Ethio telecom
332K subscribers
6.96K photos
122 videos
121 files
2.33K links
The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Download Telegram
የዲጂታል ኢትዮጵያን ራዕይ እውን በማድረጉ ጉዞ የአዳማ ሳንይስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲን የመማር ማስተማር ሂደት በአይ.ሲ.ቲ ቴክኖሎጂ በመደገፍ እና የአገልግሎት ክፍያዎችን በቴሌብር የዲጂታል ክፍያ ስርዓት አማካኝነት መፈጸም የሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከአዳማ ዩኒቨርስቲ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ማድረጋችንን ተከትሎ ዋና ሥራ አስፈጻሚያችንን ጨምሮ የኩባንያችን ከፍተኛ ኃላፊዎች ዩኒቨርስቲውን የጎበኙ ሲሆን በቀጣይ በጋራ መስራት የሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል።

#ዲጂታልኢትዮጵያን ዕውን በማድረግ ላይ
በአዳማ ቆይታችን ዋና ሥራ አስፈጻሚያችንን ጨምሮ የኩባንያችን ከፍተኛ ኃላፊዎች በኦ.ቢ.ኤን ቴሌቪዥን ጣቢያ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን ከኮኔክቲቪቲ አገልግሎት ባሻገር የቴሌቪዥን ጣቢያው እንደ ቴሌክላውድ ያሉ የዲጂታል ሶሉሽኖችን ተጠቅሞ አገልግሎቱን ይበልጥ ማሻሻል ይችል ዘንድ በቀጣይ በጋራ መስራት የሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል።

#ዲጂታልኢትዮጵያን ዕውን በማድረግ ላይ
ትናንት በ5G አዳማ ልዩ የመዝናኛ ዝግጅት ቆንጆ ቆይታ ነበርን፤ ዛሬም ነዋይ ደበበ እና ሄለን በርሄን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ እና ተወዳጅ ሙዚቀኞች የ5G ኔትወርክ መጀመርን አስመልክቶ እናንተን ሊያዝናኑ ይገኛሉ፤ ከ11:30 ጀምሮ በአዳማ አበበ ቢቂላ ስቴዲየም እንገናኝ።

መግቢያ በነፃ!
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የ5G ኔትወርክ በአዳማ ከተማ መጀመር ብስራት ከአዳማዎች ጋር ምርጥ ቆይታችን