> environmental health
               --> radiology
               --> ophtometry
               --> psychiatry

✅ ወንዶ ገነት  agriculture
📍 Location:wendo genet

   Dep'    --> plant...



ውሃ፤መብራት፤ WIFI❓

📚 መብራት እና ውሃ አይጠፋምኀለአንዳንድ ግቢዎች ለልሎች ይጠፋል ። አሪፍ የሆነ WIFI በግቢ የተለያየ ቦታ ላይ ይገኛል ።


ስለ ዮኒቨርሲቲው ❓

📚 ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሀገራችን ላይ አሉ ከሚባሉ ዩኒቨርሲቲዎች በትምህርት ጥራቱም ሆነ በግቢ ውበቱ አንደኛ ደረጃ ከሚባሉት ተርታ የሚመደብ ግቢ ነው።
ትምሮ በተወሰነ መልኩ ሊያጨናንቅ ይችላል ግን በግቢው ውበትና በከተማው ማብለጭለጭ
ካልተሸነፋቹህ የትምህርቱ ነገር ሙድ አለው።


የካፌ ምግብ ❓

📚በጣም ጥሩ የሚባል ምግብ ያቀርባሉ ..!፤ ከብዙ ዮኒቨርሲቲዎች ጥሩ ምግብ የሚሰጥ ካንፓስ ነው ።

ከካፌ ውጪ ያሉ የምግብ ቤቶች ዋጋ ❓

📚የምግብ ዋጋ በaverage ከ100-120 ብር ይደርሳል፥ የሁሉም ግቢዎች ዋጋ ይለያያል ።ቡና ምናምን 20-30 ብር
ለተማሪዎች fair በሆነ ዋጋ የሸጣሉ ትንሽ ቢወደድም ።

ሽንት ቤት ❓

📚 ጥሩ የሚባል ሽንት ቤት አለው ፤ ከብዙ ግቢዎች የሚሻል አይነት ባኞ አለው

➜ሀዋሳ ዮኒቨርስቲ 2019 መግባት የምትፈልጉ ለእናንተ ብቻ የተከፈተ Group join በማደረግ More info መጠየቅ ትችላላችሁ link👇👇👇👇
https://t.me/Hawassa_freshman2019

Any support👇👇
@Ethio_Supporter

@Ethio_unique_tutorial
❤12🤩1
#ድሬዳዋ university፦

አድራሻ ❓

📚 በድሬደዋ ከተማ የምትገኝ ፍቅር ነሆነች ዮኒቨርስቲ ነች ።

የአየር ሁኔታ ❓

📚 ሞቃታማ አዲስ ለምትመደቡ ተማሪዎች ፦ ወፍራም ብርድልብስ አያስፈልግም ፤ አንሶላ እና አልጋ ልብስ በቂ ነው፤ የመጀመሪያዎቹን አራት ወራት ትንሽ ሊበርድ ይችላል ፡ ግንቦት ላይ ምናምን ግን በጣም ሞቃት ነው።





የካንፓስ ብዛት ❓


📚 ድሬ አንድ ግቢ እና ሶስት መግቢያ መውጫ በር ያለው ሲሆን ሁሉም filed of study እዛው ነው የሚሰጠው ሌላ ቅርንጫፍ የለውም ።


🎯 በተጨማሪም ሶስት ላይብራሪ ያለ ሲሆን እነሱም፦
🏩 Tecno
🏩 Main
🏩 Fb/keranyo

✅ የሚሰጡ ፊልዶች በጥቂቱ ፦

🌐IOT
🌐FBE
🌐other social science
🌐Computitional science
🌐Fashion design
🌐Architecture
🌐 Engineering

🗻Engineering fileds
1 mechanical
2 electrical
3 chemical
4 civil
5 textile
6 cotm
7 food
8 industrial
9 survey

📚 arcthicure and Medicine መግባት ለምትፈልጉ መግቢያ ፈተናና የEntrance ውጤትም ይታያል።Software engineering የለም ።


📚 FB ( faculty of business) total social fileds House of medicine ፤ ሁሉንምhealth science ያጠቃልላሉ ።


📚 Architecture and Fashion design መግባት የምትፈልጉ የመግቢያ ፈተና ስላለው እዛያሉ ሲኒየር ተማሪዎችን ስለፈተናው ኢንፎ ብትጠይቁ አሪፍ ነው ። Marketing መግባት ለምትፈልጉ ደግሞ ድሬ ላይ ልብስ ጫማና ምግብ ቅናሽ ነው ።



የካፌ ምግብ ❓

📚 ድሮ አዛ ነበር አሁን ግን በጣም ምርጥዬ ሆኗል ፤ በቃ ኢትዮጵያ ውስጥ አሪፍ ከሚባሉት አንዱ ነው ።


ኀከካፌ ምግብ ውጪ ❓

📚ምግብ ቤቶች ብዙም ውድ አይባሉም አሪፍ ነው።
ምግብ ከግቢ ዉጪ ሁሉም የምግብ አይነት 80_90
ግቢ ዉስጥ 60_70
ቡና ዉጪ 15
ግቢ 10 birr ሻይ 5 birr
የካፌ ምግብ ከሌላዉ ግቢ አንፃር በጣም ደባሪ ነዉ


ዶርም እና ሽንት ቤት ❓


🎯 የዶርም እና የሽንትቤት ነገር አስደሳች አይደለም
ስለ ግቢው ሁኔታ ብዙ ደስ የሚል ነገር አትጠብቁ ፤
በጣም አስጠሊ ነው ።

የትምህረት ሁኔታ ❓

📚የትምህርት አሰጣጡ ምናምን በጣም አሪፍ ነው፥ ላይፉም ሙድ አለው ብቻ እናንተ ኑ ፤ የድሬ ሰዎችም ሲበዛ ፍቅር ናቸው ይህን ስትመጡ ትመሰክራላችሁ ።


የዕምነት ቦታ ❓

📚መስጂድ እና ቤተ-ክርስቲያንም በግቢው አቅራቢያ ስለሚገኝ ይበልጥ ትወዱታላቹህ ።


የረብሽ ጉዳይ ❓

📚 አልፎ አልፎ አንዳንድ አለመረጋጋቶች ይከሰታሉ ፤ በዚህ ጊዜ ተማሪዎች ወደ መስጂዶችና ውደ ቤተ- ክርስቲያናት በመሄድ ራሳቸውን ከአላስፈላጊ እንግልትና ከፌደራል ዱላ ይከላከላሉ ። በአመት አንዴም ሁለቴም ግርግር አይጠፋም ።

የዕቃ ስርቆት ❓

📚 ወደ ድሬ ስትመጡ መጀመሪያ ቀጥ ብላቹህ ወደ ግቢ ግቡ ፤ ፍሬሽ ተማሪዎች ሲመጡ በየመንገዱና በመናሀሪያ በተለይም በታክሲ(ባጃጅ) ላይ ምናምን የናንተን መፍዘዝ ready ሆነው የሚጠብቁ ብዙ ሌቦች አሉ። አሸዋ ገራሚ የዝርፊያ ቦታ ነው በተለይ ጫማ ምናምን ለመግዛት ስትሄዱ ፤ ሰባተኛ፡ ማታ ማታ walk ለማድረግ ስትፈልጉ ፤ seido፡ ቀን ላይ እነዚህን ሰፈሮች በጥንቃቄ ማለፍ ይኖርባቹሃል ። በተለይ ስልክን ገንዘባችሁን ተጠንቀቁ...!


ጫት እና ድሬ ❓

🌲 ድሬ ከተማ ላይ እንደምታቁት ጫት ከምግብ በላይ አንገብጋቢና በጣም ወሳኝ ምግብ ነው ሆኖም ግን ለግቢ ተማሪዎች ጫት ስለማይመከር ለቅምሻም ቢሆን እንዳትሞክሩ። እመኑኝ የድሬ ጫት ከጥፍጥናው የተነሳ ሱስ ያሲዛል(አሉ)....!

የውሃ እና መብራት ጉዳይ ❓

📚 መብረት አያሳስብም ጨቅ ነው ። ትንሽ ውሃና WIFI ነው እንጂ አዛ የሚያደርገው...
❤10🆒1
#የጥሪ_ማስታወቂያ
#Hawassa University

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የነባር መደበኛ ተማሪዎች የ2019 ትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚካሔደው መስከረም 21 እና 22/2019 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

ትምህርት መስከረም 25/2019 ዓ.ም ይጀመራል ተብሏል።
👍10❤3
#የማስታወቂያ_ሰዓት
Shaik shto: Turkey
#Brand New💯🔥
#imported💯🔥
#original 💯🔥🌟
Befelegachut kutr yewendm yesetm alen
On Tg/ @Mae2mn or phone /0902022165 ydewlu ,
POV: bebzat ykensal
# be 50 ml and 100 ml
Wuchi be 6000 atagegnutm 🫡🤫🤫
Endayameltachu💥🔥🔥🔥🔥🔥💯
#University_Review
እስቲ ስለ አርባምንጭ universityዛሬ🥰

💐👉አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 💐📚

አድራሻ ❓

📚Heaven of rift valley ይሏታል ፤ ብዙ መዝናኛዎች የያዘች ሀገር ናት ሁለት ሀይቆች አሏት Abaya and Chamo መገኛዋ ደቡብ ኢትዮጵያ ሲሆን ከአዲስ አበባ 515KM  ርቃ ትገኛለች ። ዩኒቨርስቲው ከተመሰረተ 34 አመታትን አስቆጥሯል ።

የአየር ሁኔታው ❓

📚 ሞቃት ነዉ እና ቀለል ያሉ ልብሶችን ብትይዙ ይመረጣል ፤ አርባምንጭ ሲባል ብዙዎቻቹህ አረንጓዴ ስለሆነች ብርዳማ ናት ምናምን እንዳትሉ ገራሚ ሙቀት ነው የሚጠብቃችሁ 🫣..!


ከካፌ ምግብ ውጪ ያሉ ቤቶች  ❓

📚 በጣም ምርጥዬ ክበብ አለ በተመጣጣኝ ዋጋ ቀላል ምግቦች ይሸጣሉ ፤ ለየአስተማሪዎችም የተሰራ መመገቢያ አለ ትንሽ ከሌሎቹ ቢወደድም ምርጥ የሆነ ምግብ ይሰራሉ ።


ፍራፍሬ እና አርባምንጭ  ❓

📚ከተማዋ ባጠቃላይ በፍራፍሬ የተሞላች ናት
ሙዝ 🍌🍌🍌
ማንጎ🍋🍋
አፕል 🍎🍒
አቮካዶ  🥑🥑   .....መገለጫዋ ናቸው  ።
ሙዝ ኪሎ=20 ብር🥺 አንዳንዴም 25 ብር🤗


ዮኒቨርስቲው በ6 campus ይከፈላል ።


1⃣የመጀመሪያው main campus ሲሆን
Arba minch መግቢያ ላይ ይገኛል
-Engineering🏤🏫🏨 እና
-Computer science 💻🖥
ብቻ ነው እዚህ ግቢ የሚሰጡት ፊልዶች ።



2⃣ ሌላኛው Chamo Campus ይባላል social science ፊልዶች ብቻ ነው እዚህ ግቢ ያሉት Like
-Law⚖⚖⚖⚖
-Business and Economics💵💴💰
-Accounting 📟📠
-political science 📰📓📔
የመሳሰሉት ይሰጣሉ ።


3⃣ሶስተኛው ግቢ ደሞ ነጭ ሳር  Or Health Campus ሲሆን ያው የጤና ፊልዶች እዛ ነው ያሉት ፦

- Medicine
-Other Health
-HO

4⃣ Abaya campus

📚 both Natural and social science Computational የደረሳቸው እዚ ነው የሚማሩት ።


5⃣አምስተኛው ደግሞ Kulfo campus ይባላል የ Agriculture ተማሪዎች campus ነዉ ።

6⃣ስድስተኛው Sawula campus ይባላል ከአርባ ምንጭ ከተማ የ4 ሰዐት ያክል መንገድ ነው ጎፋ ዞን ሳውላ ሚባል ከተማ ላይ ነው ሚገኘው ።


ከnatural Engineering Like  ፦

-Half Civil engineering🏬🏗🏢
-Hole Food engineering 🌽🍩🍪
-Hole Automotive engineering🚝✈️🛩
-Hole Electro Mechnical


በengineering ስር የሚሠጡ ፊልዶች ፦

-Civil engineering 🏠🏭🏗
-software engineering 💻📱🖨
-Architecture engineering 🗺🏛🏩
-Electrical and computer engineering ⚓️
-Mechanical engineering ⛓⚙🛠🔩
_ metal and production engineering
- metrology and hydrology
- electromechanical
_food engineering
-Hydroelectric engineering 🌊🌫
-Environmental engineering⛰🛣
-Water supply engineering⛱🏝

📚 ግቢው በhydrolic ከምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ቀዳሚ ነው።

የካፌ ምግብ ❓

📚 ምግቡ በጣም ደስ ይላል፤ ጥሩ ነው በተለይ ምሳ እና ራት ምንም አይልም ቁርስ ግን ትንሽ ግን ብሆንም አሪፍ ነው ...ግን ከብዙ ግቢዎች አንፃር  በጣም ጥሩ ነው  ።


የዕቃ ስርቆት ጉዳይ ❓

📚 ትንሽ ያስቸግራል ከተማ ምናምን ለመዝናናትና ለሸመታ በምትንቀሳቀሱበት ጊዜ መጠንቀቅ ይኖርባቹሃል ::


ሽንት ቤት ❓

📚 ምንም አይልም በየቀኑ ስለሚፀዳ ከሌሎች ግቢዎች ቢሻልም ምርጥ የሚባል  አይደለም ።

ውሃ ፤ መብራት WIFI ❓

📚 ውሃ በየቀኑ ይለቀቃል ችግር የለም ፤ መብራትም አያሳስብም ፤ WIFI በቸሻለ ደረጃ አለ አንዳንድ ዶርሞች ውስጥ ድረስ ይሰራል ።


@Ethio_Unique_Tutorial
@Ethio_Unique_Tutorial
❤14🤩1