Ministry of Education Ethiopia
119K subscribers
2.95K photos
32 videos
6 files
378 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
በትምህርት ዘርፉ እየተተገበሩ ያሉ የሪፎርም አጀንዳዎችን ውጤታማ ለማድረግ የክትትልና ድጋፍ ስርዓትን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ፤
በየደረጃው የሚገኙ የስራ ክፍሎች አፈጻጸም ምዘና ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።
----------------------------------------------
(ሚያዝያ 01/2017 ዓ.ም) በትምህርት ሚኒስቴር የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈጻሚ ይበልጣል አያሌው (ዶ/ር) በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት በትምህርት ዘርፉ እየተተገበሩ ያሉ የሪፎርም አጀንዳዎችን ስኬታማ ለማድረግ የክትትልና ድጋፍ ስርዓትን ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል።
የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማሳደግ ፣ ዝቅተኛ አፈጻጸም የታየባቸውን የስራ ክፍሎች መደገፍ፣ ልምድ መለዋወጥ ፣ የተሻለ አቅም መፍጠር እንደሚገባም ዶ/ር ይበልጣል ጠቁመዋል።
የሚኒስትር ጽ/ ቤት ሃላፊ አቶ ጌታቸው ተፈራ በበኩላቸው የስራ ክፍሎች የተናበበ እቅድና ሪፖርት ሊኖራቸው እንደሚገባ ጠቁመው የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል የግድ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር አያይዘውም ለስራ ክፍሎችና ሰራተኞች በተግባር የሚለካና ለውጤት የሚያበቃ ስልጠና መስጠት እንደሚገባም የሚስትር ጽ/ ቤት ኃላፊው አቶ ጌታቸው አስረድተዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የሁሉም ስራ ክፍሎች ኃላፊዎችና የሚመለከታቸው ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡
የ “ትምህርት ለትውልድ” ንቅናቄ የኢትዮጵያ ወላጆች ለልጆቻቸው ትምህርት ምን ያህል እንደሚተጉ ያየንበት ነው። ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፤

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ተካሂዷል።

----------------------------------------

(ሚያዝያ 03/2017 ዓ.ም) በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የአንድ ሀገር የትምህርት ሥርዓት ከተበላሸ ሀገር መሆን አይችልም፤ ለዚህም እንደ ሀገር የትምህርት ሥርዓቱን ከመሠረቱ ለማስተካከል በርካታ የሪፎርም ተግባራት ተቀርፀው ተግባራዊ እየተደረጉ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል።

በተለይም የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት በሟሟላት ምቹ የመማሪያ ከባቢን ለልጆች ለመፍጠር በተጀመረው የ”ትምህርት ለትውልድ” ንቅናቄ እስካሁን ከ52 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ሀብት በማሰባሰብ፤

ከ30 ሺ በላይ ቅድመ አንደኛ ደረጃ፣ ከ8 ሺህ በላይ አዳዲስ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ከ22 ሺ በላይ ነባር ትምህርት ቤቶች ጥገናና እድሳት ማድረግ መቻሉን ጠቅሰዋል።

ይህም የኢትዮጵያ ወላጆች ለልጆቻቸው ትምህርት ምን ያህል እንደሚተጉ ያየንበት ነበር ብለዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/1AKztzK7HV/
የሚመለከታችሁ ሁሉ
መረጃውን ለማግኝት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፣
https://forms.gle/N8uPaW7uXYTEZWQC8
ዩኒቨርሲቲዎች በትክክል የእውቀትና የምርምር ማዕከል በመሆን ከመንደር አስተሳሰብ ወጥተው ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋን ማፍራት ላይ በትኩረት መሥራት እንዳለባቸው የትምህርት ሚኒስትሩ አሳሰቡ፤

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከጅንካ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ጋር ተወያይተዋል።
---------------------------------------
(ሚያዝያ 03/2017 ዓ.ም) በዚሁ ወቅት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዩኒቨርሲቲዎች በአካዳሚክ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በሚገባ በመወጣት በአለም ሁኔታ እውነተኛ ውይይት የሚደረግባቸውና ለማህበረሰቡ አቅጣጫ የሚሰጡ እውቀቶች የሚፈልቁባቸው ተቋማት ሊሆኑ ይገባል ብለዋል።

በተለይም ዩኒቨርሲቲዎች ለእውነትና እውቀት የሚሰጡት ትኩረት አናሳ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ተማሪዎች ክፍል ከሚማሩት ትምህርት በተጨማሪ አለም አቀፍና ሀገራዊ ሁኔታዎችን እንዲያውቁና ለዛ እንዲዘጋጁ ምሁራዊ ውይይት ማድረግ ያስፈልጋል ነው ያሉት፤

ስለሆነም ዩኒቨርሲቲዎች በትክክል ልጆች የሚማሩባቸው የእውቀትና የምርምር ማዕከል በመሆን ከመንደር አስተሳሰብ ወጥተው ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋን ማፍራት ላይ በትኩረት መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሽኔ በበኩላቸው የዛሬው ውይይት ዩኒቨርሲቲዎች ከተሰጣቸው ተልዕኮ አንፃር የሪፎርም ተግባራትን እንዴት እያስኬዱ ነው የሚለውን ለመለየት ያለመ መሆኑን ጠቅሰዋል።

አክለውም በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ራሱን የሚችል፣ ሀገሩን የሚጠቅም ተወዳዳሪ የሆነ ብቁ ዜጋ ለማፍራት ዩኒቨርሲቲዎች በውጤት መለካት ይኖርባቸዋል፤ ለዚህም ሚኒስቴሩ ተጠያቂነት የሚያስከትል ስምምነት ከዩኒቨርስቲ አመራሮች ጋር መፈራረሙን ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በቻይና የሁዋዌ ቴክፎርጉድ ግሎባል ውድድርን አንደኛ በመሆን አሸነፉ።
------------------------------------

(ሚያዝያ 4፣ 2017) የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሁዋዌ ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ቴክ ፎር ጉድ ግሎባል ውድድርን አንደኛ በመሆን አሸንፈዋል።

ውድድሩ ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዝያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በሚቆየውና በቻይና ቤጂንግ እና ሼንዘን የሚገኙ የቴክኖሎጂ ማዕከሎችን ጉብኝትና የተግባር ስልጠናዎችን ካካተተው ዝግጅት ጋር የተካሄደ ሲሆን ውጤቱ ይፋ የተደረገው ሚያዝያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ነው።

በስድስት ተማሪዎች የተወከለው የኢትዮጵያ ቡድን ተማሪዎቹን ከአዲስ አበባ፣ ሃራማያ፣ ጅማ፣ ወልቂጤ እና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች አሰባስቧል። በውድድሩም ከሞሮኮ፣ ደቡብ አፍሪካ፤ አርጀንቲና አየርላንድ፣ ማላዊ፣ ቬትናም፣ አረብ ኤምሬትስ እና ሌሎችንም ጨምሮ ከዓለም ዙሪያ ከተውጣጡ 12 ልዩ ቡድኖች ጋር ተወዳድሯል። የሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ግሎባል አምባሳደር የሆነችው ኢትዮጵያዊቷ ተማሪ አሲያ ከሊፋም በዝግጅቱ በእንግድነት ተገኝታለች። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/1559cgfA9r/
የመንግስት ትምህርት ቤቶችን ብቃት በማሻሻል ለዜጎች ጥራት ያለው ትምህርት ለማድረስ እተሰራ መሆኑ ተገለጸ፤
የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ9 ወራት እቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት አድርገዋል።
------------------------------------------

(ሚያዝያ 06/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት የመንግስት ትምህርት ቤቶችን በማብቃት ጥራት ያለው ትምህርት ለዜጎች ሁሉ ለማድረስ እየተሰራ ይገኛል።

በሁሉም መስክ ያለውን ችግር መፍታት የሚቻለው መሀንዲሶች፣ ቴክኖሎጂስቶች፣ ቴክኒሻኖች፣ ቢሮክራቶችና ሌሎችምም ባለሙያዎች በጥራትና በብቃት ማፍራት ሲቻል መሆኑንም ክቡር ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።

የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል ፣ መምህራንን አቅም በማሳደግና በሌሎችም የአጠቃላይና ከፍተኛ ትምህርት ዘርፎች የተጀመሩ ሪፎርም ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ፕሮፌሰር ብርሃኑ ጠቅሰዋል።

በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምንም ተማሪ ያላሳለፉ 700 ትምህርት ቤቶችን ለማብቃት ትምህርት ሚኒስቴር እቅድ ይዞ እየሰራ መሆኑንም ክቡር ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/1GxumTSsqy/
የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) በትምህርት ዘርፍ ያለውን አበርክቶ ለማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደረገ።
---------------------------------------------------
(መጋቢት 08/2017 ዓ.ም) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ዩኔስኮ የትምህርት አመራሩን ማዕከል አድርጎ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ከተባበሩት መንግስታት ትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ድርጅት የ(UNESCO) የሚገኙ ድጋፎችን አሟጦ መጠቀም በሚቻልበት ጉዳዮች ላይ ከትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች ጋር ውይይት አድርጓል።

የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በምክክር መድረኩ ላይ በመገኘት ባስተላለፉት ቁልፍ መልዕክት አሁን ካለው የመንግስት ውስን ሀብት በተጨማሪ ድጋፎችና ትብብሮችን በማጠናከር የትምህርት ዘርፉን ለመደገፍ በሚደረገው ጥረት ውስጥ አመራሩ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚገባው አስገንዝበዋል።

በሚገኙ ትብብሮችና ድጋፎች ሴቶችን ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ ያሉ ጅምር ስራዎችን በማጠናከርና ቋጠሮዎችን በመፍታት ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ክብርት ሚንስትር ዴኤታዋ አያይዘው ገልጸዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ብሄራዊ ዩኔስኮ ኮሚሽን ተጠባባቂ ዋና ፀኃፊ አቶ አለሙ ጌታሁን በበኩላቸው ባደረጉት ገለጻ የትምህርት አመራሩ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ዩኔስኮ ተግባርና ተልዕኮዎችን በአግባቡ በመገንዘብና በመረዳት ለተፈጻሚነታቸው ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚገባው አስገንዝበዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/16LFKB3tgW/
ማስታዎቂያ
ለቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ምዝገባ https://exam.ethernet.edu.et የሚለውን ሊንክ በመጠቀም መመዝገብ የሚቻል መሆኑ እንገልጻለን።