Ministry of Education Ethiopia
119K subscribers
2.99K photos
32 videos
6 files
386 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
ኢትዮጵያ አዲስ ሥርዓተ ትምህርት በመቅረጽ ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን ቴክኖሎጂና ክህሎትን የተላበሱ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጎችን ለማፍራት በትኩረት እየሰራች መሆኑ ተገለፀ።
-------------------------------------------------
(ሚያዝያ 22.2017 ዓ.ም) ኢኖቬሽን አፍሪካ 2025 የትምህርት ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፍ የሪፎርምና የፖሊሲ እርምጃዎች ላይ ያላትን ልምድ አካፍላለች።

በመድረኩ ትምህርት ሚኒስቴርን በመወከል ፓናሊስት የነበሩ የትምህርት ፕሮግራሞችና ጥራት መሻሻል መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ዮሐንስ ወጋሶ የትምህርት ዘርፉን ለመለወጥ እየተወሰዱ ያሉ የሪፎርም ተግባራትን አብራርተዋል።

በዚሁ ጊዜ በትምህርት ሥርዓቱ የነበሩ ችግሮችን በሮድ ማፕ በመለየት ኢትዮጵያ የትምህርት ፖሊሲዋን ከመቀየር ጀምሮ ትምህርትን ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ የትምህርት ህግ ማጽደቋን ጠቅሰዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/1Fq4wfN3bj/
ሁለም ዜጎች እኩል የትምህርት እድል እንዲያገኙ እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ነገሌ አርሲ ከተማ የኡታ ዋዩ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታን አስጀምረዋል።
-------------------------------------------

(ሚያዝያ 23/2017 ዓ.ም) በዚሁ ጊዜ የመሠረተ ልማት የተሟላላቸው ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶቾን በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እየገነባ መሆኑን ጠቅሰው ዛሬ ግንባታው የተጀመረው ኡታ ዋዩ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አንዱ መሆኑን ገልፀዋል።

በዚህም ሁሉም ኢትዮጵያዊያን እኩል የትምህርት እድል እንዲያገኙ በትኩረት እየተሠራ ነው ያሉ ሲሆን፦

ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ሥርዓቱን ለመቀየር በርካታ የሪፎርም ተግባራትን ቀርፆ እየተገበረ ይገኛል ብለዋል።

ሀገሪቱ ከሌላው አለም ጋር ተወዳዳሪ እንድትሆን፤ ብቁ ተወዳዳሪ፣ ክህሎትን የተላበሱና ግብረ ገብነት የተላበሱ ዜጎችን ለማፍራት የሚያስችሉ ሥራዎችም እየተሠሩ መሆኑን አብራርተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፣ https://www.facebook.com/share/18fMXNRqbw/
ትምህርት ሚኒስቴር በአለታ ጩኮ ከተማ የሚያስገነባው ሩፎ ዋኤኖ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ ተጀመረ።
---------------------------------------------
(ሚያዝያ 23/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ትምህርት ሚኒስቴር በሲዳማ ክልል ደቡባዊ ሲዳማ ዞን አለታ ጩኮ ከተማ የሚያስገነባውን ሩፎ ዋኤኖ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታን አስጀምረዋል።

በከተማ አስተዳደሩ ያለው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አንድ ብቻ በመሆኑ ይህ በትምህርት ሚኒስቴር የሚገነባው ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያለውን ችግር በመፍታትና የተማሪ ክፍል ጥምርታውን በማመጣጠን ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል ተብሏል።

ምቹና መሠረተ ልማት የተሟላላቸው ትምህርት ቤቶች መኖር ምቹ መማር ማስተማርን ከመፍጠር ባሻገር ተማሪዎች ትምህርት ቤቶቹን ወደው እንዲመጡ ያደርጋል ተብሏል።

በመድረኩም በደቡባዊ ሲዳማ ዞን የትምህርት ጥራትን ከመሠረቱ ለመፍታት በትምህርት ለትውልድ የትምህርት ቤቶች መሠረተ ልማት ማሻሻል ህዝባዊ ንቅናቄ ስታንዳርዳቸውን የጠበቁ 21 የሚሆኑ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተገንብተው የመማር ማስተማር ሥራ መጀመራቸው ተገልጿል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ። https://www.facebook.com/share/p/15kvTMLGLq/
ትምህርት ሚኒስቴር ከሚያስገነባቸው 50 ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የአጋ ጢንጠኖ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ ተጀመረ።
-----------------------------------------------

(ሚያዝያ 24/2017 ዓ.ም) ሚኒስቴሩ በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ሻኪሶ ከተማ የሚያስገነባው አጋ ጢንጠኖ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ ተጀምሯል።

ግንባታውን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የኦሮሚያ ክልል በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ሳዳት ነሻ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ቶላ በሪሶ (ዶ/ር) አስጀምረውታል።

ትምህርት ዓለም ላይ ተወዳዳሪ ለመሆን ወሳኝ በመሆኑ የሀገራችንን የትምህርት ሥርዓት ከመሠረቱ በመቀየር ሀገር የሚገነባ ቀጣይ ትውልድ ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

ይህ በሻኪሶ ከተማ የሚገነባው ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በከተማው ያለውን የትምህርት ቤት እጥረት የሚፈታ ይሆናል።

በዚህም የከተማው አስተዳደርና አባገዳዎች ትምህርት ሚኒስቴር ያለውን ችግር በመመልከት ይህንን ትምህርት ቤት ግንባታ በሻኪሶ በማስጀመሩ ምስጋና አቅርበዋል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ። https://www.facebook.com/share/p/1KE3pqXBUV/
በተከታታይ ሦስት ጊዜ በተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከ25 በመቶ በታች ውጤት በሚያስመዘግቡ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ እርምጃ እንደሚመወሰድ ተገለፀ።

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ጋር ተወያይተዋል።
------------------------------------------------------
(ሚያዝያ 25/2017 ዓ.ም) በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዩኒቨርሲቲዎች ሰው እውቀትና እውነት ፈልጎ የሚመጣባቸው ተቋማት ሊሆኑ ይገባል ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች በተፈጥሮ የተሰጡ የአካባቢው ፀጋዎች ላይ ራዕይ ይዘው መሥራት ይገባቸዋል ያሉ ሲሆን ቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲም በማዕድን ላይ ሰፊ ምርምር በማድረግ ህብረተሰቡን ብሎም ሀገርን የሚጠቅም ሥራ መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።

አክለውም ዩኒቨርሲቲዎች የሚያስተምሯቸው ተማሪዎች ብቃት ያላቸውና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማድረግን ዋና ተግባራቸው አድርገው መሥራት አለባቸው፦
በዚህ ረገድ በተከታታይ ሦስት ጊዜ በተመራቂ ተማሪዎች በመውጫ ፈተና ውጤት ከ25 በመቶ በታች ካስመዘገቡ በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በኩል እርምጃ እንደሚወሰድ አመላክተዋል።

የዩኒቨርሲቲ አመራሮች በብቃትና በችሎታ እንዲመደቡ እየተደረገ መሆኑን አንስተው አሰራራቸውን ለማዘመንም የዩኒቨርሲቲ አመራሮች ማሰልጠኛ ተቋም ለማቋቋሞ እየተሠራ መሆኑንም ጠቅሰዋል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ፤
https://www.facebook.com/share/p/14DrZez77u9/
የያቤሎ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ ተጀመረ።
--------------------------------------------

(ሚያዝያ 25/2017 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር ለማስገንባት ካቀዳቸው 50 ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የያቤሎ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ በዛሬው እለት ተጀምሯል።

ይህ በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ያቤሎ ከተማ የሚገነባውን ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና ኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች አስጀምረውታል።

በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ይህ ሞዴል ትምህርት ቤት አርብቶ አደር በሆነ አካባቢ የሚገነባ መሆኑን ጠቅሰው ይህ ለሁሉም ዜጎች ጥራት ያለው ትምህርትን በፍትሃዊነት ለማዳረስ የምናደርገውን ጥረት ያሳያል ብለዋል።

እንደ ሀገር ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥኑ በአለም ላይ ተወዳዳሪ የሆኑ፤ ብቃትና ክህሎት ያላቸው የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጎችን ለማፍራት እንደዚህ ያሉ መሠረተ ልማት የተሟላላቸው ትምህርት ቤቶች ያስፈልጋሉ፤ ለዚህም አቅደን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ። https://www.facebook.com/share/p/1A6MsvgLh8/