TIKVAH-ETHIO
626 subscribers
661 photos
27 videos
7 files
74 links
Download Telegram
#SNNPRS

በደቡብ ክልል እስካሁን ወደ ትምህርት ቤት ያልሄዱ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ተማሪዎች አሉ።

እነዚህን ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ የመመለስ ንቅናቄ እየተካሄደ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

ከ9 ወራት በኋላ የገፅ ለገፅ ትምህርት ቢጀመርም ተማሪዎች የሚጠበቀውን ያህል በትምህርት ገበታቸው ላይ አልተገኙም ብሏል ቢሮው።

አሁን እየተካሄደ ያለው ንቅናቄ ቤት ለቤት በመንቀሳቀስ ተማሪዎች ከሰኞ ጀምሮ ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ለማድረግ ያለመ ነው።

* በደቡብ ክልል በዘንድሮው የትምህርት ዘመን 4 ሚሊዮን 200 ሺህ ተማሪዎችን ለመቀበል ከታቀደው ውስጥ 77 ነጥብ 3 በመቶ ተፈፅሟል። ቀሪውን በንቅናቄው ለማሳካት እየተሰራ ነው ተብሏል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#SNNPRS

በደቡብ ክልል መሳሪያ የታጠቀ ግለሰብ በ5 ቀናት ውስጥ እንዲያስመዘግብ ጥሪ ቀረበ።

ይህ ጥሪ የተላለፈው በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ትናንት ያካሔዱትን ውይይት መድረክ ተከትሎ ነው።

በዚህም መሰረት ማንኛውም የጦር መሳሪያ የታጠቀ አካል ከዛሬ ከጥቅምት 26 ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት በአካባቢው በሚገኙ የፖሊስ ጣቢያዎች ቀርቦ ማስመዝገብ ይኖርበታል ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ ማንኛውም #መታወቂያ የሚሰጥ አካል አዲስ መታወቂያ መስጠት አልያም የመታወቂያ እድሳት ማካሔድ ክልክል መሆኑ ተገልጿል።

አስቸጋሪ ሁኔታ ቢፈጠር እና መታወቂያ ማግኘት ግዴታ ሆኖ ከተገኘ ግን የክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ መምሪያ እዝ አውቆት ውሳኔ ሊሰጥበት ይችላል ተብሏል።

መረጃው ከደቡብ ክልል ኮሚኒኬሽን ያገኘነው ነው።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA