Ethio telecom
364K subscribers
6.77K photos
121 videos
120 files
2.24K links
The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Download Telegram
ለማንኛውም ክፍያ፤ ምርጫዎ #ቴሌብር ይሁን!
በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 1500 ሜትር ውድድር አትሌታችን ጉዳፍ ፀጋይ እና በወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል አትሌታችን ለሜቻ ግርማ ተጨማሪ የብር ሜዳሊያ ለሀገራችን በማስገኘታቸው ደስ ብሎናል፤ እንኳን ደስ አላችሁ!
🇪🇹 ሁሌም እንኮራባችኋለን 🇪🇹
ዓመታዊው ግብር ፤ በገላግሌው ቴሌብር!

የአዲስ አበባ ደረጃ ሐ ግብር ክፍያን ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ በሆነው ቴሌብር መጀመሩን የኩባንያችን ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ዋና ሃላፊ አቶ ሙሉጌታ ተፈራ ጋር የስምምነት ፊርማ ያኖሩ ሲሆን ከተቋማቱ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክ/ከ ወረዳ 10 እንዲሁም ቦሌ ክ/ከ ወረዳ 03 የግብር መክፈያ ጣቢያዎች በመገኘት አፈጻጸሙን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
በቴሌብር የግብር ክፍያ ሥርዓት ከ300 ሺህ በላይ ግብር ከፋዮች ተጠቃሚ የሚሆኑ ሲሆን፤ የክፍያ ሥርዓቱ ከጀመረበት ከሐምሌ 1/2014 ዓ.ም ጀምሮ 679 ግብር ከፋዮች 4 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ክፍያ ፈጽመዋል፡፡

ግብር ከፋዮች በሞባይል ስልካቸው ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በ7075 በአጭር የጽሁፍ መልዕክት በሚደርሳቸው የክፍያ ማዘዣ ቁጥር በመጠቀም ክፍያቸውን በቀላሉ ካሉበት ሆነው በቴሌብር መፈፀም የሚችሉ ሲሆን የክፍያ ማረጋገጫ መልዕክት ከ7075 እንዲሁም ከ127 የሚደርሳቸው ይሆናል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ bit.ly/3RD7Dvg
ግብር በቴሌብር!
ግብርዎን ካሉበት ሆነው በምቾት በቴሌብር ይክፈሉ!
የአዲስ አበባ ደረጃ ሐ ግብር ከፋዮች ከ7075 በአጭር የጽሁፍ መልዕክት የደረሳችሁን የክፍያ ማዘዣ ቁጥር በመጠቀም እና ለግብር ክፍያ አስፈላጊ የሆነውን የክፍያ መጠን ከቴሌብር ጋር ትስስር ባደረጉ ባንኮች፣ በአቅራቢያችሁ በሚገኙ ኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከላት ወይም በቴሌብር ህጋዊ ወኪሎች በኩል ተቀማጭ በማድረግ የግብር ክፍያችሁን በቀላሉ
በቴሌብር መተግበሪያ ወይም *127# በመደወል ስትከፍሉ የማረጋገጫ መልዕክትም በአጭር የጽሁፍ መልዕክት ይላክላችኋል፡፡
ዓመታዊ ግብር፤ በገላግሌው ቴሌብር!
የአ.አ የደረጃ ሐ ግብር ክፍያን በቴሌብር ይፋዊ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር
ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን በማድረግ ላይ

https://youtu.be/m4uFRHkgyDQ
ውድ ደንበኞቻችን
በኩባንያችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ስም በተከፈቱ ሀሰተኛ የማሕበራዊ ሚዲያ አካውንቶች የሚተላለፉ የተሳሳቱ መልዕክቶች ዋና ሥራ አስፈጻሚያችንን እንደማይወክሉና በሃሰተኛ ገፆቹ ላይ አስፈላጊው ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ከሚመለከታቸው ኩባንያዎች ጋር እየሰራን መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በሐምሌ ዶፍ ዝናብ ስራዎን ጥለው ሳይወጡ፤
ግዴታዎን በቴሌብር ይወጡ!
https://www.youtube.com/watch?v=J5pijXo9FBQ
If you love texting with your friends and family, then don’t think much and Buy our cheapest SMS package.
በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አትሌቶቻችን ተጨማሪ የብር እና የነሃስ ሜዳሊያ ለሀገራችን በማስገኘታቸው ደስ ብሎናል፤ እንኳን ደስ አላችሁ!
ከቴሌብር ወደ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ገንዘብ የማስተላለፍ አገልግሎት መጀመራችንን ስንገልፅ በደስታ ነው፡፡
ለቴሌብር አገልግሎቶች መተግበሪያውን ወይም *127# ይጠቀሙ!