Ethiopian Electric Power
16.5K subscribers
12.5K photos
33 videos
32 files
2.35K links
Ethiopian Electric Power (EEP) | Official Channel
Powering Ethiopia’s future ⚡️🇪🇹
Official news, updates, projects, and announcements from EEP.
Download Telegram
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የኤሌክትሪክ  ኃይል መሠረተ ልማት ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ።

የመግባቢያ ስምምነት ፊርማ መርሃ ግብር ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል ተካሂዷል፡፡

ስምምነቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ እና የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ተፈራርመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማትን መጠበቅ የብሄራዊ ደህንነት ጉዳይ ነው ብለዋል።

ተቋሙ የኢትዮጵያን ዕድገትንና ብልጽግናን ለማረጋገጥ አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል እያቀረበ ሲሆን የኃይል መሰረተ ልማቶች ደግሞ የሀገር ሀብቶች በመሆናቸው ደህንነታቸው እንዲጠበቅ የፌዴራል ፖሊስ ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ.…
https://www.eep.com.et/?amh-news=የኢትዮጵያ-ኤሌክትሪክ-ኃይል-እና-የኢትዮ&lang=am

#የኢትዮጵያ_ኤሌክትሪክ_ኃይል
❤9👍2😐1
ዛሬ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ መካከል የተደረሰው ስምምነት ዋና ዋና ጉዳዮች:-

📌 የተቀናጀ የደህንነት አስተዳደርና ጥበቃ፦ ለከፍተኛ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች (ኃይል ማመንጫዎች፣ ማከፋፈያ ጣቢያዎች፣ ማስተላለፊያ መስመሮች እና በግንባታ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች) ዘላቂ፣ አስተማማኝ እና የተቀናጀ የደህንነት ሥርዓት መዘርጋት፤

📌 ወንጀል መከላከልና ሕግ ማስከበር፦ በመሰረተ ልማቶች ዙሪያ ሕግ የማስከበር ሥራዎችን በማጠናከር፣ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር በማዋል እና ፈጣን ምርመራ በማድረግ ለዓቃቢ ሕግ ለክስ ሂደት ማቅረብ፤

📌 የመረጃ ልውውጥና የስጋት ግምገማ፦ የደህንነት ስጋት ግምገማዎችን በየጊዜው በማካሄድ ክፍተቶችን መለየት፣ መረጃዎችን መለዋወጥ እና በግኝቶቹ ላይ በመመስረት የጋራ ኦፕሬሽኖችን ማስተባበር፤

📌 አካላዊ የጥበቃ ሥራዎችና የመስመር ክትትል፦ የኃይል ማመንጫዎችን፣ ማከፋፈያ ጣቢያዎችንና ፕሮጀክቶችን እንዲሁም የዋና እና ሪጅን መ/ቤቶችን መጠበቅ፤ በከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ኮሪደሮች ላይ መደበኛ የጥበቃ ቅኝት በማድረግ የሚፈጸሙ ስርቆቶችን  እና  ሕገ-ወጥ ግንባታዎችን መከላከል፤

📌 የአደጋ ጊዜ ምላሽና ቀውስ አስተዳደር: ለደህንነት ክስተቶች፣ ለሽብርተኝነት ሥጋቶች እና ለተፈጥሮ አደጋዎች ፈጣን ምላሽ የመስጠት ሥራዎችን ማከናወን እና

ተጨማሪ ያንብቡ.…
https://www.eep.com.et/?amh-news=ዛሬ-በኢትዮጵያ-ኤሌክትሪክ-ኃይል-እና-በኢ&lang=am

#የኢትዮጵያ_ኤሌክትሪክ_ኃይል
❤19👎1
ከመቀሌ ዳሎል ተቋርጠው የቆዩ የኤሌክትሪክ ኃይል ፕሮጀክቶች በአስቸኳይ ስራ እንዲጀምሩና እንዲጠናቀቁ ከውሳኔ ተደርሷል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ልዑክ በመቀሌ የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያና በተቋረጡ ፕሮጀክቶች የመስክ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል ።

በእስካሁኑ ጉብኝቱ በመቀሌ ኃይል የማከፋፈያ ጣቢያ እና ለረጅም ጊዜ ተቋርጠው በቆዩ ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶች ችግሮችን መለየት ተችሏል።

ጉብኝቱን በመምራት ላይ የሚገኙት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የዋና ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ግርማ ግዛቸው በመቀሌ በተደረገው ቆይታ በኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ሥራ አፃፀም ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን መለየትና ያጋጠሙ ችግሮችን በመገምገም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መግባባት ላይ መድረስ መቻሉን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም ለፌዴራል ፖሊስ አገልግሎት የሚውሉ የመኖሪያ ቤቶችና የመጋዘን፤ በሃይል ማከፋፈያ ጣቢያው አካባቢ የሚገኙ የሠራተኞች መኖሪያ ቤቶችን የማሻሻል ግንባታ ስራ እንዲቀጥል ተወስኗል።

ውሳኔ የተሰጠባቸው ጉዳዮች በአጠረ ጊዜ እንዲፈጽሙና የክትትል ሥራውን እንዲያጠናክሩ ጥብቅ አቅጣጫ መሰጠቱን ዶ/ር ግርማ ተናግረዋል።

#የኢትዮጵያ_ኤሌክትሪክ_ኃይል
👏13❤7👎1
በክልሉ በኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀሙ የስርቆት ወንጀሎችን መከላከል ይገባል
…//…

በትግራይ ክልል በኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ በተደጋጋሚ የሚፈፀሙ የስርቆት ወንጀሎችን መከላከል እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡

ተቋሙ ከትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በኃይል መሰረተ ልማቶች ደህንነትና ጥበቃ ዙሪያ ውይይት አካሂዷል፡፡

የተከዜ የውሃ እና የአሸጎዳ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች በፌዴራል ፖሊስ ልዩ ጥበቃ እንዲደረግላቸው እንዲሁም የክልሉ አስተዳደር በኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ላይ የሚፈፀሙ የስርቆት ወንጀሎችን የመቆጣጠር ኃላፊነቶችን እንዲወጣ ከስምምነት ላይ ተደርሷል።

በኃይል መሰረተ-ልማቶች ላይ የሚደርሱ ወንጀሎችን ለመግታት ከተቋሙ የደህንነት አካላት አቅም በተጨማሪ ከክልሉ እና ከፌዴራል የፀጥታ መዋቅሮች ጋር ተቀናጅቶ በጋራ የመከላከል ሥራ እንደሚሰራም በውይይቱ ላይ ተገልጿል።

በመቐለ ከተማ የሚስተዋለውን የኃይል አቅርቦት እጥረት ለመቅረፍ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራም ነው የተገለፀው፡፡

#የኢትዮጵያ_ኤሌክትሪክ_ኃይል
❤15
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሞስኮ በተካሄደው 3ኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባዔ ላይ የኢነርጂ ዘርፉን በተመለከተ ካደረጉት ንግግር የተወሰደ፤
....///....

👉 ከሩሲያ ጋር በመተባበር ከዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ (IAEA) የደህንነት ደረጃዎች ጋር የተጣጣመ የመጀመሪያውን የኑክሌር የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ለመገንባት እየተሰራ ነው።

👉 የኑክሌር የኃይል ማመንጫ ጣቢያው በውሃ ላይ የተመሰረተውን የኢትዮጵያን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ስብጥር ለማስፋት ድርሻው የጎላ ነው።

#የኢትዮጵያ_ኤሌክትሪክ_ኃይል
❤8
❤3👍1
<<ሀገራዊ የኃይል አቅርቦት ፍላጎትን ለማሟላት የ10 ዓመት የኃይል መሰረተ ልማት ፍኖተ ካርታ ተነድፏል>> ኢንጂነር አሸብር ባልቻ
...///...

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በቀጣዮቹ 10 ዓመታት የኃይል ማመንጨት አቅምን ለማሳደግ፣ የማስተላለፊያ መሰረተ ልማቶችን ለማዘመን እና አጠቃላይ የግሪድ ሥርዓቱን ለማሻሻል የሚያስችል የ30 ቢሊዮን ዶላር የኃይል ልማት ዕቅድ ይፋ ማድረጉን አስታወቀ።

​የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋዜጣ ፕላስ እንደገለፁት የረጅም ጊዜ ሀገራዊ የኃይል አቅርቦት ፍላጎትን ለማሟላት የሚያስችል የ10 ዓመት የኃይል መሰረተ ልማት ፍኖተ ካርታ ተነድፏል።

​ማዕቀፉ በመላ ሀገሪቱ የኃይል አቅርቦት አስተማማኝነትን በማጠናከር ለመኖሪያ ቤቶች፣ ለኢንዱስትሪዎች እና ለንግድ ተቋማት ተደራሽነቱን ለማስፋት ያለመ ነው።

​የኤሌክትሪክ ማመንጨት አቅምን ማስፋፋት የኃይል ብክነትን ለመቀነስ ከሚረዱ ጠንካራ የማስተላለፊያ መስመሮች ጋር ሊጣጣም እንደሚገባም አብራርተዋል።

የኤሌክትሪክ አቅርቦቱን አስተማማኝነት ለማረጋገጥ የኃይል ስብጥሩን ለማስፋት መታቀዱን የጠቆሙት ዋና ሥራ አስፈፃሚው ከጂኦተርማል ብቻ ከ10 ሺህ ሜጋ ዋት በላይ የሚገመት የማመንጨት አቅም መኖሩን ገልፀዋል።

​የታቀደው የ30 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ከመንግሥት በጀት፣ ከግሉ ዘርፍ፣ ከአየር ንብረት ፋይናንስ እንዲሁም በመንግሥትና የግል አጋርነት (PPP) ከሚከናወኑ ፕሮጀክቶች በሚገኝ የገንዘብ ምንጭ የሚሸፈን መሆኑንም ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ቀጣናዊ የኃይል ትስስርን ለማጠናከር ደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያን ያካተተ የ1 ቢሊዮን ዶላር ፕሮጀክቶች የአዋጭነት (Feasibility) ጥናቶች እየተካሄዱ ይገኛሉ ብለዋል።

ፕሮጀክቶቹ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ያላትን ቀዳሚ የኃይል አቅራቢነት ሚና በከፍተኛ ሁኔታ ለማስፋፋት የተነደፉ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

​ይህ ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ኢትዮጵያ ለሀገር ውስጥ ዘላቂ ልማት እና ለቀጣናዊ ኢኮኖሚያዊ ትስስር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ መሆኑን ኢንጂነር አሸብር አብራርተዋል።

#የኢትዮጵያ_ኤሌክትሪክ_ኃይል
❤12🤨2👎1😐1