Ministry of Education Ethiopia
119K subscribers
2.99K photos
32 videos
6 files
386 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
ማስታዎቂያ
ለቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ምዝገባ https://exam.ethernet.edu.et የሚለውን ሊንክ በመጠቀም መመዝገብ የሚቻል መሆኑ እንገልጻለን።
በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት Innovation Africa 2025 ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል።
የትምህርት፣የቴክኖሎጂና የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ከ’ African Brains’ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት Innovation Africa 2025 ጉባኤ በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል መካሄድ ጀምሯል።
----------------------------------------
(ሚያዝያ 20/2017 ዓ.ም) በዚህ Innovation Africa 2025 የትምህርት፣ የቴክኖሎጂና ክህሎት ጉባኤ ላይ የአፍሪካ ሀገራት የዘርፉ ሚኒስትሮችና ልዑካን ቡድን አባላት፣ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የትምህርት አጋር ድርጅቶች፣ የግሉ ሴክተር ኢንቨስተሮች እየተሳተፉ ይገኛል።

ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ቀጣዩን ትውልድ ለመገንባት ትምህርት፣ ቴክኖሎጂና ክህሎት በጣም መሳኝ በመሆናቸው በዚህ ጉባኤ ትርጉም ያለውና የሚተገበር ውይይት እንደሚደረግ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ትምህርትና ክህሎትን ማዕከል በማድረግ በትምህርት ቤት ግንባታና መሠረተ ልማት ማሻሻል፣ በድጂታል ኔትዎርክ ግንባታ እንዲሁም በፈጠራና ክህሎት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝም አንስተዋል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ ተጭነው ማግኘት ይችላሉ። https://www.facebook.com/share/p/1ATdg6DtZU/
በአፍሪካ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የትምህርት መሰረተ ልማትን ከመገንባት ባለፈ የመምህራንን አቅም መገንባት እንደሚገባ ተጠቆመ።
…………………………………………………………………

(ሚያዝያ 20/2017 ዓ.ም) "ኢኖቬሽን አፍሪካ 2025" የአፍሪካ የትምህርት፣ የኢኖቬሽና ቴክኖሎጂ እና ክህሎት የሚኒስትሮች ስብሰባ "በ21ኛው ክፍለ ዘመን አፍሪካን ማስተማርና ማብቃት" በሚል መሪ ሀሳብ የፓናል ውይይት ተደርጓል።

በዚሁ ወቅት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ኢትዮጵያ የትምህርት ስርአቱን ለማሻሻልና ጥራትን ለማረጋገጥ ያከናወነቻቸውን ዋና ዋና የሪፎርም ተግባር በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በኢትዮጵያ የተደረገው ሀገራዊ ሪፎርም የትምህርት ዘርፉን አካታችነት ታሳቢ ያደረገ በመሆኑ የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት እኩል የሚስተናገዱበት እንዲሆን እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ከለውጡ በፊት የትምህርት ጥራት ችግር እንደነበር ያነሱት ሚኒስትሩ፤ የቅድመ መደበኛ ትምህርት በከተማ ብቻ ተወስኖ ይሰጥ እንደነበርም አንስተዋል፡፡

እንደ ሀገር በትምህርት ዘርፉ በተደረገው ሪፎርም የቅድመ መደበኛ ትምህርትን በማስፋፋት ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እየተሠራም ነው ተብለዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኝት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1BSBUYuTCK/
የሥርዓተ ትምህርት ሪፎርምን ከመምህራን ሙያዊ ብቃት ጋር ማስተሳሰር እንደሚገባ ተጠቆመ።
……………………………………………………………….
(ሚያዝያ 21/2017 ዓ.ም) Innovation Africa 2025 ጉባዔ በአፍሪካ የሥርዓተ ትምህርት ሪፎርምን ለመተግበር የመምህራን ጥራትና ብቃትን ማረጋገጥ በሚቻልበት ዙሪያ የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

በመድረኩ ፓናሊስት ሆነው የቀረቡት በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራን ትምህርት አመራሮች ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሙሉቀን ንጋቱ በትምህርት ዘርፉ የመምህራንን እና የትምህርት ቤት አመራሮችን ብቃት ለማሳደግ የተለያዩ ስትራቴጂዎች ተቀርፀው ተግባራዊ እየተደረጉ እንዳሉ አንስተዋል።

በተለይም በትምህርት ዘርፉ ከተካሄዱት ሪፎርሞች ውስጥ አንዱ የሥርዓተ ትምህርት ለውጥ መሆኑን ጠቅሰው ይህንን ሥርዓተ ትምህርት ከመምህራን ስልጠና ማዕቀፍ ጋር በማጣጣም መምህራንን በተለያዩ የስልጠና ሞዳሊቲዎች እያሰለጠን እንገኛለን ብለዋል።

በዚህም በባለፈው በክረምት ከ52 ሺ በላይ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮችን በሚያስተምሩት የትምህርት ይዘትና ስነ ዘዴ ላይ ስልጠና መሰጠቱን ጠቅሰዋል።

አክለውም በቀጣይ ክረምት 84 ሺ የሚደርሱ መምህራንን በሚያስተምሩት ይዘትና ስነ ዘዴ ላይ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ስልጠና ለመሥጠት እየተሰራ መሆኑንን አንስተው በየትኛውም ሪፎርም ለመምህራን ብቃትና ጥራት ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በመድረኩም የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በሥርዓተ ትምህርት ሪፎርም የመምህራንን አቅምና ብቃት ለማሳደግ እየሰሩ ያሉትን ሥራም አጋርተዋል።
ኢትዮጵያ አዲስ ሥርዓተ ትምህርት በመቅረጽ ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን ቴክኖሎጂና ክህሎትን የተላበሱ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጎችን ለማፍራት በትኩረት እየሰራች መሆኑ ተገለፀ።
-------------------------------------------------
(ሚያዝያ 22.2017 ዓ.ም) ኢኖቬሽን አፍሪካ 2025 የትምህርት ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፍ የሪፎርምና የፖሊሲ እርምጃዎች ላይ ያላትን ልምድ አካፍላለች።

በመድረኩ ትምህርት ሚኒስቴርን በመወከል ፓናሊስት የነበሩ የትምህርት ፕሮግራሞችና ጥራት መሻሻል መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ዮሐንስ ወጋሶ የትምህርት ዘርፉን ለመለወጥ እየተወሰዱ ያሉ የሪፎርም ተግባራትን አብራርተዋል።

በዚሁ ጊዜ በትምህርት ሥርዓቱ የነበሩ ችግሮችን በሮድ ማፕ በመለየት ኢትዮጵያ የትምህርት ፖሊሲዋን ከመቀየር ጀምሮ ትምህርትን ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ የትምህርት ህግ ማጽደቋን ጠቅሰዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/1Fq4wfN3bj/
ሁለም ዜጎች እኩል የትምህርት እድል እንዲያገኙ እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ነገሌ አርሲ ከተማ የኡታ ዋዩ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታን አስጀምረዋል።
-------------------------------------------

(ሚያዝያ 23/2017 ዓ.ም) በዚሁ ጊዜ የመሠረተ ልማት የተሟላላቸው ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶቾን በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እየገነባ መሆኑን ጠቅሰው ዛሬ ግንባታው የተጀመረው ኡታ ዋዩ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አንዱ መሆኑን ገልፀዋል።

በዚህም ሁሉም ኢትዮጵያዊያን እኩል የትምህርት እድል እንዲያገኙ በትኩረት እየተሠራ ነው ያሉ ሲሆን፦

ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ሥርዓቱን ለመቀየር በርካታ የሪፎርም ተግባራትን ቀርፆ እየተገበረ ይገኛል ብለዋል።

ሀገሪቱ ከሌላው አለም ጋር ተወዳዳሪ እንድትሆን፤ ብቁ ተወዳዳሪ፣ ክህሎትን የተላበሱና ግብረ ገብነት የተላበሱ ዜጎችን ለማፍራት የሚያስችሉ ሥራዎችም እየተሠሩ መሆኑን አብራርተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፣ https://www.facebook.com/share/18fMXNRqbw/
ትምህርት ሚኒስቴር በአለታ ጩኮ ከተማ የሚያስገነባው ሩፎ ዋኤኖ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ ተጀመረ።
---------------------------------------------
(ሚያዝያ 23/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ትምህርት ሚኒስቴር በሲዳማ ክልል ደቡባዊ ሲዳማ ዞን አለታ ጩኮ ከተማ የሚያስገነባውን ሩፎ ዋኤኖ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታን አስጀምረዋል።

በከተማ አስተዳደሩ ያለው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አንድ ብቻ በመሆኑ ይህ በትምህርት ሚኒስቴር የሚገነባው ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያለውን ችግር በመፍታትና የተማሪ ክፍል ጥምርታውን በማመጣጠን ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል ተብሏል።

ምቹና መሠረተ ልማት የተሟላላቸው ትምህርት ቤቶች መኖር ምቹ መማር ማስተማርን ከመፍጠር ባሻገር ተማሪዎች ትምህርት ቤቶቹን ወደው እንዲመጡ ያደርጋል ተብሏል።

በመድረኩም በደቡባዊ ሲዳማ ዞን የትምህርት ጥራትን ከመሠረቱ ለመፍታት በትምህርት ለትውልድ የትምህርት ቤቶች መሠረተ ልማት ማሻሻል ህዝባዊ ንቅናቄ ስታንዳርዳቸውን የጠበቁ 21 የሚሆኑ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተገንብተው የመማር ማስተማር ሥራ መጀመራቸው ተገልጿል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ። https://www.facebook.com/share/p/15kvTMLGLq/