Ministry of Education Ethiopia
119K subscribers
2.95K photos
32 videos
6 files
378 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
በኢትዮጵያ የህዋዌ ቴክኖሎጂ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ለትምህርት ሚኒስቴር ለኮቪድ 19 መከላለከያ የሚውል የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡

በሀገራችን ብሎም በአለም ላይ የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል በርካታ ተቋማት የተለያዩ ድጋፎች እያደረጉ እንዳሉ ይታወቃል ፡፡ በኢትዮጵያ የህዋዌ ቴክኖሎጂ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ለትምህርት ሚኒስቴር 100 ሳኒታይዘር፣ 10ሺህ የፊት ማስክ እና 20 የሙቀት መለኪያ መሳሪያዎችን በኢትዮጵያ የሁዋዌ ቴክኖሎጂ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ስራ አስኪያጅ Tiber Zhou በኩል ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትርም ዶ/ር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ የተደረገውን ድጋፍ በተቀበሉበት ወቅት የኮሮና ቫይረስ ስርጭቱ በሀገራችን እየጨመረ መምጣቱን አስታውሰው ይህንን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በኢትዮጵያ የህዋዌ ቴክኖሎጂ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ላደረገው ድጋፍ አመስግነው በዚህ አስቸጋሪ ወቅት በስራ ላይ የሚገኙ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች የተለያዩ የመከላከያ ቁሳቁስ ስለሚያስፈልጋቸው የተደረገው የቁሳቁስ ድጋፍ ሰራተኞች ጥንቃቄ በማድረግ ስራቸውን እንዲሰሩ ለማድረግ እንደሚውል ገልፀዋል፡፡

አሁንም በሽታውን ለመከላከል ጥንቃቄ በማድረግ ይህንን አስቸጋሪ ጊዜ ማለፍ ይጠበቃል በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡http://www.facebook.com/fdremoe
አይነ-ስውር ተማሪዎች ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ትምህርታቸውን በተሻለ ሁኔታ መከታተል እንዲችሉ የሚያግዝ የድጋፍ ስምምነት ተፈረመ፡፡
አይነ-ስውር ተማሪዎች ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ትምህርታቸውን በተሻለ ሁኔታ መከታተል እንዲችሉ የሚያግዝ የድጋፍ ስምምነት በየተስማሚ ቴክኖሎጂ ማዕከል ለአይነ-ስውራን እና በትምህርት ሚኒስቴር መካከል ተፈርሟል፡፡
የተፈረመው ስምምነት አይነ-ስውራን ተማሪዎች በኮምፒዩተር፣ በብሬይል፣ በአጋዥ መሳሪያዎች ታግዘው ትምህርታቸውን ለመከታተል እንዲችሉ የሚያደርግ በመሆኑ በተማሪዎቹ የመማር ሁኔታ ላይ ሊፈጥር የሚችለው አዎንታዊ ተጽዕኖ ከፍተኛ ይሆናል፡፡
የተስማሚ ቴክኖሎጂ ማዕከል ለአይነ-ስውራን እና ትምህርት ሚኒስቴር ለወደፊቱ በጋራ በመስራት ልዩ እገዛ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች እገዛ እንደሚያደርጉ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዘግቧል፡፡
https://www.facebook.com/fdremoe/?ref=page_internal
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የ‘’መ’’ ህጎችን በመጠቀም ራስዎን፣ቤተሰብዎንና ማህበረሰብዎን ይጠብቁ!https://www.facebook.com/fdremoe/?ref=page_internal
በትምህርት ሚኒስቴር እና ስቴምፓወር በጋራ የተቋቋመ ዲጂታል የመፈብረኪያ ቤተ-ሙከራ በይፋ ስራ ጀመረ፡፡
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር ከስቴም ፓዎር (STEMpower.org) ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ የተፈረመ ሲሆን ከቅድመ-መደበኛ እስከ ቅድመ ከፍተኛ ትምህርት ድረስ ለህፃናት መጫወቻ፣ ለፈጠራ ስራ፣ ለማስተማሪያና ለአዲስ ግኝት መፍጠሪያ ተስማሚና ምቹ የሆነ የዕውቀትና ክህሎት ቅንጅት መፍጠሪያ ቦታ የ STEMpower /fablab/ ፋብላብ (ዲጂታል የመፈብረኪያ ቤተ-ሙከራ) ተቋቁሟል፡፡
ትምህርት ቤቶች ዝግ ከመሆናቸውና ተማሪዎች ቤት ውስጥ ከመዋላቸው ጋር በተያያዘ ጊዜያቸውን ለፈጠራ ተጠቅመው የሚያመጧቸውን ፈጠራዎች ወደ ምርትና አገልግሎት ማሻሻል በመስገባት የማህበረሰቡን ችግር በመፍታት አስተዋጻኦ እንደሚኖረውም ተገልጷል፡፡
ዛሬ በይፋ የተከፈተው ዲጂታል የመፈብረኪያ ቤተ-ሙከራ የቅድመ ኮሌጅ ተማሪዎችን ትኩረት በማድረግ በተለይ ከኮቪድ 19 ጋር የተያያዙ የፈጠራ ስራዎችን በጋራ በመደገፍ በተቋቋመው የማምረቻ ላቦራቶሪ ተጠቅመው የሚሰሩና ተግባር ላይ የሚውሉ ፕሮቶታይፖችን እስከሚያመርቱ ሁለንተናዊ ድጋፍ የሚያደርግ ይሆናል፡፡
ስቴም ፓዎር (STEMpower.org) የምርት ግብዓቶችን በመግዛትና የቴክኖሎጂ ድጋፍ በማድረግ እንዲሁም የቴክኒክ እገዛ በማድረግ እየሰራ ሲሆን በዚህም በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የተለያዩ ሃሳቦች መጥተው ትምህርት ሚኒስቴር ውስጥ በሚገኘው በተደራጀው የመፈብረኪያ ላቦራቶሪ በመጠቀም የመጀመሪያ ምርቶችን ለማውጣት እየተሰራ ይገኛል፡፡https://www.facebook.com/fdremoe/?ref=page_internal
ለማህበራዊ ትስስር መገናኛ ቻናል ተጠቃሚዎች በሙሉ

የተቋሙን አዲሱንና ነባሩን ሎጎ በመጠቀም አንዳንድ ግለሰቦች የተሳሳቱ መረጃዎችን ከዚህ በታች እንደተለጠፉት ሐሰተኛ የቴሌግራም የማህበራዊ ትስስር መገናኛ ቻናሎች እየለቀቁ ይገኛሉ።
ስለሆነም እነዚህ ሐሰተኛ የቴሌግራም የማህበራዊ ትስስር መገናኛ ቻናሎች የተቋሙ አለመሆናቸውን እየገለጽን ፤ የተቋሙ ትክክለኛው የቴሌግራም የማህበራዊ ትስስር መገናኛ ቻናል https://t.me/ethio_moe መሆኑን አውቃችሁ ለሌሎችም ተጠቃሚዎች ይህን መረጃ በማስተላለፍ እንድትተባበሩን እንጠይቃለን።

“የነገ ህመምና ሞትን በዛሬ ጥንቃቄ እንታደግ!!!”