TIKVAH-ETHIO
702 subscribers
661 photos
27 videos
7 files
74 links
Download Telegram
#BREAKING

ኮሮና ቫይረስ የታላቁን አሰልጣኝ ወላጅ እናት ህልፈተ ህይወት አሰምቷል !

በስኬት ከማይታሙት አሰልጣኞች ተርታ የሚመደበው የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኞች ፔፕ ጋርድዮላ ወላጅ እናት ህይወት ማለፉ ተገልጿል ::

የፔፕ ጋርድዮላ እናት ዶሎሬስ ሳላ ካሪዮ በ #COVID-19 ቫይረስ በ 82 ዓመታቸው በማናሬሳ ባርሴሎና ህይወታቸው እንዳለፈ ተነግሯል ፡፡
#BREAKING

ባለፉት 24 ሰዓት በጅቡቲ 658 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 114 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 846 ደርሷል።

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓት 26 ተጨማሪ ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 102 ደርሷል።
#BREAKING

ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ተቀንሰው የነበሩ መኮንኖች ወደ መከላከያ ሠራዊቱ እንዲመለሱ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ትእዛዝ ተሰጥቷቸዋል።

ወደ ሰራዊቱ እንዲመለሱ ትዕዛዛ የተሰጣቸው ፦

1. ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ
2. ሌ/ጄኔራል ዬሐንስ ገ/መስቀል
3. ሌ/ጄኔራል አበባው ታደሰ ናቸው።

#PMOEthiopia
@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#BREAKING

CNN ጆ ባይደን የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ሆነው መመረጣቸውን ይፋ አድርጓል።

ባይደን በፔንሲልቬኒያ ግዛት ማሸነፋቸው ተገልጿል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#BREAKING

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ድምጽ መስጫ ቀን ግንቦት 28 እንዲሆን ሃሳብ አቅርቧል።

የአዲስ አበባ ከተማ እና የድሬደዋ ከተማ መስተዳድር የድምጽ መስጫ ቀን ሰኔ 5 መሆኑን አስታውቋል።

ቦርዱ ዝርዝር የጊዜ ሰሌዳውን ይፋ አድርጓል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#Breaking

ከ50 በላይ መንገደኞችን የጫነ የኢንዶኔዢያ የመንገደኞች አውሮፕላን (Sriwijaya Air Boeing 737) ጠፋ።

አውሮፕላኑ የተነሳው ከጃካርታ ሲሆን እስካሁን የደረሰበት አልታወቀም።

የኢንዶኔዢያ ትራንስፖርት ሚኒስትር ከጃካርታ ከተነሳ በኃላ በደቂቃዎች ውስጥ ደብዛው የጠፋውን አውሮፕላን የመፈለጉ ስራ እየተሰራ መሆኑን አሳውቀዋል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#BREAKING

የቻድ ፕሬዜዳንት ተገደሉ።

ላለፉት 30 ዓመታት ቻድን የመሩት ፕሬዝደንት ኢድሪስ ዴቢ በአማጺ ኃይሎች መገደላቸውን የሀገሪቱ መከላከያ ማስታወቁን አል ዓይን ዘግቧል።

ፕሬዝደንቱ የመንግስት ኃይሎች ከአማጺያን ጋር እያደረጉ ባለው ጦርነት ተመተው መገደላቸውን ነው መከላከያ ሠራዊቱ በሀገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ይፋ ያደረገው፡፡

ፕሬዝደንቱ በውጊያው ከቆሰሉ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ነው ህይወታቸው ያለፈው፡፡

ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ ፣ በቻድ ምርጫ እስካሁን ከተቆጠረው 80 በመቶ ድምጽ ከ79 በመቶ የሚሆነውን በማግኘት ማሸነፋቸው በዛሬው ዕለት ይፋ ሆኖ ነበር፡፡

የቻድ አማጺያን በተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ዋና ከተማዋ ኒጃሚና ከትናንት ጀምሮ በመቅረብ ላይ እንደነበሩ የሚገልጹ መረጃዎች ወጥተው ነበር፡፡

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#BREAKING

6ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በተያዘለት ቀን እንደማይካሄድ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

ቦርዱ ይህ ያሳወቀው ዛሬ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየመከረ ባለበት መድረክ ላይ ነው።

ምርጫው ግንቦት 28 ይካሄዳል ተብሎ ነበር።

የምርጫ ካርድ ምዝገባውና ሌሎች ስራዎች በተያዘላቸው ቀናት ባለመጠናቀቃቸው ምርጫው በተያዘለት ቀን አይካሄድም ተብሏል።

ምርጫ ቦርድ ድምጽ መስጫው ቀን በ3 ሳምንት እንዲራዘም ፓርቲዎችን መጠየቁን አል ዓይን ዘግቧል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#BREAKING

በሁሉም ምርጫ ጣቢያ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ እስከምሽቱ 3:00 ሰዓት ድረስ ይቀጥላል።

#Share #ሼር

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA
#BREAKING

እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ድምፅ መስጠት ይቻላል።

በመላው ሀገሪቱ ውስጥ ምርጫ እየተካሄደ ባለባቸው ጣቢያዎች ሁሉ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ እስከምሽቱ 3:00 ሰዓት ድረስ እንደሚቀጥል ምርጫ ቦርድ አሳውቋል።

#Share #ሼር

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA