TIKVAH-ETHIO
708 subscribers
661 photos
27 videos
7 files
74 links
Download Telegram
Breaking....

በምዕራብ ኦሮምያ ለወራት ተዘግቶ የነበረው የኢንተርኔት አገልግሎት ዛሬ እንደሚከፈት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ!

የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ፥ በአካባቢዎቹ የቴሌኮም አገልግሎት ዳግም ወደ ስራ እንዲመለስ የክልሉ መንግስት እና የፌደራል መንግስት በጋራ ሲሰሩት የነበረው ስራ መጠናቀቁን አስታውቀዋል።

#Share
@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
ጠቃሚ መልዕክት!

🧼 እጃችሁን በሳሙና እና በውሃ በደንብ ታጠቡ

👋🏾 አትጨባበጡ/አትሳሳሙ

🙅🏽‍♀️ ማህበራዊ መስተጋብርን በጣም ቀንሱ!

አስገዳጅ ካልሆነ በቀር ከቤት አትውጡ

☎️ ትኩሳት ፣ ሳል እና ትንፋሽ ማጠር...ምልክት ከታየባችሁ በቅድሚያ ከዚህ በታች ባሉት ነፃ የስልክ መስመሮች ይደውሉ ፦

አዲስ አበባ - 8335 /952 ፣ ትግራይ ክልል - 6244 ፣ አፋር ክልል - 6220 ፣አማራ ክልል - 6981 ፣ ኦሮሚያ ክልል - 6955 ፣ ሱማሌ ክልል - 6599 ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል - 6016፣ ደቡብ ክልል - 6929 ፣ ሀረሪ ክልል - 6864 ፣ ጋምቤላ ክልል - 6184፣ ድሬዳዋ ከተማ - 6407

#SHARE #ሼር

#HaymanotGirma
@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
😷 Mask (ጭምብል) #መቼና #እንዴት እንጠቀመው ....?

#መቼ እንጠቀመው ....

🗣--- ጤነኛ ከሆንሽ ማስክ የሚያስፈልግሽ #በ2019_ኖቭል_ኮሮና_ቫይረስ የተጠቃን ግለሰብ በማስታምሚበት ወቅት ...

🗣--- የሚያስልህና የሚያስነጥስ ከሆነ ማስክ ተጠቀም

🗣--- ማስክ(ጭምብል) ጠቃሚ የሚሆነው እጅን በአልኮል እና በሳሙና ደጋግመው እየታጠቡ ሲጠቀሙት ነው።

🗣--- ማስክ ስታጠልቂ እንዴት መጠቀምና እንዴት በአግባቡ ማስወገድ እንዳለብሽ ማወቅ ግድ ይልሻል ...

🗣--- ማስኩን ከመጠቀማችን በፊት እጆቻችንን በአልኮል ወይንም ሳሙናና ውሃ በሚገባ ማፅዳት ...

🗣--- በማስኩ አፍና አፍንጫችን መሸፈን
አለባቸው ...
#ልብ_በሉ በፊታችሁና በማስኩ መካከል(gap) ክፍተት መኖር የለበትም !

🗣--- አንዴ ማስኩን ካጠለቅክ በኋላ መነካካት አቁም!

🗣--- መጣል ባለበት ጊዜ ማስኩን በአዲስ ቀይሪ እና ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚያገለግሉትን ደግመሽ አትጠቀሚ።
(በተለይ ለህክምና ባለሞያዎች)

🗣--- ማስኩን ለማውለቅ፣ ከጆሮህ በኩል ያለውን በማውለቅ ጀምር (የማስኩን የፊት ክፍል እንዳትነካ) እንዳወጣህ ወዲያውኑ መሳቢያም ይሁን
መዝጊያ ያለው ነገር ውስጥ አስቀምጠው።

እባካችሁን ...
ይህን መረጃ #send እና #share በማድረግ #ወገኖቻችንን እንታደግ።
Join👍
@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
'ኦ/O' የደም አይነት እጥረት አጋጥሟል ፦

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የደም ባንክ አገልግሎት በኦ የደም አይነት እጥረት እንዳጋጠመው አስታውቋል።

አገልግሎቱ አሁን ላይ ኦ የደም አይነት በክምችቱ የሚገኘው ለሰባት ቀናት ብቻ መሆኑን ነው የገለፀው።

በመሆኑም ኦ/O የደም አይነት ያላቸው ዜጎች በአቅራቢያቸው ወደ ሚገኝ የደም ባንክ አገልግሎት ቅርንጫፍ በመሄድ ደም እንዲሰጡና ህይወት እንዲያድኑ ጥሪ ቀርቧል።

#Share #ሼር

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እንዳትደናገጡ ...

ዛሬ ምሽት ከ3 ሰዓት እስከ 4:30 በአድዋ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት ለግንባታ ስራ ሲባል "ድማሚት" ስለሚፈነዳ ህብረተሰቡ በሁኔታው እንዳይደናገጥ አዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።

አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው አድዋ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት ስፍራ ላይ ነው ድማሚቱ የሚፈነዳው፡፡

በመሆኑም ሕብረተሰቡ በሁኔታው እንዳይደናገጥ ኮሚሽኑ አሳስቧል።

#ሼር #Share

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#BREAKING

በሁሉም ምርጫ ጣቢያ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ እስከምሽቱ 3:00 ሰዓት ድረስ ይቀጥላል።

#Share #ሼር

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#BREAKING

እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ድምፅ መስጠት ይቻላል።

በመላው ሀገሪቱ ውስጥ ምርጫ እየተካሄደ ባለባቸው ጣቢያዎች ሁሉ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ እስከምሽቱ 3:00 ሰዓት ድረስ እንደሚቀጥል ምርጫ ቦርድ አሳውቋል።

#Share #ሼር

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ተጨማሪ አዳዲስ የደንብ ልብሶችን ስራ ላይ ማዋሉን ዛሬ አሳውቋል።

ነባሩን የደንብ ልብስ መጠቀም ማቆሙን ተቋሙ ገልጿል፡፡

ከዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ አዳዲሶቹ የደንብ አልባሳትን ብቻ መጠቀም እንደሚገባ እና ነባሩ የደንብ ልብስ ሙሉ በሙሉ መቀየሩ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ አሮጌውን የደንብ ልብስ ለብሶ የተገኘ አመራር እና አባል ላይ ጠንከር ያለ የዲስፕሊን እርምጃ ይወሰድበታል ተብሏል።

ህብረተሰቡ እና ባለድርሻ አካላት አሮጌው የደንብ ልብስ ሙሉ በሙሉ በአዳዲሶቹ መቀየሩን ተገንዝበው አሮጌውን የደንብ ልብስ የለበሰ የፖሊስ አባል ሲያጋጥማቸው መረጃ በመስጠት እንዲተባበሩ ጥሪ ቀርቧል።

በተጨማሪም የአዲስ አበባ ፖሊስ ስራ ላይ ካዋላቸው አዳዲስ የደንብ አልባሳት ጋር ወይም ከሌሎች የፀጥታ አካላት የደንብ ልብስ ጋር ተመሳሳይ ወይም ተቀራራቢ ዩኒፎርም መጠቀም ክልክል መሆኑ በህግ የተደገገ ስለሆነ ከአ/አ ፖሊስ የደንብ ልብስ ጋር ተመሳሳይ ዩኒፎርም የሚጠቀሙ አካላት ማስተካከያ እንዲያደርጉ ተቋሙ መልዕክቱን አስተላልፏል።

#AddisAbabaPolice

#Share #ሼር

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#ETHIOPIA

ማንኛውም የፀጥታ ችግር እንቅስቃሴ ሲመለከቱ ወይም ደግሞ ጥቆማ ለመስጠት ከፈለጉ ከላይ በተቀመጡት የስልክ መስመሮች ፈጥነው እንዲደውሉ የፌዴራል ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።

#ሼር #Share

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA