TIKVAH-ETHIO
702 subscribers
661 photos
27 videos
7 files
74 links
Download Telegram
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ላይ ዘጠኝ የምርጫ ጣቢያዎች ስልጠና የተሰጣቸው የምርጫ አስፈጻሚዎች በጣቢያው ሳይገኙ በመቅረታቸው ምርጫው በጣቢያዎቹ ዘግይቶ መጀመሩን ቦርዱ ገልጿል።

የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርትኳን ሚዴቅሳ እነዚህ ምርጫ ጣቢያዎች ላይ አሰልጣኝ የነበሩ ብቁ 27 አስፈጻሚዎች መተካታቸውንና ምርጫው መጀመሩን ገልፀዋል።

በተጨማሪም በአዲስ አበባ አንድ ምርጫ ጣቢያ የመራጮች መዝገብ መጥፋቱንም አሳውቀዋል።

ጉዳዩ እንደሚጣራ በመጥቀስ አሁን ላይ መዝገብ እና ምርጫ አስፈጻሚ ተልኮ በጣቢያው የተመዘገቡ ካርዳቸው ከጣቢያው መወሰዱ የተረጋገጠ መራጮች እየተመዘገቡ የምርጫ ሂደታቸውን እያከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል።

#ዘግይተው_የተከፈቱ የምርጫ ጣቢያዎችን አስመልክቶ ከጋዜጠኞች ጥያቄ የቀረበላቸው የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርትኳን ሂደቱን ተመልክቶ ቦርዱ በተለየ ሁኔታ ተጨማሪ ጊዜ ሊሰጥ እንደሚችል ገልጸዋል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA