TIKVAH-ETHIO
626 subscribers
661 photos
27 videos
7 files
74 links
Download Telegram
#የመንግስት_ማስጠንቀቂያ

የኢትዮጵያ መንግስት ሀገርን ለማፍረስ የተጠመዱ ወገኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠነቀቀ።

ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ያወጣው የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሀገርን ለማፍረስ የተጠመዱ ወገኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሲል አስጠንቅቋል።

መንግስት በመግለጫው "የሽብር ቡድኑ ማሽኖችና በሽርክና የሚሰሩ ሚዲያዎች የሽብር ወሬ እያሰራጩ ናቸው" ብሏል። ቁልፍ ኢላማቸው ደግሞ በአመራሩና ፣ በህዝቡና በወገን ጦር መካከል ጥርጣሬ እንዲፈጠር ፍርሃትም እንዲነግስ ማሸበር ነው ሲል ገልጿል።

በተለያየ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ ያሉ ተላላኪዎቻቸው የፀጥታ ችግር እንዳለ በማስመሰል የግል ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ የማግባባት ስራ እየሰሩ ይገኛሉም ብሏል።

በህዝቡና በወገኑ ጦር ውስጥ ጥርጣሪዎችን ለመፍጠር የመንግስት ባለስልጣናት ቪዛ እየጠየቁ ነው በሚል የውሸት ፕሮፓጋንዳ እየነዙ ናቸውም ሲል ገልጿል።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን በመግለጫው ከዲፕሎማሲ መርህ ውጪ የአንዳንድ ሃገር ኤምባሲዎች አዲስ አበባ እንደ ተከበበች በማስመሰልና ያሰቡት ውጥን እንዲሳካ በኤምባሲያቸው የሚሰሩ ዜጎቻቸው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ እያሳሰቡ ይገኛሉ ብሏል።

በእንዲህ አይነት መንገድ ሀገርን ለማፍረስ የተጠመዱ ወገኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ያሳሰበው መንግስት በሀገር ጉዳይ ቀልድ የለምና ከድርጊቱ ባልተቆጠቡት ላይ የማያዳግም ርምጃ ይወሰዳል ሲል አስጠንቅቋል።

* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@ETHIO_TIKVHA
@ETHIO_TIKVHA