Ethio telecom
307K subscribers
8.12K photos
163 videos
140 files
2.82K links
We Simplify lives & accelerate Ethiopia’s digital transformation & beyond via delivering reliable communications, innovative digital solutions & seamless financial services that empower communities, businesses & nations.

https://t.me/EthiotelecomChatBot
Download Telegram
ኢትዮ ቴሌኮም እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በኤክስፖርት የጥራት ደረጃ የተዘጋጁ የኢንዱስትሪ ምርቶችን በ'ዘመን ገበያ' ለሀገር ውስጥ ሸማቾች ለማቅረብ የሚያስችል ስምምነት ፈጸሙ።

ይህም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚገኙ አምራቾች ለዓለም አቀፍ ገበያ የሚያቀርቧቸውን የኤክስፖርት ደረጃቸውን የጠበቁ ምርቶች በቴሌብር 'ዘመን ገበያ' አማካኝነት ለመጀመሪያ ጊዜ ለሀገር ውስጥ ሸማቾች እንዲያቀርቡ የሚያስችላቸውን ታሪካዊ የመግባቢያ ስምምነት ነው።

ይህ ስምምነት በከፍተኛ የጥራት ደረጃ የተመረቱ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳትን፣ የቆዳና የቆዳ ውጤቶችን፣ የአግሮ-ፕሮሰሲንግ ምርቶችን፣ የኤሌክትሮኒክስና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን፣ የመድኃኒትና የሕክምና ግብዓቶችን እንዲሁም ሌሎች የማኑፋክቸሪንግ ምርቶችን በዘመን ገበያ ላይ ለግብይት የሚያቀርብ ነው።

የግብይት ሂደቱም በመረጃ በተደገፈ ዘመናዊ የክምችትና የሥርጭት አሰራር የሚከናወን በመሆኑ፣ የአምራቾችን የሎጂስቲክስና የኦፕሬሽን ወጪ በእጅጉ በመቀነስ ለሸማቾች ጥራት ያላቸው ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲደርሱ ለማድረግ ያስችላል።

ከዚህም ባሻገር አጋርነቱ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚገኙ አምራቾችን የዲጂታል ክህሎት አቅም በመገንባት፣ ምርቶቻቸውን በሰፊው በማስተዋወቅና አስተማማኝ የገበያ ትስስር በመፍጠር አጠቃላይ የሀገራችንን የንግድ ሥነ ምህዳር ወደ ዘመናዊና ተወዳዳሪ ደረጃ ለማሸጋገር የማይተካ ሚና ይጫወታል።

ይህ ኩባንያችን በነደፈው ስትራቴጂ መሠረት፣ የአምራች ኢንዱስትሪውን ዲጂታላይዝ በማድረግና የንግድ እንቅስቃሴውን በማዘመን በንግዱ ሥነ ምህዳር አስተማማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት በማቅረብ የዲጂታል ኢትዮጵያን ጉዞ ለማፋጠን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።

ተጨማሪ፡ https://bit.ly/48SdQgc
80👍30👏6🙏4👌3
የገና ስጦታ ለማን መስጠት ይሻሉ?

ለቤተሰብ፣ ለጓደኛ ወይስ ለፍቅረኛ?
ስጦታ በዘመኔ፣ በቅርብ ቀን በዘመን ገበያ ይጠብቁ!

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/ZemenGebeya1
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/zemengebeya.et/
ቴሌግራም፡ https://t.me/zemengebeya_et
ትዊተር፡ https://x.com/ZemenGebeya
ሊንክዲን፡ https://www.linkedin.com/company/zemengebeya

ዘመን ገበያ - የዲጂታል ኢትዮጵያ የግብይት መዳረሻ!

#ZemenGEBEYA
#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSuperApp #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
👍3121🥰2👏2🤔1😢1👀1
በኪዶፒያ (Kidopia) ለልጅዎ አስተማሪ እና አስደሳች ጊዜ ይስጡ!!

ከ100 በላይ እንደ ሚኪማውስ (Mickey Mouse)፣ ስመርፍስ (Smurfs)፣ ስኩፒዶ (Scoopy-Doo)፣ ስፖንጅ ባብ (SpongeBob)፣ ባግስ ባኒ (Bugs Bunny) እና ሌሎች ታዋቂ ባህሪያት ያካተቱ አስተማሪ እና አዝናኝ ጌሞችን ይዞ ቀርቧል፡፡

ለመመዝገብ ለዕለታዊ A፣ ለሳምንታዊ B፣ ለወርኃዊ C ብለው ወደ 8117 ይላኩ!

👉 3 ቀን በነጻ፤ ከወደዱት ለዕለታዊ 3 ብር፣ ለሳምንታዊ 15 ብር፣ ለወርኃዊ 75 ብር ብቻ ይከፍላሉ!

🛑 ለማቋረጥ ሲፈልጉ Stop A፣ Stop B፣ Stop C ብለው 8117 ይላኩ፡፡

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
👍3124🤩2😁1
ኢትዮጵያን ወደ ታሪካዊ ከፍታ ለማሸጋገር የሚያስችለው ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ይፋ ሆነ!

የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 የትግበራ ምዕራፍ ይፋዊ የማጠናቀቂያና ኢትዮጵያን ታሪካዊና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ወደሆነ ከፍታ የሚያሸጋግረው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በዛሬው ዕለት ይፋ ሆኗል። የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ሁሉን አቀፍና አካታች የዲጂታል አገልግሎቶች አቅርቦትን አጠናክሮ ለመቀጠል የሚያስችል፣ ፈጠራ የሚያበረታታና ሰው ተኮር ስትራቴጂ መሆኑና ይህም ሙሉ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ለማምጣት ቁልፍ ሚና እንደሚኖረው በመርሀ ግብሩ ተገልጿል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ገለጻ ያደረጉት ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ፍሬሕይወት ታምሩ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ትግበራ ባለፉት አምስት ዓመታት መጠነ ሰፊ ትሩፋቶችን ማስገኘቱን ገልጸው በቴሌኮም ዘርፍ የሞባይል ደንበኞች ቁጥርን 97 ሚሊዮን ማድረስ መቻሉን፣ ከዚህም ውስጥ 57 ሚሊዮኑ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች መሆናቸውን፣ አንድ ሺህ ሰለሳ ከተሞችም የ4ጂ ኔትወርክ ተደራሽ መሆናቸውን ገልጸዋል። በዲጂታል ክፍያ መስክ ማሕበረሰባችንን ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ መሰረታዊ የዲጂታል መደላድሎች እና የፓሊሲ ማሻሻያዎች የሞባይል መኒ አካውንት ቁጥርን 162.4 ሚሊዮን መድረሱን ገልጸው ይህም የፋይናስ አካታችነት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት በእጅጉ ማገዙን አስገንዝበዋል….
41👍16🤣5👏2😁2🤪2🤩1👀1
በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የሞባይል ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር 128 ሚሊዮን፣ የሞባይል አገልግሎት ስርጸትን 100% ፣ የ4G አገልግሎት ሽፋንን 99% እንዲሁም የ5G ሽፋንን በ100 ከተሞች፣ የኢንተርኔት አገልግሎት ስርጸትን 90% እንዲሁም የስማርት ስልክ ተጠቃሚዎችን 85% ለማድረስ መታቀዱን እንዲሁም የዲጂታል ክፍያን ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት አንጻር አሁን ካለበት ከሰባት እጥፍ በላይ እንዲያድግ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ አብራርተዋል።

በመድረኩ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ልማት የተቀረጸው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ለማሳካት ከተለመዱ አካሄዶች በላቀ ፍጥነት ለመተግበር ከመንግሰት ልዩ ትኩረት ባሻገር የባለድርሻ አካላትና የማኅበረሰቡ ከፍተኛ ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

ኩባንያችን በመሰረታዊ የቴሌኮም እና የዲጂታል መሰረተ ልማት ግንባታ፣ በሞባይል ገንዘብ እና በዲጂታል ስነ ምህዳር ለተመዘገቡ ስኬቶች የመሪነት ሚናውን በመወጣቱ እንዲሁም ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 መሰረት በመጣሉ ከፍተኛ ኩራት ይሰማናል።

#DigitalEthiopia2030
#PMOEthiopia
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
👍5041🤣13😁8😡6🤪42👏2🤩2
🌍🛩 Stay Connected from the Moment You Land!

Whether it’s your first trip or a journey back home, start with the convenience of Our Visitors’ Plan!

📶 Instant Connectivity: Get online the moment you arrive.
🎁 Exclusive Visitor Deals: Special offers just for visitors.
💸 Save More: Big savings on local and international services.
💳 Flexible Payments: Pay in your preferred currency.

Read more: https://bit.ly/4cXi8Uv

📍 Available at Bole International Airport and all service centers.

#VisitorsPlan
#StayConnected
#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSuperApp #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
31👍22💔1