የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ
1.02K subscribers
53 photos
3 videos
16 files
46 links
🛡️ ከአጭበርባሪዎች ራስዎን ይጠብቁ!🛡️



🚫 የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ እናደርግዎታለን፣ 💸 ገንዘብ ላኩ በሚሉ አጭበርባሪዎች እንዳይታለሉ ⚠️ ጥንቃቄ ያድርጉ!

✅ ለውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ህጋዊ መንገዶችን ብቻ ይጠቀሙ!
Download Telegram
ለሰባተኛ ጊዜ በኪንግደም ኦፍ ሳውድ አረቢያ እየተካሄደ ባለው የሰው ሃብት ኤክስፖ ላይ የኢትዮጵያ ልኡካን ቡድን ተሳትፏል ።

ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ የሥራ ስምምነት ተፈጽሞ በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል በከፍተኛ ሁኔታ ከምታሰማራባቸው ሃገራት መካከል ሳውድ አረቢያ ቀዳሚ ስትሆን በሥራ ስምሪቱ የዜጎችን መብት ደህንነትና ጥቅም የሚያስጠብቅ ሆኖ በቴክኖሎጂ የታገዘ ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል።

በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል አቅርቦት ላይ የተገኘውን ውጤት ተደራሽነት በማስፋት የተለያዩ ሙያ ባለቤት የሆኑ ዜጎች የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ሰፋፊ ሪፎርሞች ተግባራዊ ተደርገዋል።

የሰው ሀብት ኤክስፖ ላይ ከመሳተፍ ጎን ለጎን ኢትዮጵያውያን ሞያተኞች በሳውድ አረቢያ ያላቸውን ከፍተኛ የሥራ ተፈላጊነት በቤት ውስጥ ሥራዎች ላይ ሳይወሰን በከፊል የሰለጠነ እና የሰለጠነ የሰው ሃይል ማሰማራት የሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተደርጓል:: ጥረቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

ለተደረገልን መልካም አቀበባል ክቡር አምባሳደር ሙክታር ከድር (ዶ/ር) እና ለሥራ ባልደረቦቻቸው የከበረ ምስጋናዬ ይድረሳቹ ።

የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!

         መረጃውን ለሌሎምች ያገሩ
          ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈┈
◽️እንደዚህ አይነት መረጃዎችን ለመከታተል ይህንን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ!
❤2
ኢትዮጵያ እና ሳዑዲ አረቢያ የሥራ ገበያ የሁለትዮሽ ስምምነት ከተፈራረሙ ወዲህ በሁለት አመት ውስጥ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ኢትዮጵያውያን የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል አለ በሳዑዲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ፡፡

ኢትዮጵያ በሳዑዲ አረቢያ ሪያድ እየተካሄደ በሚገኘው 7ኛው የሰው ኃይልና ማህበራዊ ልማት ኤክስፖ ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡

በሳኡዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምሳዳደር ሙክታር ከድር(ዶ/ር) በኤክስፖው መክፈቻ ላይ እንዳሉት፥ ሁለቱ ሀገራት ዘመን ተሻጋሪ ግንኙነታቸውንና መልክዓ ምድራዊ ቅርበታቸውን በመጠቅም ለሁለንትናዊ ዕድገት በጋራ በመስራት ላይ ይገኛሉ።

የሁለቱን ሀገራት የእድገት ጉዞ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሽጋገር በኢኮኖሚ፣ በቴክኖሎጂና በእውቀት ሽግግር በትብብር እየሰሩ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

ሁለቱ ሀገራት በፈረንጆቹ 2023 በሥራ ገበያ ላይ የሁለትዮሽ ስምምነት ከተፈራረሙ ወዲህ በሁለት ዓመታት ውስጥ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል ነው ያሉት፡፡

ህጋዊ ማዕቀፍ ተበጅቶለት የተጀመረው የውጭ ሥራ ስምሪት ለበርካታ ዜጎች ሰፊ የስራ እድል በመፍጠር ለጋራ ብልፅግና የላቀ አስተዋፅኦ ማበርከት መጀመሩን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በኤክስፖው ላይ መሳተፏ በሰው ኃይልና አቅርቦት ገበያ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ተወዳዳሪ ሆና ለመቀጠል፣ የስራ እድልን ለማመቻቸት፣ የዜጎችን ሁለንተናዊ መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ህጋዊ ባልሆነ መንገድ የሚደረገውን ፍልሰት ለመቀነስ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ለመወያየት መልካም እድል የሚፈጥር ነው ብለዋል ፡፡

በኤክስፖው ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ 14 ሀገራት እየተሳተፉ ሲሆን፥ በሰው ኃይል ዘርፍ ባለድርሻ አካላትን ለማገናኘት ያለመ መሆኑ ተመላክቷል ሲል የዘገበው ኤፍ ኤም ሲ ነው፡፡
በሁለት ዓመት ውስጥ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ የሥራ እድል ተፈጥሮላቸዋል
👍2
የኢትዮጵያ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች ማኅበር እና የሳውዲ ዓረቢያው ተቋም ስትራቴጂያዊ ትብብር ፈጠሩ
የኢትዮጵያ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች ማኅበር (EYEA) እና የሳውዲ ዓረቢያ የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ተቋማት ባለስልጣን (ሙንሻአት) በዲጂታል እና በኤሌክትሮኒክስ አገልግሎቶች ዘርፍ ትብብርን ለማሳደግ የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ትብብር መፍጠራቸው ተገለጸ።

በሁለቱ ተቋማት መካከል የተደረገውን የመግባቢያ ስምምነትም የኢትዮጵያ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች ማኅበር ፕሬዝዳንት ሳሚያ አብዱልቃድር እና የ"ሙንሻአት" የጋራ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ አብዱል ሙህሲን አል ሳሊም ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን በሳውዲ ዓረቢያ የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሙክታር ከድር (ዶ/ር) እና የ”ሙንሻአት” ዋና ገዥ የሆኑት አቶ ሳሚ ኢብራሂም አልሁሰይኒ በተገኙበት ተከናውኗል።

ይህ አጋርነት በአፍሪካ በተለይም በኢትዮጵያ እና በሳውዲ ዓረቢያ መካከል በሚገኙ ሥራ ፈጣሪዎች እና ስታርት አፖች መካከል ትርጉም ያለው ትብብርን ለማሳደግ ያለመ ነው።

ትብብሩ የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግርን፣ የጋራ ሥራዎችን፣ የአቅም ግንባታን እና ድንበር ተሻጋሪ የገበያ ተደራሽነትን ለማገዝ እንደሚረዳ ተመላክቷል።

በተጨማሪም የወጣቶችን ፈጠራ ለማሳደግ፣ ከወለድ ነፃ የፋይናንስ አሠራሮችን ለማስተዋወቅ እና ወጣቶች ሁሉን አቀፍ ዕድገትን እንዲያመጡ እንዲሁም የረጅም ጊዜ የልማት ግቦች ላይ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ የሚያስችሉ ዘላቂ የሥራ ፈጠራ ሥርዓቶችን ለማጠናከር የሚያስችል ትብብር መሆኑ ተገልጿል።

በመጨረሻም በዚህ ስምምነት "ሙንሻአት" ከሁለቱም ወገን ያሉ ሥራ ፈጣሪዎች ውጤት በማስመዝገብ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች እንዲጠቀሙ፣ በዓለም ዙሪያ ካሉ የሥራ ፈጣሪ ድርጅቶች ጋር ትብብርን እንዲያስፋፉ እና ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እድገትና ዘላቂነት የሚያበረታታ የተቀናጀ የንግድ ከባቢን እንዲፈጥሩ እንዲሁም ከሳውዲ አረቢያ ራዕይ 2030 ዓላማዎች ጋር እንዲጣጣሙ የሚያስችል - ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፍ ገበያዎችን እንዲያገኙ ለማስቻል የሚሰራ መሆኑ ተጠቅሷል።

የኢትዮጵያ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች ማኅበር የወጣቶችን የመፍጠር አቅም ለማጎልበት የሚሠራ ማኅበር ሲሆን፣ የማኅበሩ ዓላማ ለወጣት ሥራ ፈጣሪዎች የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን እና ሃብት ማቅረብ እንዲሁም ቢዝነሶቻቸው ስኬታማ ይሆኑ ዘንድ የፈጠራ ሐሳቦችን የሚያገኙበትን ትስስሮችን መፍጠር ነው።

በስትራቴጂያዊ ምሰሶዎቹ እና ኢኒሼቲቮቹ አማካኝነትም ትብብርን፣ ፈጠራን እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገትን የሚያበረታታ ሕያው ሥነ-ምኅዳር ለመገንባትም ይሠራል።
❤1
ነፃ ነው! 💥

የውጭ ሀገር 🌍 ሥራ ስምሪት ምዝገባ ምንም አይነት ክፍያ 💰 የለውም! ❌

✅ በህጋዊ መንገድ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ ለመሆን፦

1️⃣ በቅድሚያ በራስዎ 📱 የእጅ ስልክዎን በመጠቀም ወይም በአቅራቢያዎ 🏢 ባለው የአንድ ማዕከል አገልግሎት በመሄድ በባለሙያ 👩🏽‍💻 ታግዘው lmis.gov.et ላይ መመዝገብ።

2️⃣ በሚደርስዎት 📩 አጭር የፅሁፍ መልዕክት የሠራተኛ መለያ ቁጥር መሰረት በማዕከሉ 🤚 የእጅ፣ 🙂 የፊት እና 👁️ የአይን አሻራ (biometric data) መስጠት።

📍ይህ የዜጎችን መብት ⚖️፣ ደህንነት 🛡️ እና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት 🤝 ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው።

3️⃣ አቅራቢያዎ በሚገኝ የሥልጠና ማዕከል 🏫 እስከ 21 ቀን 📆 የሚደርስ ስልጠና መውሰድና ብቃትዎን በምዘና 🧾 ማረጋገጥ።

⚠️ ልብ ይበሉ!
👉 ምዝገባውን ሲያከናውኑም ሆነ መረጃዎቹን ሲሞሉ 💻 ምንም አይነት ክፍያ 💵 አይጠየቁም!
👉 ማስረጃዎቹን ለመስጠት ክፍያ መጠየቅ 🚫 ህገወጥ ድርጊት ነው።

👮‍♀️ እንዲህ ያሉ ድርጊቶች ሲያጋጥምዎ በአቅራቢያዎ ለሚገኙ የህግ አካላት ⚖️ በአስቸኳይ ያሳውቁ!

☎️ በ9138 ነፃ የስልክ መስመር በመደወል ጥቆማዎትን ያቅርቡ!


ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
👍8❤4👎1
የገጠር ሥራ ዕድል ፈጠራ

ግብርና በሀገራችን ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ከተሰማራባቸው የሥራ መስኮች መካከል ቀዳሚውን ድርሻ ይይዛል፡፡

የግብርና ሥራዎች ዘርፈ ብዙ የእሴት ሰንሰለትን በውስጣቸው አካተው መያዛቸውን መነሻ በማድረግ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል አማራጭ ሆኖ እንዲያገለግል ‹‹የገጠር ሥራ ዕድል ፈጠራ›› በልዩ ሁኔታ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራበት ይገኛል፡፡

የካፋ ዞን ሥራና ክህሎት መምሪያ ይህንኑ ሀገር አቀፍ የሥራ ፈጠራ አቅጣጫ መሰረት አድርጎ ባከናወናቸው ተግባራት ባለፉት አራት ወራት ውስጥ ከ5 ሺህ በላይ ወጣቶችን ወደ ሥራ ማስገባቱን አስታውቋል።

የመምሪያው ኃላፊ አቶ ሚልዮን ኃይሌ ለቦንጋ ኤፍ ኤም 97.4 እንደገለጹት፣ በበጀት ዓመቱ በከተማና በገጠር 39,667 ወጣቶችን በቋሚነት ወደ ሥራ ለማስገባት ታቅዶ የነበረ ሲሆን፣ የ4 ወራት አፈጻጸም ከ5 ሺህ በላይ ወጣቶችን ወደ ሥራ ማስገባት ተችሏል፡፡

ከዚህም ባሻገር መምሪያው ወጣቶችን የመሬት ባለቤት የማድረግ ስትራቴጂን በመከተል 5 ሺህ ሄክታር መሬት በማዘጋጀት 359 ወጣቶችን የመሬት ባለቤት ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

መሬት የተሰጣቸው ወጣቶች በግብርና መካናይዜሽን እና በኩታ-ገጠም በማረስ ምርታማነትን የማሳደግ ሥራ በቀጣይ እንደሚሠሩም ተጠቁሟል፡፡

ህዳር /2018 ዓ.ም ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር


       መረጃውን ለሌሎምች ያገሩ
          ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈┈
◽️እንደዚህ አይነት መረጃዎችን ለመከታተል ይህንን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ!
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ
👍4❤2